Bawza Newspaper publication of the Ethiopian...

28
ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2 issue 12 Free ንኮበር በ፲፯፻፳ ዓ/ም በሸዋው ነጋሲ በመርድ አዝማች አብዬ የተመሠረተችና በአልጋ ወሪሹ መርድ አዝማች አምኀ ኢየሱስ የተስፋፋች የሸዋ ከተማ ስትሆን ከደብረ ብርሃን ምስራቃዊ አቅጣጫ ፵፫ ኪሎ ሜትር ርቀት የስምጥ ሸለቆው አፋፍ ላይ ትገኛለች። አንኮበር ከዓፄ ይኵኖ አምላክ (፲፪፻፸-፲፪፻፹፭ ዓ/ም) ዘመን ጀምሮ ለኢትዮጰያ ነገሥታት በማረፊያነት አገልግላለች። ዓፄ አምደ ጽዮን ፲፫፻፲፬-፲፫፻፵፬ ዓ/ም የድንኳን ከተማቸውን እንደተከሉባት ይነገራል። አስቲት ኪዳነ ምሕረት የርሳቸው ትክል ናት። ጦረኛዉ ዓፄ አምደ ጽዮን በ፲፫፻፴፭ ዓ/ም አዳልን ለማስገበር የዐማራን፣ የዳሞትን፣ የጐዣምን ሠራዊት ይዘው አንኮበር ሠፈሩ።ለ፬ ወራት ያህል እስከ ዘይላና በርበራ ድረስ በመዝለቅ ድል አድርገው አስገብረውታል። ዓፄ ልብነ ድንግል (፲፭፻፰-፲፭፻፵ ዓ/ም) ደግሞ በተሻለ ሁኔታ በቦለድ የባለወልድን ቤተ ክርስቲያን ለማነጽ ጀምረው እንደነበር የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ። የከተማነት ታሪኳ የጐላው ግን ከግራኝ ወረራ በኋላ ተበታትኖ የቆየውን የጥንታዊ ሸዋን ግዛት አንድ ለማድረግ የሸዋ ስርወ-መንግሥት በአቤቶ ነጋሲ በመንዝ አጋንቻ ላይ በ፲፮፻፷፭ ዓ/ም ተጀምሮ በተከታታይ እስከ ፲፰፻፹፩ ዓ.ም የጥንት ኢትዮጶያ ግዛትን ለማስመለስ አንኮበር ወደ ገጽ 12 ዞሯል በተደረገው እንቅስቃሴ ነው። የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ወደ ፲፫ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሥር መሠረቱ የረር ጥንታዊው የነገስታት መናኸሪያ - አንኮበር “ጀግና እወዳለሁ፤ ዘፋኝ ባልሆን ወታደር ነበር የምሆነው” ንግድ በገጽ 4 “የህክምና ሞያ የሚያስከፍለው ዋጋ እንዳለ ሆኖ፣ ፍቅርና ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ ሞያ ነው” ባላገሯ በአሜሪካ ህብረተሰብ በገጽ 19 ጥበብ በገጽ 9 በውስጥ ገጾቻችን Ethiopian Patriots Victory Day (PAGE 14) ‘Let us not forget the important role women played as spies, suppliers of war materials, and even strategists during the long campaign.’ ለልደት፣ ለሰርግ፤ ቤትዋን ለማከራየት፣ የስራ ማስታወቂያ ለማወጣት ባውዛ ጋዜጣን ይምረጡ ከፈለጉ 202- 387- 9303 ይደውሉ!!!

Transcript of Bawza Newspaper publication of the Ethiopian...

Page 1: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ገጽ 1

Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2 issue 12

BULUT ADDIS ABABA 2.17x1.62inc ING.indd 1 12/22/14 8:27 PM

Free

አንኮበር በ፲፯፻፳ ዓ/ም በሸዋው ነጋሲ

በመርድ አዝማች አብዬ የተመሠረተችና

በአልጋ ወሪሹ መርድ አዝማች አምኀ

ኢየሱስ የተስፋፋች የሸዋ ከተማ ስትሆን

ከደብረ ብርሃን ምስራቃዊ አቅጣጫ ፵፫ ኪሎ ሜትር

ርቀት የስምጥ ሸለቆው አፋፍ ላይ ትገኛለች።

አንኮበር ከዓፄ ይኵኖ አምላክ (፲፪፻፸-፲፪፻፹፭ ዓ/ም)

ዘመን ጀምሮ ለኢትዮጰያ ነገሥታት በማረፊያነት

አገልግላለች። ዓፄ አምደ ጽዮን ፲፫፻፲፬-፲፫፻፵፬ ዓ/ም

የድንኳን ከተማቸውን እንደተከሉባት ይነገራል።

አስቲት ኪዳነ ምሕረት የርሳቸው ትክል ናት። ጦረኛዉ

ዓፄ አምደ ጽዮን በ፲፫፻፴፭ ዓ/ም አዳልን ለማስገበር

የዐማራን፣ የዳሞትን፣ የጐዣምን ሠራዊት ይዘው

አንኮበር ሠፈሩ።ለ፬ ወራት ያህል እስከ ዘይላና በርበራ

ድረስ በመዝለቅ ድል አድርገው አስገብረውታል።

ዓፄ ልብነ ድንግል (፲፭፻፰-፲፭፻፵ ዓ/ም) ደግሞ

በተሻለ ሁኔታ በቦለድ የባለወልድን ቤተ ክርስቲያን

ለማነጽ ጀምረው እንደነበር የሚጠቁሙ መረጃዎች

አሉ። የከተማነት ታሪኳ የጐላው ግን ከግራኝ ወረራ

በኋላ ተበታትኖ የቆየውን የጥንታዊ ሸዋን ግዛት አንድ

ለማድረግ የሸዋ ስርወ-መንግሥት በአቤቶ ነጋሲ በመንዝ

አጋንቻ ላይ በ፲፮፻፷፭ ዓ/ም ተጀምሮ በተከታታይ እስከ

፲፰፻፹፩ ዓ.ም የጥንት ኢትዮጶያ ግዛትን ለማስመለስ አንኮበር ወደ ገጽ 12 ዞሯል

በተደረገው እንቅስቃሴ ነው። የኢትዮጵያ ዋና ከተማ

ወደ ፲፫ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሥር መሠረቱ የረር

ጥንታዊው የነገስታት መናኸሪያ - አንኮበር

“ጀግና እወዳለሁ፤ ዘፋኝ ባልሆን ወታደር ነበር የምሆነው”

ንግድ በገጽ 4

“የህክምና ሞያ የሚያስከፍለው ዋጋ እንዳለ

ሆኖ፣ ፍቅርና ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ ሞያ

ነው”

ባላገሯ በአሜሪካ

ህብረተሰብ በገጽ 19

ጥበብ በገጽ 9

በውስጥ ገጾቻችን

Ethiopian Patriots Victory Day

(PAGE 14)

‘Let us not forget the important role women played as spies,

suppliers of war materials, and even strategists during the long

campaign.’

ለልደት፣ ለሰርግ፤ ቤትዋን ለማከራየት፣ የስራ ማስታወቂያ

ለማወጣት ባውዛ ጋዜጣን ይምረጡ

ከፈለጉ 202- 387- 9303 ይደውሉ!!!

Page 2: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 2

Page 3: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 3

Publisher: Feker Inc.Editor-in-Chief: Yehunie Belay

Managing Director: Makonnen TesfayeAssistant Managing Editor for Kids Section: Feker Belay

Layout & Graphic Design: Feker Design Article Contributors Aneteneh Yegezaw Andrew Laurence Mitike Geremew

Bawza Monthly Newspaper is a publication of The Ethiopian Yellow Pages

www.bawza.comwww.Facebook.com/bawzanews

Bawza Ethiopian Newspaper1924th 9th St. NW

Washington DC, 20001Tel: 202 387 9302/03

Fax: 202 387 9301 Email [email protected]

ርዕሰ አንቀጽ

መልዕክቶቻችሁ

የተከበራችሁ የባውዛ ጋዜጣ አዘጋጆችና አንባቢያ በሙሉ እንደምን ሰነበታችሁ? አሁን ይችን ጹሑፍ የምልክላችሁ ሰሞኑን በተፈጠረው ኢትዮጵያውያን በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ፣ በሚዘገንንና በሚያሳቅቅ የወንድሞቻችን አሟሟት ምክንያት ሳዝን ከረምኩ:: እንደዚህ ዓይነት ጉዳይ እስከ አሁንም በኖርንበት ዘመን ታይቶ ያልታወቀ ትዕይንት ነው:: በእሳት ማጋየት፣ በካራ አንገት መቁረጥ ደም እንደ ውሃ ማፍሰስ የሰው ልጅ እንደ ጧፍ ማንደድ የጭካኔ ድርጊት በወገኖቻችን ላይ ተፈጽሞ እኔም በሀዘን የከረምኩበት ሳምንት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያነቴ አንጀት የነካ ሃዘንና ልክ የሌለው እንባ እያፈሰስኩ ነው:: በመጨረሻም የሞቱትን ነፍሳቸውን እንዲምራቸውና ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን በመማጠን ጹሑፌን አበቃለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

ከምትኬ ገረመው (ከሚሊዋኪ ውስካንስን) _______________________

በሊቢያ ለክርስትና እምነታቸው ብለው ለተሰዉት ኢትዮጵያውያን እና በተለያዩ ሀገሮች በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን እና እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ ግድያ፣ መከራና እስራት ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዬጵያውያን በመሰባሰብ ሀዘናችንን በተለያየ መልኲ ስንገልጽ ሰንብተናል:: ለአገራችን የተሻለ ጊዜ እንዲመጣ ተግተን እንጸልይ::

በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪካና በየመን በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያውያን በተመለከተ፤

የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻችው መፅናናትን እንመኛለን።

ሚሚ (ከቨርጂኒያ)

Page 4: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ገጽ 4ንግድ

ብሉናይል የህክምና ማዕከል መቼ ተቋቋመ?

ብሉናይል የህክምና ማዕከል የተቋቋመው

በ2000 ዓ.ም. ሲሆን ስራ ሲጀምር በመጀመሪያ

በሁለት ዶክተሮች ነበር፡፡ ቆየት ብሎ ግን አንድ

ዶክተር ተቀላቅሎናል፡፡ ሶስታችንም የውስጥ ደዌ

ስፔሻሊስቶች ነን፡፡ በወቅቱ የህክምና ተቋሙ ስራ

ሲጀምር የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ እየበዛ የሄደበት ጊዜ

ነበር፡፡ የኢትዮጵያን ማህበረሰብ፣ በራሱ ቋንቋ

በሽታውን በግልጽ አስረድቶ እንዲታከም ምቹ

አገልግሎት መፍጠር በመሆኑ ይሄንንም ከሞላ ጎደል

እያደረግነው እንገኛለን፡፡

ብሉናይል የህክምና ማዕከል ስንት የአገልግሎት

መስጫ ቅርንጫፎች አሉት፤ በስሩስ ስንት ሰራተኞች

አሉት?

ሁለት ቅርንጫፎች አሉት፣ ሁለቱም ቨርጂኒያ

ውስጥ ናቸው ስታፈርድ እና አሌክሳንደርያ ቨርጅኒያ

ይገኛል:: ከዚያም በተጨማሪ በሆስፒታሎች፣

ነርሲንግ ሆሞች የተለያዩ አገልግሎቶችን እንሰጣለን::

በሁለቱም የህክምና ማዕከሎቻችን ከሃያ በላይ

ሰራተኞች አሉን፡፡

ወደ ብሉናይል የህክምና ማዕከል የሚመጡ

ኢትዮጵያውያን ታካሚዎች የሚጠቀሱ የጤና

ችግሮቻቸው ምንድን ናቸው?

እንደማንኛውም ማህበረሰብ በኢትዮጵያውያንም

ላይ የስኳር፣ የደም ግፊት፣ የኮሎስትሮን በሽታዎች

ይታይባቸዋል፡፡ በተያያዘ የኮሊስትሮን(የስብ)

ችግሮች የልብ፣ የስኳር፣ የደም ገፊት፣ የመሳሰሉት

ከአበላል ጋር በተያየዘ እንደሌላው ማህረሰብ

የኢትዮጵያን ማህበረሰብ የሚያጠቁ ናቸው፡፡ ከአዲስ

ባህልና ማህበረሰብ ጋር በሚፈጠር መግባባቶች

ወይንም የትውውቅ የሽግግር ጊዜ ክፍተት

በሚፈጥረው ከአካባቢ ጋር በቶሎ ያለመላመድ

ሁኔታ ከአበላልና ከአኗኗር ለውጥ ተያይዘው

የሚመጡ ችግሮች የአእምሮ ጭንቀት፣ ድብርት

የመሳሰሉ ችግሮች የኢትዮጵያውያንንም ኮሚኒቲ

ያጠቃል፡፡ ከዚህ በተረፈም አፋጣኝ(ድንገተኛ)

የብሉናይል የሜዲካል ሴንተር/የህክምና ማዕከል በሶስት ፕራይሜሪ ኬር ሲፔሻሊስቶች በ2ሺህ ዓመተ ምህረት አካባቢ ተቋቁሟል፡፡ የህክምና ማዕከሉ የኢትዮጵያን ማህረሰብ በራሱ ቋንቋ የህክምና አገልግሎቶችን እየሰጠ

ሲሆን ከሌሎች የህክምና ባለሞያዋች ጋር በመቀናጀት ኔት ወርክ ኦፍ ዘ ዶክተርስ በመሰባሰብ በጋራ የራሳቸው ላብራቶሪ፣ የኤሜድይ ማዕከል ለመዘርጋት እንቅስቃሴዎች እያደረጉ ነው፤ በሰፊው ህብረተሰብ ለማገልገል

እንቅስቃሴ እያደረገ ነው። ባውዛ ጋዜጣ ከብሉናይል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ወልደሂር ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

ብሉ ናይል ወደ ገጽ 24 ዞሯል

“የህክምና ሞያ የሚያስከፍለው ዋጋ እንዳለ ሆኖ፣ ፍቅርና ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ ሞያ ነው”

ህክምና የሚፈለጉ ኢትዮጵያውያን ታካማዊችም ወደ

እኛ ይመጣሉ፡፡

ብሉናይል የህክምና ማዕከል እንደሚሰጠው

አገልግሎት ተጨማሪ ቅርንጫፎችን ለመክፈት

አቅዳችኋል?

በአሁኑ ጊዜ የህክምና ኢንደስትሪው ለውጥ ላይ

ነው ያለው። ይሁንና እንደ ብሉናይል ወዴት እንሄዳ

የሚለውን እያጠናን ነው፡፡ በዚህ አገር ከሌላ

ዶክተር የህክምና ቡድኖች ጋር በመቀናጀት ኔት

ወርክ ኦፍ ዶክተርስ በመሰባሰብ በጋር የራሳችን

ላብራቶሪ፣ ኢሜጅግ እና (Out patient) ማዕከል

እየፈጠሩ ለመጠንከር እየሰራን ነው፡፡

የተለያዩ ቮለንተሪ ስራዎችንስ ከአሜሪካ ውጭ

በስተግራ ዶ/ር ተድላ አንበሴ፣ በመካከል ዶ/ር ያሬድ አይታገዱና በስተቀኝ ዶ/ር ጌታቸው ወልደሂር

Page 5: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 5

Page 6: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 6

ሰላም ይሁኔ በላይ እንኴን ለ17ኛ ዓመት የልደት በዓልሽ አደረሰሽ!!! እንወድሻለን

Page 7: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 7

መልካም ልደት ለልጆቼ!! እወዳችኋለሁ::

BROOK ZELALEM BROOK ZELALEMብሩክ ዘላለም ዮሴፍ ዘላለም

ዓመትዓመት

መልካም ልደት ከቤተሰቦችህ እንወድሃለን

ኔተን ተስፉዬ

Nathan Tesfaye

Daniel Sebsebe

መልካም ልደት ከቤተሰቦችህ እንወድሃለን

ዳንኤል ሰብስቤ

እናታችሁ አቢ

Page 8: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 8ህብረተሰብ

(1)(ሲጀመር)አንድ ኢትዮጵያዊ ያለ እቅድ፣ በስህተት ይረገዛል:: ሊወለድ ሲል በወሊድ እክል ምክኒያት ይሞታል:: ከተረፈም ክትባት ባለመከተቡ 5 አመት ሳይሞላው ይሞታል፡፡አትሙት ካለው ቀንጭሮ ያድጋል፡፡ ያድግና ሽምደዳና ግርፊያ ከሞላቸው የመንግስት ትምህርት ቤቶች አንዱ ጋራ ገብቶ ይማራል፡፡10ኛ ክፍልን እንደ ጨረሰ ስራ ያጣል፣ ይቦዝናል፡፡ በኑሮ ሂደት ወይ ኤድስ፣ ወይ ወባ፣ ወይ መኪና አደጋ፣ አልያም የስደት ሰቆቃዎች ይገድሉታል፡፡ከዚህ ሁሉ ጣጣ ተርፎ እድሜው ቢረዝምና ቢያረጅ ቤተክርስቲያን አጥር ጥግ ይለምናል፤ አኪራም ከሆነ ሜቄዶንያ ጠርንፎ ይጦረዋል፡፡ከዛም ይሞታል፡፡የአንድ average ኢትዮጵያዊ ታሪክ ይሄና ይሄ ነው፣ አለቀ! ለነገሩ የሌላው አፍሪቃዊ ታሪክም ከዚህ ቢብስ ነው፡፡(2)ቪድዮውን ሠው ልኮልኝ አይቼው ስረበሽ፣ ስረበሽ፣ ስረበሽ፣ ስብከነከን ቀኔን አበላሽቼው ዋልኩኝ፡፡ . . . እነዛ የጨርቆስ ልጆች የማውቃቸው የሠፈሬ ልጆች መሰሉኝ፡፡ሳለውና ፍረድ ተፋረድ እንግዲህ!መጀመሪያ ከቤተሰብ፣ ከዘመድ፣ ከጎረቤት ብር ይበደራሉ፣ ከዛም በመተማ አድርገው ሱዳን ይገባሉ:: ከሱዳን በኤኔትሬ ተጭነው የሳሃራ በረሃን አቋርጠው

“ የወንድ ልጅ እናት ታጠቂ በገመድ ልጅሽን አሞራ እንጂ አይቀብረውም ዘመድ”

ሊብያ ይደርሳሉ፡፡ ከሊብያ በጀልባ ተሳፍረው ላምፓዱሳ ደሴት ይገባሉ፤ ከዛም እንግሊዝ ተሸግረው የስደተኛን ኑሮ ይጀምራሉ፡፡ ብድራቸውን ይከፍላሉ፡፡ ቤተሰብ ይረዳሉ:: ለበዐል ብር ይልካሉ፡፡ ወንድምና እህቶቻቸውን ቪዛ ልከው ያስወጣሉ፡፡ይሄ ነበር የኑሮ ምኞታቸው፡፡እያንዳንዱ የጉዞ ኩርባቸው በሞት ትንቅንቅ የተሞላ ነው፣ ያውቁታል፡፡ እዚህ ከኖሩት ችጋር ግን አይብስም፣ እሱንም ያውቁታል፣ ጠንቅቀው፡፡

. . .ያልጠበቁት ዐረብ እንዳውዳመት ዶሮ አርዶ ፕሮፓጋንዳ ይሰራብናል ብለው አላሰቡም፡፡.(3)መሬት ለይ ባፍጢማቸው ተክለው አስተኝተዋቸው ሊያርዷቸው ሲያዘጋጇቸው፣ በልባቸው ምን እያሉ ይሆን ይሆን?.“. . . እመቤቴ ማርያም አንቺ ታውቂያለሽ፡፡”

“. . . ይሄንን ሁሉ በረሃ አልፌ፣ ከጫፍ ደርሼ ሊያልፍልኝ ሲል ፡፡”“. . . እናቴ በጸሎት አስቢኝ፡፡”“. . . እኔስ ልሙት፣ እነ ፋዘር የስደት መሆጃ እዳዬን ኬት አምጥተው ሊከፍሉት ነው?”“. . . ምናለ አንዴ ልጄን በስልክ እንዳናግር ቢፈቅዱልኝና ቢገድሉኝ፡፡”“. . .እናቱን አፈር የበላች ይሄ ቦቅቧቃ ቡሽቲ አረብ አገሬ ቢሆን ጫፌን አይነካትም ነበር፣ ልኩን አሳየው ነበር!”(4)(The bigger picture)በዓለም አቀፍ አባላት ምልመላ፣ በፍጥነት በመራባትና፣ የጦር ቤዝ በመያዝ አልቃይዳን በዕጥፍ የሚያስከነዳው ISIS ሊብያ፣ ኢራቅና ሶርያ ላይ ከትሟል ያለው፡፡ እነኚህን አገሮች ዴሞክራሲ በሚል ሰበብ ያፈረሷቸው የነጻነትና የዴሞክራሲ አቀንቃኞቹ ምእራባውያኑ ናቸው:: ኢራቃዊ ብትሆን እና Historic identity የነበራት አገርህ በየሳምንቱ ፈንጂ የሚፈነዳባት፣ መቶ ሺዎች በየአመቱ የሚያልቁባት አውድማ ሆና ስታያት ጽንፈኛ አረመኔ ለመሆን ብትመርጥ አይገርምም፡፡ እንደ ሊብያዊ የቅንጦትና ብልጽግና ኑሮን የሚኖር፣ እንደ ሊብያዊ የተረጋጋ ህዝብ፣ እንሞሃመድ ቃዛፊ የአፍሪካ አገራት በገንዘብ የሚረዳ፣ ለአፍሪካ ህብረት እጅግ ከፍተኛ ብር የሚለግስ መሪ አፍሪቃ አልነበራትም፡፡

ሊብያ ወደ ገጽ 20

Page 9: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 9ጥበብ

ጀግና እወዳለሁ፤ ዘፋኝ ባልሆን ወታደር ነበር የምሆነው”-አንጋፋዋ ድምፃዊ ራሔል ዮሐንስን በሃበሻ ልብስ ደምቃና አምራ ነበር ያገኘኋት- ባለፈው ረቡዕ ምሽት፡፡ በተንጣለለው ግቢዋ ጋራዥ ቤት ውስጥ ሽንጣም ኒሳን መኪናዋ ቆሟል:: ግራውንድ ፕላስ ዋን መኖርያ ቤቷ በአካባቢው ካሉ መኖሪያቤቶች እጅግ ማራኪና ትኩረት የሚስብ ነው፡፡ ሳሎን ቤት ስገባ ትልቅ ድግስ የተዘጋጀ ይመስል ነበር፡፡ ጥሬ ስጋው ጠጁ፣ ጠላው ተደርድሮ ነው የደረስኩት፡፡ ራሔል እንደነገረችኝ ማክሰኞ ዕለት ቤቷ ማህበር ነበር፡፡ የስድስት ልጆች እናት ብትሆንም አሁን ልጆችዋ አብረዋት የሉም - በአሜሪካና በካናዳ ነው የሚኖሩት፡፡ እሷ ከዘመድ ልጆች ጋር ትኖራለች፡፡ በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ ወደሙዚቃ ሙያ ከገባችው ራሔል ዮሐንስ ጋር በህይወቷና በሙያዋ ዙሪያ ያላወጋነው ነገር የለም፡፡ በቤተመንግስት አጉራሽ እንደነበረች፣ በጊዮንና በሂልተን ሆቴል በዋይን ገርልነት መሥራቷን፣ አንዳንዴ ዘፈኗን በእንግሊዝኛ እንደኮሜዲ ታቀርብ እንደነበረ ወዘተ--- ነግራኛለች፡፡ ከጓደኞቿ ጋር ስላላት ማህበር እንድትነግረኝ በመጠየቅ ነው ወደ ጭውውታችንን የገባነው፡፡ ማህበሩ የጓደኞች ነው የቤተሰብ?የት/ቤት ጓደኞቼም የቤተሰብም አለኝ፡፡ ከ40 ዓመት በፊት የተጀመረ ነው፡፡ አንዳንድ ጓደኞቼ፣ እህቶቼ ቢያልፉም እስከዛሬ ይሄው ማህበሩን እንጠጣለን፡፡ ዛሬ አንቺም ወደ ቤቴ የመጣሽው የመድሃኒያለም ማህበር ትናንት አውጥቼ ነው፡፡ በጣም የተለየ ፍቅር አለን፡፡የትምህርት ቤት ጓደኞችሽ---የት ነው የተማርሽው? የቄስ ትምህርት አባታችን አስተማሪ በቤታችን ቀጥረው ነው ያስተማሩን፡፡ ከ1ኛ- 8ኛ ክፍል ደግሞ አስፋው ወሰን ት/ቤት ነው የተማርኩት፡፡ ከትምህርት ቤት ጓደኞቼ ጋር በ21 እና በ27 ማህበር አለን፤ ማህበር ሲኖር በየቤታችን አዝማሪ ይቆማል፤ ማስንቆ የሚጫወት፡፡ ወንጂና ናዝሬትም እህቶቼ አሉ፤እዛም እየሄድን እንዝናናለን፡፡ እረ እንደው ተይኝ አልኩሽ ---- የተንፈላሰሰ ዘመን ነበር፡፡በማህበራችሁ ቀን የሚጫወቱት አዝማሪዎቹ የሚታወቁ ነበሩ?አዎ፡፡ እነ ወረታው፣ ባይረሳው---- እንዴት ቆንጆ ድምፅ አላቸው መሠለሽ፡፡ እነሱ ወደ ቤታችን ሲመጡ ታዲያ ሁሉም ግጥም ሰጪ ነው፤ ሁሉም ተቀባይ ነው፡፡ ቤትም ባይመታም:: ማሲንቆዋቸውን ይዘው ይመጣሉ፤ ጨዋታው ሌላ ነው አልኩሽ፡፡ ደሞዝ እኮ የላቸውም ግን በየወሩ ፅዋ የገባበትን ቤት ስለሚያውቁ ማህበሩ በሚወጣበት ቤት ይመጣሉ፡፡ መጀመሪያ ፀሎት ይደረግና ምሳ ይበላል፣ ከምሳ በኋላ የንስሃ አባቶቻችን ያሳርጋሉ፡፡ ከዛ በኋላ አሸሸ ገዳሜ ነው የእኔ እናት፡፡ ግጥም ከመስጠት ወደ ዘፋኝነት ገባሽ ማለት ነው? ያን ጊዜ ዘፋኝነትን አልሜው አላውቅም ነበር፡፡ ድምፃዊ ሰይፉ ዮሐንስ የሚባል ወንድም ነበረኝ፡፡ ወላጅ አባታችን ዘፋኝ ሆነ መባልን ሲሰሙ የሞተ ያህል ነው ያለቀሱት:: አለማወቅ እኮ ነው--- ማን ያውቀዋል ይሄንን:: አባቴ በጣም አዘኑ…የወንድሜን መታመም ሲሰሙ ግን ድንጋጤአቸው ባሰ፡፡ በጣም በጣም ደግ ልጁ ነበረ፡፡ እርሱም ሞተ፤ አባቴ በጣም ተፀፀቱ --- ምን ታደርጊዋለሽ? አለማወቅ ይጎዳል፡፡ ወንድሜ በሞተ በዓመቱ ነው አባታችን የሞቱት፤ በእርሱ ሃዘን (እንባ) ወንድሜ ከሞተ ከአስር ዓመት በኋላ ነው ሙዚቃ የጀመርኩት፡፡አባቴ ዘፈን አይወዱም ነበር፡፡ ግን በገና ነበራቸው፤ የቅዳም ሱር እለት በገናቸውን አውጥተው ሲደረድሩ ፤የገና ዕለት ጌታን እያመሰገኑ ሲጫወቱ የድምፃቸው ማማር ልዩ ነው ---- እናቴም ጥጥ ስትፈትል እያንጎራጎረች ነበር፡፡ ‹‹…ባለድሪ›› የሚለውን ዘፈን ከእርስዋ ነው የወሰድኩት፡፡ ‹‹…ገዳማይ ---- ገዳማይ ---ገዳማይ›› እያለች ታንጎራጉራለች:: የእናቴን ድምፅ ወንበር ስር ተደብቀን ወይም ግድግዳ ተከልለን ነው የምንሰማት፡፡ እማዬ ድምፅዋ በጣም ነበር የሚያምርው፡፡ አሁን በህይወት የለችም፡፡እናትሽ የሙዚቃ ስራ ስትጀምሪ በህይወት ነበሩ? አዎ! ድምፄን የሞረድኩበትን ‹‹አንተ ባለድሪ” የሚል ዘፈን እናቴ ትወደው ነበር፡፡ በአባትዋ ጎንደሬ ስለሆነች ጨዋታው ይስባታል:: የመጀመሪያ የካሴት ስራዬንም እናቴ እንዴት ትወደው ነበር መሰለሽ፡፡ ከዘፈን በፊት ምን ነበር የምትሰሪው? “ፎር ሽፕ ትራቭል ኤጀንት” የሚባል ድርጅት ውስጥ ትኬት ኤጀንት ሆኜ እሰራ ነበር፡፡ ራስ ሆቴል ዴስክ ነበረችኝ፡፡ እዛ እንግዳ ይመጣል፡፡ እንግዶችን ተቀብሎ

የሚፈልጉትን መረጃ መስጠት፣ መኪና ማከራይት፣ ፎርም ማስሞላት፣ ዲፖዚት መቀበል ነበር ሥራዬ፡፡ ድርጅቱ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ተዘጋ፡፡ በወቅቱ የልጆች እናት፤ የቤተሰብ ሃላፊ ነበርኩ---‹‹ምን ሆኜ ነው የምኖረው..›› ብዬ ሳስብ፣ ጓደኞቼ “እነ በቀለች ክትፎ ከትፈው እየሸጡ ይኖሩ የለ፡፡ ክትፎ ክተፊ›› አሉኝ፡፡ክትፎ ግን ሞያ ይጠይቃል አይደል--ሞያ ለእኔ!! እኔ እናትሽ እኮ አንቱ የተባልኩ ባለሞያ ነኝ:: የወላጆቼ ቤት እዚህ ካዛንቺዝ ነበር፡፡ እዛው ጊቢ ውስጥ አንድ ክፍል ተሰጥቶኝ እኖር ነበር፡፡ ክትፎ ቤት ከፈትኩ:: አንድ ቀን ታዲያ ሰዎች ክትፎ ሊበሉ ቀብረር ያለውን ድምፃዊ ከተማ ይፍሩን ይዘውት መጡ፡፡ ያን ቀን አንድ ዕቃ ጠፍቶብኝ ተበሳጭቼ ነበር:: ይሄን ያህል የተበሳጨሽው ምን ቢጠፋብሽ ነው?አንድ ሙሉ ካርቶን ውስኪ፡፡ አንድ ዘመድ ነበር--- አውጥቶ ሽጦብኝ ብስጭት ብዬ ነበር፡፡ አልቅሼ ፊቴን ስጠራርገው የልጅነት መልክ ጥሩ ነው፣ ወለል ‹‹ፏ›› ነው የምለው፡፡ እነ ከተማ ክትፎውን እየበሉ ይጨዋወታሉ:: ከዚያ ከተማ መዝፈን ማንጎራጎር ጀመረ፡፡ እኔም ከጎኑ ቁጭ ብዬ አንጎራጉራለሁ:: ከዛ ከተማ ድንገት ብድግ ብሎ ‹‹እዚህ ቤት ሁለተኛ ክትፎ እንዳይከተፍ›› አለ፡፡ ‹‹ምነው አመምዎት?›› አልኩኝ ያልተስማማቸው፣ አለርጂ የሆነባቸው መስሎኝ፡፡ ‹‹ይሄን ቆንጆ ድምፅ ይዘሽ በምን ምክንያት ነው የማትዘፍኝው?›› አሉ፡፡ ‹‹ድምፅ አለኝ እንዴ?›› አልኩኝ ለራሴ‹‹ምንድን ነው የምትጠጭው?›› አሉኝ፡፡እኔ ግን እንኳን በዛ ጊዜ ዛሬም መጠጥ የሚባል አልቀምስም፡፡ ‹‹እረ እኔ ምንም አልፈልግም… አልጠጣም›› አልኳቸው፡፡ ሲያስጨንቁኝ‹‹ኮካ ይሻለኛል›› አልኩኝ፡፡ ያን ጊዜ ግሩም ነበር ኮካኮላ---ከኮካኮላው ውስጥ ሳላይ ውስኪ ጨምረውብኝ….እንደ ውሃ ጭልጥ አደረኩት፡፡ ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ደስ አለኝ… ‹‹እንዴ ምን ሆኜ ነው ደስ ያለኝ…ምን አገኘሁ›› እያልኩ አስብ ነበር፡፡ ለካ ለብታ ማለት ይሄ ነው፡፡ ከዛ በኋላ ሰንጥቄ ሰንጥቄ ለቀቅኩት ዘፈኑን፡፡ የማንን ዘፈን እንደዘፈንሽ ታስታውሺያለሽ? ከተማ እኔ ቤት የተጫወተውን ባቲ፣ ትዝታን፣ ተይ ማነሽን ተጫወትኩ --- ከአሁን በኋላ ‹‹አምቦ ውሃሽን አቀዝቅዥ፣ ቆንጆ ውስኪ አቅርቢ --- እኛ እንግዳ ይዘን እንመጣለን ---- አበቃ ክትፎ ቤት›› አሉኝ፡፡ ከዛ ምን አለፋሽ --- ከአለም አንደኛ ሆንኩኝ፡፡ በማግስቱ የምሽት ክበብ ተጀመረ?መጀመሩስ ተጀመረ፡፡ መጥተው “በይ ተጫወቺ” ሲሉኝ ከየት ይምጣ፡፡ ያቺ የለችማ የተለመደችው ብረት ለበስ….ታዲያ ወሰድ አታደርጊም ነበር---እኔ ምኑን አውቄው----በፊትም እኮ ወኔዬን ያመጣው ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ በኋላ እኮ ነው የነገሩኝ፡፡ ግን እየለመድኩ መጣሁ ---- ሌላ ሆነ እንግዳው፣ ደንበኞቼ በዙ---የብር አቆጣጠሬን ብታይ አስቅሻለሁ፡፡ እንግዶቼን ሸኝቼ ስጨራርስ----.ብር እቆጥራለሁ፡፡ ‹‹..አንድ..ሁለት…ሶስት..አራት.. እባካችሁ ተኙ እናንተ ልጆች---መሸ እኮ-- ነገ ትምህርት ቤት ወየውላችሁ..›› ብሩ ከእጄ ይንጠባጠባል፡፡ የሽልማቱ ብር ነው?ሽልማቱ ተይኝ ይረግፍ ጀመር፡፡ ማን አውቆት ቁጥሩን ----ከትራሴ ስር አድርጌው ነው የማድር --- ልጆቼ በጠዋት ሲነሱ ----ገንዘቡን ለቃቅመው እየሳቁ ‹‹..አንቺን ብሎ ቆጣሪ›› ብለው ይሰጡኛል፡፡ መኖሪያሽም የስራ ቦታሽም አንድ ቦታ ነበር ማለት ነው?መጀመርያ አዎ፡፡ በኋላ ግን ሃብት መጣ --- ካሳንቺዝ እርሻ ሚኒስቴር አካባቢ ቤት ገዛሁ፡፡ ዛሬ ንብ ባንክ ሆኗል:: ታሪኩ ብዙ ነው ባክሽ…በመሃል ታመምኩ፡፡ ሶስት ወር ሙሉ እጅና እና እግሬ ተይዞ ፓላራይዝድ ሆኜ ተኛሁ:: የቤት ስልክ ጮኸና ጨዋታችንን አቋረጠን፡፡ ከካናዳ ወንድ ልጅዋ ነበር የደወለው) ከዚያልሽ --- በጠበሉም በምኑንም ብዬ ተሻለኝ፡፡ በመሃል ስራሽን አቁመሽ ነበር?አዎ ሙሉውን አቁሜ ቤቱን አከራየሁት፡፡ መጨረሻ ላይ ያከራየኋት ሴት እገዛዋለሁ ብላ ስሙን አዛውሬላት ነበረ---በቼክ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ሰጥታኝ ነበር---ከዚያ እዛ ዱባይ የሚባል አገር ተነስታ ሄደች፡፡ ቤቱ በሃራጅ

ተሸጠና ለእኔ ስድስት መቶ ሺ ብር ተሰጠኝ፡፡ ከባንክ በቀኝ እና በግራ እጄ ሶስት መቶ ሺ፣ ሶስት መቶ ሺ ብር ይዤ ስወጣ በጣም ከበደኝ:: ‹‹ፈጣሪዬ በአቅሜ ነው የሰጠኸኝ..ያንን አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ ብር..አግኝቼ ቢሆን እንዴት ነበር የምይዘው..ተመስገን ጌታዬ ይሄንኑ በረከቱን ረድዔቱን ስጠው›› ብዬ--- (በድጋሚ የቤት ስልክ ጮኸ:: አሁንም ከካናዳ ሌላኛዋ ልጅዋ ደወሎ፤ ሰላምታ ሰጥታ ቆይቶ እንዲደውል ነግራው ዘጋች) የካሳንቺሱ ስራ ቆመ ማለት ነው --አንድ ዓመት ይህል ቁጪ አልኩኝ ያለ ስራ፡፡ ከዛም ለምንድን ነው ቁጪ የምትይው ብሎ ቁምላቸው የሚባል የፋሲካ ባለቤት ተቆጣኝ፡፡ ከዛ ኦርጋኔንና የራሴን ባንድ ይዤ እዚያ ሄድኩኝ፡፡ አብረውኝ የሚጫወቱትን ሳክሲፎኒስትና ኦርጋኒስት ይዤ ማለት ነው፡፡ ‹‹ራሄል እዚህ ገብታለች›› ሲባል…ተይኝ አልኩሽ --- ሰው እንደጉድ ይጎርፍ ጀመር፡፡ ደንበኞችሽ ታዋቂ ሰዎች፣ ባለሥልጣናትና ባለሃብት---

ነበሩ ይባላል፡፡ እንደውም አንዴ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስን ቃለ መጠይቅ ስናደርግላቸው---.የአንቺን የምሽት ክበብ በጣም ይወዱት እንደነበር ነግረውናል ---እጣ ክፍሌም እንደዛ ነገር ነው፡፡ የአዲስ አበባ መሳፍንት መኳንት፣ የራስና የደጃዝማች ልጆች፣ ማን ይቀራል…እገሌ ከእገሌ አልልሽም፡፡ የጨዋ ልጆች ይመጡ ነበር፡፡ ስርዓት ለሌለው እንኳን ስርዓት አስተምሬ ነው የምለከው፡፡ በጃንሆይም ጊዜ ከቤተመንግስት ሰዎች ጋር ነበር ቅርበቴ፡፡ በቃ ይወዱኛል፡፡ ዘፋኝ ሳልሆንም እኮ ነው፡፡እንዴት ወደ ቤተመንግስት ለመቅረብ ቻልሽ? ያኔ ቤተመንግስት ቱሪስቶች ሲመጡ አጉራሽ ይፈለግ ነበር:: ቤተ-መንግስት ሄደን እንጀራ እናጎርሳለን፡፡ የቤተመንግስት እንጀራ እንደዚህ ሶፍት ነጭ ነበረ(በእጅዋ የያዘችውን ሶፍት እያሳየችኝ) ፈረንጆቹ ናፕኪን እየመሰላቸው እንጀራውን እንደ ሶፍት ይጠቀሙበታል፡፡ ቤተመንግስት

ዋይን ወደ ገጽ 21 ዞሯል

ድምፃዊ ራሔል ዮሐንስን

Page 10: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 10

Page 11: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ገጽ 11

Page 12: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 12

| እንጦጦ እስከዞረበትና በኋላም አዲስ አበባ

እስከተቆረቆረችበት ጊዜ ድረስ በቀዝቃዛ አየሯ

የምትታወቀው አንኮበር ለአምስት የሸዋ ነገሥታት

በማእከልነት አገልግላለች።

አንኮበር የሸዋ ነገሥታት ቋሚ መናኸሪያ ለመሆን

የበቃችው ከመርድ አዝማች አምኀየሱስ ዘመነ

መንግሥት ሲሆን በ፲፱ኛው መቶ ክፍለ ዘመን

መጀመሪያ ላዶ ሥልጣን በያዙት በንጉሥ ሣህለ

ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በይበልጥ ተስፋፍታ ነበር።

ንጉሡ የእጅ ባለሙያዎችን በከፍተኛ ደረጃ ያበረታቱ

ስለነበር፣ በርካታ የእደ ጥበብ ሥራዎች ይከናወኑባት

ነበር። በቤተ መንግሥት የሚተዳደሩ ከሺ በላይ

አናጺዎችና ግንበኞች በተለይም ባሩድ ቀማሚዎች፣

የጦር መሣሪያ ሠራተኞችና አንጥረኞች በወቅቱ

ነበሩባት።

የንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ዐልጋ ወራሽ ንጉሥ ኃይለ መለኮት

ተተክተው ፰ ዓሙታት ያህል እንደገዙ ሸዋ በዓፄ

ቴዎድሮስ ሠራዊት ተወረረ። የቴዎድሮስ ሠራዊት አንኮበር

ከተማ ግቢው ቅጥሩ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ሹማምንቱ

የግቢውን ቤተ መንግሥቱን አቃጥለውታል። ዓፄ

ቴዎድሮስም በቦታው ድንኳን ጥለው ጥቂት ቀናት ቆይተው

የራሳቸውን ወኪል ሾመው ተመልሰዋል። ጥቂት ቆይቶ

የሸዋ መኳንንት በአቤቶ ሰይፉ ሣህለ ሥላሴ መሪነት የዓፄ

ቴዎድሮስን ተወካይ በዛብህን አባረው ግቢዉን ሲይዙ ዓፄ

ቴዎድሮስ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ሸዋ ዘምተዉ በተካሄደው

ከፍተኛ ጦርነት አንኮበር ክፉኛ መዘረፉንና፥መቃጠሏን

መረጃዎች ይገልፃሉ።

የ፲፩ ዓመቱ ምኒልክና የሸዋ መኳንንት በግዞት ወደ ጎንደር

ተወስደዋል። ምኒሊክ በዓፄ ቴዎድሮስ እጅ በእስራት

ከነበሩበት መቅደላ አምልጠው ሲመለሱ አንኮበር እንደገና

ተቋቁማ የጥንት ማዕረጓ ተመልሷል።

ዛሬ በአንኮበር ከዓፄ ምኒሊክ ቤተ መንግሥት ፍርስራሽ

በተጨማሪ በተለያዩ ዘመናት የተሠሩ አምስት አብያተ

ክርስቲያናትና ዘመናዊ የጎብኚዎች መቀበያ ይገኛሉ።

እነሱም፦ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፣ የአንኮበር

ቅዱስ ሚካኤል ቀሳውስት 1842 ዓ.ም.፣ ጥምቀት

በአንኮበር ቅዱስ ሚካኤል፣ ፲፰፻፴፬ ዓ.ም.፣ ቅዱስ

ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን፣ አንኮበርና የአካባቢው መልክዓ

ምድር የአንኮበር መሪዎች መኖሪያ በ1877 እና 1880 ዓ.ም.

መካከል፣ በ፲፯፻፴፫ ዓ/ም በአምኀ ኢየሱስ የተሠራው

አንኮበር ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን፣ በ፲፯፻፷፯ ዓ/ም

በአስፋ ወሰን የታነጸው አንኮበር ማርያም ቤተ

ክርስቲያን - ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ በ፲፰፻፲፯

ዓ/ም ያሠሩትአንኮበር ሚካኤል እና በ፲፰፻፳፩

ዓ/ም ያሠሩት አፈር ባይኔ ተክለ ኃይማኖት

ንጉሥ ምኒልክ እና ወይዘሮ ጣይቱ ብጡል

የፋሲካ ዕለት ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፲፰፻፸፭ ዓ/ም

አንኮበር ከገጽ 1 የዞረ

የጋብቻ ሥነ ስርዓታቸውን ሲፈጽሙ ቅዱስ

ቁርባን የተቀበሉበት የአንኮበር መድኀኔ ዓለም

ቤተ ክርስቲያን። ይህ ቤተ ክርስቲያን በ፲፯፻፸፪

ዓ/ም ቢጀመርም የተፈጸመው በንጉሥ ኃይለ

መለኮት በ፲፰፻፵፮ ዓ/ም ነው።

በአሁኑ ጊዜም የአንኮበር ከተማ አከባቢ

መስህቦችን አቅፎ የያዘ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ

የሚኒሊክ ቤተመንግስት የቤተመንግስቱ

ፍርስራሽ፣ማድቤት ፍርስራሽ፣የሚኒሊክ ስልክ

ቤትና ሰገነት ሊጎበኙ የሚችሉ ሲሆን በአንኮበር

ቤተመንግስት አከባቢ ሊጎበኙ ከሚችሉት ሰው

ሰራሽ ቅርሶች በተጨማሪ ማራኪ የሆነ የተፈጥሮ

የመሬት ገጽታና ድንቅዬና ብርቅየ የዱር እፅዋት

ይገኙበታል፡፡

በጊቢው ውስጥ የሚገኙ ዘመን ያስቆጠሩ ዕፅዋት

Page 13: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 13

Fairfax, VA በሚገኘው

ቤታችን ውስጥ ከሰኞ እስከ

ዓርብ ልጆች የሚጠብቅልን

መኪና የሚነዳ ሰው እንፈልጋለን፡

፡ (703) 379 2377 ይደውሉ፡፡

(ካጡን መልክት ይተው)

Hyattsvile, MD

በሚገኘው ቤቴ ውስጥ ልጅ

የሚጠብቅልኝ እፈልጋለሁ፡፡

(240)4813415 ይደውሉ፡፡

Springfiled, VA

በሚገኘው ቤቴ ውስጥ ልጅ

የሚጠብቅልኝ እፈልጋለሁ፡፡

(571)215 2365 ይደውሉ፡፡

በቤትዎ ውስጥ ልጆችዎን

በተመላላሽ እጠብቃለሁ፡፡

(571)290 1160 ይደውሉ፡፡

በቤትዎ ውስጥ ልጆችዎን

እንደ ልጆቼ በእትነት ፍቅር

እጠብቃለሁ፡፡ (703)599 9810

ይደውሉ፡፡

Alexandria, VA

Beauregard St. & Sanger

Woodbridge, VA የራሱ

መውጫ፣ ሁለት መኝታ ቤት፣ መጣጠቢያና

ማብሰያ ያለው Basement ለማያጨስ ሰው

ለማከራየት እናከራያለን፡፡ በ(703)565

4999 ይደውሉ፡፡

Springfield, VA Back

lick & Braddock Rd. ላይ ለትራስፖርት

ምቹ፣ የራሱ መውጫ፣ መታጠቢያ፣

ማብሰያ፣ ሳሎን፣ ኢንተርኔትና ኬብል ያለው

Basement ለመከራየት (703)992 3550

ይደውሉ፡፡

Alexandria, VA Beauregard

& N. Morgan ለትራስፖርት አመቺ ሁለት

መኝታ ቤትና ሁለት መታጠቢያ ያለው

አፓርትመንት ውስጥ ኢንተርኔት ያለው

አንድ መኝታ ቤት ለመከራየት (240) 421

8061 ይደውሉ::

Alexanderia, VA 4410

Groom bridge way ላይ የራሱ መታጠቢያ

ያለው ፈርሺድ የሆነ ክፍል ለመከራየት

(703)229 3250 ይደውሉ፡፡

Springfield, VA Backlick

Rd. & Vila Park ላይ ለSpringfield Mall

& Metro ቅርብ መውጫ፣ ማብሰያ ሳሎን፣

መኝታ ቤትና መታጠቢያ ያለው Basement

(571) 276 6337 ወይንም (703)470

9483 ይደውሉ፡፡

Alexandria, VA Richmond

Hwy. ላይ ለWalmart ቅርብ የሆነ

Basement ለመከራየት (703)509 5998

ይደውሉ፡፡

Alexandria, VA 225 S.

Whiting St. ላይ Landmark Mall አካባቢ

የሚከራይ ቤት

ልጆዎትንእንንከባከብልዎ

የራሱ መታጠቢያ ኢንተርኔትና ኬብል ያለው

አንድ መኝታ ቤት ለመከራየት (301)841

5135 ይደውሉ፡፡

Arlington, VA George

Mason & Colombus St. ላይ ሶስት

መኝታ ቤት ያለው Basement እያንዳንዱን

ክፍል $550 (ዲፖዞት $500) ለመከራየት

(703)933 0267 ይደውሉ፡፡

Arlington, VA አፓርትመንት

ወስጥ አንድ መኝታ ቤት ለማታጨስና

ለማትጠጣ ሴት እናከራያለን፡፡ በ(571)251

0011 ይደውሉ፡፡

Alexandria, VA Holmes

Park Pkw. & Duke St. አካባቢ Landmark

አጠገብ የራሱ መታጠቢያና ኢንተርኔት ያለው

ፈርኒሽዱ የሆነ መኝታ ቤት $750 ይከራያል፡፡

በ(571)338 7845 ይደውሉ፡፡

Alexandria, VA Landmark

Mall አካባቢ የራሱ መታጠቢያ ያለው አንድ

መኝታ ቤት አለን፡፡ ለመከራየት በ(571)215

1088 ይደውሉ፡፡

Lorton, VA Richmond

Hwy ላይ አውቶብስ መሳፈሪያ ቅርብ የሆነ፣

የራሱ መውጫ ያለው፣ ኢንተርኔትና ኬብል

ያለው ፈርኒሽድ የሆነ ሁለት ክፍል ያለው

Basement ለመከራየት (571) 309 ወይም

(703) 339 6422 ይደውሉ፡፡

Woodbridge, VA Lake Ridge

አካባ የራሱ መውጫ፣ ማብሰያ፣ መታጠቢያ፣

ኢንተርኔትና ኬብል ያለው Basement ውስጥ

ሁለት መኝታ ቤቶች አሉት ለመከራየት

(703)209 2557 ይደውሉ፡፡

Alexandria, VA 6300 S.

King Hwy ላይ ለHuntigton Metro ቅርብ

የሆነ የጋራ ማብሰያ ያለው ክፍል ለማታጨስ

ሴት እናከራያለን፡ በ(703)608 3726

ይደውሉልን፡፡

Alexandria, VA 314 S.

Whiting St. ላይ ሁለት መኝታ ቤትና ሁለት

መታጠቢያ ያለው አፓርትመንት ወስጥ አንዱ

መኝታ ቤት ለማያጨስ ሰው እናከራያለን፡፡

በ(571)490 1372 ይደውሉ፡፡

Annandale, VA ሲንግል

ሃውስ ውስጥ ጠራሱ መውጫ፣ የጋራ

መታጠቢያ፣ ኬብልና ኢንተርኔት ያለው

አንድ መኝታ ቤት ለወንድ እናከራያለን፡

፡ በ(703)300 251 ደውሉልን፡፡

N. Springfield, VA Edsall

Rd. & Backlick አካባቢ ለትራስፖርትና

ሾፒንግ አመቺ የሆነ የጋራ መታጠቢያ

ያለው አንድ መኝታ ቤት Basement

ውስጥ እናከራያለን፡፡ በ(703)981 2527

ደውሉልን::

Alexandria, VA Seminary

Rd. & Kenmore ላይ ለመኝታ ቤት

ያለው አፓርትመንት ውስጥ መኝታ ቤት

ለአንድ ወይም ለሁለት ሰው እናከራያለን፡

፡ በ(571)471 4158 ይደውሉ፡፡

Arlington, VA Troy St. &

26 St. ከPentagon City ሁለት ደቂቃ

ለትራስፖርት አመቺ የሆነ የራሱ መውጫ፣

ማብሰያ፣ መታጠቢያና ኢንተርኔት ያለው

Basement እናከራያለን፡፡ በ(425)829

2220 ይደውሉልን፡፡

አድራሻው አሌክሳንደሪያ፣ ቨርጂኒያ በሆነ ነጠላ ቤት ውስጥ የሚገኝ ፎቅ ላይ ያሉ ሁለት

ፈርኒሽድ ክፍሎች ውስጥ የሚከተሉት አገልግሎቶች ያሏቸው ማለትም፤

አልጋ፣ ፍራሽ፣ አንሶላ፣ አልጋ ልብስ፣ ትራስ፣ ድሬሰር(ቁምሳጥን)፣

ሰፋ ያለውን መኝታ ክፍል በ$650 እንዲሁም አነስ ያለውን በ$625 እናከራያለን፡፡ ከዚህም

በተጨማሪ ምድር ቤት ውስጥ የሚገኙ ፈርኒሽድ መኝታ ክፍሎች ሰፋ ያለውን በወር $625 አነስ

ያለው ደግሞ በ$600 እናከራያለን፡፡ ተጨማሪ ክፍያ በማድረግ አንዱን ክፍል በጋራ ለመከራየት

ይቻላል፡፡

አድራሻው ለሃኒንግተንና ለቫዶርን ሜትሮ ቅርብ ከመሆኑም በላይ ነፃ የኢንተርኔት አገልግሎት

ከጋራ መታጠቢያ ክፍልና ፍሪጅ ጋር አካቷል:: እንዲሁም የተሟላ ቁሳቁስ ያው ወጥቤት በጋራ

ከባለቤቱቹ ጋር አብረው የሚጠቀሙበት ተዘጋጅቷል፡፡ የልብስ ማጠቢያ ማድረቂያ በጋራ ሲሆን

ክፍሎቹንና የመጸዳጃ ቤቱን የጽዳት ወጭና እንዲሁም የመጸዳጃ ቤቱን መገልገያዎች ወጭዎችን

ባለቤቶቹ በነጻ ይሸፍናሉ፡፡

የአንድ ወር ቅድሚያ የቤት ኪራይ መያዣ እንጠይቃለን፡፡ ቢያንስ የ3ወራት የኪራ ውል

እናስፈርማለን፡፡

ለመከራየት የሚፈልጉ በ703-329-0575 ይደውሉ፡፡

Ave. አካባቢ በሚገኘው ቤቴ

ውስጥ ልጆችዎን ከልጄ ጋር

እጠብቃለሁ፡፡ (571)295 0515

ይደውሉ፡፡

በቤትዎ ውስጥ

ልጆችዎን እጠብቃለሁ፡፡

(301)674 1203 ይደውሉ፡፡

Alexandria, VA

22304 በሚገኘው ቤቴ

ውስጥ ልጆችዎን እንደ

ልጆቼ እጠብቃለሁ፡፡

(571)551 1773 ይደውሉ፡፡

Wheaton, MD

Georgia Ave, ላይ

በሚገኘው ቤቴ ውስጥ

ልጆችዎን እንደ ልጆቼ

በፍቅርና በእንክብካቤ

እጠብቃለሁ፡፡ (301)526

6831 ይደውሉ፡፡

ልዩ ማስታወቂያ

የሚከራይ ቤትየኢትዮጵያ የሎው ፔጅ የማስታወቂያ (Marketing)ሴልስ ባለሞያ አወዳድሮ

ለመቅጠር ይፈልጋል:: በዚህ ሞያ ልምድ ካለዋት ዛሬውኑ

ይደውሉልን::

202-387-9302/3

Page 14: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 14ባህል

(1)

በጎንደር ቤተ መንግስት የአጼ ቴዎድሮስ ባለቤት

እቴጌ፣ ለመኳንቶቻቸው ታላቅ ግብዣ አድርገው ሳሉ፣

ለተጋባዦች አንድ ጥብቅ የሆነ ትዕዛዝ ያስተላልፋሉ፤

“ትዕዛዙም ማንም ሰው ከግብዣው አዳራሽ ለሽንት

እንዳይወጣ” በሚል፡፡

ተበላ፣ ተጠጣ አንድ ፊኛው አልችል ያለ ሰው ወደ አለቃ

ገብርሐና ተጠግቶ ጠየቃቸው፡፡

“አለቃ ምንው ዛሬ ዘዴ ጠፋብህሳ፣ ከዚህ ጉድ

አትገላግለንም ወይ?” አላቸው

አለቃ አሰብ አደረጉና ወደ ንግስቲቱ አመሩ፣

“ንግሥት ሆይ፣ 5መቶ እና 5መቶ ስንት ነው” ብለው ጥያቄ

አቀረቡ፡፡ ንግስቲቱም ፈጠን ብለው ምላሽ ሰጥዋቸው፡፡

“5መቶና 5መቶ…ሺ ነዋ” ብለው መልስ ይሰጣሉ፡፡

ከንግስቲቱ አፍ የወጣው ቃል መኳንንቱን ፈወሳቸው፡፡

ከአለቃ ገብረሐና ተረት

(2)

አለቃ ገብረሐና ብዙ ጊዜ ከወጣት ሴቶች ጋር መዳራት

ያበዛሉ፡፡ ጃንሆይ ይህን ሰው ዛሬ ቅዳሜ ይማግጥ እንደሆን

ጠብቃችሁ ንገሩኝ ብለው ለጠባቂዎ ትዛዝ ሰጡ፡፡

እንደተፈራው አለቃ ገብርሐና ከኮርዶች ጋር ተጫውተው

እሁድ ጠዋት ወደ ሥላሴ ቤተክርስቲያን ለማስቀደስ

ቤተክርስቲያል ሊገቡ ሲሉ፣ ዛሬ መግባት አይችሉም

ይሏቸዋል ጠባቂ ዘበኛ፡፡

እሳቸውም የተከለከሉበትን ምክንያት ሲጠይቁ ቅዳሜ

ከሴት ቤት ሲጫወቱ እንዳደሩ አይተነዎታል ስለዚህ

አይገቡም” አላቸው፡፡

እሳቸው ጠባቂ ያደረገባቸውን ተንኮል ሳይክዱ፤ በሴቶች

በር ይሄዱና በመቋሚያቸው እየተከላከሉ አንደ ሴት

ከቤተክርስቲያን አይገባም? ብለው ከለከሉዋቸው፡፡

ሴቶችም “ምክንያቱ ምንድን ነው?” ሲሉ ጥያቄ

አቀረቡላቸው፡፡

አለቃ ገብረሐና “እኔ አንድ ጊዜ አጥቅሼ በወጣሁ

የተከለከልኩ፣ እናንተ ሁሉንም ይዛችሁ መግባት

አትችሉም” ብለው ገለጹላቸው፡፡

ጃንሆይም “አባ ሐና ሴቶችን ቤተክርስቲያን ገብተው

እንዳያስቀድሱ ከለከሉ” ብለው ሲነግሯቸው

“እሱም ይግባ፣ ሴቶችም ይግቡ” ተባለ፡፡

መኰንን ውቤ (ዲሲ)Although Ethiopia is the only country in Africa to escape colonialism, besides Liberia’s establishment by former slaves

from the US, it has been attacked by various nations throughout its two thousand or so year history. Since the sixteenth century Ethiopia has had to defend itself from Islamic, Turkish, and Egyptian incursions. After Ethiopia defeated Italy in the Battle of Adwa in 1896, Italy sought revenge and again attempted to defeat the Ethiopians and regain its former glory.

Having joined the League of Nations after WWI, Emperor Haile Selassie protested Italy’s intention to take Ethiopia. Unfortunately, Britain and France refused to intervene as they were worried Italy might take up with Germany in the prelude to WWII. When their fears came true it was too late. With an embargo of arms to Ethiopia, Italy would spend the next five years dropping mustard gas and committed untold atrocities and massacres on the defiant Ethiopians.

Active resistance among Ethiopian patriots continued throughout the occupation. Close to 30,000 of the western educated Ethiopians were summarily executed to thwart the potential of an organized counterforce. Ethiopian churches were destroyed along with thousands of monks, priests, deacons and bishops who were also executed for providing encouragement to the patriots. The total number of civilian Ethiopian deaths resulting from the Italian punitive actions were placed by some at approximately a quarter of a million but postwar estimation of casualties was considerably higher.

With few notable exceptions, most of the

patriots in Ethiopia and loyalists to the imperial family, continued to resist the idea of permanent Italian occupation. The guerilla warfare by the patriots numbered close to 300,000, forcibly transformed the occupation into more or less a garrison presence. Let us not forget the important role women played as spies, suppliers of war materials, and even strategists during the long campaign. While in exile in Britain, Emperor Selassie was appealing to the Western democracies to embrace his cause, along with numerous publications from throughout the world on the side of Ethiopia.

When Italy entered WWII on the side of the Axis powers, Britain launched a military campaign including soldiers from Ethiopia, Nigeria, Ghana, the Sudan, and southern Africa. With the aid of pamphlets and newspapers and the proliferation of oral traditions, patriotic songs and poetry, Ethiopia not only resurrected its past histories on behalf of the new cause for victory, but also launched a new clarion call for national unity and development.

On January 20, 1941, Haile Selassie arrived in Ethiopia and consolidated the local resistance groups under his command and by the end of the year Ethiopia would eject Italy from its land. It would take him another three years to wrestle Ethiopia from British designs and declare its independence. Ethiopia would be the only country not included in receiving relief from the Post World War Crimes Tribunal. However, Italy’s invasion of Ethiopia became the catalyst for international anti-colonial activities and the domestic civil rights and anti-racial movements in Africa, Europe and the Americas.

Ethiopian Patriots Victory Day

By Andrew Laurence

‘Let us not forget the important role women played as spies, suppliers of war materials, and even strategists during the long campaign.’

Page 15: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 15ጤና

ጭንቀት ምንድን ነው?ጭንቀት በአካባቢያችን ያለ ነገር ላይ ለውጥ ሲመጣ ሰውነታችን የሚያሳየው መጠበብና መሸማቀቅ ነው::

ጥሩ ጭንቀትና መጥፎ ጭንቀቶች አሉ፡፡ ጥሩ ጭንቀት የምንለው ለምሳሌ በስራችን ላይ ሆነን ተጨንቀን ብዙ ሰርተን እድገር የምናገኝበት አይነት ሲሆን፤ መጥፎ ጭንቀት ደግሞ ከሰው ጋር ተጣልተን የምጨነቀው አይነት ጭንቀት ነው፡፡ቤተሰብ፣ ገንዘብ፣ ስራ እና ትምህርት በጣም የተለመዱ የጭንቀት መነሻ ምክንያቶች ናቸው:: ብዙ ጭንቀት ለህመምና ከወዳጅና ቤተሰብ ጋር መጠጥ ሊዳርግ ይችላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ጭንቀት የበዛበት ነገር በተደጋጋሚ ሲገጥማቸው በጣም ቁጡ እና ጯሂ ይሆናሉ፡፡

አንዳንድ የጭንቀት ምልክቶች ምንድን ናቸው?የእራስ ምታት እና የጀርባ ህመምየእንቅልፍ ማጣትመበሳጨትና መነጫነጭአንድ ነገር ላይ አተኩሮ የመስራት ችግርማልቀስ

ሰዎችን ማግለልየሆድ ህመም እና ቃር ሽፍታከፍተኛ የደም ግፊት፣ የልብ ህመም እና የልብ ድካምጭንቀትን እንዴተ ማስወገድና ማከም ይችላሉ?ሁልጊዜ የአካል እንቅስቃሴ (ስፖርት) ያድርጉ፡- በቀን ውስጥ ከ 20 እስከ 30 ደቂቃ የሚቆይ ስፖርት (የእግር ጉዞ፣ ሩጫ፣ ወይም ቁጭ ብድግ) አእምሮን ሊያፀዳ እና ለማሰብም ጊዜ ሊሰጦት ይችላል፡፡

የመንፈስ እረፍት፡- በጣም ዘና የሚያደር ሙዚቃ ይክፈቱና አይኖን ከ 10 እስከ 20 ደቂቃ ድረስ ይክደኑ፡፡ በረጅሙም እየተነፈሱ አእምሮዎን ከሀሳብ ነፃ ያድርጉ፡፡ በእንግሊዘኛው አጠራር ሜዲቴሽን እንለዋለን፡፡ስሜቶን በወረቀት ላይ ያስፍሩ ወይም ለሰው ያዋዩ፡- የሚሰማዎትን ስሜት በአጠቃለይ በወረቀት ላይ ማስፈር ወይም ለሚያምኑት ሰው ማማከር/ ማዋየት ለሚያስጨንቆ ነገር መፍትሄ እንዲያገኙለት ሊረዳዎ ይችላል፡፡ ይህ ባይሆን እንኳን የቀልሎታል፡፡ጤናማ አመጋገብን ይከተሉ፡- ጤናማ ምግቦችን መመገብ ውስጦ ጥሩ ስሜት እንዲኖሮት ይረዳል፡፡እምቢ/አይሆንም ማለትን ይወቁ፡- ይሉኝታ አያጥቃዎች፡፡ ማድረግ ከሚችት በላይ በይሉኝታ ለማድረግ አይጣሩ፡፡

ጭንቀት

የጀርባ ሕመም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የኅብረተሰባችን ክፍል እያጠቃ የሚገኝ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ በአብዛኛው ይህ ሕመም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የተለመደ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ግን በወጣትነት የዕድሜ ክልል ባሉ ሰዎች ላይም እየተበራከተ ይገኛል፡፡

የጀርባ ሕመም ለምን ይከሰታል?

የጀርባ ሕመም ከማንኛቸውም የሰው ጀርባን ከሚሰሩ የሰውንት ክፍሎች ሊነሳ ይችላል፡፡ እነዚህም፤የጀርባ ጡንቻዎች መሳሳብ (መሸማቀቅ)ከባድ ዕቃን ያለአግባብ ለማንሳት መሞከር ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ እንቅስቃሴየዲስክ መንሸራተትየመገጣጠሚያ ላይ ኢንፌክሽንየአጥንት መሳሳት

የጀርባ ሕመም ከዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታችን ጋር ይያያዛል፡፡

ከባድ ዕቃን በመግፋት ወይንም በመጎተትከባድ ዕቃን በመሸከም ወይም በማንሳትለብዙ ሰዓት በመቆምለብዙ ሰዓታት አጎንብሶ መቀመጥያለ ዕረፍት ለብዙ ሰዓታት መኪና ማሽከርከር

የጀርባ ሕመምን እንዴት መከላከል ይቻላል?

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፡- ኤሮቢክስ የሚባለውን የስፖርት ዓይነት መሥራት የሰውነታችንን አቅም ከመጨመር ባለፈ ክብደታችንን በመቀነስ የጀርባ ሕመም ይከላከላል፡፡ሲጋራ ማጤስን ማቆም፡- ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሲጋራን የሚያጤሱ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ለጀርባ ሕመምተጋላጭ ናቸው፡፡የሰውንት ክብደት መቀነስ፡- የሰውነት ክብደታቸው የጨመረ ሰዎች የጀርባ ሕመም ይኖርባቸዋል፡፡የተስተካከለ አቀማመጥ፡- በምንቀመጥበት ጊዜ ጀርባችንን የሚደግፍ እና እጃችንን የምናሳርፍበት ቀጥ ያለ አቀማመጥ መያዝ፡፡የተስተካከለ አቋቋም፡- በምንቆምበት ጊዜ የሰውነት ክብደታችን በሁለቱም እግሮቻችን በእኩል መጠን እንዲያርፍ ማድርግ እና ቀጥ ብለን ሳንቆለመም መቆም፡፡ክብደት ያላቸውን ዕቃዎች በአግባቡ ማንሳት፡- ክብደት ያላቸውን በምናነሳበት ጊዜ ክብደቱን ከወገባችን/ከጀርባችን ይልቅ በእግሮቻችን ላይ እንዲያርፍ ማድርግ ተገቢ ነው፡፡ ዕቃዎችን በምናንቀሳቅስበት ጊዜ ከመጎተት ይልቅ መግፋትተመራጭ ነው፡፡ጫማ፡- የጀርባ ሕመም እንዳይሰማን የምንጫማቸው ጫማዎች ምቹ ሊሆኑ ይገባል፡፡መኪና በምንሽከረክርበት ወቅት ጀርባችንን መደገፍ፡፡ ለረጅም ሰዓት የምናሽከረክር ከሆነ በየማሃሉ ከመኪና በመውረድ ሰውነትን ማንሳሰቀስና ዕረፍት መውሰድ ተገቢ ነው፡፡የአልጋ ፍራሽ ምቾት፡- የምንተኛበት የአልጋ ፍራሽ ቀጥ ያለ መሆን አለበት፡፡ የጀርባ ሕመም ከባድ የሆኑ የጤና ችግሮች ምልክት ሊሆን ስለሚችል በቀላሉ ሊመለከቱት አይገባም፡፡በመሆኑም ከዚህ በታች የሚጠቀሱት ተጫማሪ ምልክቶች ካሉ ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡እነዚህም፤በድንገተኛ የመኪና አደጋ ወይንም መውደቅን ተከትሎ የመጣ የጀርባ ሕመምከወር በላይ የቆየ እና እየባሰ የመጣ የጀርባ ሕመምበሕመም ማስታገሻ እና ዕረፍት በመውሰድ ለውጥ የማያመጣ የጀርባ ሕመምከወገብ በታች የመደንዘዝ ስሜትደም የቀላቀለ ሽንት መኖርከፍተኛ ትኩሳት መኖር እና ሆድ ሕመም መሰማት ናቸው፡፡ በቤቶ ሆነው ሊያከናውኑት የሚችሉትን ይህን ቀላል የ አካል ብቃት እንቅስቃሴ በዚህ አድራሻ ማግኘት ይችላሉ።

የጀርባ ሕመም

ምንጭ ማኅደረ ጤና

Page 16: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 16

Page 17: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 17ለልጆች

ልጆች ፊደል እንማር

“ልጅነቴ፣ ልጅነቴ ማርና ወተቴ”

ጨዋታ

By Feker belay

ከጥናት በኋላ ከጓደኛዬ ጋር ገመድ እየዘለልን እንጫዋታለን

ፊቴን ታጥቤ ቁርሴን በልቼ ወደ ትምህርት ቤት ከእህቴ ጋር እሄደለሁ

የእኔ ቢራቢሮ ደስ ትለኛለች

[email protected]

ተረት ተረት?!አንደ ጊዜ አይጦች ጥጋብ ተሰማቸውና ቅጡ

ጠፍቶባቸው

“ማን አለብን” በማለት ይንቀባረሩና ሜዳ ለሜዳ ይዘሉ

ነበር:: ጊዜው መከር እንደመሆኑ መጠን ገበሬ የዘራውን

እህል አጭዶ ሰብስቦ እከመረው ስር መኖሪያቸውን

ቆፍረው በዛ ክመር ስር በሰላም ከነቤተሰባቸው

ተቀምጠው ይኖራሉ፡፡

እራብ እንዳይነካቸው ያ ትጉህ ገበሬ ለፍቶ በበጋ ከአፈር፣

በክረምት ከጭቃ፣ ሲያሼት ከዝንጀሮ፣ ካሳማና ከጃርት

ከሰማይ ወፎች ጋር ታግሎ የሰበሰበውን ያላንዳች ሀሳብ

እየበሉ ሲኖሩ ጥጋባቸው በዝቶ

“ማን ይነካናል፤ ማንስ ይደፍረናል” እያሉ ይፎክሩና

ይሸልሉ ጀመር፡፡

ታዲያ አንድ ቀን የነኝህ አይጦች ምቾት እዳር

ሆኖ የሚመለከት አንድ የዱር ድመት ተናደደና

“እንዴት ቢዳፈሩና ቢንቁኝ ነው ማን አለብን ብለው

የሚንቀባረሩት እስቲ ወዳጅ መስዬ እቤታቸው ልግባና

እንዴት እንደሚቀበሉኝ ልመልከት” ብሎ ጓደቸው

ሄደና

አይጥና ድመት

“እዚህ ቤት እንደምን ዋላችሁ?” ሲል ሰላምታ ሰጠ፡፡

እናት አይጥም “እንደምን ዋሉ አቶ ድመት፣ ዛሬስ ከየት

መጡ ይግቡ ይግቡ ቤት ለእንግዳ ነው እመደብ ላይ

ይቀመጡ” አለችው፡፡

“እንዳው በዚህ ሳልፍ ሳልጠይቃችሁ አላልፍም

ብዬ ነው ባለቤትሽ የለም እንዴ?” ብሎ ሲጠይቃት

ልጆቹ በዚህን ጊዜ ከየጉድጓዳቸው ብቅ ብቅ ብለው

እናታቸውን ከበው ቁጭ ቁጭ አሉ፡፡

አቶ ድመትም የልጆቹን ብዛት እያየ በመደነቅ ሳቅ ሳቅ

እያለ

“ለመሆኑ እነኝህ ሁሉ የናንተ ልጆች ናቸው?” ብሎ

ጠየቃት:: እናት አይጥም

“አዎ እዙህ ክምር ከመጣን ወዲህ ብዙ እረብተናል

የሚደፍረንም የለም፡፡” እያለች አለመደፈሯን ትናገር

ጀመር:: በዚህ ጊዜ አቶ ድመትም በጉልበታቸው

መመካታቸውን ካደመጠ በኋላ

“በሉ ደህና ዋሉ፡፡” ብሎ ወጥቶ ሄደ፡፡

የአይጦች አባት ከቤቱ ውስጥ ድመቱ ሲወጣ በሩቁ

አይቶት ኑሮ ሲገሰግስ እጎሬው ገባና ሚስቱን በኩራትና

በጉብዝና በተመላው አንደበት እንዲህ ሲል ጠየቃት፡፡

“ማነው እኔ ቤት ውስጥ ደፍሮ የገባው በይ?” ብሎ

ጠየቃት እሷም በፍርሃት

“እረ አቶ ድመት ነው፡፡” አለችው እሱም መለሰና

“ታዲያ ምን አለሽ በይ?” አላት፡፡

“እረ ምንም አላለኝ፡፡ ብቻ እነዚህ ሁሉ ልጆች የእናንተ

ናቸው፡፡” ብሎ በትህትና እጅ ነስቶኝ ሄደ በዚህ ጊዜ አቶ

አይጥ ተቆትቶ

“እንዴት ቢደፍረኝ ነው እቤት ውስጥ ገብቶ ልጆቼን

በአይኑ ሙሉ ገምግሞ የሄደው ቆይ ብቻ ያጋጥመኝ

አሳየዋለሁ” ብሎ ፎክሮ ከቤት ወጣ እንዳለ አቶ ድመት

እበሩ ጋር ቆሞ ያዳምጠው ስለነበረ ብቅ ሲል ማጅራቱን

አንቆ ወደ ሜዳ ወስዶ እንደ ኳስ አጎኖ ተጫወተበት፡፡

“ስለወንድ ልጅ አምላክ ተወኝ” እያለ ሲለምነው

እንክትከት ዱቁስቁስ አድርጎ በላው፡፡ ቀጥሎም ወደ

አቶ አይጥ ቤተሰቦች ጋ ሄዶ ከእናት እስከ ልጆቹ ከአይት

እስከ ቅድመ አያት ሙጥጥ እድርጎ በልቶ ምንም

እንዳልቀምስ አፋን እየጠራረገ ወደ ጫካው ገባ፡፡

ልጆች “ማን አለብኝ” “ማን ይነካኛል” “ማንስ

ይደፍረኛል” ብሎ ከማለት ይልቅ

“ይሄንን ባደርግ ይሰማብኛልን፣ ጥፋት ይሆናል” ብሎ

ማሰብንና ማመዛዘን ስለሚገባው ያለሀሳብ በግድየለሽ

ከመናገር መቆጠብን ተግባራችሁ እንዲሆን አድርጉ፡፡

“አመል ያወጣል ከመሀል” እንደሚባለው ሁሉ

እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፡፡

ስሄድ አገኘኋት ስመለስ አጣኋት? = ጤዛ

እንቆቅልህ? ምን አውቅልህ?

እግር እያለው ወንዝ አይሻገር? = አልጋ

ትንሽ ዕቃ ከገደል ተጣብቃ? = ጆሮ

Page 18: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ገጽ 18ጥበብ

ያጀብህ እንባዬናፍቆቴ!!

‹‹ደህና ሁኝ ልትለኝ ቆመሃል ከፊቴ?ቁርጥ መሆኑ ነው

አንተም የመሄድህ እኔም የመቅረቴ፡፡እንዲህ ከሆነማ!

ስንሰነባበት ከአንገት ከደረትህ ያፈሰስኩት እንባ፣

አጅቦ ያድርስህ ሀገርህ እስክትገባ፡፡አንተ የሰው ሀገር ሰው

ከቶ ሳላስብህ ሳላልምህ ደርሰህ፣ የልቤን ስብራት በፍቅርህ ጠግነህ፣

የጨለማ ህይወቴን በብርሃን ተክተህ፡፡ሆነኸኝ ነበረ ደስታ ፈንጠዝያ፣

የህይወቴን ክፍተት ጎዶሎዬን መሙያ፡፡ ግና….

ታይቶ እንደሚጠፋ የጠዋቷ ፀሃይ ነው የተፈረደ

ጅምሩ ፍቅራችን እንዲህ ሆኖ እንዳናይማንን እከሳለሁ? ከማ እጋፋለሁ?

ቁርጥ ከሆነማ!እኔም የመቅረቴ አንተም የመሄድህ፣

‹‹ደህና ሁኝ ስትለኝ››ያፈሰስኩት እንባ ከአንገት ከደረትህ፣

ሀገርህ እስትገባ አጅቦ ያድርስህ!

አጭር ልቦለድ

በህሊና ተፈራ 1996 ተጻፈ (እንደጠዋት ጀምበር ብቅ ብሎ የጠፋ የፍቅር

አጋር ለገጠማቸው)

ያማልእና እንደነገርኩሽ የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ፡

የነፍሰጡርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ፡ባልታሰበ ናዳ ተመቶ እንደመድቀቅ፡

ከተስፋ ጉልላት ተገፍቶ እንደመውደቅ።

ታምር በበዛበት በዚች ቡዋልተኛ አለም፡

ከዚህ የበለጠ ምንም ህመም የለም።

አውቶብሱ ያማል፡

ሚኒባሱ ያማል፡

ላዳ ታክሲው ያማል፡

የማይጎድል የሰው ጎርፍ ደራሽ መእበሉ፡

የእንባ ቅጥልጥሉ፡

ምን ብዬ ልንገርሽ ያማል ይሄ ሁሉ።

እና እደነገርኩሽ የሚወዱት ሰው ቀጠሮ ካረፈደ፡

የሚያፈቅሩት ሰው ቀጠሮ ካረፈደ።

ነገር ተበላሸ ህመም ተወለደ ጨጓራ በገነ፡

እሳት በእንፋሎት መልክ በኧታ ተነነ፡

የሚሆነው ሳይሆን የማየሆነው ሆነ።

ሁሉ ተቀይሮ ተተካ በሲቃ፡

ምን ብዬ ልንገርሽ ይህም ያማል በቃ።

ወጪው ተራማጁ፡

አስመሳይ ሰጋጁ።

ፀሀዩ ዝናቡ

የ ለምን ምክንያት የ ለምን ሰበቡ፡

ተቆራጭ አበባ ሊቆረጥ ማበቡ፡

ውል የለሽ ደመና ተራራ መክበቡ፡

እልፍ አእላፋት ኮኮብ ጨረቃን ማጀቡ።

ደሞ ለእርሷ ግጥም እናትዋን ጨረቃ፡

ምን ብዬ ልንገርሽ ይህም ያማል በቃ።

እና እደነገርኩሽ ጉንጭ የማትሞላ ኬክ አስር ብር የሸጠ፡

የካፌ አሳላፊ ወደኔ አፈጠጠ

ዘይት የነካውን መንታ እጁን አጣምሮ፡

ምን ልታዘዝ ይላል ቁልቁል አቀርቅሮ።

ምን ልታዘዝ? ይላል ፡እንዴት ቅጥሉ ሰው ቅጥሉን ሰው ያዛል።

ማኪያቶ ልዘዝ?

ካፑቺኖ ልዘዝ?

ጥቁር ቡና ልዘዝ?

ለምን ሰው አላዝም?

መታዘዝ መናዘዝ እርግማን የሆነውም።

ካፌውን ሲያሳልፍ ፡

እራሱ ግን የሚያልፍ።

ቁልቁል አቀርቅሮ፡

ሞቱን በአንገቱ ቀብሮ።

ምን ልታዘዝ? ይላል፡

1 ማካያቶ ከ 1 እርሷዋ ጋር ልበል?

1 ካፑቺኖ ከ 1 እርሷዋ ጋር ልበል?

ከ ጥቁር ቡና ጋር እርሷዋን አምጣ ልበል?

ተይ አታስለፍልፊኝ ይህ ሁሉ ያማል፡

የላስቲክ አበባ የአርቲቡርቲ ስዕል፡

የጭቃ እሾህ ወግቶት እዥ ያወጣ ቁስል

ትልቁ ነቀዝ ሰው የማንቀዙን ያህል፡

ብዙ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል።

እና እንደነገርኩሽ ላንቺ የያዝኩት አበባ መጠውለግ

አመጣ፡

ፀሐይ ገባ ወጣ፡

ዝናብ ቀረት መጣ።

ጨረቃ የለችም እናትዋን ስላልኩዋት?

ደግሜ ሰድቤ ሺ አመት እንዳይገርማት።

እናትዋን እናትዋን ጨረቃ፡

ተይ አታስለፍልፊኝ ይህም ያማል በቃ።

ግን እኔ አንቺን ስወድሽ

እኔ አንቺን ስወድሽ ፡

ይህን ሁሉ ችዬ ነው የምጠብቅሽ።

ቢሆንም ግን ያማል።

(ሰለሞን ሳህለ)

በጉለሌ የነበረው የታወቀ ዶሮ ነጋዴ ማነው ብለው ከገፈርሳ እስከ ደጃዝማች ይገዙ ሰፈር ለጠየቁ ሰዎች፤ ተበጀ ሰካራሙ

ተበጀ ዶሮ ነጋዴው፤ ተበጀ ነው ብለው ይነግሯቸዋል፡፡

የሕይወቱ ታሪክ ፍፁም ገድል ነው፡፡ ጢም ያለው ሽማግሌ ሰው ነው፡፡ ራሱን ጠጉር ውሃ ወይም መቀስ ነክቶት

አያውቅም፡፡ ማለዳ አይናገርም፡፡ በጠርሙስ የከመረውን ከጠጣ በኋላ ሲራገም ወይም ሲሳደብ ሲፈክር ወይም ሲያቅራራ

ድምጡ ከፈረንጅ ውሻ ድምጥ ይወፍራል፡፡ ቢያውቀውም ባያውቀውም ላገኝው ሁሉ ማታ ሰላምታ ይሰጣል፡፡

ቢያውቀውም ባያውቀውም ካገኝው ሁል ጋር ማታ ይስቃል::

ቢውቀውም ባያውቀውም የሰላምታው አይነት እንደ ወታደር

ወይም እንደ ሲቪል ቢሆን ለእርሱ እንደተመቸው ነው፡፡ ከሰላምታው ጋር ድምጥ ትሰማለችሁ፡፡ ከአፉ ከሚወጣው

ከሚወጣው ግን አንድ ቃል መለየት አትችሉም፡፡

ቡን በተፈላ ጊዜ በጉለሌ በየምድጃው ሥር የሰካራም ተረት በየተጫወተ ሰው ሁሉ የተናገረ በተበጀ ላይ ነው፡፡ መልኩን

አይተውት ያላወቁት ባልቴቶች እንኳ ከፍንጃል ቡን ፉት እያሉየሌላውን ሰካራም ተረት በተበጀ ላይ ያላክኩት ነበር፡፡ይህ

እውነት ነበር፡፡ በጠባዩ ከተባለለት የባሰ ሰካራም ይሁን ወይም የጉለሌ ባህር ዛፍ ውስጥ ወጥቶ እንደ አዲስ እንግዳ ሰው

ሆኖ ለአዲስ አበባ ታይቷል፡፡

ከዱሮ የእንጨት ጉሙሩክ አጠገብ ወደ ምሥራቅ ሲል ሲል ካለው ወንዝ ማዶ ድልድዩን ወደ ምሥራው ተሻግሮ

መጀመሪያ የሚገኝው አነስተኛ ሳር ክዳን ቤት የተበጀ ቤት ማለት ያ ነው፡፡ በዚያ በቤቱ በዚያ በጉለሌ በሠፈሩ ኖረ፡፡

እንጨቱን ተሸክሞ አፈሩን ቆፍሮ ቤቱን የሰራው እርሱ ነው፡፡ ዋጋ ከፍሎ አስከድኖታል፡፡

ተበጀን ኩራት ተሰማው፡፡ ቆይቶ ደግሞ አይኖቹ እንባ አዘሉ፡፡ በጉንጩም የእንባ ዘለላ ወረደው፡፡ በግራ እጁ መዳፍ

ከጉንጩ የተንከባለለውን እንባ ጨፈለቀው፡፡ ዓይኖቹ እንባ ያፈሰሱ ለራሱ ጎጆ ስላለው ነው፡፡ ሊነገር በማይችል ደስታ ልቡ

ተለውስዋል፡፡

ዝናም ያባረራቸው ም ከቤቱ ጥግ ሊያጠለሉ ይችላሉ፡፡ ቤት የእግዚአብሄር ነውና ውዥብ እንዳያገኛቸው ከቤት ውስጥ

ዝናቡ እስኪያባራ ይቆያሉ፡፡ ተበጀን ‹‹ ቤትህን ይባርክ ›› ሊሉት ነው፡፡

እንግዲህ መንገደኛው ሁሉ ‹‹ ይህ የማን ቤት ነው ? ብሎ ሲጠይቅ የተበጀ ሊባል ነው ›› አለ፡፡

ቀጥሎ ደግሞ ‹‹ ተበጀ የትኛው ነው ሲባል ዶሮ ነጋዴው ሊባል ነው ›› አለ፡፡

‹‹ ዶሮ ነጋዴው የትኛው ነው ›› ሲባል ያ የጉለሌው ሰካራም ሊባል ነው፡፡ አወይ፤ እኔ ተበጀ፤ ተበላሽቻለሁ አለና ደነገጠ፡፡

ከዚህ በኋላ ስለቤቱ ክብር እንኳ መጠጥ መተው ይገባኛል አለ ፡፡መጠጥ ለመተው ያሰበበት የመጀመሪያ ጊዜው ይህ ነው፡፡ ሰካራምነት ጉዳት መሆኑ ተሰምቶት እንደሆን ይናገር ስለ ቤት

ክብር ማለቱ ግን ወደ ዳር ይቆይ፡፡ ስለ ቤት ክብር ምን ያውቃል? ዶሮ ነጋዴው ተበጀ ሰካራሙ ተበጀ አይደለምን ?ሰካራሙ ተበጀ የሰራውን የገዛ ቤቱን ከፍቶ ገበና ኩራዙን አስቀምጦ ክብሪቱን ለመጫር ሲያወጣ በሐሳብ ተሰቅዞ እንደዚህ

አሰበ፡፡ መምረጥ አለብኝ፡፡ ከዚህ ቤት ያለው መጠጥ ሁሉ አንድ ሳይቀር እየወጣ ይፍሰስ፤ ከዚህ በኋላ ክብሪቱም ኩራዙም

በቤት ይደር፤ በአዲሱም ቤት ብርሃን ይዙርበት፡፡ አለዚያም በአዲሱ ቤት መጠጥ ይዙርበት፤ ኩራዙም ክብሪቱ ከቤት

ይውጣና ይፍሰስ፡፡ ሊደረግ የሚገባ ከሁለቱ አንዱ ነው እንጂ፤ በሰካራሙ ተበጀ ቤት መጠጥና እሳት በአንድነት ይህች

ውሸት አለና ሳቀ፡፡

ከሁለቱ አንዱ ለማድረግ ሳይቆርጥ መብራቱን አቃጠለና ተቀመጠ፡፡ እንደገና ደግሞ እንደዚህ አሰበ፡፡ አያድርገውና ዛሬ

ሰክሬ ይህ ቤት ቢቃጠልብኝ አመዱን አይቶ በሰካራሙ ተበጀ ላይ ለመሳቅ ድፍን ጉለሌ ነገ ከዚህ ነው የሚቆም ! ጉለሌ ምን

ባለኝ? ወሬ ከማቡካት በቀር ጉለሌ ምን ሥራ አለው; ለአዲስ አበባም የስድስት ወር መሳቂያ በሆንኩ ነበር፡፡ መንገድ

አላፊዎችም ነገ በዚህ ሲያልፉ አመዱን አይተው ይህ የተቃጠለው ቤት የማን ነበር ሲሉ የተበጀ ሊባል ነው፡፡ በሰካራሙ

ተበጀ ቤት መጠጥና እሳት ባንድነት ይህች ውሸት !ወደ ውጭ እንደ እርም ወርውሮት የነበረውን የመጠጥ ጠርሙስ ሁሉ በጨለማው ዳብሶ አንድ በአንድ ለቃቀማቸው፡፡

አንዱን ግን ቀና አደረገና ከአፍንጫው አስጠግቶ አሸተተው::

በጠርሙሱ ቅርፅ የመጠጡን አይነት አወቀው፡፡ ዊስኪ ነበርና

ስለዚህ ነው ሰው እንዳይሰማ ቀስ ብሎ የሳቀ፡፡ የጠርሙሱን ግማሽ ከጠጣ በኋላ ግን በአፉ ቡሽ ቢወትፍበት ለሳቁ መጠን

የለውም፡፡

‹‹ ጉለሌ ተኝቷልና ከዚሁ ከባሕር ዛፍ ሥር ቁጭ ብየ ብጠጣ የሚታዘበኝ የለም›› አለና አሰበ፡፡ እውነቱን ነው፡፡ ጉለሌስ

ተኝቶ ነበር ነገር ግን አሁን እርሱ ጠጥቶ የሰከረ እንደሆነ ጉለሌን ሊቀሰቅሰው ነው እርሱ ከጠጣ በጉለሌ ማን ይተኛል?ጠርሙሱን ከከፈተው በኋላ ብርጭቆ ያስፈልገው እንደነበር ትዝ አለው፡፡ ሶስት የሚሆን ደኅና ጉንጭ ጠርሙሱን ከአፉ

አስጠግቶ ጨለጠ፡፡ ከዚያ በኋላ የሚጠጣበት ብርጭቆ ሊያመጣ አሰበ ከዚያ በኋላ ደግሞ በሶስት ጉንጭ ምን ያህል

ጠርሙሱን ቀና አድርጎ በጨረቃዋ ተመለከተ፡፡ ‹‹ግማሹን ያህል ሰርጉጀዋለሁ›› አለና በሳቅ ፈነዳ፡፡ ‹‹ ለዚህችስ ብርጭቆ

ማምጣት አያሻም›› እያለ ጠርሙሱን አምቦጫቦጨው፡፡ በቀኝ ክንዱ መሬቱን ተረክዞ የቀረውን ጅው አድርጎ ወደ ውስጥ

ወረወረው፡፡ ባዶውን ጠርሙስ ደግሞ በጁ እየጠነቆለ ‹‹አንተን ደግሞ ለአንድ ዶሮ ለውጩ ሞያ እይዛለሁ የዊስኪ ቅርፍቱም

ዋጋ አለው አይጣልም›› አለ፡፡

‹‹እንዲሁ ሲጠጣ ሌሊቱን አጋመሰው፡፡ ቀጥሎ ከእግሩ በታች የወደቀውን ጠርሙስ እየቆጠረ ይህን ሁሉ እንደጠጣሁት

አላምንምና በጉለሌ አፈርሳታ ይደረግልኝ እነናቄ እነተሰማ አጎቴም ይጠጣሉ›› አለ፡፡ የጠርሙሱ መጠጥ ሁሉ እስኪያልቅ ድረስ ከዚያ ከዛፉ ሥር ተቀምጦ ያን ጠንካራ ትምባሆውን ከአፉ አላየውም፡፡ በሳቅ ጊዜ

ብቻ መልሶ ዝም እስኪል ድረስ መጠጡ ወይም ትምባሆው ከአፉ ያቋርጣል፡፡ የመጠጥና የትምባሆ ጊዜው ተበጀ ይህ

ነው፡፡ማለዳ በቀዝቃዛ ውሃ ታጠበ፡፡ ቋንጣም እንቁላልም ጠበሳና በዳቦ በላ፡፡ የጦም ቀን ነበር ‹‹ ለአባ ተክለ አረጋይ

አልናገርምና ነፍሴ ሆይ ግድ የለም አለ››፡፡ የነፍስ አባቱን ማለቱ ነው፡፡ ምናልባት በዓመት እንኳ አንድ ጊዜ ጠየቋቸው

ወይም ጠይቀውት አያውቁም፤ እርሱንም አያደርሰውም፤ እርሳቸውም ከበዓታቸው አይወጡም፤ አንዳንድ ጊዜ የዛሬውን

እሑድ ዕረፍት አደርገዋለሁ ያለ እንደሆነ እግሩን ደኅና አድርጎ የሚታጠብበት ቀን ማለት ነው፡፡

ደክሞት ነበርና ደኅና እንቅልፍ ተኝቶ ነበር፡፡ ዝናሙን ነጎድጓዱን ጎርፉን ውሃ ምላቱን አልሰማም፡፡ አንዳች ነገር ሰማ፡፡ ዘፈን

እና እልልታ የሰማ መሰለው፡፡ ትናንት ከጠጣው መጠጥ ኃይል መሰለውና ይህስ ዕብደት ነው እንጂ ስካር አይደለም አለና

ተመልሶ ተኛ፡፡

እንደገና አዳመጠ፡፡ የእርዳታ ጥሬ ጩኸት ሰማ፡፡ ከ አልጋው ዘልሎ ከወረደ በኋላ ቤቱን ለመዝጋት ጊዜ አላገኝም፡፡ በትልቁ

ወንዝ ዙሪያ ቁመው ይጮሁ የነበሩ ሰዎች የውሃው ምላት የሾገሌን ገረድ እንደጠለፋት ነገሩት፡፡ ጉርፍ የወሰደው ሾገሌን

ራሱን ቢሆን ወይም የሾገሌን ገረድ ለተበጀ ማዕረግ ምኑም አይደለም፡፡

‹‹ ገረዲቱን እናንተ በመጨረሻ ያያችኋት ወዴት ነው? ›› ብሎ ጠየቀና እየጠለቀ በዋና ይፈልግ ጀመር፡፡ ስለ ሾገሌ ገረድ

በትኩስ ውሃ ምላት ለመግባት አንሠዋም ያለው ጉለሌ በዳር ተሰልፎ ቁሞ ተበጀን ይመለከት ነበር፡፡

ብዙ ጠልቆ ከቆየ በኋላ ብቅአለና ‹‹ አገኝኋት መሰለኝ ›› ብሎ በዳር ላሉት ጮሆ ተናገረ፡፡ ለሰው ሁሉ ደስታ ሰጠው፡፡

ከሁሉም ይልቅ እርሱን ደስ አለው፡፡ የጠለቀውና የዋኝው ረጅም ጊዜ ስለሆነ ደክሞት ነበር፡፡ ነገር ግን ሊያወጣት

ይገባዋል፡፡ ጠለቀና አገኛት፡፡ በአሸካከሙ ላይ ጥበብ ያስፈልጋል::

አለዚያስ ውሃው ምላት እንደገና ይነጥቀዋል፡፡

እንደተሸከማት ውስጥ ለውስጥ ዋኝና ከዳር ብቅ አለ፡፡

ከሸክሙ ክብደት ኃይል የተነሣ ወዲያው ወደቀ፡፡ እርዳታ ተነባበሩለትና ጎትተው እርሱንም እርሷንም አወጧቸው፡፡

ተበጀ ተንዘራግቶ በብረቱ ውጋት እያቃተተ የጉለሌ ሰው በሳቅ ሲፈነዳ ሰማ- ከራሱ ነኩል ቀና አለና ‹‹ ሴትዮዋ ድናለች? ››ብሎ በርኅራሄ ድምፅ ጠየቃቸው፡፡

አንዱ ቀረበና ‹‹ አሳማ ነው ያወጣሃው ›› አለው፡፡

የሚያቃትተው ተበጀ ከወደራሱ ቀና አለና ‹‹አሳማ?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ‹‹ ለመሆኑ ከእናንተ ውሃ ወሰደባችሁ ሰው ነበር ወይስ አሳማ ኑርዋል? ›› ብሎ ተበጀ ጠየቀና ያቃትት ጀመር፡፡

ጎረቤትህን እንደነፍስህ ውደድ ቢባልም ሰዎችን እነ እቲላን ነበር እንጂ የእቲላን አሳማዎች አልነበረም፡፡ እቲላ ጎረቤቱ አሳማ

አርቢ ነው፡፡ ውሃው ምላት ነጥቆ ወስዶ የነበረ የእቲላን አሳማ ሳለ ያላዩትን ቢያወሩ ግድ የሌላቸው ሰዎች የሾገሌን ገረድ

ውሃ ወሰዳት ብለው አውርተው የተበጀ ነፍስ ለአንድ አሳማ ነፍስ ሊያስለውጡት ነበር፡፡

መልካሙ የሰማዕትነት ሥራው ሁሉ ደግሞ እንዲሁ ርካሽ ሆኖ የሚቆጠር የሆነበት ዘወትር የሚሰክር ሆኖ ስለታወቀ ነው፡፡

በሞራልም (ግብረ ገብነት) መሠረት አደረግሁት የሚለውን ሁሉ ሳያውቀው እንደሚያደርገው ይቆጥሩበታል፡፡ ‹‹ በጎ ሥራህን ሁሉ በትኩስ መቃብር ውስጥ አፈር አልብሰው አንተ ሰው ሁን ሚስት አግባ ልጆች ይኑሩህ›› ይሉትና ይዘልፍት

ነበር፡፡

ድኃ ቢሆን ወይም ባለጠጋ ሰካራም ቢሆን ወይም ትኅርምተኛ ሁሉም የጉለሌ ልጆች ነን አባታችንም ጉለሌ ነው ብሎ ራሱን

ከሚያሰክር ሁሉ ትኅርምተኛ ለመሆን ብዙ ጊዜ አስቦ ነበር፡፡ ሰክሮ ያደረበት ሌሊት አልፎ ብርሃን በሆን ጊዜ ከእንግዲህ

ወዲህ ‹‹መጠጥ አልቀምስም›› እያለ እየቀኑ በብርሃን ተበጀ ምለዋል፡፡ በነጋዉ የበለጠ ጠጥቶ የባሰ ሰክርዋል፡፡ ለመስከር

ይጠጣል፡፡ ደስ ያለው እንዲመስለው ይጠጣል፡፡ ብስጭቱን ጉለሌ ወደ ገጽ ዞሯል 20

የጉለሌው ሰካራምበተመስገን ገብሬ

‹‹እንዲሁ ሲጠጣ ሌሊቱን አጋመሰው፡፡ ቀጥሎ ከእግሩ በታች

የወደቀውን ጠርሙስ እየቆጠረ ይህን ሁሉ እንደጠጣሁት

አላምንምና በጉለሌ አፈርሳታ ይደረግልኝ እነናቄ እነተሰማ አጎቴም

ይጠጣሉ›› አለ፡፡

Page 19: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 19ህብረተሰብ

እረ እናታለም፣ እረ እምየዋ፣ እረ እንዴት ሰንብተሽልኛል..አገሩ፣ ከብቱ፣ ጉብላሊቱ፣ ሁል እንዴት ሰነበተ?..ይዘንባል፣

ታርሳላችሁ? ከቆላው ያሉ ዘመዶች እንዴት ሰነበቱ አያ!!? እህ አያ ጥጋቡሳ፣ ዛሬም ንዳዲቱ ታስቸግረው? እህ እንግዲህ አርባ

ተንሳ ይሁንትጂ!!!

የከብቶችን ቤት አንድ የሚለው ሁነኛ ሰው አግኝተሸ ይሆን?..ያን ሰሞን አንድ ፊቱን፣ ከቆላ የመጡ የአበ ዘመዶች… ረድተውሽ

ቢሆን ሸላይ ነበር፡፡

የከብቶች ቤት ..በሴማ ታጠረ ምነ?…አሳብ ሁኖኝ ሰነበተ እኮ? እሱስ የእኔይቱ አየለሽ፣ ሌባ ሆነ አውሬ ከብቶችን ልዳፈር ቢል፣

ታመድ ታገቢው!!!

አዋ ልንገርስ/አጎቴ እንዴት ሰነበተ? በውል ተሻለው? እረ ወዲያልኝ!! እኔማ እመዋዬ የአሜሪካ መና አልጠጋኝ ብሎ ‹‹ከታች

ላይ›› ሲለኝ ሰነበተ:: .አሁን ማን ይሙት ሰው ‹‹አሜሪካ ምድር እህሉ አልተስማማኝም፣ አየሩ አልተለባኘኝም›› ቢል እውን

ይመስላል? ልግጥ አይመስልም? …እህ!! እኔ ተይት አምጥቸው? አሜሪካስ ቢሆን ሰው ነውንጂ ከፍ ያረገው፣ መጻፉ ቅዱሱ

ሆነ ቁራኑ እንደሁ አንድ!!!

እልሻለሁ…መሰንበቻዬን ሰውነቴ እህል ያሰኘው እንደሁ፣ አፌን ገና ሳረጥበው ‹‹ሬት፣ ሬት…›› ቢለኝ…ብለሃተኛይት እናቴ

የቋጠርሽልኝን ዳቦ ቆሎ ስቆረጥም፤ ቋንጣ ሳመነዥክ..ትንሽ ተገግ እላለሁ፡፡ እህ ምን ምሆነው ነኝ? ተጓሮ እሸት አልሸመጥጥ፣

‹‹የክፍ ቀን›› ብዬ የዘራሁት የለኝ:: የሰው አገር ሰው!!

እንዲ ስልሽ ‹‹መላ ሁኔታዬን ላጫውትሽ›› ብዬ እንጂ..በሆነው ባልሆነው..‹‹ልጄን ውሃ በላት!!›› ብለሽ እንድትሰለሰይ አየለም፡፡

እረ ወዲያልኝ!!..‹‹ሚስ ዩኒቨርስቲ›› ተብዬ እኔማ ሞላልኝ፣ አድባርም ቀናኝ ብዬ አገሬን በአሜሪካ ምድር ለማስተዋወቅ ባገኘሁት

እድል ከዓለም ቆነጃጅት ጋር ተደንቤ…አንድዜ በመኪና፣ አንድዜ በአየር ሲልም በባቡር ከአገር አገር ስንጓል…ብሰነብትም ህም!!

እረ ወዲያልኝ!!..አገሬን አርባ ተንሳን ሳስባት እንባዬ ይተናነቀኛል፡፡ ፍኖተ ሠላም፣ አርባተንሳ፣ ባከል ገብርኤል፣ ገራይ/ላህ ወንዝ…ጋራ ሸንተረሩ በአይኔ ሽው ሲል እግ ተይኝ አደራሽ!!! እንደ ምንሜናስ

ያደርገኛል፡፡

ፍክ ይልሻል? ከኢትዮጵያ አሜሪካ የሚያስጉዘኝን መሳፈሪያ ካርኒውን እኔ የቆረጥሁት ይምስል ‹‹በሰንበት መንገድ ጥሩ አየለም፣ በአዞቦቱ

ይሻላል›› ብለሽ ያንዜ የተቃወምሽኝ? ምክርሽን አስልቼ፣ ወደ አየሩ ስሰቀል ‹‹አቡነ ዘበሰማያትን›› ደግሜ ነው፡፡ እህ የማን ልዥ ሁኜ!! ዋ!!

‹‹የመርጀታ ደግ ሰው ቢወጣ፤ የታድፌ አካላት ልዥ›› አየለሁ ዝም ብዬ አልጠነቦቅ፡፡

‹‹አየር ስትሰቀይ፣ እውሽጥ ኸሰው መሀከል ሽቅብ እንዳይልሽ..ገላጣ መሬት ሲታይሽ መስኮት ከፍተሽ እንጂ.. እንዳትሞኝ ያልሽኝን›› እያሰብኩ..

አይ እናታለም፣ ወለላይቱ....አፈር ያብላኝ..!! አንቺንማ ‹‹በአየር አሰቅየሽ ሙቼ!!›› ብዬ ተመኘው፡፡

እንደ ሰተቴ ድስት ወደ ተንሰራፋው አየር ከዘለኩ ኋላ፣ በካርኒዬ ላይ ያለውን የመቀመጫዬን ስፍራ ቁጥር አይቼ ከመስኮት ጥግ ሲሆን እስቲ

ያልሽኝን ልተርጉመው፤ ለሁሉም ሸጋ ነው ብዬ ተመቀመጤ፤ ወደ ውጪ አልፎ የሚያሳየኝን መስኮት ለመክፈት ብጣጣር አልሆነም፡፡

‹‹እራ ሰዎቼ ያለ ውቀቴ እንዳላበላሽ፣ ሰው እንደሆነው እሆናለሁ›› ብዬ ስልስ ከቴም መስኮት መክፈት፣ያውም ፌስታል!!..እረ ወዲያልሽ!!

ሲልስ አየሩ ለመንቀሳቀስ ሲያሟሙቅ..አንዲት ሸጋ ጠንበለል በአየሩ ከተሰቀለው ሰው ፊት ለፊት እንደመቆም ብላ.. ትዛዝ ታስተላልፍልሽ

ጀመረ፡፡

‹‹አየሩ ቢገለበጥ..ቢያማችሁ..እንዲህ ቢሆን..ይህን ያህል ሰዓት ከኛ ጋር ትጓዛላችሁ›› እያለች እንዱንም አንዱንም ስትል ተሁሉ ሁሉ

ምን ጠላሽ” ብትይኝ እንደ ተጫነ አህያ ‹‹ተጠርንፋችሁ ታሰሩ!!›› መባሉ

‹‹ወይው…ምነ ያለችውን ሁሉ ሳላውቅ፣ ሳልሰማ..ያን ሁሉ መንገድ ተኝቼ በመዳረሻዬ ነቅቼ በሆነ›› ነው ያልሁ፡፡

ከአዲስ አበባ ተነስተን በአየር ላይ ሸመጠጥን:: እነዚያ ጠንበለል ያልሁሽ ጉብሎች(ሆስተስ) ድግሱ እንደሰመረለት ባለ ማህበር እንደ ወታደር

ጥንቅቅ ብለው ለብሰው..አንድዜ የሚጠጣውን አንድዜ..እህል እህል የማይለውን ሩዝ፣ በምንሜና እያመላለሱ

ብይ፣ ጠጪ” ይሉኛል::

“ምን ተመኘሽ” አትበይንጂ…

‹‹እኔስ አንድ ጣሳ ቅራሪ ሰጠውኝ በቅምጤ ሸምጥቼው ጥሜን ጠጥቼ በሞትሁ›› ነው ያልሁ፡፡

‹‹መቼም ታገሩ የወጣ ከአገሩ እስቲመለስ፣

ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ›› ነው ፡፡

‹‹አልሽ አትበለኝ ጌታዬ ልብ ስጠኝ›› ብዬ ያለ ልቤ መጭውን ለመቀበል ተየይዠዋለሁ፡፡

እመየዋ ከዚህ በታች የማወጋሽን ሁሉ ለጨዋታ ታንቺ አሳልፈሽ ለቡና ሚያጣጡሽ ለጎረቤት በተለይም ለነፍስ አባትሽ ለመርጌታ አወቀ

የነገርሽው እንደሁ ከፍተኛ ጾም ጸሎት ነው ሚጥልብሽ፡፡

እንግዲህ በአየር ተሰቅዬ ወደ አሜሪካ እያመራሁ ሳል… እንዳጫወትሁሽ፣ ከአስራ ስድትስ ሰዓት በላይ ነው የምንበር::

“ዋ ዋ ዋ..አይ እኔን ብሎ ባለ ውቀት!!” አስራ ስድስት ሰዓት ነው ምጓዝ ማለቴ ነው፡፡ ተቆላ ያሉ ዘመዶቻችንን መጠየቅ እንደምንጓዘዉ

መንገዱ ያህላል::

አንች ለስንቅ ቢሆንሽ ብለሽ የሰጠሸኝ ዳቦ ቀሎ፣ በቅቤ የታሸ በሶ፣ ቋንጣ ይሄ ሁል የተሰቀለው ከአውሮፕላኑ እቃ መጫኛ ላይ ሆነብኝ እንጂ

እሱን ነበር የምበላ፡፡ መንገዱ ያልሽ እንደሆን፣ ቢሄዱት ቢሄዱት አይልቅም፡፡ እነዚያ እንደወታደር ለብሰው የሚያስተናብሩ ጠንበለሎች

አንድዜ ሚጠጣውን..አንድዜ ሚታኘከውን በአይነቱና በግብሩ ሲያቀርቡ

“አልበላም!” እያልኩ ስቃወም… “በሞቴ አፈር ስበላ?” ብለው አያግደረድሩሽ ወይም ሚጠጣውን ለሰው ከማቀበላቸው ፊት ለራሳቸው

ቀምሰው አይሰጡ…፡፡ የገባዥ፣ ቀብቃባ መሰሉኝ!! ኋላ አፌን ሬት ሬት ሲለኝ አንዱን ሁላ ነገር ስታቀብለኝ “አሁንስ የመጣው ይምጣ!!” ብዬ

ወደ አፌ መስደድ!!…ጨው ጨው አለኝ፡፡ “ይሄስ ሸጋ ነው” ብዬ በልቼ ታበቃሁ ኋላ ..

“የበላሁትን ነገር፣ ምድነው” ብዬ ልጣጩን ሳነብልሽ፤ የአሳማ ስጋ!! እራ ውሃው በላኝ!! ብዬ ደንግጬ ወደላይ ሽቅብ ሊለኝ!! እንደምንም ብዬ

ትኩሱን ሻይ ሸመጥቼ ጠጣሁት፡፡ አሁን ለነፍስ አባታችን ለመምር የውል ሰው

“ልዠ፣ ተሰስታ የአሳማ ስጋ በላች” ብለሽ ብትነግሪያቸው፤ ብዙ ጦምና፣ ምህላ ነው የሚጥሉብሽ፣ አበባሌ ፣ እኔም አሜሪካ ተገባሁ ኋላ ጦም፣

ጸሎት ይዤ ሰንብቻለሁ፡፡ ጨዋታውን ላውጋሽ ብዮ እንጂ፣ እራሴው ተወጥቼዋለሁ ብዬ ነው። በይ በቀጣይ ደሞ ማጨዋውትሽ ብዙ ወግ

አለኝ፡፡ (ልጅሽ ሰዋሰው ደግሰው ቢወጣ)

ባላገሯ በአሜሪካ

ማስታዋሻባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን

አዬ፣ ምነው እመ ብርሃን? ኢትዮጵያን ጨከንሽባት?ምነው ቀኝሽን ረሳሻት?እስከመቼ ድረስ እንዲህ፣ መቀነትሽን ታጠብቂባት?ልቦናሽን ታዞሪባት?ፈተናዋን፣ ሰቀቀኗን፣ ጣሯን ይበቃል ሳትያት?አላንቺ እኮ ማንም የላት….አውሮጳ እንዲሁ ትናጋዋን፣ በፋሽስታዊ ነቀርሳታርሳ፣ ተምሳ፣ በስብሳሂትለራዊ እባጭ ጫንቃዋን፣ እንደኮረብታ ተጭኗትቀና ብላ እውነት እንዳታይ፣ አንገቷን ቁልቁል ጠምዝዟትነፍሷን ድጦ ያስበረከካትሥልጡን፣ ብኩን፣ መፃጉዕ ናት፤ ….እና ፈርቼ እንዳልባክን፣ ሲርቀኝ የኃይልሽ ውጋገንአንቺ ካጠገቤ አትራቂ፣ በርታ በይኝ እመ ብርሃንቃል ኪዳኔን እንዳልረሳት፣ እንዳልዘነጋት ኢትዮጵያን፡፡አዎን፣ ብቻዬን ነኝ ፈራሁእሸሸግበት ጥግ አጣሁእምፀናበት ልብ አጣሁእማማ ኢትዮጵያን መንፈሴ፣ ተፈትቶ እንዳይከዳት ሠጋሁ …አዋጅ፣ የምሥራች ብዬ፣ የትብት ምግቤን ገድፌከእናቴ ማኅፀን አርፌከአፈርዋ አጥንቴን ቀፍፌደሜን ከደሟ አጠንፍፌከወዟ ወዜን ቀፍፌበሕፃን እግሬ ድሄባት፣ በህልም አክናፌ ከንፌእረኝነቴን በሰብሏ፣ በምድሯ ላብ አሳልፌከጫጩት እና ከጥጃ፣ ከግልገል ጋር ተቃቅፌ፤በጋው የእረኛ አደባባይ፣ ክረምት እንደወንዙ ፍሳሽበገጠር የደመና ዳስ፣ በገደል ሸለቆ አዳራሽከቆቅ እና ከሚዳቋ፣ ከዥግራ ጠረን ስተሸሽበወንዝ አፋፍ ሐረግ ዝላይ፣ መወርወር መንጠልጠል ጢሎሽከፍልፈል ጋር ሩጫ ስገጥም፣ ከቀበሮ ድብብቆሽከናዳ ጫፍ ሣር አጨዳ፣ ለግት ላሜ ትንሽ ግጦሽለጥጃዬ የሌት ግርዶሽለጥማድ በሬዎች ራት፣ ለማታቸው ትንሽ ድርቆሽለግልገሌ ካውሬ ከለልእማሳው ሥር ጎጆ መትከል

ጴጥሮስ ያቺን ሰዓትለፀሐይ የሾላ ጠለል፣ ለዝናብ የገሳ ጠለልውሎ የንብ ቀፎ ማሰስ፣ ያበባ እምቡጥ ሲፈነዳየግጦሽ ሣር ሲለመልም፣ ሲሰማሩ ሰደድ ሜዳአዝመራው ጣል ከንበል ሲል፣ ከብቱ ለሆራ ሲነዳፈረስ ግልቢያ ስሸመጥጥ፣ ከወፎች ዜማ ስቀዳልቤ በንፋስ ተንሳፎ፣ በዋሽንት ዋይታ ሲከዳ …..ያቺን ነው ኢትዮጵያ የምላትእመ ብርሃን እረሳሻት?ያቺን የልጅነት የምሥራች? የሕፃንነት ብሥራትየሣቅ የፍንደቃ ዘመን፣ የምኞት የተስፋ ብፅአትያቺን የልጅነት እናት?አዛኚቱ እንዴት ብለሽ፣ ጥርሶችሽን ትነክሺባት?ሥሜን በሥምሽ ሰይሜ፣ ባገልግሎትሽ ስዋትትከዜማ ቤት እቅኔ ቤት፣ ከድጓ ቤት እመጻሕፍትካንቺ ተቆራኝታ ዕድሌ፣ ካንቺ ተቆራኝታ ነፍሴከቀፈፋ ደጀሰላም፣ ከቤተልሔም ቅዳሴእኰ፣ ቀፎ ዳባ ለብሶቅኔ ዘርፎ ግስ ገሦመቅደስ አጥኖ ማኅሌት ቆሞበልብስ ተክህኖ አጊጦ፣ በብር አክሊል ተሸልሞእመ ብርሃን ያንች ጽላት፣ ነፍስ ላይ በእሳት ታትሞየመናኒው ያባ ተድላ፣ ረድ ሆኜ፣ አብሮኝ ታድሞሕይወቴ እምነትሽን ጸንሶሥጋ ፈቃዴ ተድሶለሕንፃሽ መዲና ቆሞ፣ ለክብርሽ ድባብ ምሰሶሥሜን በሥምሽ ሰይሜ፣ ሆነሺኝ የእምነቴ ፋኖስለዋዜማሽ ግሸን ማርያም፣ ለክብርሽ ደብረ ሊባኖስስሮጥ፣ በወንበሩ አኖርሺኝ፣ በአንበሳው በቅዱስ ማርቆስታዲያ ዛሬ ኢትዮጵያ ስትወድቅ፣ ከምትሰጪኝ የፍርሃት ጦስምነው በረኝነት እድሜ፣ ዓይኔን በጓጎጣት የሎስየጋኔል ጥንብ አንሳ ከንፎ፣ ወርዶ በጨለማ በርኖስባክሽ እመ ብርሃን ይብቃሽ፣ ባክሽ ምስለ ፍቁር ወልዳጽናት ስጪኝ እንድካፈል፣ የእናቴን የኢትዮጵያን ፍዳ፣ከነከሳት መርዝ እንድቀምስ፣ ከነደደችበት እቶንየሷን ሞት እኔ እንድሞታት፣ ገላዋ ገላዬ እንዲሆን፡፡ …..አዎን፣ ብቻዬን ነኝ ፈራሁእምፀናበት ልብ አጣሁ፡፡ …..

(ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን)

ጹሐፌ ተዋኔትና ባለቅኔ ሎሬት ብላቴን ጸጋዬ ገብረ መድህን (1928-1998) ባዳ ተብላ በምትታውቅ

አምቦ ካተማ አካባቢ በምትገኝ ተራራማ ቦታ ተወለዱ። በአምቦ ማአረገ ሕይወት ቀኃሥ ትምህርት ቤት

ከዚያም ጀነራል ዊንጌትና በአዲስ አበባ የንግድ ትምህርት ቤት በአገር ውስጥ ትምህርታችውን ከገፉ

በኋላ በቺካጎ ብላክስቶን በህግ ትምህርት ተመርቀው በ1952 እንደ ውጡ በለንደን ከተማ የቴአትር

ትምህርት በሮያል ኮርት ቴአትርና በፓሪስ ኮሜዲ ፍራንሴዝ ተከታትለዋል። ከ1954 እስከ 1964

የቤሄራዊ ቴአትር በአርቲስቲክ ዳይሬክተርነት አገለግለዋል። ከዚያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር

ዲፓርትመንትን አቋቁመዋል።

ሆኖም በ1960ዎቹ ደርግ አብዛኛውን የቴአትር ስራዎቻቸውን ሲያግድ እሳቸውንም አስሩዋቸው ነበር።

ብላቴን ሎሬት ጸጋዬ በርካታ ግጥሞችን፥ የቴአትር ሰራዎችን የተለያዩ መጣጥፎችንና ዘፈኖችን

አበርክታዋል። ጸጋዬ በ1990 ለጉበት በሽታ ሕክምና ወደ ማንሃታን በሄዱበት አርፈዋል። በአዲስ አበባ

በስላሴ ቤተክርቲያን ተቀብረዋል።

1998 ዓ/ም በአማረኛና በእንግሊዘኛ ከደረሱዋቸው ተዋኔቶች ባሻገር የእንግሊዛዊው ደራሲ ዊልያም

ሼክስፔር ተዋኔቶች (ሐምሌት፣ ማክቤዝ፣ ኦቴሎ፣ ንጉስ ሊር) የሞሊየር (ታርቲዬፍ፣ የፌዝ ዶክተር)

በመተርጎም ይታወቃሉ።

“ሀሁ በስድስት ወር” (1966)

“አቡጌዳ ቀይሶ” (1968)

“መልዕክተ ወዛደር” (1971)

“መቅደም” (1972)

“ሀሁ ወይም ፐፑ” (1985) ቲያትሮችን ለመድረክ አብቅተዎል::

Page 20: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ገጽ 20

( በኢትዬጵያ የድርሰት ታሪክ የመጀመሪያው አጭር ልቦለድ በ1941 ዓ.ም ህዳር 22 አዲስ አበባ ነፃነት ማተሚያ ቤት ታተመ )

በደሙ ላይ እንደተጋደመ አራት ቀኖች አለፉ፡፡ እግሩ እንደቀረበታ

ተነፋ፡፡ እንደ ቅጠልያ ያለ እዥ ወረደው፡፡ ከወደቀበት

ያነሳው የመንግስት አምቡላንስ ባገኝው ጊዜ ፈፅሞ በስብሶ ነበር፡፡

ጉለሌ ከገጽ 18 የዞረየሚረሳ መስሎት ይጠጣል ይህ ነው ተበጀ፡፡

‹‹ ይህን መስከርህን ካልተውህ ላንተ አበ ነፍስ አልሆንህም›› ብለው የመጀመሪያ ንስሐ አባቱ ብዙ ከመከሩት በኋላ መንፈሳዊ

ልጅነቱን ከርግመት ጋራ አስወግደውታል፡፡

ገረዶቹም ለርሱ ተቀጥሮ መሥራትን ከውርደት ቆጥረውት እየነቀፉት ሂደዋል፡፡ ‹‹ መጠጥ ካልተውህ አናገባህም›› ብለው

እየጊዜው ለጋብቻ ጠየቋቸው የነበሩ በቁመናው አሰናብተውታል::

በሰምበቴ በማኅበርም ማኀበርተኛ ለቦሞን የጠየቃቸው

ነፍሱን ሳይቀር ንቀውታል፡፡

ይህ ሁሉ በእርሱ ዘንድ ከኢምንት አይቆጠርም፡፡ ያሉትን ቢሉ እርሱ ምን ቸገረው ገንዘብ እኮ አለው፣ ገንዘቡም ጥሬ ብር

ነው፡፡ ባለጠጋ ነው፡፡ መስከረም የባለጠጎች ነው፡፡ ትኅምርተኛ መሆንም የድሆች ነው፡፡ እንደ ልዩ አመፅ አድርገው ለምን

በእርሱ ይቆጥሩበታል? እንዲህ በተከራከረ ነበር፡፡

ነገር ግን ልዩነት አለው፡፡ እርሱ ብዙ ጊዜ ሰክሮ አውቶሞቢል በላዩ ላይ ሒዶበታል፡፡ ሰክሮ በበነጋታው ከእንቅልፉ ሲነቃ

ብዙ ጊዜ ከእስር ቤት ውስጥ አድሮ ራሱን አግኝቶታል፡፡ በጉለሌ መንገድ ዳር ባሉት በብዙ የውሀ ጉድጓዶች ሰክሮ

ገብቶባቸው እየተጮኸ ጉለሌ አውጥቶታል፡፡ ሰክሮ የጎርፍ ውሀ ከወሰደው በኋላ ብዙ ጊዜ እሳት አደጋ ደርሶለታል፡፡ ሰክሮ

ከቤቱ መድረስ እያቃተው ከወደቀበት ባቡር ምንገድ ሳይነሳ ብዙ ጊዜ ጎርፍ በላዩ ላይ ሲሄድበት አድርዋል፡፡

ይህ ሁሉ ውርደት እና ርክሰት ነው እንጂ ክብር ከቶ አይደለም፡፡ እንግዲያውስ ክቡር ደሃ ነው ገንዘብ ስለሌለው ራሱን

መግዛት ይችላል፡፡ ባለጠጋ ደግሞ መናኛ ተራ ነው፡፡ ገንዘብ ስላለው ራሱን መግዛት አይችልም፡፡ ይህን ሁሉ አሰበ፡፡ ስለኖረ

ባይማር እንኳ ብዙ ከማወቅ ደርሰዋል፡፡ ‹‹ ባለጠጋ ሆነ ወይም ደሀ፣ ሰው ከራሱ የበለተ መሆን ይገባዋል››፡፡ አለ፡፡

ቤቱን ከሠራ ከአምስት ወራቶች በኋላ ጀምሮ ተበጀ መጠጥ ከቶ አልተጠጣም ስለቤቱ ክብር መጠጥ እርም ነው ማለት

ጀምሯል፡፡ ያለፈውንም ዘመን መራርነት እያሰበ ተንገፍግፈዋል፡፡ አንድ ብሎ ለመጀመር ከወደቀበት ትቢያ አንስቶ ዕድሉን

ሲራግፍ እነደ ራዕይ ያያል፡፡ ያበላሸው እድሉ አሳዘነው ‹‹ በዚህ እድሜየ ሁሉ ሚስትም አላገባሁ ልጅም የለኝም›› አለና አዘነ፡፡ ውሾቹ እየተባሉ ሲጫወቱ

ተመለከተና ‹‹አመሌ ውሻ ነበርና ከውሾች ጋር ኖርኩ›› ብሎ ራሱን ረገመ፡፡ በውሾች ፈንታ አሁን በዚህ እድሜው ልጆቹ

ዙሪያውን እየተጫወቱ ሲፈነጩ ባየ ነበር እንዲሁ አሰበ፡፡

ቀልድና ወዘበሬታ ስለሚያውቅ እንደዚህ እያለ ይቀልድ ነበረ፡፡

ጉጃም የአበባውንና የግራር ማሩን ይጭናል፡፡ የተጉለትና የአምቦ ወረዳ ጌሾውን ያቀርባል፡፡ የሆላንድ የቢራ ፋብሪካ ቢራውን

ያወጣል የኢጣሊያ ፋብሪካ ወይን ጠጅ (ነቢት) ያፈላል፡፡ መደቅሳና ዘቶስ በግሪክ አገር ይጣራል በስኮትላንድ ዊስኪ

ይጠመቃል፡፡ ይህ ሁሉ የሚደረገው በአራዳ የሚቀመጡትን እንዳይተማቸው ነው፡፡ በዚህም ምክንያት መዋሻዋ

እንደምትጮህ ጉጉት ሰካራሞች በከተማይቱ ይጮሃሉ፡፡

‹‹በደብረ ሊባኖስ ግን ድምጡን ዘለግ አድርጎ የሚናገር ወፍ እንኳ የለም፡፡ ውሃ እንኳ የሚጠጣ በመቅነኑ ነው፡፡ በአራዳ

አሁን ወይም በገዳም ምንም ገንዘብና ቢስቲን ለሌለው ውሀ ደግሞ እጅግ አድርጎ ይጣፍጣል፡፡›› ይህን የመሰለ ቀልድ

ይቀለድ ነበር፡፡

ሰካራሙ ተበጀ ግን ገንዘብ እያለው ወሀ ጣፍጦታል፡፡ ልዩ በሆነው በዚያ ማታ ወደ አልጋው ወጥቶ በተኛ ጊዜ መጠጥን

እርም ካደረገው አንድ አመት ከዘጠኝ ወር ከዘጠኝ ቀን እንደ ሆነው ጊዜውን ቆጥሮ አወቀው፡፡ ጊዜውንስ ማወቅ ለምን

አስፈለገው? ‹‹ እንደ ጉድፍ ( ጥንብ) መጣያ ትንፋሼ ተበላሼ፤ አፌም እነደ እሬት መረረኝ ሹልክ ብየ ዛሬ ብቻ፤ ጥቂት ብቻ፤

አንድ ጊዜ ብቻ፤ እኔ ብቻ፣ ብጠጣ ምን ይጎዳል›› ብሎ ተመኝቶ ስለመበረ ነው፡፡ ነገር ግን ወደ አልጋው ወጥቶ ተጋደመ

ከተጋደመም በኋላ ተነሥቶ መጠጥ ቤት ለመሄድ ከባድ ከነበረው እንቅልፉ ለበላቀቅ ታገለ፡፡

በመጨረሻ ወደ መጠጥ ቤት በሄደ ጊዜ በውኑ ወይንም በሕልሙ እንደነበረ ራሱን ተበጀ አላውቀውም፡፡

የጠጣም እነደሆነ ከሁለት መቶ ዓመት በፊት ይደረግ በነበረው የአረመኔ ቅጣት እጁን እግሩ ከመቆረጥ ይደርሳል ብሎ

አላሰበም፡፡ አናጢ የጠረበው እንጨት ከቅልጥሙ ይቀጠላል ብሎ ክፉ ሕልም አላለመም፡፡ አንድ ሰካራም አንካሳ በአንድ

ዓመት ስንት የእንጨት እግር ይጨርሳል ብሎ ስለዋጋው አልተጨነቀም፡፡ ደኅና ምቾት ያለው አንካሳ ለመሆንም ገንዘብ

ያስፈልጋል፡፡

አንካሳው ሰው ሰካራም እንደሆን በእንጨት እግሩ በሰላም ጊዜ ይሄድበታል፡፡ በሁከት ጊዜ ደግሞ ይማታበታል፡፡ ሲማታበት

ይሰበራል ሲሰበርም ሌላ የእንጨት እግር መግዛት ያስፈልገዋል፡፡ ስለዚህ የእንቸጥ እግር የሚሰሩ አናጢዮች ለደንበኞቻቸው

ትርፍ መጠባበቂያ እግር በሜንጦ ሰቅለው ያስቀምጡላቸዋል ይባላል፡፡ ተበጀን እንደዚህ ያለ ሕይወት አያጋጥመውም፡፡

በበቀለች ዓምባ መጠጥ ቤት ደረጃውን ተራምዶ ተበጀ በገባ ጊዜ የጥንት ወዳጆቹ ስካሮች በእቅፍ ልይ ተነባበሩ፡፡

እንደተወደደ መሪ በጫንቃቸው ላይ ተሸክመው እየተቀባበሉት በዕልልታ ጮሁ፡፡ ከመጠጥ ቤት ጠፍቶ የነበረው

ተመልሰዋልና በስካሮች ሁሉ ዘንድ ደስታ ሆነ፡፡ እንኳን በደኅና ገባህ! የመጠጥ ጠርሙሶቹን እንደ ዘንባባ ይዘው ተቀበሉት

ቁማርተኛው ያረጀ ግሪክ እየሳለ ተናገረ ሁሉም በደስታ ይጮሁ ስለነበረ አንድም የሰማው የለም፡፡ ረስቶት የነበረው መጠጥ ጣዕሙን ገና ሳያውቀው ገና ከጫብቃቸው ሳይወርድ በጩኸቱም በመጠጡም ተበጀ ሰከረ፡፡

ከጫንቃቸው ወደ ቁልቁል ጣሉት ፡፡ የሕፃንነት ዘመን አልፉልና

ራስህን ችነል መሄድ ይገባሃል አሉት፡፡ ሰማህ? አቅም

አንሶህ መሄድ አቅቶሃልና እንደኩብኩባ እየዘለለህ መሄድ ትችል እንደሆነ ምርኩዜ ይኸውልህ ብሎ አንካሳው በየነ

አቀበለው፡፡ ምረኩዙን ለመያዝና ለመጨበጥ እጁን ሲዘርር በግምባሩ ከበሬት ላ ተደፋ፡፡ እንደ ወደቀም ሳለ፤ እስኪነቃ

ድረስ በመካከሉ ስንት ሰዓት አልፎ እንደነበረ ለማስተዋል አልቻለም፡፡

የመጠጥ ቤቱ እመቤት ጊዜ አልፏልና ከውጭ ጣሉትና ቤቱን ዝጉት ብላ አዘዘች፡፡ ወደቤቱ የተመለሰ መስሎት ሄደ፡፡ ማወቅ አልቻለምና ወዴት እንደሄደ ግን አላወቀም፡፡ አንድ መንገድ ሲያቋርጥ ተሰናከለና ወደቀ፡፡ ከወደቀበትም ምድር ላይ በዳሰሰ ጊዜ ለእጁ የገጠመው የባቡር ሀዲድ ነው፡፡ ቤቱ ያለ በጉለሌ ነው፡

፡ የሰከረበት

ደግሞ የበቀለች መተጥ ቤት ነው፡፡ መጠጥ ቤቱም ከዩሃንስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ነው፡፡ ምን ያህል ቢክር ነው የጉለሌ

መንገድ ጠፍቶት እስከ ባቡር ሀዲድ ድረስ ተሳስቶ የሄደ; ራሱን ይዞ ለመጮህም ራሱ ወዴት እንዳለ ማወቅ አቃተው፡፡

እንደ ቤቱ መንገድ ጠፋበት፡፡ ጥቂት መስማት ከቻለ በኋላ ጩኸት በስተ ኋላው የነፋ ነበረ የእሳት አደጋ ወይስ ባቡር ኑርዋል; እያፎደፎደ ሲሄድ ከወደ ኋላው በኩል ምን እንደገፋው አላወቀም፤ ከኋላው በኩል ትልቅ ሀይል መታው፤ ከፊቱ በኩል ቀበሮ ጉድጓድ ተቀበለው፡፡ እግሩ እንደ ብርጭቆ ነከተ፡፡ ከወደቀበትም ሌሊቱን ሁሉ ደም ከእግሩ ዘነመ፡፡ ትንኝም እንደ ንብ በላዩ ሰፎ ደሙን መጠጠው፡፡

ቀና ብሎ በአጠገቡ የወደቀውን የአህያ ሬሳ አሞራዎች ሲግጡት አየ፡፡ የቀረው ልቡ በድንጋፄ ተመታ የእርሱ እድል ከአህያው

ሬሳ ዕድል ቀጥሎ ሆነ፡፡ በስካሩ ምክንያት እስከ ዘላለም ድረስ ከአህያ ሬሳ እንደ ማይሻል ተረዳው፡፡ ነገር ግን የአሁኑ

መረዳት ለምን ይበጀዋል? ማወቅ የሚያስፈልግበት ጊዜ አልፏል፡፡

በሕይወቱ ሳለ እንደ ወደቀ ያህያ ሬሳ መነሳትአልቻለምና በተራው አሞራዎቹን ዓይኑን ሊመነቁሩት ነው፡፡ ሥጋውን በልተው

ከጨረሱት በኋላ አጥንቱን ሊግጡት ነው፡፡ሌሊት ደግሞ ቀበሮዋች ሊረፈረፉበት ነው፡፡ ይህን እንዲያመልጥ ለመሸሽ

ከወደቀበት ሊነሣ እቃተተ ሞከረ፡፡ ባልተቻለው ጊዜ ግን ተጋደመ፡፡

በደሙ ላይ እነደተጋደመ አራት ቀኖች አለፉ፡፡ እግሩ እንደቀረበታ ተነፋ፡፡ እንደ ቅጠልያ ያለ እዥ ወረደው፡፡ ከወደቀበት

ያነሳው የመንግስት አምቡላንስ ባገኝው ጊዜ ፈፅሞ በስብሶ ነበር፡፡

ዶክቶር ክሪመር ባዩት ጊዜ ከሰማይ በታች ሊደረግለት የሚችል ሕክምና ምንድር ነው; ደሙ አልቅዋል፡፡ በሽተኞችን ለመርዳት በጎ ፈቃድ ካላቸው ሰዎች የተለገሰውን ደም ለሚሰክር ጥጋበኛ አልሰጥም፡፡ እርሱን መንካት መርዙን ያስፈራል::

ከዚህ በፊት ይህ እንዳይደርስበት እንዳይሰክር ብዙ አስጠንቅቀነው ነበር አሉ፡፡ ከንፈሩ ተንቀሳቀሰ፡፡ ላብ በፊቱ እንደ ውሀ ፈሰሰ፡፡ ለመናገር ጣረ:: በመጨረሻ ግን መናገም ስይሆንለት ቀረ፡፡

ሐኪሞችም የገማውን ልብሱን ገፈፉት፡፡ እንደ ቅባትም ያለ መድኃኒት ቀቡት፡፡ ከግማሽ ሊትር የበለጠ ደም ሰጡት፡፡

በመጠጥ ከተጉዳው ከልቡ ድካም የተነሣ ኤተር ለመቀበል አለመቻሉን ከተረዱ ዘንድ የሚያፈዝ መድኃኒት ጀርባውን

ወግተው ሰጡት፡፡ አንዱ ሐኪም ከጉልበቱ ይቆረጥ አለ፡፡

ሌላው ግን ሁለተኛ እንዳይሰክር ከቂጡ አስጠግቼ እቆርጠዋለሁ አለና ከቂጡ አስጠግቶ ቆረጠው፡፡ የተቆረጠውን እግሩን

ከፊቱ መዝናችሁ አስታቅፉት ብሎ አስታማሚዎችን አዘዘ፡፡

እግሩን ከፊቱ መዘኑትና አሥር ኪሎ የሆነው እግርህ ይኸውልህ ታቀፈው ብለው አስታቀፉት፡፡

በዚህ ጊዜ በአጥንት የተጣሉት ውሾች በላዩ ላይ ተረፈረፉበትና በድንጋፄ ከእንቅልፉ ነቃ፡፡ ይህ ሁሉ የደረሰበት በሕልሙ

እንደነበር ማወቅ አቃተው፡፡ ከአልጋው ላይ ወረደና ገረዱን ወይዘሮ ጥሩነሽን ከመኝታቸው ቀስቅሶ እየጮኸና እየተንዘረዘረ

ስንት እግር ነው ያለኝ ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ወይዘሮ ጥሩነሽም ‹‹ድሮ ስንት እግር ነበረዎ ጌታ?›› ብለው ጠየቁት፡፡

እየጮኸ ሶስት ጊዜ ‹‹ ሁለት ሁለት ሁለት ነበረኝ›› አላቸው፡፡

ሶስት ጊዜ ሁለት ስድስት ማለት ነው፡፡ ልጆቼን ያሳደገች ላም ካራት እግር የበለጠ አልነበራትም ሰለዚህ የእርስዎም እግሮች

አራት ናቸው አሉት፡፡

‹‹የምሬን ነው የምጠይቅዎት;›› አለና ጮሆ ተንዘረዘረ፡፡

‹‹በእርግጥ ሁለት እግሮች አሉዎት ጌታ›› አሉት፡፡

ተበጀ እግሩን አጎንብሶ ለመሳም ሞከረና ራቀው፡፡ ወደ ሰማይ እያየ መጠጥ ማለት ለእኔ ሞት ማለት ነው አለ፡፡ ጊዜውም

ሌሊት ነበር፡፡

እንደዚህ የማሉበት ሌሊት ያልፋል ብለው ወይዘሮ ጥሩነሽ መለሱለት፡፡

ዛሬ በዴሞክራሲ ማስክ፣ በጸደይ አብዮት ጅኒ ጃንካ ሊብያ የለችም፡፡ በጦር አበጋዞች የተከፋፈለችና የወደመች ኢያሪኮ ነች፡፡ኢራን ቀጣይዋ ተረኛ ፈራሽ ናት፣ እንደ ምኞታቸው:: (5)(እስላም. . ??)በዚህ አሰቃቂ ክንውን ሰበብ እስልምናን፣ ወይንም የኛን አገር ሙስሊሞች በገደምዳሜ ማጥላላት ቀላል ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ቀድሞም Islamo Phobia ከነበረብህ ‘ዱሮም እነሱ’ የሚል ቀፋፊ ማሽሟጠጥን በየካፌው በየድራፍት ቤቱ ታጋግል ይሆናል፡፡ግን አትሸወድ፣በCIA ዳታና በኛ መንግስት እስታቲስቲክስ መሰረት መሰረት ሩብ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ነው፡፡ በብሄር ብዛት ሶስተኛ የሆነው ኢትዮጵያዊው ሱማሌ ሙሉ ለሙሉ ሙስሊም ነው፡፡ እንደውም በታሪክም ሆነ አሁን ደግሞ

ሊብያ ከገጽ 8 የዞረ

Eyob Mihreteab ፌስ ቡክ ገጽ የተወሰደ

በMainstream Ethiopian narration ላይ የሚገባቸውን ስፍራ፣ መብት እና ድርሻ ያልተሰጣቸው ናቸው፣ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች:: ይልቅስ አንድ መሆናችንን፣ በዕምነት ሽፋን የሚደረግ ጭፍጨፋ ይባስ እንደሚያጠናክረን እንጂ እንደማይከፋፍለን የምናሳይበት አጋጣሚ ነው፡፡(6)(መንግስትና ተቃዋሚ፣ አዝጎች!)ቀላል ነው፡፡ ቀዌ ተቃዋሚው ወያኔን ማስመቻ አሪፍ መጯጯህያ አጀንዳ አግኝቷል፣ ቋቅ እስኪልህ አብዮት ይሰብክሃል፣ ወያኔ ወያኔ ይልሃል ፡፡መንግስት ደግሞ እነ ድምጻችን ይሰማን ጃስ ማስባያ ጸዴ የፕሮፓጋንዳ ካርድ አግኝቷል፣ ፒፓውን ሆ! አስብሎ ሰላማዊ ሰልፍ ያስወጣበታል፡፡ ሌላው ወግ ማረግ ነው፣ The-በጥብቅ - አወገዘ - political – correctness - stuff.መንግስት ሁኔታዎች ተመቻችተውለት የሃይል

እርምጃ ከወሰደ ወይ ቂል ነው፣ ወይንም በዜጎቹ ላይ ጨካኝ ነው ማለት ነው፡፡አንሸወድ እንጂ!ISISን ጫፉን ከነካነው፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት አልባ የሆነችው ሊብያ ውስጥ አሉለት፤ አንድ በአንድ ይፈጃቸዋል፡፡ It’s a bit complicated ነገር፡፡(7)(በመጨረሻም፣ የጠርጣራ ሠው ኮንስፓይራሲ ወርውሬ ላምልጥ)ስኡዲ፣ የመን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ከዛም ሊብያ፡፡ አራቱም አገራት ላይ የድረ Mapping ነገር ከሰራን አንድ ነገር ያመሳስላቸዋል፡ የአራቱም አገራት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፣ ከግማሽ ሚልዮን የሚበልጡ፣ አሰቃቂ ጉዞዎችን አልፈው በህገወጥ ደላላዎች ድንበር የተሻገሩ የድሃው መደብ ክፍሎች ናቸው፡፡ ሰዎቹን የማሻገሩ ቢዝነስ የእልፍ ሚልዮን

ብሮች ጨዋታ ነው፡፡ ተዋናዩም በየ እርከኑ ነው፡፡መልማይ አለ፣ መንገድ መሪ አለ፣ ደላላ አለ፡፡ የደላሎቹ ጠርናፊ አለ፡፡ ቢዝነሱ እንዳይቀዛቀዝ ለጠርናፊው አስፈላጊውን ሽፋን የሚሰጥ የጨለማ ሰው አለ:: (የመጨረሻውን ዐረፍተ ነገር አንተው ከደፈርክ በልጥጠው፤ እኔ የቂሊንጦ ኮንዶሚንየም እንጂ የቂሊንጦ እስር ቤት አልናፈቀኝም፡፡)የጨለማው ሽፋን ሰጪ ተፈርቶ ነው እንጂ መቶ ሁለት መቶ ሁለት መቶ ዋና ደላሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ቢወሰድ ኖሮ ስደቱም፣ ሰቆቃውም፣ እልቂቱም ቀጥ ይል ነበር፡፡.ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን. . ምናምን ብዬ ወሬዬን አልዘጋውም:: ቪድዮው እንዳስለቀሰኝ ግን ሳልነግርህ አልሰናበትህም፡፡

Page 21: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 21

ውስጥ በጣም ስለተቸገሩ--- እስኪ ቆነጃጅትን ፈልጉ ተባለ፡፡ አንድ እኔን በጣም የሚያውቅ ሰው ነበረ…ነፍሱን ይማርና ኮማንደር እስክንድር ‹‹ዋይን ገርል ራሄልን ጥሩ›› አለ፡፡ ዋይን ገርል ነበርሽ እንዴ?አዎ፡፡ ዋይን ስፔሻሊስት ነኝ፡፡እንዴት--- የት ተማርሽው? ታሪኬ ብዙ ነው አላልኩሽም፡፡ እስቲ አውጊኛ ----ዛሬ እንግዲህ አብረን ማደራችን ነው፡፡ግዴለም አጫውቺኝ ----ስሚ----.ድሮ ሁለቱን ልጆቼን እንደወለድኩ ባሌን ፈታሁ ከዛ ‹‹ራስ ሆቴል ኮርስ መውሰድ አለብኝ›› ብዬ አሰብኩና ለሶስት ወር ያህል የገበታ ዝግጅት (tabel set up) የእንግዳ መስተንግዶ አሰጣጥ (how to serve the guest) ሰለጠንኩ፡፡ እንግሊዝኛውም ሌላ ነው--- እንደ አሜሪካን ነው የምናወራው:: የእኛ ትምህርት ቤት እንደአሁኑ ቀላል መስሎሻል---ከሶስተኛ ክፍል በኋላ በእንግሊዝኛ ነው የምታወሪው፡፡ በተለይ በእንግሊዝኛ አስተማሪ በኩል----እኛ የተማርንበት ዘመን ሌላ ነበር፡፡ በጣም ቆንጆ ትምህርት ቤት ነው የተማርነው ግን አልሰራንበትም፡፡ እኔን ያልሽ እንደሆነ ግን በጣም የገባኝ አራዳ ስለነበርኩ በወቅቱ ሰርቼበታለሁ፡፡ እና የ‹‹ዋይን ገርል›› ኮርስ ስጨርስ ምርጫ ተሰጠኝና ጊዮንን መረጥኩ፡፡ ያኔ የነበሩት ሆቴሎች በጣም ትንሽ ናቸው፡፡ ዋቢ ሸበሌ ገና እየተጠናቀቀ ነበር:: በተረፈ ጊዮን ሆቴልና ኢትዮጵያ ሆቴል ናቸው፡፡ እኔ ጊዮን ሆቴል ገባሁ፡፡በአስተናጋጅነት ነው? ስለ በቬሬጅ (መጠጥ) ነበር ያጠናሁት፡፡ ስለ ኮክቴል አሰራር አውቃለሁ --- አንድ መጠጥ ከአንድ መጠጥ ጋር ኮክቴል ይደረጋል፡፡ አፕሬቲቩ፣ ዳይጄስቲቩ----የተለያዩ የዋይን ዓይነቶች አሉ--- ሬድ፣ ዋይት፣ ሮዜ፣ ድራይ፣ስዊት፣ ሚዲየም… ከምን ከምን ምግብ ጋር እንደሚወሰዱ አውቃለሁ፡፡ ካስተመሮቹ በጣም ይደነቁ ነበር፡፡ የት ነው የተማርሽው፤ የት አወቅሽው ይሉኛል፡፡ስንት ዓመት ሰራሽ በዋይን ገርልነት?አራት ዓመት ከስድስት ወር ነው የሰራሁት፡፡ ስራውን ብወደውም እየሰለቸኝ መጣ፡፡ አንድ ቀን አኩርፌ ተቀምጬ አንድ ደንበኛችን አዩኝ፡፡ የአርጀንቲና አምባሳደር ነበሩ፡፡ ስሚ----ብዙ ካስተመሮቼ የሚያውቁኝ በጣም ሳቂታ፣ ደስተኛ፣ ተጫዋች መሆኔን ነው፡፡ የሚያኮርፍም ሰው አልወድም፡፡ ኩርፊያም አልወድም፡፡ ስለዚህ ‹‹ምነው ዛሬ አልሳቅሽም?›› አሉኝ፡፡‹‹ደከመኝ የሌሊት ስራ ደከመኝ›› አልኳቸው፡፡“So?” አሉኝ፡፡‹‹በቃ ሰለቸኝ አስጠላኝ…›› መለስኩላቸው “Why don’t you come to my embassy, I am go-ing to move by next week.” (ለምን ወደ እኔ ኤምባሲ አትመጪም? በሚቀጥለው ሳምንት እገባለሁ)እሽ ብዬ ሄድኩ፡፡ እቃ ግዢ ክፍል (ፐርቼዘር) አደረጉኝ:: ከዚያ የጣሊያን ክልስ ፀሃፊና አራት ዘበኞች ቀጠርኩለት፡፡ ሁለት የማታ፣ ሁለት የቀን፡፡ የዘበኞች

ዩኒፎርም(የቤተመንግስት ልብስ ሰፊ ነበር) እሱ ጋ ሄጄ አሰፋሁ፣ ባርኔጣቸውን አሰራሁ:: ሁለት ሾፌሮችም ቀጠርኩ፡፡ የኤምባሲ ሾፌሮች የሚለብሱትን አውቃለሁ:: ወጥ ቤትም ቀጠርኩ---የፅዳት ባለሙያ (ሃውስ ኪፐር) እንዲሁም አትክልተኛ ሁሉ ቀጠርኩ፡፡ ሥራ ብቻ ነው ወይስ ሌላም ግንኙነት ነበራችሁ? ኦኦ---ባለትዳር እኮ ነው፡፡ እኔ ስራውን ነው የፈለግሁት፡፡ (የቤቷ ስልክ ለሦስተኛ ጮኸ…)እንግዲህ ቻይው---- ልጆቼ አሜሪካና ካናዳ ነው ኑሮዋቸው…ልክ ሲነጋ የኔን ድምፅ ሳይሰሙ ቀናቸውን በስመዓብ አይሉም…(ከአሜሪካ ሴት ልጅዋ ነበረች የደወለችው)---ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የአምባሳደሩ ሚስት መጣች፡፡ ይሄኔ ችግር ተፈጠረ፡፡ ‹‹ምንድን ነች?›› ብላ አፈጠጠች፡፡‹‹ይሄን ሁሉ የሰራችው እስዋ ናት›› አሏት፡፡ ‹‹ሰዎችን ከመቅጠር ጀምሮ..ፈረስ ቤቱን፣ አበባውን …የቤቱን ቀለም..ይሄን ሁሉ የሰራች እስዋ ናት›› በማለት አስረዷት፡፡ በጣም ሃርድ ወርከር ናት…ብላ ብታደንቀኝም ከጥቂት ጊዜ በኋላ አልተመቸኋትም መሰለኝ---ደሞዜም በጣም ብዙ ነበር፡፡ምን ያህል ይደርሳል?2ሺ ብር---ይሄ ሁሉ ከሙዚቃው በፊት ነው አይደል--ሙዚቃ ባልታሰበበት ጊዜ እኮ ነው የማወራሽ፡፡ እዚህና እዚያ አስረገጥሺኝ እኮ፡፡ እንዳልኩሽ የሰውየው ሚስት አልተመቸኋትም፡፡ ስርዓት አለኝ---ሰው አከብራለሁ---ሰው ስነሥርዓት ከሌለው አልወድም---ወዲያውኑ ነው የማስወግደው:: ሁለተኛ ማየት አልፈልግም፡፡ እናም‹‹..በቃ ወደ ውጪ መሄዴ ነው ….›› ብዬ ስነግረው አምባሳደሩ በጣም ደነገጠ፣ ተጨነቀ፡፡ እኔ ግን ትዕግስቴና ፍላጎቴ ተዘግቶ ስለነበር ትቼው ወጣሁ፡፡ይሄን ሁሉ ያስታወሰን እኮ ለአጉራሽነት ወደቤተመንግስት መግባትሽ ነው----.የአጉራሽነቱስ ጉዳይ---አጉራሽነትማ----ጃንሆይ ጥሩ ጥሩ ልጆችን አምጡ ብለው አዘዙ:: ‹‹እንደውም ጊዮን ሆቴል ሁለት ዌይትረስ አሉ አምጡዋቸው›› ተባለ፡፡ ቤተመንግስት ገብተን ፈረንጆችን እናጎርስ ጀመር፡፡ ፈረንጆቹ..“Oh my God. What is this? Is this napkin or what?...’” እያሉ ይወናበዱ ነበር፡፡ ስናጎርሳቸው ደስ እንዲላቸው ብለን ፊታቸው እጃችንን እንታጠብ ነበር----ከዛ ስናጎርሳቸው ተደስተው ሊሞቱ፡፡ ቆንጆ ነሽ----አድናቆት ምናምንስ አልነበረም? “you have a beautiful smile, you Ethiopians are beautiful” ይላሉ (ውብ ፈገግታ አለሽ--እናንተ ኢትዮጵያውያን ውብ ናችሁ) ----ምን ልበልሽ--- አድናቆት በአድናቆት ነው----ልዕልቶቹም ያዩናል፡፡ የሆነ ዝግጅት ሲኖር በመካከላቸው ካናፒ እናዞራለን፡፡ ‹‹እንዴት ቆንጆ ናት›› ይሉኝ ነበር፡፡ የአልጋ ወራሽ ሚስት በጣም ያደንቁኝ ነበር፡፡ ልዕልት ተናኘ ወርቅ ነፍሳቸውን ይማረው፡፡ …አረ ተይኝ---አድናቆታቸው ራሱ ገንዘብ ነው፡፡ አክብሮታቸው…ሰላምታቸው…አመለካከታቸው..ነገረ ስራቸው ሌላ ነበር፡፡በነገስታቱ ተሸልመሽ ታውቂያለሽ?እጅግ በጣም ብዙ ሽልማት እንጂ…የአንገት ወርቅ፣ የእጅ ወርቅ አምባር፣እንዲሁም ሰንጋ መግዣ ተብሎ 500 ብር ተሰጥቶኛል:: .የእኔ ልጅ---- ባሳለፍኩት ዕድሜ ቁጭ ማለትን አልወድም፣ የሰው እጅ መጠበቅን አልወድም፣ ስራ መስራት ያስደስተኛል፣ መጫወት መደሰት ቁምነገር መስራት---እጅግ ሰው እወዳለሁ..ስራ አልንቅም፡፡ የሚገባኝን ነገር አውቃለሁ፡፡ የሰው ነገር አልነካም፡፡ ለዚህም ነው ያልነካሁት የስራ ዓይነት የለም የምልሽ----.ቆይ ልቁጠርልሽ አርጀንቲና ኤምባሲ፣ ታንዛኒያ ኤምባሲ፣ ፊሊፕስ… ሾው ሩም ውስጥ ሁሉ እሰራ ነበር፡፡ የዋቢሸበሌ ፐርሶኔል አንዴ መብራት ሊገዙ መጥተው‹‹ምን ልትሰሪ ያለ ፊልድሽ መጣሽ?›› ብለው ዋቢሸበሌ

ወሰዱኝ..እዚያ ስሰራ ደግሞ የሂልተን ሆቴል ..“ፉድና ቤቨሬጅ ማኔጀር” መጡ፣ የውጪ ዜጋ ዋናው የሂልተንን ሃላፊ ጭምር ይዘው፡፡ ‹‹ምንድን ነው የምትበሉት?›› አልኳቸው፡፡‹‹አዘናል›› አሉ፡፡ ያዘዙትን ጠየቅሁ - ስጋ፣ ዶሮ፣ አሳ ነበር ያዘዙት፡፡ ሁለት ዓይነት ወይን ማዘዝ አለባቸው፡፡ አንድ ቀይ ዋይን፣ አንድ ነጭ ዋይን አልኩኝ፡፡ አለበለዚያ ሁለቱንም የሚያባላ ሮዜ ዋይን..አልኩና ሄጄ ጠየቅኋቸው፡፡ ‹‹ምንድን ነው የምትጠጡት? ምን ዓይነት ዋይን ላምጣላችሁ?›› አልኳቸው፡፡ ‹‹የምንበላውን ካወቅሽ አንቺ ጠቁሚን ምን ይሻለናል?›› አሉኝ፡፡ሞያዊ ትንታኔ ሰጠኋቸው፡፡ በጣም ተገረሙ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደዚህ ዓይነት ባለሞያ አለ ብለው ተደንቀዋል፡፡ ከመሄዳቸው በፊት ‹‹ፈቃድሽ ከሆነ..ሰኞ ጠዋት ሂልተን ሆቴል እንድትመጪ›› አሉኝ፡፡ ‹‹የት ነው ሂልተን ሆቴል?›› ብዬ ጠየኳቸው፡፡ ‹‹እዚህ እዚህ ቦታ….›› ብለው ነገሩኝ፡፡‹‹እኔ የሆቴል ስራ ሰልችቶኛል..ሆቴል እንዳይሆን ስላቸው..››‹‹ኖኖ እንደዚህ አይባልም..ስራ እንደዚህ አይባልም እንድትመጪ..›› አሉኝ፡፡ ሂልተን ሆቴል ሄድኩኝ---“.አይዞሽ ሲደክምሽ ማረፊያ ክፍል እንሰጥሻለን” አሉኝ፡፡ “መቼሽ ቲፑ ሌላ ነው----በጣም ቆንጆ ቦታ ነው፡፡ የተወሰነ ቦታ ነው የምትሰሪው” ብለው አግባቡኝ፡፡ አሒአ(አዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል) የሚል እንዴት ያለ የሚያምር የአበሻ ቀሚስ ተሰራልኝ መሰለሽ ---ላይት ብራውን እንደ ጎልዲሽ ዓይነት --- አቤት መልክ---አቤት ቁመና…፡፡ሂልተንስ ስንት ዓመት ሰራሽ?ከአራት ዓመት በላይ ሰርቻለሁ፡፡ በዘፈኖችሽ ላይ ንጉሶችን ማነሳሳት ትወጂያለሽ ---.የጣይቱ ጠጅ ነው…የምኒልክ እልፍኝ-- ትያለሽ?እኔ የሰርቶ አደር ልጅ ነኝ፡፡ ግን እነዚህ አብሬያቸው ያሳለፍኳቸው እንግዶች..ክብር ያላቸው፤ ለሰው ልጅ ጥሩ የሚመኙ፤ ደጎች ናቸው፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ የሰውን ልጅ ሲፈጥረው አንድ ነገር ይሰጠዋል…ሁሉን በፕሮግራም ነው የሚፈጥረው፡፡ እግዚአብሄር እኮ እኔን አድሎን ነው እንጂ---እኔ ማን ነኝ I am no body af-ter all. ከማንም አልበልጥም:: ሰው ስለምወድና ስለማከብር…አባቴ ሰርቶ አደርም ቢሆን አስተዳደጋችን እንዴት ሸጋ ነበር --- ልጆቼንም በዛ መንገድ ነው ያሰደግኋቸው፡፡ውጪ አገር ስራዎችሽን አቅርበሽ ታውቂያለሽ? በፍጹም፡፡ አንድ ጊዜ ብቻ አምባሰል የሚባል ሙዚቃ ቤት ዋሺንግተን ናይት ክለብ ነበረው፡፡ ለስድስት ወር ለመስራት ተስማምቼ ሄጄ ---.ለአራት ወር ያህል ከሰራሁ በኋላ ኢትዮጵያኖች እርስ በእርስ ሊጋደሉ ሲሆን ስራውን ትቼ ወደ አገሬ መጣሁ፡፡ ብዙም እንደዚህ ዓይነት ቦታ አይመቸኝም---የትዳርሽ ጉዳይስ---ልጆቼን ብቻዬን ነው ያሳደግሁት.--- ጠንካራ እናት ነኝ፡፡ .ባሎች ትንሽ አስቸጋሪዎች ነበሩ፡፡ ምን ይጎለኛል---ልጆቼን ለማሳደግ ብዬ ልውሰድም ቢሉ እሽ አልልም---.ይሄው ልጆቼን አሳደግሁኝ ዳርኩኝ--እግዚአብሄር ይመስገን፡፡ የዘመኑን ዘፈኖች ትሰሚያለሽ? እንዴት ነው ዘፈን ድሮ ቀረ ትያለሽ ወይስ ----ድምፁ የወጣው አሁን ይመስለኛል፡፡ ወጣቶቹ ቆንጆ ቆንጆ ድምጽ አላቸው፡፡ ሲዲውን ስሰማው ጥሩ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የምሰማው ወይ ስለ ሃገር፣ ስለ አንድ ታሪክ፣ ወይም ስለኢትዮጵያ ሊሆን ይችላል፡፡ ኢትዮጵያ ታሪክዋ ሰፊ ነው፡፡ አንዳንዱን እያነሱ አንስቶ መስራቱ ጥሩ ነው፡፡ የፍቅር ነገር መቼም እንዳለ ነው አያረጅም፡፡ ፍቅር ትልቅ ነገር ነው፡፡ ሁልጊዜ ግን ስለ ፍቅረኛ፣ ስለ ባል፣ ስለ ሚስት--- ተጣላኝ ታረቀኝ አባረርከኝ…መለስከኝ…እንደዚህ ዓይነት በጣም ሲበዛ ጥሩ አይደለም፡፡ አንችዬ አርጅቼ ይሆን እንዴ? ግን አይደለም…ድሮም ይሄው ነው ስሜቴ…ሁሉም ይቅር እያልኩ አይደለም፡፡ በየመሃሉ ቁምነገር ቢገባበት ማለቴ ነው፡፡ እንጂ ድምፅማ የመጣው አሁን ነው፡፡ በድሮና በአሁን ዘፈኖች መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው ትያለሽ?ምርጫቸውና የደረሱበት ቴክኖሎጂ ነው፡፡ በአብዛኛው የፈረንጅ መዚቃ፤ የፈረንጅ ሲኒማ፤ የፈረንጅ ዘፋኞች የሚሆኑትን ነው የሚሆኑት፡፡ ከአሁኑ ዘፋኞች ቴዲ አፍሮን ---- ጎንደር ብዙ የተጫወቱ ልጆች አሉ --ማዲንጎ እስከ ወንድሙ…ግሩም ናቸው:: ማዲንጎን ያየሽ እንደሆን የበላይን ታሪክ አስቀምጦታል--- በደንብ --- ታምር ነው መቼም፡፡ እኔማ ያሳዝነኛል ያንን ሲጫወት::

እነዚህ ቁም ነገር ያላቸው ነገሮች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ባህል እኮ ተወርቶም አያልቅ፡፡ መጸሐፍም አይችለው፡፡ አስተማሪዎች ያስፈልጋሉ፡፡ እኛ እኮ ድሮ ትምህርት ቤት ስንማር መጀመርያ ስለሃገራችን ጋራ ሸንተረር..ተምረን ነው ወደ ውጪ የምንሻገረው:: አሁን ማን ያስተምራል….እዚህም አገር አማርኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ እየታየ ነው፡፡ እኛ ድሮ በትምህርት ቤት ውስጥ ባንዲራ አውርደን ክፍል እንደገባን ፀሎት እናደርጋለን፤ ከፀሎት በኋላ የሚገባው አስተማሪያችን የግብረገብ ነው፡፡ ከዛ በኋላ ነው ትምህርቱ የሚቀጥለው፡፡ ኢትዮጵያ ከአለም አንደኛ ናት ብል----.አላፍርም፡፡ስለ ሃገሬ ተናግሬም አልጨርሰው፤አቅሜም አይችለው፡፡ አገራችን፣ ህዝባችን፣ አለባበሳችን፣ ምግባችን፣ አየሩ…በክረምቱ ሰዓት ክረምቱ የታወቀ ነው፤ በበጋው ሰዓት በጋው የታወቀ ነው፣ በበልግ ሰዓት በልጉ የታወቀ ነው፤ አለቀ፡፡ አየራችን ደግሞ ልዩ ነው፡፡ የምታኮራ አገር የሚያኮራ ህዝብ ነው ያለን..ይሄ ራሱ ቢዘፈንለት አይበቃም፡፡ስንት ካሴት በነጠላ እና በጋራ ሰራሽ..ወደ 12 ካሴቶችን ሰርቻለሁ፡፡ “ምኒልክ” የሚለው ዘፈኔ ዜማውን የሰራሁት እኔ ነኝ፡፡ የሁሉም ካሴቶቼ ግጥም ድርሰት የይልማ ገብረ አብ ናቸው፡፡ የድምፅሽን ለዛ ስለሚያውቀው በይልማ መርጦ የሚሰጥሽአዋ፡፡ ይልማ በአንድ ወቅት አንድ ስራ ገጥሞት አንድ ካሴቴ ላይ ብቻ ሶስት ዘፈኖች የሌላ ሰው ነበሩ፡፡ ከይልማ ጋር ስንሰራ ግጥሞችን መክረንባቸውና ተነጋግረን ነው - ይሄ ይውጣ ይሄ ይግባ ብለን፡፡ አንድ ጊዜ ምን ሆነ…‹‹በደሳሳ ጎጆ ቁጭ ብዬ ብቻዬን ሳለቅስ..›› ምናምን የሚል ግጥም ..መጣልኝ…እኔ እንደዚህ አይነት ነገር …ምንድን ነው በፍፁም አልዘፍንም አልኳቸው፡፡ ችግርም የለብኝ..ይቅርታ አድርጉልኝ የእኔ ስሜት ለእንደዚህ ዓይነት ነገር አይሰራም አልኳቸው፡፡ በጣም ሳቁ..ጭንቅ አልወድም ሌግዠሪ ነገር ነው የምወደው…ዝም ያለ ቆፍጠን ያለ…ለሰውም ቀለል ሲል..ነው፡፡ የእኔን ለቅሶና ሃዘን ህዝብን ስማልኝ ማለት ምንድን ነው:: የሆነ ድባብ እኮ ይፈጥራል፡፡ ይቅርታ እንግዲህ እኔ እንደዚህ አይነት ታይፕ የለኝም፡፡ ከተሸመ አሰግድ፤ ጋሽ ባህሩ፣ ጋሽ ይርጋ፣ ከተማ መኮንን፣ ዳምጠው…ኡፍ ለዛ አላቸው እኮ፡፡ my God!! የማይሰለቹ እኮ ናቸው፡፡ ስሚ የዛን ዘመን ዘፋኞች..እነ ወረታው…የወረታው ድምፅ እኮ..ራሱ ጊታር ነው፤ ራሱ ሳክስፎን ነው፤ራሱ ቤዝ ጊታር ነው፤ በጣም ጎልደን ድምፅ እኮ ነው ያለው:: ከብዙዎች ጋር ሰርቻለሁ፡፡ ልረሳ ነው እንዴ..እረ አንቺ ልጅ ይሄ ነገር ያሰጋል---- እርጅና መጣ መሰለኝዕድሜሽ ግን ስንት ሆነ?63 ዓመቴን ባለፈው የፋሲካ ዕለት አከበርኩ.---.ገና ልጅ እኮ ነኝ፡፡መልካም ልደት፣ ረጅም ዕድሜ ተመኝተንልሻል፡፡ በሶስት መንግስታት ውስጥ በአርቲስትነት ትታወሻለሽ--የደርግ ጊዜን ሳልነግርሽ፡፡ በምሽት ክበቤ ውስጥ ..እረ ገዳዬ፣ እንደው ዘራፌዋ፣ እንደ ኮሜዲ አድርጌ የምጫወተው ስራ ነበረኝ:: እረ ገዳዬ የሚለውን በእንግሊዝኛ እለው ነበር---እስኪ አሁን በይልኝ-- Oh killer oh killer The useless goat give birth to nineShe is died and her childrenI love the killer I love the killer As well as the shooterWhen I feel tired I rest under the umberella of ጀግናዬ hair.ብታይ ሰው ይሄን እንደ ኮሜዲ ነው የሚሰማው----.ትርጓሜው ደግሞ ትክክል ነው፡፡እረ ገዳዬ አረ ገዳዬየማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለችልጆችዋም ያልቃሉ እስዋም ትሞታለች፡፡ ስሚ እኔ ጀግና እወዳለሁ፡፡ ዘፋኝ ባልሆን ወታደር ነበር የምሆነው፡፡ በጣም በጣም ነው ወታደር መሆን..ለመዝመት አስበሽ አታውቂም ታዲያ-- አይ ልጄቼን ከወለድኩ በኋላ ..ሃላፊነቱም አለ..፡፡ የአሁኑ አልበምሽ..ከስንት ጊዜ በኋላ ወጣ?ከ7 ዓመት በኋላ…ሰርቼው ቁጭ አድርጌው ነበር…ኮፒ ራይቱም አስጨናቂ ስለነበረ..ሰርቼ ቁጭ አደረኩት:: የምገዛ ሲጠፋ:: አቶ ቁምላቸው ገብረስላሴ የፋሲካ ባለቤት/የሚሞ ባለቤት…የተፈጠረውን አጫወትኩት፡፡ ከፈቃደ ዋሬ የአምባሰል ሙዚቃ ቤት ባለቤት ጋር እንደ ወንድም ነው የሚተያዩት፡፡ ተነጋገሩና ይሄው ባለፈው ለሰው አፍ አበቁልኝ፡፡ምን ያህል ገቢ አገኘሽበት ?እሱን ተይውከአሁን በኋላስ ምን ታስቢያለሽ? አገሬ ላይ ቁጪ ብዬ እግዚአብሄርን ማመስገን ነው…የምስጋና መዝሙር ነው ሃሳቤ፡፡ ደስተኛ ነኝ…እንምታይው ሁሉ ሙሉ ነው..ተመስገን ለእግዚአብሄር ምን ይሳነዋል፡፡ አይንሽን አሞሽ ነበር?አዎ… ሼክ ሙሃመድ አሊ አሙዲ ናቸው ያሳከሙኝ…የምዘፍነው:: የኢትዮጵያን ህዝብ በሙሉ እወዳቸዋለሁ::

(አዲስ አድማስ ጋዜጣ በ2013 ዓ.ም. ከአርቲስቷ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ)

‹‹እኔ የሰርቶ አደር ልጅ ነኝ፡፡ ግን እነዚህ አብሬያቸው ያሳለፍኳቸው እንግዶች..ክብር ያላቸው፤ ለሰው ልጅ ጥሩ

የሚመኙ፤ ደጎች ናቸው፡፡››

ዋይን ከገጽ 9 የዞረ

Page 22: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 22

A recent survey of 10,000 consumers was conducted by the Temkin Group (findings fully

reported at www.credit.com); they reveal that the “best” insurer is USAA.

The ratings reflect consumer satisfaction with how the company resolved issues and how easy or hard it was to work with the company.

#2 was State Farm, followed by GEICO, The Hartford, Progressive, Allstate, AAA, Nationwide, Travelers, and then Liberty Mutual.

You should first be concerned about your coverages.

Get “high” (at least $100,000.00) liability coverage limits. This

protects you if an accident is your fault and someone is injured or killed. It also protects you if someone was driving your car with your permission and causes an accident. I actually recommend you get limits of $500,000. The premium differential between $100K and $500K is not that much!

Next, get high Uninsured Motorist coverage limits (at least $100K, consider $500K). This protects you if someone else causes the accident, and they do not have insurance, or they have lower limits. You can then use your insurance to properly compensate you if you are injured, and your insurer CANNOT cancel your policy or increase your premium because you used the coverage.

My advice for this Issue is about Being smart when choosing

automobile insurance.You may be interested in how much you pay for these coverages. Of course, it is important -- but not as important as getting the right coverages, above, and the amounts of those coverages.

Certainly, compare between companies, but compare apples to apples. Do not use different coverage amounts to compare...

Of interest also is what traffic violations can do to your premiums.

The folks at www.bankrate.com advise that a DWI or DUI can lead to a 25% increase in your premiums. Reckless driving will trigger a 15% jump. Speeding will increase your rates about 10%, unless it is your first violation and

your were within 10 miles of the posted limit. Finally, both running a red light and driving without a valid license can cause a 10% increase in your premiums.

Choose wisely, drive safely.

Virginia & Maryland Injury Claims

703-761-4343 or

301-949-1515

(Paul A. Samakow)

Page 23: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ገጽ 23

DC7 ELEVEN STORESNorth East Divison1115 U Street, NWWashington, DC(202) 232 3234

Abyssinia Market141 Florida Ave. NW,Washington, DC (202) 332-0894

ADAMS MORGAN COFFEE SHOPE2204 18th Street N.WWashington, DC (202) 588-0599

DUKEM MARKET AND RESTAU-RANT1114 U Street NWWashington DC(202) 667-8735

ENAT ETHIOPIAN INTERNATION-AL MARKET & DELI6224 Georgia Ave. NWWashington, DC (202) 541-9550

ESHET ENJERA & GROCERY829 Kennedy St. NW Washington Dc 20011(202) 545 1670/ (301) 793 8132

ETHIOPIAN RESTAURANT & MART 4630 14th St. NWWashington, DC (202)291-5150

FAMILY FOOD MART 3713 New Hampshire Ave, N.WWashington, DC (202) 723-6017

HABESHA MARKET & CARRYOUT1919 9TH St NWWashington DC202) 232-1919

LENA MARKET & CARRYOUT1206 Underwood St NWWashington, DC (202) 291-0082

NILE MARKET & RESTAU-RANT7815 Georgia Ave. NWWashington, DC (202) 882-1130

ZELALEM INJERA2260 25th N.EWashington DC(202) 832-0281(703) 628-5716

ZENEBECH INJERA & CARRY OUT

608 T St NWWashington, DC (202) 607-6700

MDADDISU GEBEYA8107 Fenton St.Silver Spring, MD(301) 589-8417(301) 589-8423

ARADA INTERNATIONAL MARKET6844 New Hampshire Ave.Takoma Park, MD (301) 270-3224

ARAT KILO MARKET & TRAVEL AGENCY818 Easley StreetSilver Spring, MD (301) 588-0077

BLACK LION GROCERY7607 Maple Ave,Takoma Park, MD (301)270-2721

DASHEN ETHIOPIAN GROCERY8474 Piney Branch RDSilver Spring, MD (301) 562-4040

DESSIE GROCERY2655 University Blvd.Wheaton, MD (301) 933-5580

ETHIO PLUS 11303 Georgia Ave.Wheaton, MD (301) 962-3544

FAIRLAND MARKET13318 Old Columbia PikeSilver Spring, MD (301) 384-8323

HABESAH INTERNATIONAL MARKET2311 Varnum St.Mt. Rainier, MD .(301) 277-6070

REBECCA ETHIOPIAN RESTAURANT7443 Annapolis RdNew Carlton, MD (202) 722 0999

SHEGER MARKET912 East West Hwy.Takoma Park, MD (301) 270-0200

SPICE OF INDIA1335-A University Blvd. E.Langley Park, MD(301) 431-3361

TANA MARKET623 Sligo Ave.Silver Spring, MD(301) 562-9322

WESENYELESH MARKET901 Silver Spring AveSilver Spring, MD (301) 588-2390

WODER ETHIOPIANGROCERY & EXOTIC MARKET7845 Eastern AveSilver Spring, MD (301) 562-5901

VAABAY MARKET3811-A South. George Mason Dr.Falls Church, VA(703) 998-5322

AFGHAN MARKET5715 Edsall RdAlexandria VA(703)-212-9529

AL-AMAL SUPER MARKET3817-G S. George Mason Dr. Falls Church, VA(703)-820-2988

AMANAH MARKET3811-1 S. George Mason Dr.Falls Church, VA (703-379-5539)

ASNI MARKET, INC1045 S. Edgewood St.Arlington, VA (703) 979-3944)

AWASH MARKET & BUTCHER SHOP3825-B S. George Mason Dr.Falls Church, VA(703) 931-4180

AZIEB MARKET3823 F S. George Mason Dr.Falls Church, VA (703) 820-4800

BERHAN MARKET 3823-B1 S. Geoge Mason Dr.Falls Church, VA

(703)845-1004(202)299-7625

BROOK MARKET2522 Columbia Pike,Arlington, VA 22204(703) 271 8529

DAMA MARKET1503 Columbia PikeArlington, VA (703) 920-3559

DEWAN CAFÉ3403 Payne St. Falls Church, VA(703) 347-9489

KARE INTERNATIONAL WHOLESALE AND RETAIL MARKET503 S. Pickett St Alexandria VA(703) 370 2606)(703) 575 9200)KHAN EL-KHALIL5826 Seminary Rd.Falls Church, VA(703) 671-1286

LANDMARK BAKERY & CAFÉ INC670 S. Pickett St. Alexandria, VA (703) 370-7941

LIDETA MARKET2630 Colombia PikeArlington, VA (703) 920-3099

LOZA MARKET10 South Jordan StAlexandria, VA (703) 751 2947

MARHABA MARKET 3819 G South George Mason Dr.Falls Church, VA (703) 820-7589

MEAZA RESTAURANT, CAFÉ & MARKET5700 Columbia PikeFalls Church, VA(703) 820 2870

MEDITERRANEAN GOUR-MET MARKET6122 Franconia Road,

Alexandria VA(703) 971-7799

MENA FARM3451 Logmill RdHaymarket, VA(571) 222-7222 (703) 869-7842

MENA MARKET INC6222 Rolling Rd.Springfield, VA(703) 913-7133

MERKATO MARKET6815 Bland St.Spring field, VA 22150(703) 663 8635

NAZRET CULTURAL FOODS3821 E S. George Mason Dr.Falls church, VA (703) 365-7843

SORA ETHIOPIAN MAR-KET5145-C Duke St, Alexan-dria, VA(703 566 3855)

TEDY MARKET14418 Jefferson Davis Hwy Woodbridge VA 22191 (571) 408 4285)

TENADAM INTERNATION-AL MARKET3817-C S George Mason Dr.Falls church VA(703) 933-6038)

TSEDAY ABEBA GROCERY, CAFÉ & CARY OUT672 South Picket St.Alexandria, VA (703) 461-9420)

WUBE BERHAN MARKET3823 A S. George Mason Dr.Falls Church, VA . . . . . . (703)820-0889(703)933-0040

የኢትዮጵያ የገበያ ቦታዎች/Groceries/

Page 24: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ገጽ 24

በህክምና ዘርፉ ትሰራላችሁ?

ከአሜሪካ ውጭ ከሶስት ዓመት በፊት ደቡብ

ሱዳንን ጎበኘን፣ የህክምና አገልግሎት አልነበረም

ምክንያቱም ገና አዲስ አገር ስለነበረ፡፡ ከተለያያ

ዓለም ወደ ደቡብ ሱዳን በመጓዝ ለስራም ለጉብኝት

ሃገሪቱ አዲስ በመሆኗ የሰው ሃይል ይፈልጉ ነበር::

ስለዚህ የብሉናይል ግሩፕ ሆስፒታል ለመገንባት

አስበን፣ እየተንቀሳቀስን ነው፡፡ ነገር ግን የእርስ በርስ

ጦርነት ስለተነሳ በአሁኑ ጊዜ ስራውን ገትተነዋል::

በሌላ በኩልም ሶስት መቶ የሚሆን ቁጥር ያለው

“ኢትዮጵያን አሜሪካን ዶክተርስ ግሩፕ” የሚባል

የዶክተሮች ስብስብ አለ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ

ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል ለመስራት እንቅስቃሴ

ተጀምሯል:: በቡድኑ ውስጥ እኛም አለንበት፡፡

ስለ እድገትዋ እናውራ?

እድገቴ አዲስ አበባ መርካቶና ዊንጌት አካባቢ ነው::

ቤተሰቦቼ ለትምህርት የተለየ ስፍራ ነበራቸው፡፡

የአንደኛ ደረጃ ትምህርቴን የተማርኩት ካቴድራል

ሲሆን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የገባሁት ሴንጆሴፍ

ነው፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ሳጠናቅቅ ነጥብ

ስለመጣልኝ ጎንደር ኮሌጅ ኦፍ ሜዲካል ሳይንስ

ተማርኩ፡፡ ከስድስት ዓመት የህክምና ትምህርት

ምርቃት በኋላ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ጄነራል

ፕራክትሽነር ተብለን ነው የወጣነው፡፡ የመጀመሪያ

ስራ የጀመርኩት በዘውዲቱ ሆስፒታል፣ የውስጥ

ደዌ በሽታዎች ክፍል ሆኙ ሶስት ዓመት ሰራሁ፡፡

በ1995ዓ.ም. ወደ አሜሪካ መጣሁ፡፡ በ1997ዓ.ም.

ሚችገን ስቴት ውስጥ በኢንተርናል ሜዲሲንና

ፒዲያትሪክስ ስፔሻላይዝድ አደረኩ፡፡ ትምህርቴን

እንደአጠናከኩ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ መጣሁ፡፡

``ብሉ ናይል `` ብለን ስራ ጀመርን;;

ቤተሰብ መስርተዋል?

ሁለት ልጆች አሉኝ፡፡ የአስርና የአስራ አምስት

አመት ልጆች አሉኝ፡፡ ከባለቤቴ(ከልጆቼ እናት) ጋር

አብረን ነው ያደግነው ማለት ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ

በመጣሁ ከስድስት ወር በኋላ ነው ባለቤቴ ወደ

አሜሪካ የመጣችው፡፡ ኢትዮጵያ እያለን ጓደኞች

ነበርን፡፡ ባለቤቴ ወደ እንግሊዝ አገር እሄዳለሁ እንጂ

ወደ አሜሪካ እመጣለሁ የሚል ሃሳብ አልነበራትም::

ምክንያቱም ወንድሞችዋ እንግሊዝ አገር ስለነበሩ

አሜሪካን የመምጣት ሃሳቡ አልነበራት:: ስለዚህም

እኔ ወደ አሜሪካ ስመጣ መልካም እድል ተመኛኝተን

ነው የተለያየነው፡፡ ነገር ግን ወደ አውሮፕላን ማረፊያ

እኔን ሸኝታኝ ስትመለስ ዲቪ ደረሳት፡፡

እርስዎ ወደ አሜሪካ ጉዞ በጀመሩ እለት…?

አዎ፡፡ በተመሳሳይ ቀን፡፡ ዲቪ ደረሳት እኔ ወደ

አሜሪካ ከመጣሁ ከስድስት ወር በኋላ ዋሽንግተን

ዲሲ መጣች፣ እኔ በወቅቱ ሚችጋን ስቴት ነበርኩ::

እኔ ወደአለሁበት አገር ጋበዝኳት መጣች፤ ተገናኘን

በዛን ጊዜ የተጀመረ ፍቅር ይሄው ዛሬ ተጋብተን

ሁለት ልጆችን ወልደናል፡፡

በምንኖርበት አገር በርካታ ትዳሮች በአጭር

ይቀጫሉ፣ ቤተሰቦች ይበተናሉ?

የትዳር ጓደኛ የሚሰጠው አምላክ ነው። ለዚህ

ደግሞ የኛ ታሪክ ምስክር ነው። መዋደዱ ፍቅሩ

ካለ ትናንሽ ነገሮችን አለመመልከት፣ መደማመጥ፣

መቻቻል የትዳር መሰረት ናቸው፡፡ በትዳር ውስጥ

ልጆች ካሉ ነገሮች ሁሉ ጥቃቅን ነገሮች ይኖራሉ::

ሰው እንኳን ከሁለተኛ ወገን ከራሱ ጋር ሲጣላ

ይውላል:: ትናንሽ ነገሮችን በትላልቅ ነገሮችን

ሊሸፍናቸው ይገባል፡፡ አብሮ መኖሩ ራሱን የቻለ

ኮምፕሮማይዝ(Comprimse) የማረግ ሂደት ነው::

በኢትዮጵያ ውስጥ በቂ ዶክተሮች አሉ ብለው

ያምናሉ?

ኢትዮጵያ ውስጥ በቂ ዶክተሮች አሉ ብዬ አላምንም::

ከሀያ ዓመት በፊት የህክምና ትምህርት ቤቶች ሶስት

ነበሩ ጎንደር፣ ጅማ፣ አዲስ አበባ ሶስት መቶ ዶክተር

በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ያስመርቁ ነበር፡፡ በዚያን

ወቅት የኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር ከ30 እስከ 40

ሚሊዩን ይደርስ ነበር፡፡ ዛሬ ዛሬ ግን የኢትዮጵያ

ህዝብ ቁጥር 90 ሚሊዩን አካባቢ ሆንዋል እያደገ

ነው፡፡ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች

ተከፍተው በርካታ ባለሞያ ቢያስመርቁም ኢትዮጵያ

የሚኖር አብዛኛው ዶክተር ወደ ውጭ አገር ይሄዳል::

በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያን ዶክተርስ በተለያዩ የዓለም

ብሉናይል ከገጹ 4 የዞረ

ክፍሎች አሉ፡፡ አዲስ ተመራቂ ዶክተሮችም በተለያየ

ዓለም ይሄዳሉ፡፡ ስለዚህም በኢትዮጵያ የዶክተሮች

እጥረት ሊኖር ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡

በህክምና ሞያ ለመማርና መሰማራት ለሚፈልግ

ወጣቶች የሚያስተላልፉት መልዕክት አለዎት?

ሞያው መስዕዋትነትን ይጠይቃል፡፡ ከአስራ ሁለት

ዓመት እስከ አስራ አምስት ዓመት ትምህርት ቤት

ያስኬዳል:: ለዚህም የተሰጠ መሆንን ይጠይቃል::

ወጣቶቹ ፕሮፌሽኑን ወደውት እንዲገቡ

እመክራለሁ፡፡ የሚገኘው ገንዘብ ታስቦ የሚገባ

ከሆነ በጣም አስቸጋሪ ነው የሚሆነው:: የህክምና

ሞያ ሪዋርዲንግ ነው፡፡ በሽተኛ ተሽሎት ሲታይ

ደስታ ይሰጣል፡፡ ስራው ላይ ሲኮን የሚሰማ ደስ

የሚል ዓይነት ስሜት ነው፤ የሙያ እርካታ አለው።

የህክምና ሞያ የገንዘብ አቅም ከዓመታት በፊት

ከነበሩት በተለየ የገቢ ምንጩ አስተማማኝ አይደለም

ይባላል?

ህክምና በታሪክ በርግጥ የሚያረጋጋ ስራ ነው::

በየትኛውም ዓለም፡፡ ስራው ሁልጊዜም አለ::

ተመጣጣኝ ገቢም ይኖረዋል፡፡ ነገር ግን የዛሬ

ሰላሳ ዓመት የነበረው የህክምና ባለሞያዎች የገቢ

ሁኔታና ዛሬ ያለው ይለያያል:: የቀድሞዎቹ ሃኪሞች

የገቢያቸው ደረጃ ክፍያውም ከፍተኛ ነበር በአሁኑ

ጊዜ መካከለኛ ገቢ ማለት ይቻላል፡፡

ስለ ሰጡን ጊዜ እናመሰግናለን

Page 25: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 25

Page 26: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 26ስፓርት

Page 27: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 27

Page 28: Bawza Newspaper publication of the Ethiopian …bawza.com/wp-content/uploads/2015/05/Bawza-Newspaper...ገጽ 1 Bawza Newspaper publication of the Ethiopian Yellow Pages May 2015 Vol.2

ባውዛ ጋዜጣ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፩

ገጽ 28