12 03 2009.pdf

48
በኩር ለህብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን! 22ኛ ዓመት ቁጥር 50 ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም ዕትም ዋጋ 2 ብር ገጽ 11 ገጽ 48 - የመኸሩ ተስፋ - ባቲ እንደ ቅኝቱ በስፖርቱ… ገጽ 23 ገጽ 3 ገጽ 15 - አዝጋሚው ጉዞ - የታካሚዎች ስጋት - “አረቦን” ገጽ 17 - ሁለተኛው ገጽ ስርጭቱን በናይል ሳት ገጽ - 5 በውስጥ ገፆች ) Frequency- 12341 ) Symbol rate - 27500 ) FEC- 3/4 ) Polarization – horizontal መከታተል ይችላሉ:: ወደ ገጽ 20 ዞሯል ትኩረት የሚሻው ሌሽማኒያሲስ አብርሃም በዕውቀት በአራት ቀን አንዴ ውኃ ለማግኘት ረዣዥም ሰልፎች ይፈጠራሉ አብርሃም አዳሙ አዲሱ አያሌው ነዋሪዎች በመጠጥ ውኃ እጥረት እየተቸገሩ መሆኑን ገለጹ ደብረ ብርሃን፡- ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳ ረሻ እየሆነች ነው ተባለ የእግረኞች ጥንቃቄ ‘የትራፊክ አደጋን ቀንሷል’ የደብረ ብርሃን ከተማ ተመራጭ የኢንሸትመንት መዳረሻ እየሆነች መምጣቷን ከተማ አስተዳደሩና ባለሀብቶች ገለፁ:: የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ታገል አምሣሉ ለበኩር እንደገለፁት በከተማዋ የሚካሄደው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ ፈጣን እድገት እያሳየ መጥቷል:: በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር እግረኞች የሚያደርጉት ጥንቃቄ በእግረኞች ላይ ይደርስ የነበረውን የትራፊክ አደጋ መቀነስ መቻሉን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ:: በመምሪያው የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማረጋገጫ ዋና የሥራ ሂደት መሪ ም/ኮማንደር አዳሙ ይሁን እንደተናገሩት ከ2006 ዓ.ም አጋማሽ አንስቶ እስከ 2008 ዓ.ም ማጠናቀቂያ ባሉት 30 ወራት በእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ችግር የተከሰተ የትራፊክ አደጋ የለም:: ለውጡ በረዥም ጊዜ ጥረት የመጣ መሆኑንም ም/ኮማንደር አዳሙ ተናግረዋል:: የባንጃ ወረዳ ነዋሪ የሆነው አዲሱ ዓለማየሁ በበኩሉ የአካባቢው ነዋሪዎች የመንገድ አጠቃቀም የተሻሻለው የትራፊክ ፖሊሶች ሕብረተሰቡ በሚገናኝባቸው መድረኮች ሁሉ እየተገኙ ተከታታይ ትምህርት በመስጠታቸው መሆኑን ተናግሯል:: ሕብረተሰቡም የሚሰጠው የመንገድ ደህንነት ትምህርት ለራሱ ሕይወትና አካል ደህንነት የሚበጅ መሆኑን አምኖ መተግበሩ ለለውጡ አወንታዊ ሚና መጫወቱንም አስረድቷል:: ወ/ሮ አቡኔ አዱኛ የተባሉ የፋግታ ለኮማ ወረዳ ነዋሪም “ስለመንገድ አጠቃቀም በትራፊክ ፖሊሶች ለረዥም ዓመት ትምህርት ሲሰጠን ኖሯል፤ ወደ ገጽ 20 ዞሯል በደቡብ ወሎ ዞን ሳይንት ወረዳ የአጅባር ከተማ ነዋሪዎች በመጠጥ ውኃ ዕጥረት እየተቸገሩ መሆኑን ገለፁ:: በሳይንት ወረዳ አጅባር የከፍተኛ መሰናዶ ትምህርት ቤት የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ቃልኪዳን መኮንን ወደ ገጽ 20 ዞሯል ከተማዋ ከአዲስ አበባ በቅርበት መገኘቷ፣ ቀልጣፋ የአገልግሎት አሠጣጥ መኖሩና የመሠረተ ልማቶች መስፋፋታቸው ባለሃብቶች ከተማዋን እንዲመርጧት አድርጓታል ብለዋል:: ከነዚህ ምቹ ሁኔታዎች ጀርባ ያለው ትክክለኛ ፖሊሲና ስትራቴጅ ዋናው አቅም እንደሆነም አብራርተዋል:: በአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ግንባታ ለማካሄድ እንቅስቃሴ የጀመረው የጅኒፐር ግላስ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሠነ የግል ኩባንያ ኘሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ ሙሉጌታ እንደተናገረችው ተማሪዎች በጠዋት ተነስተው ከማጥናትና ትምህርት ቤት ለመሄድ ከመዘጋጀት ይልቅ የውኃ ወረፋ ለመጠበቅ ተገደዋል:: በተለይ የጥዋት ፈረቃ በሚሆኑበት ጊዜ የውሃ ወረፋ ሲጠብቁ ስለሚረፍድባቸው ቁርስ ሳይበሉ ትምህርት ቤት ስለሚሄዱ ትምህርታቸውን ለመከታተል እንደተቸገሩ ገልፃለች:: የአጅባር ከተማ ነዋሪዋ ወ/ሮ ሙሉ ተገኔም የውኃ ችግሩ እሳቸውን ጨምሮ በግቢያቸው ውስጥ ቤት ተከራይተው የሚኖሩ የመንግሥት ሰራተኞችንም ለችግር መዳረጉን ተናግረዋል:: እነዚህ የመንግሥት ሰራተኞች ምግብ እንኳን አሁን ላይ ጥቅሙ ለራሳችን ሕይወትና አካል ደህንነት ከፍተኛ ስለሆነ ሁሌም አቶ አዲሱ ወርቅነህ

Transcript of 12 03 2009.pdf

Page 1: 12 03 2009.pdf

በኩርለ ህ ብ ረ ተ ሰ ብ ለ ው ጥ እ ን ተ ጋ ለን !

22ኛ ዓመት ቁጥር 50 ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም ዕትም ዋጋ 2 ብር

ገጽ 11

ገጽ 48

-የመኸሩ ተስፋ

- ባቲ እንደ ቅኝቱ በስፖርቱ…

ገጽ 23

ገጽ 3

ገጽ 15

- አዝጋሚው

ጉዞ- የታካሚዎች

ስጋት

-“አረቦን”

ገጽ 17

-ሁለተኛውገጽ

ስርጭቱን በናይል ሳት

ገጽ - 5

በውስጥ ገፆች

) Frequency- 12341 ) Symbol rate - 27500 ) FEC- 3/4

) Polarization – horizontal

መከታተል ይችላሉ::

ወደ ገጽ 20 ዞሯል

ትኩረት

የሚሻው

ሌሽማኒያሲስ

አብርሃም በዕውቀት

በአራት ቀን አንዴ ውኃ ለማግኘት ረዣዥም ሰልፎች ይፈጠራሉ

አብርሃም አዳሙ

አዲሱ አያሌው

ነዋሪዎች በመጠጥ ውኃ እጥረት እየተቸገሩ መሆኑን ገለጹ

ደብረ ብርሃን፡- ተመራጭ

የኢንቨስትመንት መዳረሻ እየሆነች ነው ተባለ

የእግረኞች ጥንቃቄ ‘የትራፊክ አደጋን ቀንሷል’

የደብረ ብርሃን ከተማ ተመራጭ የኢንሸትመንት መዳረሻ እየሆነች መምጣቷን ከተማ አስተዳደሩና ባለሀብቶች ገለፁ::

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ታገል አምሣሉ ለበኩር እንደገለፁት በከተማዋ የሚካሄደው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ ፈጣን እድገት እያሳየ መጥቷል::

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር እግረኞች የሚያደርጉት ጥንቃቄ በእግረኞች ላይ ይደርስ የነበረውን የትራፊክ አደጋ መቀነስ መቻሉን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ::

በመምሪያው የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማረጋገጫ ዋና የሥራ ሂደት መሪ ም/ኮማንደር አዳሙ ይሁን እንደተናገሩት ከ2006 ዓ.ም አጋማሽ አንስቶ እስከ 2008 ዓ.ም ማጠናቀቂያ ባሉት 30 ወራት በእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ችግር የተከሰተ የትራፊክ አደጋ የለም:: ለውጡ በረዥም ጊዜ ጥረት የመጣ መሆኑንም ም/ኮማንደር አዳሙ ተናግረዋል::

የባንጃ ወረዳ ነዋሪ የሆነው አዲሱ ዓለማየሁ በበኩሉ የአካባቢው ነዋሪዎች የመንገድ አጠቃቀም የተሻሻለው የትራፊክ ፖሊሶች ሕብረተሰቡ በሚገናኝባቸው መድረኮች ሁሉ እየተገኙ ተከታታይ ትምህርት በመስጠታቸው መሆኑን ተናግሯል:: ሕብረተሰቡም የሚሰጠው የመንገድ ደህንነት ትምህርት ለራሱ ሕይወትና አካል ደህንነት የሚበጅ መሆኑን አምኖ መተግበሩ ለለውጡ አወንታዊ ሚና መጫወቱንም አስረድቷል::

ወ/ሮ አቡኔ አዱኛ የተባሉ የፋግታ ለኮማ ወረዳ ነዋሪም “ስለመንገድ አጠቃቀም በትራፊክ ፖሊሶች ለረዥም ዓመት ትምህርት ሲሰጠን ኖሯል፤

ወደ ገጽ 20 ዞሯል

በደቡብ ወሎ ዞን ሳይንት ወረዳ የአጅባር ከተማ ነዋሪዎች በመጠጥ ውኃ ዕጥረት እየተቸገሩ መሆኑን ገለፁ::

በሳይንት ወረዳ አጅባር የከፍተኛ መሰናዶ ትምህርት ቤት የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ቃልኪዳን መኮንን ወደ ገጽ 20 ዞሯል

ከተማዋ ከአዲስ አበባ በቅርበት መገኘቷ፣ ቀልጣፋ የአገልግሎት

አሠጣጥ መኖሩና የመሠረተ ልማቶች መስፋፋታቸው ባለሃብቶች ከተማዋን እንዲመርጧት አድርጓታል ብለዋል:: ከነዚህ ምቹ ሁኔታዎች ጀርባ ያለው

ትክክለኛ ፖሊሲና ስትራቴጅ ዋናው አቅም እንደሆነም አብራርተዋል::

በአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ግንባታ ለማካሄድ እንቅስቃሴ የጀመረው

የጅኒፐር ግላስ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሠነ የግል ኩባንያ ኘሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ ሙሉጌታ

እንደተናገረችው ተማሪዎች በጠዋት ተነስተው ከማጥናትና ትምህርት ቤት ለመሄድ ከመዘጋጀት ይልቅ የውኃ ወረፋ ለመጠበቅ ተገደዋል::

በተለይ የጥዋት ፈረቃ በሚሆኑበት ጊዜ የውሃ ወረፋ ሲጠብቁ ስለሚረፍድባቸው ቁርስ ሳይበሉ ትምህርት ቤት ስለሚሄዱ ትምህርታቸውን ለመከታተል

እንደተቸገሩ ገልፃለች::የአጅባር ከተማ ነዋሪዋ ወ/ሮ ሙሉ

ተገኔም የውኃ ችግሩ እሳቸውን ጨምሮ በግቢያቸው ውስጥ ቤት ተከራይተው የሚኖሩ የመንግሥት ሰራተኞችንም ለችግር መዳረጉን ተናግረዋል:: እነዚህ የመንግሥት ሰራተኞች ምግብ እንኳን

አሁን ላይ ጥቅሙ ለራሳችን ሕይወትና አካል ደህንነት ከፍተኛ ስለሆነ ሁሌም

አቶ አዲሱ ወርቅነህ

Page 2: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 2

ርዕሰ አንቀፅ

ይድረስ ለበኩር

በኩርዋና አዘጋጅ፡-

ጥላሁን ቸሬ ስልክ፡- 0918 70 60 08 E mail– [email protected]

ምክትል ዋና አዘጋጆች ፡- ዜናና ትምህርታዊ ዓምዶች፡- ይህዓለም መለሰ

Email- [email protected] መዝናኛ ዓምዶች ፡- አብዮት ዓለም Email- [email protected]

በኩር በአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በየሳምንቱ የሚታተም የሰኞ ጋዜጣ

አዘጋጆች፡-

ጌታቸው ፈንቴ አባትሁን ዘገየ Emial [email protected] ጌትነት ድልነሳ [email protected] ሙሉ አብይ [email protected]

ህትመት ክትትልና ስርጭት፡- ደምሴ ሃሰን

አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ዋጋው አድማሱ አድራሻ ፡- አማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዋናው መ/ቤት - ባህር ዳር

ፖ ሳ.ቁ 955 ሾ.ቁ /+251/ 058 226 50 18 E-mail [email protected] Web www.amma.gov.et

በጽሁፍ መልዕክት(sms) ab. በማስቀደም 8200

የማስታወቂያ አገልግሎት ፡ ስልክ ቁጥር 05 82 26 49 88 05 82 26 57 32 ፋክስ ቁጥር 05 82 20 47 52

[email protected] [email protected]አታሚ፡- ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

አዲስ አበባ

ታህሳስ 7 1987 ተመሰረተ

ከፍተኛ ሪፖርተሮች፡- ታምራት ሲሳይፀጋዬ የሽዋስ [email protected]አዲሱ አያሌውአብርሃም አዳሙአብርሃም በዕውቀትሙሉጌታ ሙጨ [email protected]ደረጀ አምባውሱራፌል ስንታየሁ

ሪፖርተር፡-ጌትሽ ኃይሌ[email protected]

ፎቶ ሪፖርተር፡- ሰለሞን ሀዲስተባባሪ የካርቱን ባለሙያ፡- ብርሃኑ ክንዱ

የኮምፒዩተር ፅህፈት እና ግራፊክ ዲዛይነር፡- የኔሰው ማሩእመቤት አህመድአለምፀሐይ ሙሉደጊቱ አብዬ

ለ ህ ብ ረ ተ ሰ ብ ለ ው ጥ እ ን ተ ጋ ለን !

ይህ ገጽ በበኩር ጋዜጣ ላይ ለህትመት በዋሉ መጣጥፍ፣ ዜናዎችና አጠቃላይ

ስለ ጋዜጣው የአንባብያን አስተያየቶችና ጥያቄዎች የሚስተናገዱበት ነው

ስለዚህ፡- ) በ(sms) ab. በማስቀደም 8200 ) በኢሚል [email protected] ) በስልክ ቁ. 0582 26 50 18

ሀሳባችሁን ግለፁልን መልሰን ወደ እናንተው እናደርሳለን

ኢትዮጵያ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ በነበረችበትና ተስፋ በጠፋበት ወቅት የተመሰረተው ኢህዴን/ብአዴን ይሄው የ36 ዓመት ጐልማሳ ሆኗል:: ትንሿን ጭላንጭል ብርሃን መነሻ አድርጐ “ባለመንበርከክ” እሴቱ እየጐለመሰ የመጣው ኢህዴን/ብአዴን ዛሬ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የአማራ ክልል ኗሪዎች ጥላ ከለላ ሆኗል::

የመልማት ተስፋቸውንም አለምልሟል:: በልማት፣ በዴሞክራሲና በፖለቲካ ነፃነት ጥማት ፈጣሪያቸው ዕድሜያቸውን እንዲያሳጥረው ይለምኑ የነበሩ ዜጐች ዛሬ “እንኖራለን ገናን!” መዘመር ጀምረዋል::

ኢህዴን/ብአዴን ከምስረታው ህብረብሔራዊ በመሆን ሌሎች የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መታገያ እንዲያገኙ ያደረገው አስተዋጽኦም በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ጉልህ ቦታ አለው:: መታገያ ማግኘት ብቻ ሳይሆን ብሔራዊ ድርጅት እንዲመሰርቱ ማድረጉም ታሪክ ሲዘክረው የሚኖር ነው::

በዳር አገር ታጥሮ የነበረው ፀረ ደርግ ትግልም ወደ መሐል አገር እንዲስፋፋና የጨቋኙ ስርዓት እድሜ እዲያጥር የማይተካ ሚና ተጫውቷል:: በዚህም የድል መሰረቱ ትክክለኛ ዓላማ እንጂ ወታደራዊ አቅም አለመሆኑን ለአንባገነኖች አስተምሯል:: የሌሎች አጋር ድርጅቶችን አመለካከትም ቀይሮ ከጐኑ አስልፏል::

ኢህዴን/ብአዴን በመርህ ላይ ቆሞ የመነጋገርንና ልዩነትን አቻችሎ ለአንድ ዓላማ መሥራትን ለድርጅቶች ብሎም ለህዝቡ በማስገንዘብ በኢትዮጵያ አዲስ የመደማመጥና የመከባበር ባህል አንዲጐለብት አርዓያ ሆኗል:: በብሔራዊ ድርጅቶች መካከል ያለው ግንኙነትም ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን በመርህ ላይ ቆሞ ታግሏል፤ በዚያም ውጤት አስመዝግቧል::

ለኢትዮጵያ ህዝቦች የአማራ ገዥ መደብንና የአማራ ጭቁን ህዝብን ነጣጥሎ በማሳየት የትምክህትና የጠባብነትን ሴራ አኮላሽቷል፤ የአማራ ጭቁን ህዝብ ባለፉት ስርዓቶች የደረሰበት የመደብ ጭቆናም ከሌሎች ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር እኩል መሆኑን በማስረጃዎች እየተነተነ አሳይቷል:: በዚህም ሌሎች ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ስለአማራ ጭቁን ህዝብ ያላቸው አመለካከት በአወንታዊ እንዲቀየር አድርጓል::

ኢህዴን/ብአዴን ብዝኃነት ባለበት ሀገር ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን በማስገንዘብ ከህገ መንግስት ማርቀቅ እስከ ማፅደቅ ባለው ጊዜ ጉልህ ሚና ተጫውቷል:: በህገ መንግስቱ የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ የሆነው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብት ምላሽ እንዲያገኝ የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል:: በምላሹም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የስልጣን ባለቤት ሆነዋል:: የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው መወሰን ችለዋል። ራሳቸውን በራሳቸው ያስተዳድራሉ፤ በቋንቋቸው ይጠቀማሉ፤ ባህላቸውን ያሳድጋሉ፤ ማንነታቸውን በአደባባይ ይገልፃሉ፤ ለዚህ ነፃነትም ኢህዴን/ብአዴን ከሌሎች ዴሞክራሲያዊ ድርጅቶች ጋር በመሆን ላብ፣ ደምና ህይወት ከፍሏል::

ኢህዴን/ብአዴንበኢኮኖሚውና በማህበራዊዉ ዘርፍም የተለያ ተግባራት አከነዉኗል:: ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤቶችን፣ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችን ተደራሽ በማድረግ ለዕድገት ወሳኝ የሆነውን የሰው ሀይል ልማት በማከናወን ላይ ይገኛል::

በአጠቃላይ ኢህዴን/ብአዴን ከህዝቡ ጋር በሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት መጪው ጊዜ ብሩህ ቢሆንም ፍፁም ነው ማለት እንዳልሆነ ግን ልብ ሊባል ይገባል::

ዛሬም ኢህዴን/ብአዴን 36ኛ ዓመቱን እያከበረ ባለበት ወቅት በመልካም አስተዳደር እጦት የሚያለቅሱ ዜጐች ብዙ ናቸው:: በየመሥሪያ ቤቱ የሚያዳምጣቸው፣ አዳምጦ መልስ የሚሰጣቸው አካል አጥተው የብአዴንን ፈጣን ምላሽ የሚጠብቁ በርካታ ናቸው:: ዛሬም በዜግነታቸው ሊያገኙት የሚገባቸውን አገልግሎት በገንዘብ መግዛትን (ኪራይ ሰብሳቢነትን) ህጋዊ አሠራር አድርገው የሚጠቀሙ፤ የሚገዙት ጥቂት አይደለም:: ዛሬም የክረምት ዝናብ ሲስተጓጐል ጓዳቸው ባዶ የሚሆን ዜጐች በርካታ ናቸው::

ዛሬም አገርና ወገንን ሊጠቅሙ በሚችሉበት አፍላ ዕድሜያቸው በሥራ አጥነት እየተጦሩ ያሉና ስርዓቱን የሚያማርሩ ከዚያም አልፎ ለሁከተኞች መሳሪያ ሲሆኑ ታይቷል:: ዛሬም በከተሞች በመኖሪያ ቤት እጥረት የሚንገላቱ እማወራዎችና አባዎራዎች የትየለሌ ናቸው:: በአጠቃላይ ዛሬም እየተጣሩ፣ “አቤት!” የሚላቸው ያጡ አሉና ኢህዴን/ብአዴን በ36ኛ ዓመቱ የበለጠ ተነቃቅቶ “አቤት!” ሊላቸው ይገባል!

ስለዚህ ብአዴን ከሚያካሂደዉ የጥልቅ ተሀድሶ ግምገማ በኋላ በመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት በእርሱ ላይ እምነታቸዉ እየተሸረሸረ የመጡትን ዜጎች ˝አቤት !አለሁ!˝ ሊላቸዉ ይገባል! እናም የብአዴን 36ኛ ዓመት የልደት በዓል ዋና መገለጫ የጥልቅ ተሀድሶዉ ዉጤት ሊሆን ይገባል!

ግብፆች በዓባይ ወንዝ ዙሪያ ያላቸውን አቋምና ኢትዮጵያ እንዳትጠቀምበት ስትከተለው የነበረውን ስልት በጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓ.ም የትዝብት አምዳችሁ አስነብባችሁናል፤ በግሌ ከጽሑፉ ብዙ ተምሬበታለሁ፡፡ ግብፃውያ ኢትዮጵያውያን ጥበበኞች እንዲጠሉ የተለያዩ ስያዎችን በመስጠት ጭምር በሀብታችን እንዳንጠቀም ሲያደርጉ ኖረዋልና ጽሑፉ አስተማሪ ነበር፡፡ በቀጣይም ዓባይ የሚወስደው አፈራችን ምን ያህል ሊያለማ እንደሚችልና እንዳልተጠቀምንበት በደንብ ገላጭ የሆነ ጽሑፍ እጠብቃለሁ፡፡

ዮሐንስ ተረፈ ከምሥ/ጎጃም ደጀን

በችግር ውስጥ ለሚገኙት የበለጠ ጆሮ መስጠት ይገባል

በጥቅምት 28/2009 ዕትም “የህዳሴው ግድብ የመወሰንና የመፈፀም አቅምን አጐልብቷል” በሚል ርዕስ በዜናና ዜና ትንታኔ ያቀረባችሁት ጥሩ እና ዝርዝር መረጃ የሚሰጥ ነው:: ግድቡ በአሁኑ ወቅት የደረሰበትንም ስለሚያሳይ በተስፋ እንጠብቀዋለን:: ዘጠነኛው እና 10ኛው ተርባይኖች ኃይል ለማመንጨት እየተዘጋጁ መሆኑም በከተማችን ያለውን የመብራት መቆራረጥ ይቀንሳል የሚል ተስፋ አለኝ::

አቶ ጌታቸው ሽበሽሐይቅ

Page 3: 12 03 2009.pdf

ገጽ 3በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. ኢኮኖሚና ልማት

ወደ ገጽ 28 ዞሯል

አጫጭር ዜናዎች

በምስራቅ ጐጃም ዞን በደብረ ኤልያስ ወረዳ ለአጨዳ የደረሱ ሰብሎች ወቅቱን ባለጠበቀ ዝናብ እንዳይበላሹ አርሶ አደሩ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አሳሳቡ::

ዋና አስተዳዳሪው አቶ ምንያምር አባይነህ ከወረዳው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት በወረዳው በምርት ዘመኑ ለአጨዳ የደረሱ ሰብሎች ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብና በሌሎችም ሁኔታዎች ሳይበላሹ በመሰብሰብ አርሶ አደሮች ለወረዳው የምርት ጥራት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል::

እንደ ዋና አስተዳዳሪው ገለፃ በወረዳው በምርት ዘመኑ ከ42 ሺህ 725 ሄክታር በላይ በተለያዩ ሰብሎች በዘር የተሸፈነ መሆኑን ገልፀዋል:: ከዚህም ውስጥ ከአንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይሰበሰባል ተብሎ ይጠበቃል::

ዋና አስተዳዳሪው በማከልም ለአጨዳ የደረሱ ሰብሎች ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይበላሹም አርሶ አደሩ የቤተሰቡን ጉልበት እና ዘመናዊ የምርት መሰብሰቢያ መሣሪያዎች ስለቀረቡ እነርሱን በመጠቀም ምርቱን በጥራት መሰብሰብ ይኖርበታል ብለዋል::

ሰብሎች በዝናብ እንዳይበላሹ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት

ተገለፀ

በአማራ ክልል በመጥፋት ላይ ላሉ አገር በቀል የዛፍ ዝርያዎች ጥበቃ እና እንክብካቤ እያደረገ መሆኑን የአማራ ክልል ደን ኢንተፕራይዝ አስታወቀ::

በክልሉ እየጠፉ የመጡ ሀገር በቀል የዛፍ ዝርያዎችን ከአደጋ ለመከላከል ገበያ ተኮር የሆኑ የውጭ ዛፍ ዝርያዎችን በማልማት የዘር ፍላጐት አቅርቦትን ለማርካት የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ በ2006 ዓ.ም የደን ዘር ማዕከል ማቋቋሙን ገልጿል::

የአማራ ክልል ደን ኢንተርፕራይዝ የደን ዘር ማዕከል ስራ አስኪያጅ አቶ ቻሌ በየነ እንደገለፁት የደን ዘር ማዕከሉ ስራ ከጀመረ 54 ዓይነት የዛፍ ዘሮችን በሳይንሳዊ መንገድ ዘር በመሰብሰብ እና የብቅለት ደረጃቸውን በላብራቶሪ በመፈተሽ ለደን አልሚዎች እና አርሶ አደሮች እያቀረበ ይገኛል::

ከዚህ ጋር በተያያዘ በክልሉ የሚገኙ ወጣቶች በዘር መሰብሰብ ስራ ተደራጅተው ተጠቃሚ እንደሆኑም አቶ ቻሌ ተናግረዋል:: የአማራ ክልል ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ፈፃሚ አቶ ደግአረገ አሰፋ እንደገለፁት በ2008 በጀት ዓመት የክልሉ ወጣቶች በ63 ማህበራት ተደራጅተው ዘር በመሰብሰብ አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ብር ገቢ አግኝተዋል:: በቀጣይ ወጣቶችን በዘርፉ በማሠማራት የራሳቸውን የገቢ ምንጭ እንዲፈጥሩ ለማስቻል ኢንተርፕራይዙ እየሰራ መሆኑን የኢንተርፕራይዙ ግንኙነት ባለሙያ ገልፀዋል::

የአማራ ክልል ደን ኢንተርፕራይዝ የደን ዘር ማዕከል ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ከ477 ኩንታል በላይ የዛፍ ዘር ሰብስቦ ለዘር ፈላጊዎች ማሠራጨቱንም ኢንተርፕራይዙ ያደረሰን ማረጃ ያስረዳል::

በመጥፋት ላይ ያሉ የዛፍ ዝርያዎች ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑ

ተጠቆመ

አዲሱ አያሌው

ከዝናብ አቁሮ በመሰብሰቡ ለልማቱ ቅድመ ዝግጅቱን ጀምሯል፡፡

በ018 ቀበሌ አምባ መጣያ ጐጥ በኩታ ገጠም ከተዘራው ስንዴ ውሰጥ ግማሽ ጥማድ መሬት የሚሆነው የወ/ሮ እታገኝ አስሬ ነው፡፡ ወ/ሮ እታገኝ በዚሁ መሬታቸው ላይ ካሁን በፊት ምንም አይነት ሰብል ዘርተው አይጠቀሙም ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቦታው “ምርት አይሰጥም” ተብሎ ይታሰብ ነበርና፡፡ ታዲያ ዘንድሮ የእነ አቶ ተስፋዬን አምና እና ታች አምና በአካባቢው በተግባር ስንዴ ዘርተው ማብቀላቸውን በመመልከታቸውና በባለሙያዎች ድጋፍ ተበረታትተው ባለፈው ዓመት በግማሿ ጥማድ መሬታቸው ስንዴ ዘርተው ሶስት ኩንታል አካባቢ የሚሆን ምርት አግኝተዋል፡፡

በዚሁ ተበረታትተው የባለሙያ ምክር እና ግብአትን ተጠቅመው ዘንድሮ የዘሩት ስንዴ ደግሞ ቁመናው የበለጠ ያማረ ሆኖላቸዋል፡፡ ወይዘሮዋ ዘንድሮም እስከ አራት ኩንታል ምርት እንደሚያገኙበት ተስፋ አድርገዋል፡፡

በጥቅምት ወር አጋማሽ አካባቢ ባለፈው ዓመት በድርቅ ተጠቅቶ ወደነበረው የምስራቁ የክልላችን አንድ አካባቢ አቅንተን ነበር፡፡ በዚህ አካባቢ ከነፋሱ እንቅስቃሴ ጋር በተጣጣመ መልኩ ከወዲያ ወዲህ ዘንበል ቀና በሚል እና ለመብላት በሚያስጐመጅ የስንዴ ሰብል የተሸፈነ ሰፋ ያለ ማሳ መዳረሻችን ሆኗል፡፡

ለዓይን የሚማርከውና እንኳን የአርሶ አደሮቹን የኛን ተስፋ የሚሞላው የስንዴ ሰብል መስመርን ተከትሎ የተዘራ መሆኑን በቀላሉ ለማወቅ አይከብድም፡፡ ታዲያ ይህን ተስፋን በሚሞላ የስንዴ ሰብል የተሸፈነ ማሳ የተመለከትነው በደቡብ ወሎ ዞን ዝናብ አጠር የሆኑ ቀበሌዎች በሚገኙባት የሳይንት ወረዳ ነው፡፡

በወረዳው 018 ቀበሌ አምባ መጣያ በሚባለው ጐጥ ሰፋ ባለ መሬት ላይ በኩታ ገጠም ማሳ ተዘርቶ በጥሩ ቁመና ላይ የሚገኘውና ተስፋን የሚሞላው የስንዴ ሰብል የአርሶ አደሮችና የባለሙያዎች ተናቦ የመስራት ውጤት መሆኑን ከአካባቢው ኗሪዎች ለመረዳት ችለናል፡፡

አቶ ተስፋየ በላይነህ በዚሁ አካባቢ በግማሽ ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ ዘርቷል፡፡ እርሱ እንዳረጋገጠው የስንዴው ቁመና ዘንድሮ በጥሩ ሁኔታ ይገኛል፡፡ አምና እና ታች አምና ከነበረው ጋር ሲነፃፀርም በጣም የተሻለና ተስፋ ሰጭ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ ዘንድሮ ከነበረው በቂ የዝናብ ስርጭት በተጨማሪ ከበፊቱ በተለየ የተሰጠውን የክህሎት ስልጠና መሰረት አድርጐ ማሳውን ደጋግሞ በማረሱ፤ በወቅቱ በመዝራቱ እና አረምን ተከታትሎ ማረም በመቻሉ ለሰብሉ በጥሩ ቁመና ላይ መገኘት የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዳበረከቱም አቶ ተስፋየ ነግሮናል፡፡

አቶ ተስፋዬ አክሎም ለአካባቢው ተስማሚ የሆኑ ቀቀባና ዳንቴ የተባሉ ውጤታማ የስንዴ ዝርያዎች እና በቂ ማዳበሪያ በመንግሥት በኩል

መቅረባቸውም ለሰብሉ ቁመና በጥሩ ሁኔታ ላይ መገኘት አጋዦች እንደሆኑ ገልፆልናል፡፡

በፊት “ለምርት አይሆንም” ተብሎ ብዙም ትኩረት ይሰጠው ባልነበረው በዚሁ አካባቢ የባለሙያዎችን ምክር፣ ቴክኖሎጅ እና ግብዓት በመጠቀም ባለፈው የምርት ዘመን ስንዴ ዘርቶ ከግማሽ ሄክታሩ 12 ኩንታል ምርት ማግኘት እንደቻለ አቶ ተስፋዬ አጫውቶናል፡፡ ዘንድሮ ባለሙያ የሚሰጠውን እያንዳንዷን ምክር በመተግበሩ ደግሞ የሰብሉ ቁመና ጥሩና ካለፈው ዓመት የተሻለ ሊሆን እንደቻለም ገልፆልናል፡፡ አቶ ተስፋዬ ዘንድሮ በግማሽ ሄክታር መሬት ያማረ ቁመና ላይ ከሚገኘው የስንዴ ሰብል 15 ኩንታል የሚደርስ ምርት እንደሚያገኝ ገምቷል፡፡

ሰብሉ እንደደረሰ በወቅቱና በአግባቡ ለማንሳት በባለሙያዎች በተሰጠው ምክር መሰረት መዘጋጀቱን የገለፀልን አቶ ተስፋዬ፤ ይህን ሰብል ካነሳ በኋላ በመስኖ ሽንኩርት፣ ጐመን እና የመሳሰሉትን የጓሮ አትክልቶች ለማልማት አቅዷል፡፡ ታዲያ ለዚህ የሚሆነውን ውሀም ጉድጓድ ቆፍሮ በማዘጋጀት

ከክረምት ዝናብ ለመስኖ የተሰበሰበ ውሃ

ካለፈው ዓመት በሶስት ኩንታል ብልጫ ያለው የስንዴ ምርት እንደሚያገኝ ተገምቷል፡፡ - አቶ ተስፋዬ በላይነህ

መኸሩ ተስፋየ

Page 4: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 4 ዜና ትንታኔ

ወደ ገጽ 34 ዞሯል

አብርሃም አዳሙ

ደብረ ብርሃን ተመራጭ የኢንዲስትሪ መዳረሻ እየሆነች ነው

በአማራ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ከተሞች አንዷ የሆነችው ደብረ ብርሃን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ፈጣን የሆነ የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ እየታየባት ነው:: በአጭር ዓመታት ውስጥም ረዥም ልምድ ካላቸው የኢንዱስትሪ ከተሞች እኩል መራመድ ጀምራለች:: ከዚህ ባለፈም በከተማዋ የተመዘገበው ፈጣን የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በክልልና በሐገር አቀፍ ደረጃ ከታወቁ የኢንዱስትሪ ከተሞች ጋር ተፎካካሪ ሆኗል፤ እናም ይህንን ፈጣን ለውጥ ብዙዎች “የኢንድስትሪ ግሽበት” ሲሉ ይጠሩታል:: ለመሆኑ የለውጡ ሚስጢሮች ምንድን ናቸው? ኩባንያዎች ለምን ወደ ደብረ ብርሃን ያመራሉ? ማንስ ተጠቀመ? ፈተናና ተስፋዎችስ ምንድን ናቸው? እነዚህን ጉዳዮች በዜና ትንታኔያችን እንመለከታቸዋለን::

ከ600 ዓመታት የሳር ዘመን ወደ 10 ዓመታት የእንዲስትሪ ዘመንደብረ ብርሃን የመካከለኛው ዘመን የፓለቲካና

የሐይማኖት ማዕከል ከመሆን በስተቀር ከዚህ ታሪክ ያተረፈችው ነገር የለም::እድገቷ የእድሜ ጠገብነቷን ያህል እንዳልሆነ ነዋሪዎቿና ወዳጆቿ ይናገራሉ::

ደብረ ብርሃን እንደ ትላልቆቹ የአክሱም፣ ሮሃና ጐንደር ከተሞች ረጃጅም ህንፃዎች ሣይሆኑ ረዣዥም ሣሮች መገለጫዎቿ ሆነው ቆይተዋል:: በእርሷ የሣር ክምሮችና በሌሎቹ የህንፃ ቁልሎች መካከል ያለው ብቸኛ መስተጋብር ቢኖር ረጅም ዘመንና የስልጣን ወንበር ብቻ ነው::

በ600 ዓመታት ምንም ለውጥ ሳታሳይ የኖረችው ደብረ ብርሃን “መቼም የማትለውጥ” ከተማ ተደርጋ ስትታይ ቆይታለች:: ከአዲስ አበባ በቅርብ መገኘቷ ደግሞ አንደ እድልኛ ሳይሆን እንደ መከረኛ አስቆጥሯታል:: አሁን ግን ይህ ጊዜ ያለፈ ይመስላል:: ሣር አብቃይ የነበሩት የደብረ ብርሃን ሠፋፊ ሜዳዎች ኢንዱስትሪዎችን ወደ ማብቀል ተሸጋግረዋልና::

አቶ ቅጣው ማሞ የዚህች ከተማ ነዋሪ ናቸው:: ከ1970ዎቹ ጀምሮ በዚህች ከተማ ይኖራሉ:: እርሳቸው እንደሚናገሩት ያኔ በከተማም የባንክ አገልግሎት የሚሰጥበት አንድ ፎቅ ብቻ እንደነበር ያስታውሣሉ:: ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ይህ ሁኔታ በፍጥነት እየተለወጠ መምጣቱን ነው የሚናገሩት::

“ብዙ ኩባንያዎች እየተቋቋሙ ነው፤ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ አጠቃላይ የከተማዋ እንቅስቃሴ ተለውጧል:: በከተማዋ ትላልቅ ህንፃዎች ተገንብተዋል:: ኢንቨስትመንቱን ተከትሎም ብዙ ህዝብ ወደ ከተማዋ እየገባ ነው:: የንግዱ እንቅስቃሴም አብሮ እያደገ መጥቷል:: ወደፊት የተያዙ ትላልቅ የኢንቨስትመንት ኘሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ደግሞ ብዙ የሠው ኃይል የሚይዙና የከተማዋን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ይሆናሉ ብየ ተስፋ አደርጋለሁ” ሲሉ ገልፀዋል::

በደብረ ብርሃን ከተማ በ1985 ዓ.ም ገደማ በአገልግሎት ዘርፍ የተሠማራው ኘሮጀክት አንድ ብቻ ነበር:: ሂደቱም ለብዙ ዓመታት አዝጋሚ ሆኖ ቆይቷል:: ነገር ግን የኢንቨስመንት እንቅስቃሴው ከ2000 ዓ.ም ወዲህ መለወጥ ጀምሯል:: በተለይ በ2002 ዓ.ም 45 ኘሮጀክቶች ወደ ኢንቨስትመንት መግባት እንደቻሉ ከከተማ አስተዳዳሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል:: ትልቁ የኢንቨስትመንት ፍሠት የተመዘገበው ግን በ2007 ዓ.ም ነው:: በወቅቱ የአገልግሎት ዘርፉን ሳይጨምር በአምራች ኢንዱስትሪ ብቻ 36 ኩባንያዎች ፈቃድ መውሰድ ችለዋል፤ ሂደቱም ከአገልግሎት ወደ ኢንዱስትሪ ለመሸጋገሩ ምክንያት ሆኗል::

በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ የሥራ ሂደት መሪ የሆኑት አቶ ሽፈራው ማሞ በአሁኑ ወቅት 337 የኢንቪስትመንት ኘሮጀክቶች ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ ገብተዋል:: አጠቃላይ ካፒታላቸውም ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል:: የአመራች (manu-facturing) ዘርፍ ከፍተኛን ድርሻ መውሰዱን የተናገሩት አቶ ሽፈራው በዘርፉ 13 ቢሊዮን ብር ካፒታል ይንቀሣቀሣል:: ለዚህ አገልግሎት ሲባልም 345 ሄ/ር መሬት ለባለሐብቶች መሰጠቱን ገልፀዋል:: ምንም እንኳ ኘሮጀክቶቹ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ

ሲገቡ ከ21 ሺህ በላይ የስራ ዕድል የሚፈጥሩ ቢሆንም አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን ከ15 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጐች የሥራ ዕድል መፍጠር ችለዋል፤ ፍሠቱም ከግዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ገልፀዋል::

“የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው በአስገራሚ ፍጥነት እያደገ መሆኑን እያየን ነው:: ደ/ብርሃን በአሁኑ ወቅት ተመራጭ መዳረሻ እየሆነች ነው:: አሁን ያለውን አጭር ጊዜ እንኳ ብንመለከት ከሐምሌ 2008 ዓ.ም እስከ መስከረም 2009 ዓ.ም ባሉት ሦስት ወራት ብቻ 60 ባለሐብቶች የኢንቨስትመት ኘሮጀክት አስገብተዋል:: ይህ በጣም ትልቁ ለውጥ ነው” ነበር ያሉት::

የደብረ ብርሃን ከተማ ከንቲባ አቶ ታገል አምሣሉ በበኩላቸው የደብረ ብርሃን ከተማ በኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዋ አርአያ እየሆነች መምጧን ተናግረዋል:: በ600 ዓመታት ውስጥ “የነበረውና አሁን ያለው የኢንቪስትመንት ዕድገት የጨለማና የብርሃን ያክል

ልዩነት ያለው ነው” ያሉት ከንቲባው:: ከረጅሙ የእድሜ ዘመን ይልቅ በ10 ዓመታት ውሰጥ ደብረ ብርሃን ስር ነቀል ለውጥ ማምጣቷን አብራርተዋል:: በእርግጥም ደ/ብርሃን እንደገና እየተሠራች ያለች ከተማ መሆኗን አስመስክራለች:: ከዘመናዊ የመስታዎት ህንፃዎች አንስቶ በብዙ ቢሊዮን ብር እስከሚገነቡት ግዙፍ ኢንዱስትሪዎች ድረስ ከተማዋ እንደ አዲስ እየታደሠች ትገኛለች::

ለምን ደብረ ብርሃን?ኢንቨስትመንትን ለመሳብና ለማበረታታት

እንዲሁም ምቹ ሁኔታ ይፈጥራሉ ተብለው በዓለም አቀፍ ደረጃ በጥናት ከተረጋገጡ ጉዳዮች መካከል በግልጽነትና በቅልጥፍና የሚሠራ የአስተዳደር ስርዓት መዘርጋት አንዱ ነው:: ከዚህ ባለፈም ምቹ የኢንቨስትመንት ፓሊሲ፣ ዕምቅ የተፈጥሮ ሐብት፣ የተረጋጋ ሠላም፣ የሠለጠነ የሠው ኃይል፣ ሠፊ የገበያ ፍላጐትና ወጥነት ያለውና የተረጋጋ የማክሮ

በአንድ ዓመት ውስጥ ሥራ የጀመረው አዚላ ኤሌክትሮኒክስ

Page 5: 12 03 2009.pdf

ገጽ 5በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. እንግዳችን

ወደ ገጽ 26 ዞሯል

አብርሃም በዕውቀት

አቶ አዲሱ ወርቅነህበጤና ጥበቃ ቢሮ የሌሽማኒያሲስ እና ሌሎች ቬክተር ወለድ በሽታዎች መከላከል ባለሙያ

ሙቀትም ስለሆነ ወጣቶቹ ስስና ሰውነትን የማይሸፍኑ አጫጭር ልብሶችን

ይጠቀማሉ፤ ይህም ለአሸዋ ዝንቧ ያላቸውን ተጋላጭነት ከፍ ያደርገዋል፡፡

ለማረፍ ሲፈልጉም ከግራሮቹ ሥር ነው የሚቀመጡት፤ ማታ ማታም ውጭ ላይ

የማምሸትና ሌሊቱንም ውጭ ላይ የማሳለፍ ሁኔታዎች፣ በቂ ምግብ ያለማግኘት

ጉዳይም ይኖራል፡፡ እነዚህ ሁሉ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ናቸው፡፡

ሌሽማኒያሲስ

አቶ አዲሱ ወርቅነህ ይባላሉ፤ በአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ የሌሽማኒያሲስ እና ሌሎች ቬክተር ወለድ በሺታዎች መከላከል ባለሙያ ናቸው:: የዛሬ የበኲር እንግዳችን በመሆን ስለሌሽማኒያሲስ በሽታ ምንነት፣ መንስኤና መከላከያ መንገዶቹ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እንዲሰጡን አድርገናል፤ መልካም ንባብ!

ሌሽማኒያሲስ ምንድነ ነው?

ሌሽማኒያሲስ በፕሮቶዝዋ አማካኝነት ከሚመጡ ተላላፊ የበሽታ ዓይነቶች አንዱ ነው:: በዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት ከሚሹ የሞቃታማው የአየር ንብረት ክልል በሽታዎች ከሚባሉት ውስጥ የሚመደብ ነው:: የበሽታው አምጭ ተሕዋስያን “ሌሽማኒያ” በሚል ስያሜ ይታወቃሉ:: በዓለም ላይ ከ20 በላይ የተለያዬ ዝርያ ያላቸው የተለያዬ ዓይነት የሌሽማንያ በሽታ የሕመም ስሜቶችንና ምልክቶችን የሚያስከትሉ ዝርያዎች አሉ::

ሌሽማኒያሲስ የሚተላለፈው እንዴት ነው?

በሽታው ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው የአሸዋ ዝንብ በበሽታው ከተያዘ ሰው ደም በመምጠጥ ወደ ጤነኛው ሰው ወስዳ ስታሸጋግረው ነው:: ልክ እንደ ሴቷ የወባ ትንኝ ሴቷ የአሸዋ ዝንብ ነች የበሽታው አስተላላፊ:: ነገር ግን አስቀድሞ በበሽታው የተለከፈ ሰው ከሌለ የትንኟ ንክሻ ብቻውን በሽታውን አያመጣም::

የአሸዋ ዝንብ ምን ዓይነት ዝንብ ነች? መገኛዋስ?

የአሸዋ ዝንብ በመጠን ከወባ ትንኝ ሲሶ ያክል ናት:: መገኛ ምቹጌዋ (ቦታዋ) የምስጥ ኩይሳ፣ የቀይ ግራር ቅርፊት፣ ዋልካ አፈርና በተለይ ጨለም ያለና ብስባሽ የሚበዛበት ሞቃታማ አካባቢ ነው:: ከአየር ንብረት አኳያ ከአንድ ሺህ 500 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ ከፍታና ከዚያ በታች ያላቸው አካባቢዎች ይመቿታል:: በተለይ ብስባሽ ያለበትና ጨለም ያለ ቦታ በዚሁ የአየር ንብረትና ከፍታ አካባቢ ሲገኝ ይመቻታል::

በኢትዮጵያ በብዛት የሚከሰቱ የሌሽማንያሲስ ዓይነቶች የትኞቹ ናቸው?

በአጠቃላይ በሦስት ከፍለን ልናያቸው እንችላለን፡- አንደኛው የቆዳ ላይ ሌሽማንያሲስ የሚባለው ነው፤ ይህም በአብዛኛው በደጋና ወይና ደጋ አካባቢዎች የሚከሰተው የሌሽማኒያሲስ ዓይነት ነው:: ሁለተኛው የቆዳና የቆዳ ሥር ሌሽማኒያሲስ ይባላል፤ ይህም ልክ እንደ አንደኛው በደጋና ወይና

ደጋ አካባቢዎች ሊከሰት የሚችል ነው:: ሦስተኛው የሌሽማንያሲስ ዓይነት ደግሞ በተለምዶ ካላዛር የሚባለው አደገኛና ገዳይ የበሽታ ዓይነት ነው:: ካላዛር በአብዛኛው ከፍታቸው ከባሕር ወለል በላይ ከአንድ ሺህ 500 ሜትር በታች በሆኑ ሞቃታማ አካባቢዎች የሚከሰት ነው:: በአብዛኛውም የሚያጠቃው እንደ ጣፊያ፣ ጉበት፣ አንጀት፣ … ያሉትን የውስጥ አካላት የሚጎዳ በሽታ ነው፤ ካላዛር::

በክልላችን የተለመደው የትኛው የሌሽማኒያሲስ ዓይነት ነው?

ሦስቱም ዝርያዎች አሉ! በመተማ፣ ቋራ፣ አርማጭሆ፣ በለሳና ሊቦከምከም፣ … አካባቢዎች የሚገኘው ገዳዩ የሌሽማኒያሲስ ዓይነት (ካላዛር) ነው:: በደቡብ ወሎ አምባሰል፣ ተውለደሬ፣ ደሴ ዙሪያ አካባቢ፣ በአዊ ብሔረሰብ አንከሻ፣ በምዕራብ ጎጃም ደጋ ዳሞት፣ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰሀላ ሰየምት፣ ጋዝጊብላና ደሀና አካባቢ፣ በደቡ ጎንደር ፋርጣ፣ ጋይንትና በመሣሰሉት ደግሞ የቆዳ ላይና የቆዳ ውስጥ ሌሽማኒያሲስ ዝርያዎች ይገኛሉ::

ሦስቱ የሌሽማኒያሲስ ዝርያዎች ተመሳሳይ የበሽታ ምልክት ነው ያላቸው?

በሺታዎቹ የሚያሳዩት ምልክት የተለያዬ ነው:: ለምሳሌ ካላዛር የሰውነት መድከም፣ ከሁለት ሳምንት በላይ የሚቆይ ሙቀት፣ የክብደት መቀነስ፣ … ምልከቶቹ ናቸው፤ በአብዛኛው ከወባ በሽታ

ምልክቶች ጋር ተቀራራቢ ባሕርይ አለው:: የቆዳ ላይ ሌሽማኒያሲስ ደግሞ በአንዳንድ አካባቢዎች ቆንጭር በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ ጎርምጥ በሚል መጠሪያ ይታወቃል:: የቆዳና የቆዳ ውስጥ ሌሽማኒያሲስ ደግሞ በአፍና አፍንጫ አካባቢ ቁስለት የሚያመጣ በሽታ ነው:: አፍና አፍንጫን እስከ መቆራረጥ ይደርሳል::

በበሽታው የተጠቃ ሰው በምን ያህል ጊዜ ምልክቶችን ያሳያል?

እንደ ዝርያዎቹና እንደ ግለሰቡ በሽታን የመከላከል አቅም የሚወሰን ነው:: ለምሳሌ የውስጥ ደዌ ሌሽማኒያሲስ ከሆነ ከሁለት እስከ ስድስት ወር ባሉት ጊዜያት ሊታወቅ ይችላል:: የቆዳ ላይ ሌሽማኒያሲሱም ከሳምንታት እስከ ወራት በፈጀ ጊዜ ምልክቶቹ ሊታዩ ይችላሉ::

ሕክምና በበቂ ሁኔታ ይሰጣል?

እስከ ቅርብ ጊዜ ሕክምናው የሚሰጠው በተመረጡ የጤና ተቋማት ማለትም በመተማ ሆስፒታል፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል፣ አብደራፊ ጤና ጣቢያ፣ አዲስ ዘመን ጤና ጣቢያና ባሕር ዳር ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ነበር:: ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ የቆዳ ላይ ሌሽማኒያሲስ እየተስፋፋ በመሆኑ ክልሉ ደብረ ታቦር፣ ፍኖተሰላም፣ ቦሩሜዳና ተፈራ ኃይሉ ሆስፒታሎች ላይ ሕክምናው እንዲሰጥ ግብዓቶቹን እያሟላ ነው::

የጤና ባለሙያዎች በሽታውን የመለዬት አቅማቸው ምን ያህል አድጓል?

የባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ ሰፊ ሥራ ተሠርቷል፤ አሁንም እንደቀጠለ ነው:: ሕክምና በሚሰጥባቸው አካባቢዎች ያሉ አብዛኞቹ የጤና ባለሙያዎች ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል:: አዲስ ወደ ሌሽማኒያሲስ ሕክምና ለሚገቡ የጤና ተቋማት ባለሙያዎችም በተለይ ለላቦራቶሪ እና ክሊኒካል ነርስ ባለሙያዎች ስልጠናውን እየሰጠን ነው:: በእርግጥ አንዳንድ በሽታው ያልተለመደባቸው አካባቢዎች ሰዎች ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ ታመው ወደ ጤና ተቋም ሲሄዱ በቀላሉ ባለሙያዎቹ ያለመለዬት ችግሮች አሉ፤ እሱንም ቢሆን ለመቅረፍ እየተሠራ ነው::

ትኩረት የሚሻው

Page 6: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 6 መዝናኛ

ቅምሻ

ታምራት ሲሳይ

• የልብ ድካምን ይከላከላል• የደም ግፊትን ይቀንሳል• የስኳር በሽታን ይታደጋል• የፀጉር መነቃቀልን ለመግታት ይረዳል• ትኩሳትን ይቀንሳል• በጉንፋን መጠቃትን ያስወግዳል• የሽንት ቱቦ መለብለብን ያስቀራል• ድርቀትን ያስወግዳል• በሰውነት ውስጥ የተስተካከለ የደም

ዝውውር እንዲኖር ይረዳል• ጉንፋን እንዳያገረሽና እንዲሻል ያደርጋል::

ምንጭ- Juicing- for-health.com

ቀይ ሽንኩርትን መመገብ

በተባበሩት አረብ ኢምሬት ውስጥ የሚገኝ ጐልማሳ ወጣት ሚስቱን ባገባት

በማግስቱ መኳኳያ ሳትጠቀም ለመጀመሪያ ጊዜ ስለተመለከታት ሊፈታት ችሏል::

ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገፅ እንዳስነበበው የ28 ዓመቷ ወጣት ባጋጠማት ድንገተኛ እና ያልታሠበ ፍች ምክንያት ለደረሠባት ከፍተኛ የሥነ ልቦና ጫና እርዳታ እንዲደረግላት በጠየቀችው የስነ ልቦና ሀኪም ዶክተር አብዱል አዚዝ ኦሳፍ አማካኝነት ይህ ግራ የሚያጋባ ሪፖርት ተደርጓል:: ዶክተሩ የልጅቷን ምስጢር ለመጠበቅ ማንነቷን ያልገለፀ ቢሆንም ገልፍ ለተሠኘው የዜና አገልግሎት በሠጠው መረጃ መሠረት ወጣቷ ከ34 ዓመቱ ጐልማሳ ጋር ለስድስት ወር ያህል በመተጫጨት ቆይታ አድርገዋል:: በዚያ ስድስት ወር የቆይታ ጊዜያቸው ግን ጐልማሳው ወጣቷን አንድም ቀን መኳኳያ ሳትጠቀም ተመልክቷት አያውቅም ነበር::

በቻይና ውስጥ ጉያኒግ ተብላ በምትጠራ ግዛት ውስጥ የሚገኝ ከገደል ሥር ተቦርቡሮ

የተሠራ የምግብ ቤት ባለቤት የተጠቃሚዎችን ቀልብ ለመሣብ ብሎ ባቀረበው አጓጊ የሆነ ደግነት ምክንያት የ15 ሺህ ዶላር ኪሳራ ደርሶበታል::

ሊው ዥያንጂ እና ሁለት የንግድ አጋሮቹ የጨዋታ አቀናባሪዎች ሲሆኑ አዲሱን ምግብ ቤታቸውን አዲስ ባወጡት “የቻልከውን ክፈል”

በዝሆን ጥርስ ማጌጥ እጅግ ውድና ብርቅ በሆነበት በዚህ በያዝነው ዘመን የደች

ተወላጇ ሞዴል ከራሷ በወለቀ ጥርስ የጆሮ ጊጦችዋን ሠርታለች::

ሉሲ ማጃሪስ በራሷ ጥርስ ጌጥ የመሥራት ሀሣቡ የመጣላት ጥርሷ በወለቀበት ጊዜ ነበር:: የወለቁ ጥርሶቿን አስቀምጣቸው ዘግየት ብሎ ሀሣቡ መጣላት

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሰልጣኞቻቸው በርካታ አማራጮችን ያቀርባሉ፡፡ ወደ ተቋማት የገቡ ተማሪዎች እንደየፍላጐታቸው እና ምኞታቸው እንዲሁም ዝንባሌያቸው ለቀጣይ ህይወታቸው ይሆነኛል ያሉትን መስክ መርጠው ይማራሉ።

መከታተል የሚፈልጉትን መስክ ሲመርጡም በጓደኞቻቸው ግፊት፣ ወይም በትምህርቱ ቅለት መሆን እንደሌለበት ሙህራን ይመክራሉ፡፡

ስለዚህ ሰልጣኞች የወደፊት የትምህርት መስኮችን ሲመርጡ ሥራ ማስገኘት መቻሉ፣ ጥሩ ደመወዝ የሚያገኝበት እና በሙያው ሊረኩበት የሚችሉበት መሆን ይኖርበታል ባይ ናቸው፡፡

በመቀጠልም ፕሪንስተን ሪቪው የተባለ ድረገፅ በጥናቶች ላይ ተመሥርቶ የሚከተሉትን የትምህርት መስኮች በቀዳሚነት አስቀምጧል፡-

5ኛ. ኢኮኖሚክስይህ በግለሰብ፣ በመንግሥት፣ በንግድ ውስጥ

ያለን ሀብት ጊዜንና ገንዘብን እንዴት አጣጥሞ በአግባቡ ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም እንደሚገባ የሚያስተምር መስክ ነው፡፡

ጠንቃቃ ስብዕና እንዲኖር የሚያደርግ፣ ለምርት ለማከፋፈል፣ የሸቀጣሸቀጥና የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ አተኩሮ ዕውቀት ያስጨብጣል፡፡ ለሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ በህግ፣ በህዝብ አስተዳደር ዓለማቀፍ ጥናቶች ላይ ማድረግ ያስችላል፡፡

4ኛ. ቢዝነስከፍተኛ ተግባቢነትን የሚሻ፣ የገንዘብ

አጠቃቀም፣ የገበያ ሁኔታ፣ የሰው ሀይል አስተዳደር፣ የንግድ ዕውቀትን የሚያስጨብጥ መስክ ነው ፡፡

ያለን ሀብት እንዴት? የት? መቼ? ለምን? ወዘተ መጠቀም እንዳለብን ያስተምረናል፡፡ ከአንስተኛ የሥራ ፈጠራ እስከ ውስብስብ ግዙፍ የንግድ እንቅስቃሴዎች ተፎካካሪ ሆኖ በአሸናፊነት ቀድሞ ለመገኘት ክሂሎትን ያስጭብጣል፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ ቀዳሚ

የትምህርት መስኮች3ኛ. የፖለቲካ ሳይንስ

ይህ የመንግሥት አስተዳደርን፣ ፖሊሲን፣ በአገር ውስጥ እና የውጭ ፖሊሲ፣ የውጭ ጉዳይና ግንኙነቶችን፣ የፖለቲካ ርዕዮተዓለምን፣ አማራጭ መንግሥታዊ አስተዳደርን የሚያጠና መስክ ነው፡፡

አርቆ አሳቢና የትናንት ታሪክን እና ባህልን ጠንቅቆ ማወቅና ልዩ የተግባቢነት ወይም የግንኙነት ዕውቀት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችል ነው፡፡

መፃፍ፣ ማንበብ፣ ህግ፣ ፖለቲካና ተግባቦትን እንዲካኑ ያደርጋል፡፡

2ኛ. ኮሙኒኬሽንሀሣብን በወጉ አደራጅቶ የመግለጽ፣ እያዋዙ

የመግባባት ስብዕናን ያላብሳል፡፡ በንግግር በፅሁፍ በመልዕክት አዘገጃጀትና በንግግር የመደመጥ፣ የፈለጉትን በመግለፅ በአድማጭ ልቦና የማስረፅ ሀይልን ያጐናፅፋል፡፡

በቃልም በምልክትም በመግባባት በታዳሚ ላይ ስሜት በማጫር የራሱ የሆነ ድባብ ለመፍጠር የሚያስችል ነው፡፡

በንግድ፣ በማስታወቂያ፣ በሰው ሀይል ልማት፣ በህዝብ ግንኙነት፣ በትምህርት፣ በብዙሀን መገናኛና ማህበራዊ አገልግሎት ለመሠማራት ያስችላል፡፡

1ኛ. ኮምፒውተር ሳይንስስለ ኮምፒዩተር ሃርድ ዌር እና ሶፍት ዌር ብቻ

ማወቅ ሳይሆን እንዴት? መቼ? ለምን? መጠቀምና መገልገል እንደሚገባና እንደሚቻል የጠለቀ ዕውቀት ይገበይበታል፡፡

በዚህ መስክ ከሰለጠኑ ስለሮቦቲክስ፣ ስለኮምፒውተር ፕሮግራም፣ ስለቁጥር ትንተና፣ በየትኛው ኢንዱስትሪ ምን? መቼ? እንዴት? መጠቀም እንደሚቻል ውጤታማነቱን ጨምሮ ጠንቅቀው ዕውቀት ይገበዩበታል፡፡

መኳኳያ ለትዳር መፍረስ

በዚህም ምክንያት ውበቷ ሥላሳመነው ከእርሷ ጋር የመጋባት ህልሙን አመነበት:: ከስድስት ወር በኋላ የጋብቻ ሥነ ሥርዓታቸው ተከበረ::

“ጉድና ጅራት ከወደኋላ ነው” እንደሚባለው ሁሉ የጋብቻ ሥርዓታቸው በተከበረ በማግስቱ

“ያሻህን ክፈል” የሚለው አንድ የቻይና ምግብ ቤት ለ15

ሺህ ዶላር ኪሣራ ተጋለጠ

በራሷ ጥርስ የከበረ ጌጥ የሠራችው ፋና ወጊ

“የራሳችን በሆኑ ነገሮች ማጌጥ ለራሳችን ነገሮች ዋጋ የማንሰጠውም ለምንድን ነው?” ስትል ራሷን በራሷም ጠየቀች::

እናም በራሷ ጥርሶች ያልተለመዱ ውድ ጌጦችን በመሥራቷ ፋና ወጊ አድርጓታል - በማለት ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገፅ ዘግቧል::

በዋና ለመዝናናት ወደ ውሀ ዳር አመራች:: በመዋኘት ላይ እያለች ውሀው የተጠቀመችውን መኳኳያ ሙሉ በሙሉ እጥብጥብ አደረገባት:: በዚያን ሰዓት ሙሽራው ወደርሷ አምርቶ ውሀ ውስጥ የተደበቀ ፊትዋን ለመጀመሪያ ጊዜ መኳኳያ ሳትጠቀም ይመለከተዋል:: በዚህ ድርጊቷ የተናደደው ሙሽራ ለድርጊቷ ከዚህ በላይ እንደማይታገሳት ነገራት:: ወጣቱ ያገባትን የውሸት ዓይን ቅንድብን ጨምሮ በርካታ መኳኳያ ተጠቅማ ስላታለለችው እና ከሠርጋቸው በፊት የተመለከታትን ያህል ስለማታምር ከሷታል::

በሚል ስልት ማስተዋወቁ ጥሩ ሀሣብ ነው በማለት ወሰኑ::

ኦዲቲ ሴንትራል እንደዘገበው በሶስቱ የንግድ ጓደኛሞች አስተሣሠብ በሀገሪቱ ውስጥ የምግብ ቤት ባለቤቶች የፈለጉትን ዋጋ ከሚጠይቁበት የክፍያ ሥርዓት ወጥተው ያላቸውን ከፍለው እንዲሄዱ ለበርካታ ተጠቃሚዎች አሣማኝ እና ምክንያታዊ ነው ይላሉ::

ሙሽሪቱም ከጋብቻ ሥርዓታቸው በፊት በተደጋጋሚ መዋቢያ እንደምትጠቀምና በቋሚነት ሰው ሠራሽ የዓይን ቅንድብ ትጠቀም እንደነበር ለባሏ የመንገር ሀሣብ የነበራት ቢሆንም በመዘግየቷ የወንዙ ወስጥ ክስተት የሷን ማንነት አጋለጠባት::

(በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋዜጠኝነትና ተግባቦት ትምህርት ክፍል የ3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ደጀኔ

በቀለ በበኩር ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በተግባር ልምምድ ላይ እያለ ያዘጋጀው)

ምክንያት ሲሆን

ወደ ገጽ 40 ዞሯል

Page 7: 12 03 2009.pdf

ገጽ 7በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. ትዝብት

ወደ ገጽ 42 ዞሯል

የሺሀሳብ አበራ

በሥነ-ልሳን ስያሜና ተሰያሜ ምንም ዓይነት የባህሪ ግንኙነት የላቸውም:: ቋንቋ በባህሪው ደመነፍሳዊ (ዘፈቀዳዊ)

ነውና:: ለምሳሌ ጣፋጭ የምትባል አንዲት ኮረዳ ጣፋጭ የሚለው ስያሜዋ ለልጅቱ ውስጠ ማንነት የሚገልፀው ነገር የለም::

በታሪክ፣ በባህል እና በሥነ ልቦና ግን ይህ ሀቅ ይሻራል:: በስያሜና በተሰያሜ መካከል የጠበቀ ግንኙነት አለ:: ለአብነት የሺሀሣብ አበራ የሚለው ስም በራሱ በብሔር አማራ፣ በሐይማኖት ክርስቲያን መሆኔን ሊያመለክት ይችላል፤ ስም በራሱ ባህልና ታሪክ ነጋሪ ነውና::

በዚህ ሀሣብ ተንደርድረን ሌሎቸ ሀገረኛ ጉዳዮችን እንቃኝ::

ራስ ዳሸን ወይስ ራስ ደጀን?የአፍሪካ አራተኛ ትልቁ ተራራ ራስዳሽን ወይም

ራስ ደጀን በሚል በተቀያያሪ ስያሜ ይጠራል:: ራስ ዳሸን ምን ማለት ነው? ራስ ደጀንስ?!

ወደ ሰሜን ጐንደር ዝለቁ:: በተለይም በየዳ፣ ጠለምት፣ ጃናሞራ እና ደባርቅ አካባቢዎች:: በእነዚህ አካባቢዎች የመሬት መብት፣ የመሬት አናት ነው

ውድ አንባቢያን በባሕር ዳር በትዝብት ዓይኔ መሀከል የጣና ሐይቅን

ተመርኩዤ ስሜቴን ላካፍላችሁ ወደድኩ::የጣና ሐይቅ በትልቅነቱ ከሀገራችን ቀዳሚ

ነው:: መቼም ወደ ባሕር ዳር የመጣ ሰው ብዙ ስለሚባልለት የዓባይ ፏፏቴ /ጢስ አባይ/ እና ጣና ሐይቅን ሳይመለከት የተመለሰ እንደሆን ከጊዮን ታላቅ የጥበብ ማዕድ እንዳልተቋደሰ እቆጥረዋለሁ::

ስደተኛ

“የላጭን ልጅ . . .”

ለማለት ራስ ደጀን ሲሉ ይተረጉሙታል:: ይሁን እንጅ የውጭ ሀገር ሰዎች በተኮላተፈ ልሳን ራስ ደጀንን ራስ ዳሸን ብሎ መጥራቱ እየተለመደ መጥቷል:: ራስ ዳሸን ትርጉም የለውም:: እንዲያውም ፈረንጀኛ ራስ ደጀንን “Head guard” ብለው ሲተረጉሙትም ይስተዋላል:: ስያሜ ታሪክ ነጋሪ፣ ባህል ተሸካሚ… ከሆነ ራስ ዳሸን ከማለት ይልቅ ራስ ደጀን በሚል ስያሜ መጥራቱ በራሱ ተራራው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኝ ያመለክታል::

ከሁለት ዓመት በፊት የሱዳን የታሪክ ሙህራን በመፅሀፍ ቅዱስ ሱዳን እንጅ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አትታወቅም ማለታቸው ይታወሳል:: ምክንያታቸው ደግሞ መፅሀፍ ቅዱስ ወደ ግዕዝ ከመተርጐሙ በፊት ኢትዮጵያ የሚል ስያሜ አልነበረም:: ኩሽ ኑብያ ይል ነበር:: ኑብያ ደግሞ ሱዳን ናት:: ስለዚህ ይህችን ቃል በመያዝ ብቻ የኢትዮጵያን የመፅህፍ ቅዱስ ታሪክ ሙሉ በሙሉ ወደ ሱዳን አስገቡት::

ሱዳን እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች:: ነበር ዥጉርጉርነቱን ሱዳናዊ መልኩን አይቀይርም ሲሉም ተደመጡ:: የዚህ ሁሉ ድምዳሜ መነሻቸው ግን በእብራይስጥ ቋንቋ የተፃፈው “ኩሽ ኑብያ” የምትለዋ ስያሜ ብቻ ነበረች::

በእርግጥ መፅሀፍ ቅዱስ ከእብራይስጥ በፊት መፃፊያ ቋንቋው ግዕዝ እንደነበርም መገንዘብ የፈለጉ አይመስሉም።

ስያሜ ታሪክን ስለሚናገር ኑብያ ደግሞ የሱዳን ክፍል ስለሆነች አንድ ቃል ይዘው ተከራከሩ:: ዳሩ በወቅቱ የኢትዮጵያ ግዛት የሚባለው የየመን፣ ኤርትራን፣ ጅቡቲን፣ ሱዳንን ያካልል ስለነበር በታሪክ ሳይረቱ ቀርተዋል::

ሆኖም ግን ያንዲት ቃል ስያሜ ያመጣችውን የታሪክና የባህል ሽሚያ መመልከተ ይቻላል:: ስያሜዎች ታሪክና ባህል አዝለው የሚጓዙ የታሪክ መንገደኞች ናቸውና::

ዓባይ 85 በመቶ በላይ ውህው ከኢትዮጵያ ይመነጫል:: 15 ከመቶውን ብቻ ሌሎች ሀገራት ይጋራሉ:: ይሄን ያህል መጠን የምታመነጨው ኢትዮጵያ ግን ዓባይ የሚለው ስያሜ ዓለም አቀፋዊ ሊሆንላት አልቻለም:: አባይ ሱዳን ሲደርስ ናይል ተብሎ ይጠራል:: ናይል አረብኛ ነው:: ለዚህም ናይል የሚለውን ስያሜ በመያዝ ብቻ እስከ 18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ዓባይ ሱዳን አሊያም ግብፅ አካባቢ እንደሚመነጭ ይታመን ነበር:: ዓባይ ዓለምአቀፋዊ ስያሜ ቢሆን ግን “ዓባይ” የሚለውን ቃል በማየት ብቻ ኢትዮጵያ ላይ እንደሚመነጭ መናገር ይቻላል:: ስያሜ ታሪክ፣ ማንነት እና የትመጤነት ገላጭ ነውና::

ጤፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ስለሚገኝ “ጤፍን” እንግሊዝኛ አያውቀውም:: “Teff” ይለዋል:: እንግሊዝኛ በአማርኛ መጠቀሙ የትመጤነቱን ያሳያል:: እንጀራ “Enjera” ነው:: ምክንያቱም የኢትዮጵያ ብቸኛ ምግብ ነውና::

ውድ አንባቢያን ከጣና የጥበብ ዓምድ መካከል ዓሳም አይረሳም። አዎ የትዝብቴ ማጠንጠኛ የባህርዳር ዓሳ ነው::

የነጭ አሳ መረቅ እጅ ያስቆረጥማልየቀረሶ ጥብሱ አምጡ ውሀ ይላልቢበሉት ቢጎርሱት መቼ ይጠገባልየሚታፈስበት አሳ በብዛትውል አለኝ ባሕር ዳር ጥጋብ ያለበት::

እኒህን በመሳሰሉ ስንኞች ምክንያት የጣና ሐይቅን ዓሳ ለመብላት ማን የማይጓጓ አለ! አሁን አሁን ግን ሐይቁም የሰው ያለህ! ሰውም የዓሳ ያለህ! የሚሉ ያህል ይሰማኛል:: ታዲያ ያልታየ ግን የሚነበብ፤ የማይሰማ ግን የተፃፈ የደወል ጥሪ በሁሉም ጆሮ ያቃጭላል::

እንዲያ የተነገራላቸው ዓሳዎች የት ገቡ? ማለቱም

አይቀርም። በሐይቁ ዳርቻ የዓሳ መሸጫዎች ጥቂት ናቸው:: ያሉትም ዋጋቸው የትየሌለ ሆኗል:: ህገወጥ አስጋሪዎቹ አሳዎቹ ገና ሳይጠኑ በእንጭጭነታቸው ያጠምዷቸዋል:: ያለ ዕድሜያቸው ይጠብሷቸዋል::

በጣና ሐይቅ ዳርቻ ባለው የእግረኛ መንገድ ሲጓዙ ዓሳ የሚሸጡ ሰዎች ማህበራት መመልከት እያማረን ይቀራል:: ውሀን መሠረት አድርገው ከተመሰረቱ ከተሞች ባልተለመደ መልኩ በጣና ሐይቅ ዙሪያ ዓሳ የሚሸጥ ማግኘት አይቻልም:: በተለይም ሀዋሳ እና ባሕር ዳር ከተሞችን ለማየት ዕድሉን ያገኘ ሰው በሐይቁ ዳርቻ ያለው ትልቅ ልዩነት አይጠፋውም::

መቼም በጣናም ሆነ በሀዋሳ ሐይቆች ዓሳ የመኖሩ ጉዳይ የታወቀ ነው:: መሠረታዊ ልዩነት ያለው ሐይቁን በአግባቡ የመጠቀምና ያለመጠቀም ነው:: የዓሳ ምርት አቅርቦት ሰንሰለትን የማስፋትና ያለማስፋት ጉዳይ ማለት ነው::

በሀዋሳ ሐይቁን መሠረት አድርገው የተመሰረቱ ብዙ ሆቴሎችንና የዓሳ መሸጫ ቤቶችን መመልከት የተለመደ ነው:: የሀዋሳ ሐይቅን ለመጎብኘት የሚመጣም ሆነ ነዋሪው በሐይቁ ዳርቻ ባለው የእግረኛ መንገድ በየደረሰበት ከዓሳ ጥብሱ እስከ ዓሳ ሾርባ እንደልብ ማግኘት ይችላል::

እንዲያውም በሐይቁ ዳርቻ የሚኮለኮሉ ጎብኝዎች አይስክሬምና ፒዛ ከመግመጥ ይልቅ ለዓሳ ልዩ ቦታ ይሰጣሉ::

በጣና ሐይቅ ዳርቻ ባለው የእግረኛ መንገድ የዓሳ መሸጫ ቤቶችን ማግኘት አይቻልም:: አንድ የዓሳ ጥብስ ለመብላት የፈለገ ሰው ጣይቱ መዝናኛ ገብቶ በሰው ብዛት ምክንያት የሚቀመጥበት ቦታ አጥቶ ይወጣል:: አማራጭ የዓሳ ቤቶችን ማግኘትም አይሳካለትም::

ስያሜዎች

ወደ ገጽ 40 ዞሯል

Page 8: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 8 ዜና ትንታኔ

ወደ ገጽ 32 ዞሯል

አብርሃም በዕውቀት

በፋግታ ለኮማ ወረዳ የአዲስ ቅዳም ከተማ የመንገድ አጠቃቀም፤ ቅዳሜ መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም የተወሰደ ምስል

የእግረኞች ጥንቃቄ ‘የትራፊክ አደጋን ቀንሷል’

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የተለያዩ ወረዳዎች በእግረኛ መንገድ አጠቃቀም ላይ ትኩረት ተሰጥቶ በመሠራቱ የትራፊክ አደጋ እንዲቀንስ ማድረጉ ተገለፀ:: ነዋሪዎቹም በትራፊክ ፖሊስ አባላት በየጊዜው ተከታታይ ትምህርት በማግኜታቸው የባሕሪ ለውጥ በማምጣት የግራ መስመራቸውን ብቻ ይዘው እንደሚንቀሳቀሱና በዚህም ከአደጋ እንደተጠበቁ ተናግረዋል::

አዲሱ ዓለማየሁ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ባንጃ ወረዳ የቸውሳ ቀበሌ ነዋሪ ወጣት ነው:: አዲሱ እንደተናገረው ቀደም ባሉት ዓመታት ለእግረኛ መንገድ አጠቃቀሙ ትኩረት አይሰጥም ነበር:: ይሁን እንጅ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በተከታታይ በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ እየተገኙ በሰጡት ትምህርት የእርሱና የአካባቢው ማህበረሰብ የመንገድ አጠቃቀማቸው በእጅጉ መሻሻሉን ተናግሯል:: “በትምህርት ቤቶች፣ በቤተ ክርስቲያናት፣ በበዓላት ወቅት፣ በለቅሶ ቦታ፣ በልማት ሥራዎች ላይ፣ … እየተገኙ ስለመንገድ አጠቃቀም፣ ማድረግ ስለሚገባን ጥንቃቄ፣ የእግረኛ ማቋረጫን ስለመጠቀም፣ … በተከታታይ አስተምረውናል፤ በዚህም ተለውጠናል” ብሏል አዲሱ::

“ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ያገኙትን፣ ወላጆች ከቤተ ክርስቲያንና ከሌሎች አካባቢዎች ስለመንገድ አጠቃቀም የተማሩትን ትምህርት በየቤቱ ያስተምራሉ፤ ራሳቸውም ትምህርቱን ይተገብሩታል:: ለምሳሌ እኔ ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት የግራ መስመሬን ለቅቄ ተጉዤ አላውቅም የእግረኛ መንገድ አጠቃቀማችን በመሻሻሉም መኪና እርስ በእርሱ ተጋጭቶ ወይም ተገልብጦ ሰው ይሞታል እንጅ እግረኛ ተገጭቶ ሲሞት አላየሁም፤ ይህም ትምህርቱ ያመጣው ለውጥ ነው ብዬ አምናለሁ” ብሏል አዲሱ::

ከባሕር ዳር- በቡሬ- አዲስ አበባ ከሚወስደው አስፋልት መንገድ ዳር ተቀምጦ ጭራ ሠርቶ በመሸጥ የሚታዳደረው አዲሱ ከመንገዱ በግራ በኩል ዛፍ ሥር ተቀምጦ እየሠራና እየሸጠ ነበር አግኝተን ያነጋገርነው:: ስለተቀመጠበት ቦታ ሲናገርም “ገዥዎች ከመኪና ወርደው ሊገዙኝ የሚችሉት በእርግጥ በቀኝ በኩል ብሆን ነው፤ ነገር ግን እግረኞችም እኔን ለማግኜት ሲሉ በቀኝ በኩል መምጣት ስለሌለባቸው በግራ በኩል ሆኜ ነው የምሠራው” ብሎናል::

መለሠ መኩሪያ ደግሞ ከምዕራብ ጎጃም መስተዳድር ዞን ወንበርማ ወረዳ ለዘመድ ጥየቃ በመጣበት ባንጃ ወረዳ አግኝተነዋል:: መለሠ እንዳለው ደግሞ በወንበርማ ወረዳ ሲኖር የእግረኛ መንገድን ሲጠቀም ምንም ዓይነት ጥንቃቄ አያደርግም ነበር፤ ይሁን እንጅ ወደ አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ሲመጣ የሕብረተሰቡ የመንገድ አጠቃቀም ሕግን የተከተለ በመሆኑ ከሕብረተሰቡ ላለመነጠል ሲል እርሱም የግራ ጠርዙን ይዞ እንደሚጓዝ ነግሮናል:: “በመኪና መንገድ ዳር ሲጓዙ ግራ መስመርን መያዝ እንደሚገባ በእኛም አካባቢ ይታወቃል፤ ግን ማንም ትኩረት ሰጥቶ አይተገብረውም” ያለው መለሠ ለወደፊት እርሱ በሚኖርበት አካባቢም ባንጃ አካባቢ ያየውን ተሞክሮ ለማስቀጠል እንደሚሠራ ተናግሯል::

ወ/ሮ አቡኔ አዱኛ ደግሞ የፋግታ ለኮማ ወረዳ ነዋሪ ናቸው:: እርሳቸውን ደግሞ ከአዲስ ቅዳም ከተማ መግቢያ አካባቢ የመንገዳቸውን የግራ ጠርዝ ይዘው ሲጓዙ አገኘናቸውና ስለልምዳቸው ጠየቅናቸው:: “ስለመንገድ አጠቃቀም በትራፊኮች ትምህርት ሲሰጠን የኖረው ለረዥም ዓመታት ነው፤ አሁን ላይ ጥቅሙ ለራሳችን ሕይወትና አካል ደህንነት ከፍተኛ ስለሆነ ሁሌም እየተጠነቀቅን:: አስፋልቱን ስናቋርጥም ነጭ ቀለም በተሰመረልን በኩል

ነው፤ ተዚያ ውጭ መንገድ አናቋርጥም፤ መንገዱ አስፋልት ካልሆነ ግን ምልክት ስለማይኖረው መኪና አለመኖሩን አረጋግጠን እንሻገራለን” ብለዋል::

ወ/ሮ አቡኔ እንዳሉት በመንገድ አጠቃቀም በኩል በአካባቢያቸው ከከተማ ይልቅ የገጠር ሰዎች የተሻሉ ስልጡኖችና የትራፊክ ፖሊሶችም ሆኑ

ሌሎች ሰዎች የሚያስተምሯቸውን የሚተገብሩ ናቸው:: “እኛ የገጠሮቹ ፊደል ሳንቆጥር የፖሊሶቹ ትምህርት ሲዘልቀን ከተሜው ግን ግራና ቀኙን መለዬት አቅቶት በየጊዜው በመኪና እየተገጨ ነው፤ መሰልጠን ሕግን ማወቅ ሳይሆን ሕግን ማክበር ነው” ሲሉም ለከተማ እግረኞች መልዕክት አስተላልፈዋል::

አቶ ያዬህ በላይነህ የተባሉ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪ በበኩላቸው “አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ትምህርቱ እንዴት እንደተሰጠ ባላውቅም በመንገድ አጠቃቀም በኩል እጅግ ስልጡን ሕዝብ ያለበት ነው፤ የትራንስፖርት ስምሪት ወደ አዊ ሲደርሰኝ በጣም እደሰታለሁ፤ ምክንያቱም እግረኞቹ የግራ ጠርዛቸውን በመያዝ በስርዓት የሚንቀሳቀሱና መንገድም በእግረኛ ማቋረጫ ብቻ የሚያቋርጡ ናቸውና” ሲሉም ተናግረዋል::

በተለይ ደቡብ ጎንደር እና ወሎ አካባቢ ሲመደቡ በእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ክፉኛ እንደሚቸገሩ የተናገሩት አሽከርካሪው አቶ ያዬህ በሌሎች አካባቢዎች ያለው የመንገድ አጠቃቀም ችግር ካለማወቅ ሳይሆን የሚያውቁትን ሕግ ለመከተል በቂ የአዕምሮ ዝግጅት ካማድረግና ከቸልተኝነት የሚመጣ እንደሆነም ተናግረዋል:: እርሳቸው እንዳሉት መንገድ ያለአግባብ የሚጠቀሙት በሙሉ ቢጠየቁ ትክክለኛው አካሄድ የመንገዱን ግራ ጠርዝ ይዞ መጓዝ እንደሆነ ማስረዳት ይችላሉ፤ ነገር ግን አዕምሯቸውን በዚያው ልክ ባለማሰልጠናቸው በቸልተኝት ሕጉን ሳያከብሩት ለአደጋ እየተጋለጡ ይኖራሉ:: ይህንንም ችግር ለማስቀረት በየአካባቢው እንደ አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የትራፊክ ሕግን አክብሮ የሚንቀሳቀስ ንቁ ሕብረተሰብ እስኪፈጠር አስገዳጅ ሕግ ማውጣትና በቅጣት ጭምር ማስተማር እንደሚገባም አቶ ያዬህ ተናግረዋል::

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማረጋገጫ ዋና የሥራ ሂደት መሪ ም/ኮማንደር አዳሙ ይሁንም የብሔረሰብ አስተዳደሩ የእግረኞች መንገድ አጠቃቀም እጅግ የተሻለ መሆኑን መስክረዋል:: ነገር ግን ይህ ለውጥ የመጣው በአንድ ዓመት ጥረት ሳይሆን ከመዓታት እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ መሆኑንም አስረድተዋል::

ስለመንገድ አጠቃቀም፣ ማድረግ ስለሚገባን ጥንቃቄ፣ የእግረኛ ማቋረጫን ስለመጠቀም፣ … በተከታታይ አስተምረውናል፤ በዚህም ተለውጠናል” - አዲሱ ዓለማየሁ

“እኛ የገጠሮቹ ፊደል ሳንቆጥር የፖሊሶቹ ትምህርት ሲዘልቀን ከተሜው ግን ግራና ቀኙን መለዬት አቅቶት በየጊዜው በመኪና እየተገጨ ነው፤ መሰልጠን ሕግን ማወቅ ሳይሆን ሕግን ማክበር ነው”ወ/ሮ አቡኔ አዱኛ

Page 9: 12 03 2009.pdf

ገጽ 9በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. ማህበራዊ

ተማሪዎች እንደልብ የማይቦርቁበት የትምህርት ቤቱ ግቢ በከፊል

አጫጭር ዜናዎች

ወደ ገጽ 20 ዞሯል

አዲሱ አያሌው

ረጃውን የጠበቀ ደ ትየባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን

ኢንተርኔት ክፍያ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠራ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባህር ዳር ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢሳያስ ስይፉ አስታወቁ::

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባህር ዳር ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢሳያስ ስይፉ እንደገለፁት የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በኢንተርኔት የገንዘብ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠራ ነው። በአገልግሎቱም ተማሪዎች በኢንተርኔት የገንዘብ ክፍያን፣ ባንኪንግ አገልግሎት እንዲሁም የኢቴኤምና ቪዛ ካርድ ተጠቃሚ እንዲሆኑና ተደራሽነቱንም ለማስፋት እንደሚያስችል አስታውቀዋል::

አቶ ኢሳያስ እንደገለፁት 98% የሚሆኑት ተማሪዎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞ በመሆናቸው ይህንን መልካም ጅምር ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማደረግ ተማሪዎችን ባማከለ መልኩ፣ መጉላላትን በመቀነስ የተፋጠነ የባንክ አገልግሎት መረብ ለመዘርጋት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝም አስረድተዋል::

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ኡስማን መሀመድ “የሞባይል ባንኪንግ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ፈጣን፣ ቀልጣፋ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ባንክ ቤት ድረስ ሳልሔድ በቀላሉ ካለኝ ሒሳብ ላይ ተቀናሽ አድርጌ ወደ ሌላ ሰው የሂሳብ ቁጥር መላክ፣ ያደረኩትን ወጪ እና ገቢ ሒሳቤን ማየት እና የወለድ መጠኔን መመልከት የሚያስችል ቀልጣፋ አገልግሎት ከባንኩ በማግኘቴ ያለ አግባብ የሚባክነውን ጉልበትና ጊዜዬን ቀንሶልኛል” ብሏል::

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በፔዳ ካንፓስ ተማሪ ዬናስ ፍቃዱ በበኩሉ በዩኒኒቨርሲቲው የተተከሉ የኤቲኤም ማሽኖች አልፎ አልፎ እየተፈጠረ ያለው የኔትወርክ መስተጓጐል ሊታሰብበት እንደሚገባ ጠቁሟል::

አቶ ኢሳያስ ለችግሩ መፍትሔ ነው ያሉትን የኔትወርክ መቆራረጥ በዘላቂነት ለመቅረፍ ከ ኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ኮርፓሬሽን ጋር በጋራ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል:: ባለሙያዎችን በፍጥነት የኢቲኤም ማሽን አገልግሎት ችግር የተፈጠረበት ቦታ ድረስ በመላክ እየተፈታ መሆኑን ተናግረዋል:: በተጨማሪም በዘንዘልማ ካምፓስም በቅርቡ የኤቲኤም ማሽን ለመትከል ዝግጅቱ መጠናቀቁን ገለፀዋል::

አቶ ኢሳያስ በተጨማሪ ተማሪዎችን የባንክ ሒሣብ ደብተር ያለ ክፍያ የሚከፍቱበት ሂደት መኖሩንም ገልፀዋል::

(በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋዜጠኝነትና ተግባቦት ትምህርት ክፍል የ3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ደርሶ አማረ በበኩር ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በተግባር ልምምድ ላይ እያለ ያዘጋጀው)

የዩኒቨርሲቲ

ተማሪዎችን

የኢንተርኔት ክፍያ

ተጠቃሚ ለማድረግ

እየተሠራ ነው

በክልላችን ደረጃቸውን የጠበቁና አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት ለመማር ማስተማሩ ሂደት ምቹ የሆኑ ትምህርት ቤቶች አሉ ብሎ መናገር እንደማይቻል ባለፈው መስከረም ወር ላይ ክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም መናገራቸው ይታወሳል:: ይህ በመሆኑም በክልሉ የትምህርት ጥራትን በተፈለገው ደረጃ ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ከመሆኑም በላይ ለተማሪዎች ውጤት ማሸቆልቆልም ድርሻው ከፍ ያለ ነው:: ይህ የመማሪያ ቁሳቁስ አቅርቦት እጥረት፣ የመምህራን ብቃትና ፍላጐት ውስንነት እና ሌሎችም ችግሮች ሲደመሩበት የጥራትን እና የውጤትን ጉዳይ የበለጠ ቁልቁል እንዲሽቀነጠር ማድረጉ በተግባር ታይቷል::

እኛም ባለፈው ጥቅምት ወር ወደ ደቡብ ወሎ ዞን ሳይንት ወረዳ በእንደዚህ አይነት ችግሮች ውሰጥ ካሉ ትምህርት ቤቶች ወደ አንዱ አቅንተን ነበር:: በትምህርት ቤቱ ውሰጥ ተገኝተን አጠቃላይ ያለውን ችግር፣ ችግሩ እያስከተለው ያለውን ተፅዕኖ እና ችግሩን ለመቅረፍ በቅድመ ዝግጅቱ ወቅት የተሰሩ እና ወደፊት የሚሰሩ ስራዎችን እንደሚከተለው ቃኝተናል::

በሳይንት ወረዳ አጅባር ከተማ ከሚገኙት ትምህርት ቤቶች መካከል የአጅባር አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን የቅኝታችን ትኩረት አድርገናል:: ትምህርት ቤቱ በእንጨት አጥር በተከለለ ጠበብ ያለ ግቢ ውስጥ ይገኛል:: በግቢው ውስጥ ከአምስት ህንፃ የማይበልጡ በጭቃና እንጨት የተገነቡ፣ ወለላቸው ደግሞ አፈር እና ሲሚንቶ የሆኑ ያረጁ የመማሪያና የሌሎች አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን ይዟል:: በግቢው ውስጥ ለዓይን የሚማርክ ነገር የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም::

የአጅባር አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ1945 ዓ.ም ሲቋቋም፣ ሰፋ ያለ ግቢ እና በግንብ የተሰሩ የመማሪያ ክፍሎች ነበሩት:: ይሁን

እንጅ ፤ ግቢ ለቴክኒክና ሙያ ትምህርት መስጫ ሲውል በ1996 ዓ.ም ትምህርት ቤቱ ወደ አሁኑ እና ምቹ ወዳልሆነው ቦታ ሊዛወር ችሏል::

በመሆኑም አሁን ተማሪዎች የሚማሩበት ግቢና የመማሪያ ክፍሎች ምቹ አለመሆን፣ የመማሪያ ቁሳቁስ እጥረትና ሌሎችም ችግሮች በመማር ማስተማሩ ሥራ፣ በጥራትና ውጤት ላይ ችግር እየፈጠሩ እንደሚገኙ ያነጋገርናቸው ተማሪዎች ገልፀውልናል::

አይናለም ወንድሙ በአጅባር አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ናት:: አይናለም የስምንተኛ ክፍል የሚኒስትሪ ተፈታኝ በመሆኗ ውጤቷን ለማሳመር ዝግጅት የጀመረችው በክረምቱ ወራት የተሰጠውን የማጠናከሪያ ትምህርት በመከታተል ነው:: በ2ዐዐ9 የትምህርት ዘመንም የስምንተኛ ክፍል ትምህርቷን በጥሩ መንፈስ ጀምራለች:: ምክንያቱ ደግሞ ባለፉት

ዓመታት በትምህርት ቤቱ ይስተዋሉ የነበሩና በውጤታቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ከነበራቸው ችግሮች የተወሰኑት ይፈታሉ የሚል ተስፋን በመያዟ እንደሆነ ትናገራለች:: ይሁን እንጅ፤ ትምህርት ከጀመረች በኋላ ችግሮቹ ፈቀቅ አለማለታቸውን ስታይ ግን ለሚኒስትሪ የምታደርገው ዝግጅት ከባድ እንቅፋት እንደገጠመው ሰግታለች::

አይናለም እንደነገረችን ከሚያስፈልጋቸው ዘጠኝ የመማሪያ መፅሀፍት ውስጥ የደረሳቸው ስድስት ያህሉ ናቸው:: በየግላቸው የደረሷቸው ደግሞ ሶስቱ ብቻ ሲሆኑ ሌሎች ሶስቱ ግን ለአራትና ለአምስት የተሰጧቸው ናቸው:: ስለሆነም መጽህፍት በየግላቸው ይዘው የቤት ሥራ ለመሥራትም ሆነ ለማጥናት አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል:: ቤተ ሙከራው አለመሟላቱም የሳይንስ ትምህርቶችን በተግባር እንዳይማሩ እንቅፋት መሆኑን ተናግራለች:: ያረጁት የጭቃ መማሪያ ክፍሎች በግንብ ባይተኩ እንኳን መፍትሄ ይፈለግላቸዋል ተብለው የነበሩት አቧራማ ወለሎች እንዳሉ በመቀጠላቸው ለጤናቸው ጠንቅ እንደሆኑም አይናለም ገልፃለች::

እነዚህ ሁሉ ችግሮች ተጋርጠውባቸው በክልሉ ከሚገኙ ሌሎች የሚኒስትሪ ተፈታኝ ተማሪዎች ጋር ተወዳድሮ ውጤታማ መሆን እንደሚያስችግር አይናለም ተናግራለች:: የሚመለከታቸው አካላት የተወሰኑትን ችግሮች እንኳን በአፋጣኝ እንዲፈቱላቸው ጠይቃለች::

የስምንተኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሰብለ ደባልቄ እንደነገረችን ደግሞ በትምህርት ቤቱ ውስጥ የመማሪያ ክፍሎች ዕጥረት በመኖራቸው በተቃራኒ ፈረቃቸው የማካካሻ ትምህርት (ቱቶሪያል) የሚወስዱት ሜዳ ላይ ነው:: በትምህርት ቤቱ ውስጥ ቤተ መፅሀፉት ቢኖርም አጋዥ መፅሀፍትን ተውሰው ወደ ቤታቸው በመውሰድ የሚያነቡበትና በግላቸው ዝግጅት የሚያደርጉበት ዕድልም አልተፈጠረላቸውም:: ግቢው ጠባብ በመሆኑ ምንም አይነት የስፖርት ማዘወተሪያ ሜዳ የለውም:: ስለሆነም በስፖርት ክፍለ ጊዜ የተለያዩ ስፖርታዊ

“ግቢው ጠባብ በመሆኑ የሥፖርት ሜዳ የለውም” ሰብለ ደባልቄ

ትምህርት ቤት ለትምህር ጥራ

Page 10: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 10

ሳምንቱ በታሪክታሪክ

(ታምራት ሲሳይ)

የጀርመን ጦር በሶቬየቶች መከበብ

የደቡብ ጣሊያን በርዕደ መሬት

መመታቱበደቡብ ጣሊያን በአብዛኛው የዕለተ

እሁድ ሐይማኖታዊ ስርዓት በመከታተል ላይ የነበሩ ኗሪዎች በተከሰተው ርዕደ መሬት ህይወታቸው ያለፈው ህዳር 14 1973 ዓ/ም ነበር:: በርዕደ መሬቱም ከ3 ሺህ በላይ ኗሪዎችን ለሞት ዳርጓል።

7.2 ሬክተር ስኬል የተላካው ርዕደ መሬት የሳት ቃጠሎ ያስነሳ ሲሆን የኃይል ማስተላለፊያዎችንም እንዲቋረጡ አድርጓል::

ርዕደ መሬቱ ጐዳናዎችን፣ የባቡር መስመሮችን አፈራርሷል:: አደጋው አካባቢውን በጭጋጋማ ጭስ በመሸፈን 300 መቶ ሺህ የሚሆኑ ኗሪዎችንም ቤት አልባ አድርጓቸዋል::

የጆን ኤፍ ኬነዲ መገደል

35ኛው የአሜሪካ ኘሬዘዳንት ጆን ፊዝጌራልድ ኬነዲ ላዩ ክፍት በሆነ መኪና ህዝብ በብዛት በተሰበሰበት መካከል በመጓዝ ላይ እያሉ በአቅራቢያቸው ከነበረ ህንፃ በተተኮሰ ጥይት ተመተው ከ30 ደቂቃ በኋላ ህይወታቸው ያለፈው ህዳር 14/1956 ዓ/ም ነበር፡፡

የኘሬዝዳንቱ አስክሬን ያረፉበት ህዳር 16/1956ም የሃዘን ዕለት እንዲሆን ተወስኗል::

ስርዓተ ቀብራቸው በመቶ ሺህዎች የሚቆጠር ህዝብ እና የ99 አገራት መሪዎችም በተገኙበት ተፈፅሟል::

የሶቬየት የቀዩ ጦር ባደረሰው የመልሶ ማጥቃት 250 ሺህ የሚሆን የጀርመን ጦር በዶን ወንዝ አካባቢ ስታሊንግራድ ውስጥ በጥቃት ቀለበት ውስጥ የወደቀው ህዳር 13/ 1935 ዓ/ም ነበር::

የጀርመኖች የኋላ ደጀን በመመናመኑ፣ በሶቪየት የክረምቱ ቅዝቃዜ እንዲሁም የአገሬው ሽምቅ ውጊያ በማየሉ 65 ሺህ የሚሆኑ ጀርመናውያን በሶቬየቶች ቁጥጥር ሥር ሊውሉ ችለዋል:: የጀርመኑ መሪ ሂትለር እስከ መጨረሻው እንዲዋጉ ትዕዛዝ ቢሰጥም በፅናትና በቁርጠኝነት የተዋጉት ሶቬየቶች ጀርመኖች እጅ እንዲሰጡ አስገድደዋቸዋል::

የድምፅ መቅጃና ማጫዋቻ መፈጠሩ

አሜሪካዊው ኤዲሰን ድምፅ የሚቀዳና የሚያጫውት መሳሪያ የፈጠረው ህዳር 12/1870 ዓ/ም ነው:: ኤዲሰን የስልክ ድምፅ መቅጃ ለመሥራት በቤተሙከራው እየጣረ ሳለ ነበር የድምፅ መቅጃ እና መልሶ ማዳመጫን ለመሥራት የቻለው::

ኤዲሰንም ግኝቱን ለተመልካች ይፋ አድርጐ ታዋቂነትን አትርፎበታል:: በመቀጠልም ከዓመት በኋላ በ1871 ዓ/ም ብርሃን አስተላላፊ አምፖል ወደ መስራት ተሸጋግሯል::

ኤዲሰን 1ሺህ93 የባለቤትነት መብት ያገኘባቸውን ፈጠራዎች አበርክቶ በ1924 በ84 ዓመቱ ህይወቱ አልፏል::

ጌትሽ ኃይሌ

“መኪና እንኳን ቢቀር ግመል ላስጭን እስቲ፣ጓዜን ሰባስቤ እንድገባ ባቲ” በዕድሜ ጠገቧ የሐገራችን የሙዚቃ ቅኝት

የተሰየመችው ባቲ ከተማ በፍቅር የተለከፉ ሰዎች ለስሜታቸው ማስታገሻ የቋጠሩት ስንኝ ነው:: ስንኙም እንደከተማዋ ዕድሜ ጠገብ ይመስላል:: ምክንያቱ ደግሞ እንደ አሁኑ ዘመናዊነት ሳይስፋፋ ከተማዋ ከግመል ጋር የተዋሃደች ነበረችና::

በምሽቱ ነፋሻማ አየር ታጅቦ ከኢንዱስትሪ መንደሯ ኮምበልቻ ከተማ የጀመረው ጉዟችን ከ75 ደቂቃዎች በኋላ ባቲ ላይ ማረፊያውን አገኘ:: ምንም እንኳ ጉዟችን ምሽትን ተገን ያደረገ ቢሆንም ከመነሻችን እስከ መድረሻችን ያስተዋልናቸው ሁሉ ባተሌዎች ናቸው::

ከኮምቦልቻ - ሚሌ የሚዘረጋውን አስፋልት መንገድ በምሽቱም ያቀላጥፋታል:: በመዳረሻው ያሉ ሱቆችም ሆኑ ሌሎች አገልግሎት ሰጪዎችን እንዳስተዋልናቸው ጐረቤቶቿ ሁሉ ባቲ ከተማም ባተሌ ሆና ተቀበለችን:: በርካታ ከባድ ተሽከርካሪዎችም በዚህችው ከተማ ከትመዋል:: በተለይ የልጃገረዶችና ጎረምሳዎች ባህላዊ አለባበስ “ባቲ ከተማ የባህል መገላጫ” የሚሉ ቃላትን በአዕምሯችን እንድንስለው ያደርጋል:: ቀኑንም በጉጉት እንድንጠብቀው እንዲሁ::

አቶ መሐመድ የሱፍ ባቲ ከተማ ተወልደው ያደጉና አሁንም እዚያው የከተሙ ናቸው:: ባቲ ከተማ ከአመሰራረቷ አሁን እስካለችበት ያለውን ታሪክ ባቲ በወለደቻቸው የስንኝ ቋጠሮዎች እያዋዙ አጫወቱን::

በሐገራችን ካሉ ጥንታዊ ከተሞች አንዷ የሆነችው ባቲ የተመሰረተችው በ1872 ዓ.ም እንደሆነ ይነገራል:: እንደ አቶ መሐመድ ገለፃ የከተማዋ ስያሜ በዋናነት ሁለት አፈ- ታሪኮችን መሰረት ያደረገ ነው:: ከምስረታ ጊዜዋ በፊት ምንም ሰው የማይኖርባት ጫካ የበዛባት ነበረች:: በወቅቱም ሁለት ጓደኛሞች የእርሻ መሳሪያ ለመቁረጥ ከዚሁ ጫካ ገብተው ተጠፋፉ:: ሲገናኙም ባቲ ባቲ ብለው ተጠራርተው እንደተገናኙና ይህም የስያሜዋ መነሻ ሆኖ እንደቀረ ነው የመጀመሪያው አፈታሪክ የሚያስረዳው::

ባቲ የኦሮምኛ ቃል ሲሆን ወጣች፣ ፈነጠቀች እንደማለት ነው:: ሁለተኛው የስያሜዋ መነሻ ደግሞ በተቆረቆረች በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈጣን ለውጥ በማሳየቷ ያገኘችው ስያሜ እንደሆነ ነው ታሪክ ነጋሪው ያጫወቱን:: ድዴ ባቲ ሲሉም አወደሷት፣ (እምቢ ብላ ወጣች፣ ፈንጠቀች እንደማለት ነው::)

ባቲ ይሄን ስያሜዋን ከማግኘቷ በፊት ዲንሰሩ የሚል መጠሪያ እንደነበራት አቶ መሐመድ ያስታውሳሉ:: የቃሉ መነሻም አፋርኛ ሲሆን የመኝታ

ከተማ

ጥንታዊቷ የወደብ

ልብስ እንደማለት ነው:: ምክንያቱ ደግሞ ባቲ ከምስረታዋ ጀምሮ የአፋሮች ዋነኛ ተመራጭ ከተማ ነበረችና ነው::

ከ137 ዓመታት በላይ ዕድሜን ያስቆጠረችው ባቲ የብዙ ነጋዴዎች መገናኛ ድልድይ ናት:: አርጐባዎች፣ አማራዎች፣ አፋሮች፣ ኦሮሞዎችና ትግሬዎች ይኖሩባታል::

ከተማዋ ከምስረታዋ ጀምሮ የሐገራችን ዋና የንግድ ማዕከል ነበረች:: የንግድ ማዕከልነቱም የመንና አሰብ ድረስ የሚዘልቅ ነበር:: በመሆኑም ጅቡቲዎችና የመኖች ባቲ ከተማን የንግድ መናኸሪያቸው አድርገዋት ነበር:: ሁሉም የንግድ ልውውጥም በግመል የመጓጓዣ አገልግሎት ሰጭነት የተመሰረተ እንደነበር ከታሪክ ነጋሪያችን አቶ መሐመድ ተረድተናል::

አልባሳት፣ ጌጣጌጦች፣ ቆዳና ሌጦ፣ ሸቀጣሸቀጥና እንስሳት ደግሞ ዋና ዋናዎቹ የንግድ ቁሳቁሶች ናቸው::

ባቲ ከተማ ስትነሳ የዜማ ውዳሴዋ አብሮ እንደሚነሳው ሁሉ ሰኞ ገበያም ከከተማዋ ጋር የማይነጣጠል ነው:: ዘወትር ሰኞ የሚካሄደው ግዙፉ የባቲ ገበያ ከመርካቶ ቀጥሎ የሚጠቅስ የግብይት ማዕከል ነው::

ቀደም ባሉት ጊዜያት ገበያው ይካሄድ የነበረው ከከተማዋ ማዶ እንደነበር አቶ መሐመድ ያብራራሉ:: ይሁን እንጅ በወቅቱ የኮንትሮባንድ ንግድም አብሮ ተስፋፍቶ ነበርና የፀጥታ ችግርና ዘረፋ አድማሳቸውን አስፍተው ነበር:: ችግሩን ለመቅረፍ ያስችል ዘንድ የገበያው ቦታ ወደ ከተማዋ መዛወሩን በምክንያትነት ያነሳሉ::

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ሌላኛው የባቲ መገለጫ ደግሞ በግዙፉ የገበያ ቦታ መሃል ላይ የሚገኘው የወንጀለኞች መቅጫ የብረት ምሰሶ ነው:: በአፄ ኃይለስላሴ ዘመን በ1942 ዓ.ም የከተማዋ ገዥ በነበሩት በብላታ ካሳ ማሩ እንደተተከለ ታሪክ ያስረዳል:: ለዚሁ የብረት ምሰሶ መተከል ታሪካዊ ዳራ ደግሞ በሁለት አፋሮች ባሏ የተገደለባት ወይዘሮ "የሞት ፍርድ ይፈረድልኝ" አቤቱታ በንገሱ ዘንድ

አሁን ላይ ዋና የጎብኝዎች መዳራሻ የሆነው የወንጀለኞች መቅጫ ብረት የተተከለበት ዋና ዓላማ ወንጀል እንዳይፈፀም ለማስፈራራት ነበር ይላሉ:: በወቅቱም የከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ከመሆኑ ጐን ለጐን ወንጀልና ዘረፋም በሰፊው ይስተዋሉ ነበር:: ከገበያው መሐል ላይ መተከሉም በርካታ ሰዎች የሚገበያዩበት በመሆኑ ራሳቸውን ከወንጀል እንዲያርቁ በጐ ተፅዕኖ ለማሳደር ነው::

በባቲ ከተማ አስተዳደር የቱሪዝም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የባህል ልማት ባለሙያና ተወካይ የስራ ሂደት ወይዘሮ ሲሳይ ኃይሉ ከወንጀለኞች መቅጫው ብረት ጋር በተያያዘም የአቶ መሐመድን ሐሳብ ይጋራሉ:: የብረት ምሰሶው በተተከለበት ወቅት በስቅላት የሞት ቅጣት ተፈፀመባቸው የተባሉት ሁለት ሰዎች ቅጣታቸው የተፈፀመው ግትር ተራ በተባለበት ቦታ መሆኑን በማንሳት:: አንዱ የቱሪስት መዳረሻ የሆነው ይሄው የብረት ምሰሶ የተተከለበት ዋና አላማውም ወንጀል እንዳይፈፀም ለማስፈራራት ታስቦ መሆኑን አብራርተዋል::

እቅዱም ፍሬ አፍርቶ ከዚያ በኋላ ወንጀልና ዘረፋ በእጅጉ ሊንቀስ ችሏል::

ባቲ ከተማ የሐገራችን ኪነ ጥበብ ማጣፈጫ ቅመም ናት:: ኪነ ጥበቡም የባቲን ልጆች ውበት፣ ድንቅ ባህልና ቀደምትነት አስተጋብቶላታል::

አቶ መሐመድ ግን የባቲ የሙዚቃ ቅኝት የቀደመ ስልጣኔዋን የሚናገር መሆኑን ይናገራሉ:: ምክንያቱ ደግሞ ዕድገቷና ዕድሜዋ የማይመጣጠኑ በመሆኑ ነው::

በቀደመ የንግድ ማዕከልነቷ የምትታወቀው ባቲ ከተማ ከየመንና ጅቡቲ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንደነበራት ይነገራል:: አማርኛ፣ ትግርኛ፣ አፋርኛ፣ ኦሮምኛና አርጐብኛ ቋንቋዎችን መግባቢያ ያደረጉ ብሔረሰቦችም ይኖሩባታል::

ሰው ሁሉ በሽታው ራስ ወገቡን ነው፣የእኔስ በሽታዬ ባቲን ነው ባቲን ነው:: ተብሎ

የተገጠመላትስ የዚህ ምስጢር መገላጫ አይደለምን!! ይህንንም ከአቶ መሐመድ ባሻገር የእኛ የባቲ የቀናት ቆይታችን ምስክር ነው::

ይህች እድሜ ጠገብ ከተማ የቱሪስቶች መናኸሪያም ነች:: በተለይ ደግሞ እሁድ እና ሰኞ ከአራቱም አቅጣጫ የሚመጡ እንግዳዎች ይከትሙባታል:: ምክንያቱ ደግሞ በእለተ ሰኞ የሚከናወነውን ግዙፉን የባቲ ገበያ ለመታደም ነው::

በመጨረሻም አቶ መሐመድ መጤ ባህል የምንኮራበትን ባህላችንንና ማንነታችንን እያሳጣን በመሆኑ ሁላችንም የባህላችን ዘቦች አንሁን በማለት ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት::

ወይዘሮ ሲሳይ ኃይሉ ባቲ ከተማ ከዕድሜ ጠገብነቷ ባሻገር የብዙ ውብ ባህሎች መገኛ ናት ይላሉ:: ባህሉን ሳይበረዝ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍም ሰፊ የግንዛቤ ፈጠራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል::

የከተማዋን እምቅ ባህላዊ ትውፊቶች ይበልጥ ለማስተዋወቅ ደረጃውን የጠበቀ ሙዚዬም ለማቋቋም በዕቅድ መያዙን ከወይዘሮ ሲሳይ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል::

እሽታን በማግኘቱ እንደሆነ ይነገራል::ታጥቀህ ታገል እንዳትንገላታ፤አስተውለህ ተሟገት እንዳትረታ::

ነውና ነገሩ የአቤቱታ አቅራቢዋ ተሟገች ፍርድ ተግባራዊ ተደረገላት::

ይሁን እንጅ አንድም ሰው የስቅላት ሞት እንዳልተፈፀመበት ነው ከአፈ-ታሪክ ያገኙትን መረጃ ዋቢ በማድረግ አቶ መሐመድ ያጫወቱን:: ሁለቱ የሞት ፍርደኞችም ግትር ተራ በሚባለው ከፍታ ቦታ ላይ መገደላቸውን ይተርካሉ:: ነገር ግን ይህንን በተመለከተ አሁንም ድረስ የፅሑፍ መስረጃ ማግኘት አልተቻለም::

በአፃ ኃይለ ስላሴ ዘመን የተተከለው የወንጀለኞች መቅጫ የብረት ምሰሶ

የባቲ ከተማ ጥንትዊ ገጽታ

የባቲ ከተማ የአሁኑ ገጽታ

Page 11: 12 03 2009.pdf

ገጽ 11በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. ጥበብ

ወደ ገጽ 30 ዞሯል

ከመፃሕፍት ገፆች

ገፅሁለተኛውአብዮት ዓለም

የስምንተኛ ክፍል የባዮሎጂ አስተማሪያችን እትዬ መክሊት በጣም አይናፋር ሴት ነበረች::

‘ምዕራፍ ዘጠኝ የስነተዋልዶ አካላት የሚል ርእስ ላይ ስንድርስ ፊቷ ቀልቶ እያፈረች ስታስተምረን ትዝ ይለኛል::

“የስነ ተዋልዶ አካላት እንግዲህ… ያው… ወንድ እና ሴት… ያው…” ጭንቅ ይላታል እትዬ መክሊት፣ እኛ ደግሞ ጆሮ ብቻ እንሆናለን:: ስልሳ የምንሆን የአንድ ክፍል አጉል ዕድሜ ላይ ለምንገኝ ተማሪዎች ይሄ ጉዳይ የነፍስ ጉዳይ ነበር… የምንጓጓለት፣ ለመስማት የምንሰስትለት፣ የስነተዋልዶ አካል ነገር ልባችንን ሰቅሎት ትንፋሻችንን ውጠን እንቁለጨለጫለን:: በክፍለ ጊዜው መርፌ ቢወድቅ ይሰማል ፀጥታው::

“ውይ… ምነው ሁልጌዜ እንዲህ በትኩረት በተከታተላችሁ…! አያችሁ መማር ለራስ ነው፣ ትምህርት አገርን ይቀይራል:: ያደጉት አገሮች ዝም ብለው አላደጉም::… ትምህርት…” ኤጭጭ እኛ ስለስነተዋልዶ አካላት ለመስማት ጓጉተን እትዬ ምክር… መክራ፣ መክራ ምክሯ ሲያልቅባት…

“ወንድ ልጅ ሲጎረምስ ፂም ማውጣት የተለያየ የሰውነት ክፍሉ ላይ ፀጉር ማብቀል እና ድምፁ መጎርነን ይጀምራል… ገባችሁ?”

ስምረት እጇን ታወጣለች፣ “ፀጉር የሚወጣባቸው የተለያዩ አካላት የትኞቹ ናቸው ቲቸር?

“ውይ አንች ደግሞ ፈተና ላይ የማይመጣ ነገር ምን አጠያየቀሽ?” ትልና ታፍራለች እትዬ፤ ሁላችንም እንስቃለን::

መስፍን እጁን ያወጣል በተራው፣ የመስፍን እጅ ማውጣት ይገርመናል፤ በገመድ አስረውም ቢጎትቱት እጁ የማይዘረጋ ልጅ ዛሬ እጁን ሲያወጣ ይገርመናል:: በግርምት እንመለከተዋለን::

“ሴት ስትጎረምስ ምን ምልክት ይታይባታል?” ብሎ ይጠይቃል፤ ክፍሉ በሳቅና በጩኸት ይደበላለቃል:: እትዬ ታፍራለች::

“ዝም በሉ ልክ ነው ጥያቄው፣ የምን መገልፈጥ ነው:: እስቲ ከእናንተ ይህን ጥያቄ የሚመልሰ” ትልና እኛኑ ታጋፍጠናለች:: ቶማስ እጁን ያወጣል “ሴት ስትጎረምስ ያው…አለ አይደል…” ብሎ ደረቱ ላይ እጆቹን ያሳርፍና እንደ ጡት ያጎብጣቸዋል:: የክፍሉ ተማሪ በሳቅ ያውካካል::

እትዬ በሃፍረት መግቢያው ይጠፋበታል፤ ድንገት አንደኞችንን ትጣራለች::

ዶክተር አሸብር እና ሌሎችምአሌክስ አብርሐም

ማዘንጊያ ማዝገሚያአጊጦ አምሮፓውደር ፐውድሮሽቶ ሽው ሽው አርጎ ኩል ተኳኩሎከል ለብሶጥርስ ፍቆ፣ ቦርሾለባል አድን ጉዞለድረስ ብሎየእጎቱን ሚስት ወንድምየልጅ ልጅ ልጅ ለቅሶ::አዎ¡ጥቁር፣ ኮት፣ ሱሪ ለብሶካፖርት ብጤ፣ ደርቦፒፓ ብጤ፣ ነክሶእቁባት አድን ጉዞለየባንኮኒው ጓደኛ፣ ጉዲፈቻለየጡት ልጁ እህትለጓደኛው ጓደኛ ሚስት‘ኦ’ዛሬ ሥራ አልገባም! አለብኝ “ብሎ”ለቅሶ”እቁባት አደን ጉዞ::ከዛም ለቅሶ ቤትለይሉኝታ ዓይን ጠረግ-ጠረግከንፈር መጠጥ፣ ጎን በስ -ጎንበስአንገት-ቀ ለስአዘናግቶ ቀና ብሎ ሁዋላ ባሻገር ለመጥቀስ::

አያ ጎሽሜፈቃደ አዘዘ

“ፍቅር ማለት እንደ ረድኤትና ተፈራ ነው” ሲባል መስማት የተለመደ ነበር:: የሰፈሩ ልጆች የልጅነት ዕድሜያቸውንም ጨርሰው ልክ እንደ ረድኤት እና ተፈራ ያሉ ፍቅረኛሞች ለመሆን ትልቅ ምኞታቸው ነበር::

ረድኤት አሰፋ፤ ጠይሟ ለግላጋ:: ‘ስጋ ምን ሊረባኝ’ ብላ ነው መሠል በሰውነቷ ላይ ስጋ አልጫነችም:: ቀጥ ያለ ሐረግ የመሠለ ቁመና:: ፀጉሯ አጭርና ከርዳዳ ከመሆኑ በስተቀር መልኳማ የውብ ውብ ነው:: አ.አ.አ…. እዚህ ላይ ትንሽ የተጋነነ ይመስላል:: ስትስቅ የጐደላት ነገር አላት፤ ‘ምንድን ነው የሚጐድላት?’ ተብሎ ሲታሰብ ግን ቶሎ የሚመጣ ነገር የለም:: አዎ ብዙ ካሥተዋሏት ብዙ ካወጡ ካወረዱ ረድኤት አሰፋ ስትስቅ የሚጐድላትን ነገር ያውቁታል::

ጥርሶቿ! ጥርሶቿ አደራደራቸው ወልጋዳ ሆነው አይደለም:: ንጣትም የሚጐድላቸው ሆነው አይደለም፤ እንዲያውም በረዶ የሚመስሉ ናቸው:: ጥርሶቿ አጫጭር ናቸው፤ “አይጥ ጥርስ” ይሏቸው ዓይነት:: እናም ስትስቅ የተሟላ ውበት እንዳታሣይ የሚያደርጓት እነዚያ “አይጥ ጥርሶቿ” ኮንፈሯን አልፈው በመውጣት ብርሀን ለመፈንጠቅ አቅም ስለሚጐድላቸው ነው::

ተፈራ ሰንደቁ ቆንጆ አይደለም:: ግን ወንዳወንድ ነው:: ትክለ ቁመናው ወንድ ነው፤ የፊቱ ግርማ እውነትም እንደስሙ የሚፈራ ነው:: በቂ ቁመት፣ ፍፁም የተስተካከለ ሰውነት፤ መዘላበድ የማያበዛ ንግግሩ ቁጥብ ነው:: ንግግሩ ግን መሬት ጠብ አይልም:: እናም እነዚህ ሁለት ሰዎች ገና በ19 እና በ20 ዓመታቸው ላይ የመሠረቱት ፍቅር በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ ሦስት የሚፎከርበት፤ ተከታይ ወጣቶች ሁሉ የሚመኙት ሆኗል፤ ምን ያደርጋል ታዲያ ሁሉም እንደተቀናበት አይቀር::

በ1982 ዓ.ም ቀውጢ ጦርነት ወቅት ተፈራ ከረድኤት ይልቅ ጦር ግንባርን አፍቅሮ ዘመተ:: ረድኤት አበደች፤ ጦፈች፤ ያዙኝ ልቀቁኝ አለች:: ቤተሠቦቿ ቢሉ ቢሠሯት እየየዋን ሊያሥተዎት አልቻሉም:: ሲውል ሲያድር እየለመደችው ብትመጣም 1983 ዓ.ም ግን ሐዘኑ ባሰባት። ደርግ ተሸንፎ በሕይወት የተረፉት የደርግ ሠራዊት አባላት ወደ ትውልድ ቦታቸው ተመለሡ:: ከተፈራ ጋር

አብረው ከሄዱት ጓደኞቹም የተረፉት ሲመለሱ እሱ ግን ልቡ አልራራም:: ወይ መሞቱ አይታወቅ ወይ መኖሩ ግራ የገባው ነገር ሆነ:: ረድኤት የለየላት ዕብድ ሆነች::

አልቅሳ አልቅሳ ወጥቶላት ሰዎችን የማታናግር ዝምተኛ ሆናለች:: 1984፣ 85፣86 . . . ዓመታት ነጐዱ::

ለ10 ዓመት ያህል ተፈራን ጠበቀችው:: በየዕለቱም ለተፈራ ሳታላቅስ የዋለችበት ቀን የለም:: ‘ከተፈራ በኋላም ወንድ አያሳየኝ’ ብላ ቀርታለች:: ሁልጊዜም ሥለ እሱ ከማሰቧ የተነሳ

ልብሷን አወላልቃ ስትተኛ እንኳ ሰውነቷን በእጆቿ እየዳሰሰች “ከተፈራ ውጭ እኮ ማንም አያውቅህ፤ ተፈራ የመጀመሪያህም የመጨረሻህም ነው!” ማለት ታዘወትራለች::

ዛሬ 1994 ዓ/ም ሆኗል፤ ወደ 31 ዓመትም ተሸጋግራለች፤ 30 ዓመቷን ጨርሳለች:: ተፈራ ያኔ ወደ ጦርነቱ ሲጓዝ ሃያ አንደኛ ዓመቱ ሆኖት ነበር:: ጦርነቱ ከተጠናቀቀ 10 ዓመቱ ሆኖታል:: 33 ዓመቱ ደፍኗል ማለት ነው:: የተፈራ ቤተሰቦች ብዙም ሳይቆዩ በሞት አለቁ:: አንድም የቀረው የለም:: እናት አባቱ እሱ ወደ ጦርነት በሄደ በዓመቱ ተከታትለው ሞቱ:: ብቸኛ እህቱም ወላጆቿ በሞቱ በሁለተኛው ዓመት በመሞቷ የሰፈሩ ሰው “ምን ያርጉ፤ ወይ ‘ሞተ’ የለ፣ ወይ ‘አልሞተም’ የለ! ይሄንንም እነሡ መሆናቸው ነው! ማን ቆሞ ይሄድ ነበር!” እያለ

ለመጨረሻ ጊዜ ሸኛቸው::“ረድኤት ጊዜው እኮ እየሄደ ነው! ….” አሉ አባቷ

አንድ ቀን::፡“የምን ጊዜ አባዬ?” ረድኤት አባቷ ሊጠይቋት

የፈለጉትን ብታውቀውም እዳላወቀች ጠየቀች::“ተይ ልጀ እንደማታውቂ አትሁኝ! በየጊዜው

እየተነጋገርንበት!” አሉ ጋሽ አሰፋ ሽበት የተሥረገረገበትን የራስ ፀጉራቸውን ንዴት የቀላቀለ በሚመሥል ኃይል እያሻሹ:: ጋሽ አሰፋ ንግግራቸውን ቀጠሉ፣

“ዳሩ አንቺ የአባት… የወላጅ ምክር መች ትሠሚያለሽ?”

“አለመሥማት አይደለም፤ እሠማችኋለሁ:: ግን ጊዜ ሥለምትሉት ነገር… የራሡ ጉዳይ? ቅርጥፍ ይበል” አለች ረድኤት ቀድሞውንም ነገሩን አውቃው ሥለነበር ወደ ጉዳዩ ገብታ::

“የሚቀረጥፍ ይቀርጥፍሽ እንዳልልሽ በኋላ ሀዘኑን አልችለውም! እንዲያው ግን ግትር ደረቅ ነሽ! ይሄው ስንት ዓመታችን… ለፈለፍን ለፈለፍን የጥፍርሽን ያህል እንኳ ልትቆጥሪን አልቻልሽም… አሁን ለማን ይነገራል!...ማንን አማልዱን ይባላል?...” ጋሽ አሰፋ ከነበሩበት ቁጣ መለስ ብለው ተለማመኑ::

ረድኤት ትምህርቷን ጨርሳ የመጀመሪያ ዲግሪዋን በማኔጅመንት ተቀብላለች:: ሁለተኛ ዲግሪዋንም በኢኮኖሚክስ ሠርታ የራሷን የንግድ ማማከሪያ ድርጅት ከፍታ ባህር ዳር ውሰጥ ትኖራለች:: አሁንም ከወላጆቿ ጋር ነው የምትኖረው::

የዕድሜዋ መሄድ በየጊዜው የሚያሣሥባቸው እና በትምህርቷም ስኬታማ መሆኗን የሚረዱት ወላጆቿ ሁልጊዜ አንድ ጉዳይ ያሣሥባቸዋል:: እናቷ ወይዘሮ አትጠገብ ኃይሌ ብዙም ባያሥቸግሯትም ጋሽ አሰፋ ግን የጊዜው መንጐድ ያሥከፋቸዋል:: “እንግዲህ ምን ቀራት?... በቃ ለምን አግብታ እሷንም እኛንም አታሥደስተንም” የሚለው የዘወትር ንግግራቸው ሆኗል:: ዛሬም ጭቅጭቁ ይሄው ነው::

“መቼስ አንች ግፍ አልሠራሽበት:: ይሄን ሁሉ ዓመታት ጠብቀሽዋል:: በጦርነቱ ይሙት አይሙት ሳይታወቅ 10 ዓመት አለፈው::… እና አንቺ…” ረድኤት አላስጨረሰቻቸውም!

“በቃህ! አባየ በቃህ! በቁስሌ ላይ እንጨት አትሥደድ! በቃችሁ!… ሁላችሁም በእኔ ዕድሜ መሄድ አያገባችሁም!”ረድኤት ሀዘንና ቁጣን ቀላቅላ ተንተገተገች::

ጋሽ አሰፋ አላረፉም:: የረድኤት ንግግር ሊያሥታግሳቸው አልቻለም::

Page 12: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 12 ማስታወቂያ

ባህር ዳርወ/ሮ ዘውዲቱ አህመድ ጅብሪል በባ/ዳር ከተማ በላይ ዘለቀ ክ/ከተማ ላላቸው ቤት የስም ማዛወሪያ ካርኒ ቁጥር 83446 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የባ/ዳር ከተማ ል/ኮ/መምሪያ---------------------------------------

በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር 0002475213 የቅ/ጽ/ቤታችን ግብር ከፋይ የሆነው ኮብል ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ያልተሰራበት የእጅ በእጅ ሽያጭ/ቫት/ ደረሰኝ ከ62101 እስከ 62200 ሁለት ጥራዝ የጠፋባቸው መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በመሆኑም ይህን የጠፋውን ደረሰኝ በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣት ጀምሮ እስከ 10 ቀን ድረስ ቀርቦ ካላመለከተ የቀረበውን አቤቱታ የምንቀበል መሆናችንን እናሣውቃለን፡፡

በኢትዮጵያ ገ/ጉ/ባለስልጣን የባ/ዳር ቅ/ጽ/ቤት---------------------------------------

ተከሣሾች ታደለ ጥሩዬ ፣ግዛቸው ወርቅዬ እና እንደሻው ደለለ እና በከሣሽ እነ ተዋበ አስማረ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ ተከሣሾች መከሰሣችሁን አውቃችሁ ለ16/03/2009 ዓ/ም ለሆነው ቀጠሮ ከጠዋቱ 2፡30 እንድትቀርቡ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባ/ዳርና አካባቢዋ ከፍ/ፍ/ቤት---------------------------------------

ወ/ሮ አዝመራ ደስታ ተፈራ በባ/ዳር ከተማ ህዳር 11 ክ/ከተማ ላለቸው ቤት የምሪት ካርኒ ቁጥር 88784 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የባ/ዳር ከተማ ል/ኮን/መምሪያ---------------------------------------

የገጠር ቴክኖሎጅ ማዕከል በባ/ዳር ከተማ በላይ ዘለቀ ክ/ከተማ ላላቸው ቤት ካርታ ቁጥር 3090 እና የግንባታ ኘላን ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የባ/ዳር ከተማ ል/ኮ/መምሪያ---------------------------------------

በአመልካች ማስተዋል ከፌ እና በተጠሪ ይበሉ አስረስ መካከል ባለው የገንዘብ ክርክር ጉዳይ ተጠሪ ከቀጠሮው በፊት ከመዝገብ ቤት ቀርበው የቀረበብዎን ክስ በማየት መልስዎን በጽሁፍ በ3 ኮፒ በማዘጋጀት በ19/03/09 ዓ/ም ይዘው እንዲቀርቡ፤ የማይቀርቡ ከሆነ ግን ጉዳዩ በሌሉበት ታይቶ ውሣኔ የሚሰጥ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባ/ዳር ከተማ ወ/ፍ/ቤት---------------------------------------

እነ ታገኝ ማሞ 5 ራሣቸው በባ/ዳር ከተማ ግሽ አባይ ክ/ከተማ ላላቸው ቤት ካርታ ቁጥር 30387/06፣ በውል ቁጥር 6/101 የተመዘገበ የስም ማዛወሪያ ቅጽ ፣ የስም ማዛወሪያ ካርኒ ቁጥር 106426፣ የግንባታ ኘላን እና ዝርዝር ግምት ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የባ/ዳር ከተ/ል/ኮ/መምሪያ---------------------------------------

በአመልካች የሰውዘር ነጋሽ እና በተጠሪ ወ/ሮ ፍሬመልካም ነጋሽ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ መዝገቡ ለሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ያስቀርባል ተብሎ በመታየት ላይ ስለሚገኝ ተጠሪ ይህን አውቀው ታህሣስ 14 ቀን 2009 ዓ/ም ለሆነው ቀጠሮ ቢሮ ቁጥር 20 ከጠዋቱ 2፡30 እንዲቀርቡ፤የማይቀርቡ ከሆነ ጉዳዩ በሌሉበት ታይቶ የሚወሰን መሆኑን አውቀው እንዲቀርቡ ሰበር ሰሚ ችሎቱ አዝዟል፡፡

የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት---------------------------------------

በአመልካች የሰውዘር ነጋሽ እና በተጠሪ ወ/ሮ ሽዋባየሽ ነጋሽ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ መዝገቡ ለሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ያስቀርባል ተብሎ በመታየት ላይ ስለሚገኝ ተጠሪ ይህን አውቀው ታህሣስ 14 ቀን 2009 ዓ/ም ለሆነው ቀጠሮ ቢሮ ቁጥር 20 ከጠዋቱ 2፡30 እንዲቀርቡ፤የማይቀርቡ ከሆነ ጉዳዩ በሌሉበት ታይቶ የሚወሰን መሆኑን አውቀው እንዲቀርቡ ሰበር ሰሚ ችሎቱ አዝዟል፡፡

የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት---------------------------------------

በአመልካች የሰውዘር ነጋሽ እና በተጠሪ አቶ ቴዎድሮስ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ መዝገቡ ለሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ያስቀርባል ተብሎ በመታየት ላይ ስለሚገኝ ተጠሪ ይህን አውቀው ታህሣስ 14 ቀን

2009 ዓ/ም ለሆነው ቀጠሮ ቢሮ ቁጥር 20 ከጠዋቱ 2፡30 እንዲቀርቡ፤የማይቀርቡ ከሆነ ጉዳዩ በሌሉበት ታይቶ የሚወሰን መሆኑን አውቀው እንዲቀርቡ ሰበር ሰሚ ችሎቱ አዝዟል፡፡

የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት---------------------------------------

በአመልካች የሰውዘር ነጋሽ እና በተጠሪ አቶ እንደሻው ነጋሽ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ መዝገቡ ለሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ያስቀርባል ተብሎ በመታየት ላይ ስለሚገኝ ተጠሪ ይህን አውቀው ታህሣስ 14 ቀን 2009 ዓ/ም ለሆነው ቀጠሮ ቢሮ ቁጥር 20 ከጠዋቱ 2፡30 እንዲቀርቡ፤የማይቀርቡ ከሆነ ጉዳዩ በሌሉበት ታይቶ የሚወሰን መሆኑን አውቀው እንዲቀርቡ ሰበር ሰሚ ችሎቱ አዝዟል፡፡

የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት---------------------------------------

ምዕራብ ጐጃምአቶ ይበልጣል ለይኩን በአዲስ አለም ከተማ ቀበሌ 01 የሚገኘው የመኖሪያ ቤት ቦታ ቁጥር 45 በካርታ ቁጥር 53 እና በአዋሣኝ በሰሜንና በምስራቅ መንገድ፣ በደቡብ ይሁን አመራ፣በምዕራብ እንዳዬ ጐባው መካከል የሚገኘው የቦታ ምሪት ካርኒ ቁጥር 0532 እና 0189 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የአዲስ ዓለም ከተማ መሪ ማ/ቤት---------------------------------------

ከሣሽ ፈንታሁን አደመ ተከሣሽ ጌታቸው አለኸኝ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ ተከሣሹ ለህዳር 16 ቀን 2009 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 እንዲቀርብ ፍ/ቤቱ አዝዟል

የሜጫ ወረዳ ፍ/ቤት---------------------------------------

በከሣሽ ወ/ሮ ዝና መኮንን በተከሣሽ አቶ ዘለቀ ደበበ መካከል ስላለው የልጅ ቀለብ እና የንብረት ክስ ክርክር ጉዳይ ተከሣሽ ህዳር 23 ቀን 2009 ዓ/ም ለሆነው ቀጠሮ ከጠዋቱ 3፡00 እንዲቀርቡ፤ ባይቀርቡ ግን ጉዳዩ በሌሉበት ታይቶ የሚወሰን መሆኑን እንዲያውቁት ፍ/ቤቱ አዝዟል

የይልማና ዴንሣ ወ/ፍ/ቤት---------------------------------------

በከሣሽ ወ/ሮ ንብረቴ አንጫጫው እና በተከሣሽ አቶ ይታየው ሙጨ መካከል ስላለው የባልና ሚስት ክርክር ጉዳይ ተከሣሽ መከሰስዎን አውቀው ለህዳር 15 ቀን 2009 ዓ/ም 7ኛ የፍታብሔር ችሎት እንዲቀርቡ፤ ባይቀርቡ ጉዳዩ በሌሉበት የሚታይ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የይልማና ዴንሣ ወ/ፍ/ቤት---------------------------------------

አመልካች ህፃን አይተነው አዘነ ካሴ ከዚህ በፊት እጠራበት የነበረው ስሜ ተቀይሮ በአባቴ ህፃን አይተነው እያያ አስፋው ተብየ እንድጠራ ሲል አመልክቷል፡፡ ተቃውሞ ያለው ካለ ለህዳር 15 ቀን 2009 ዓ/ም እንዲቀርብ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የይልማና ዴንሣ ወ/ፍ/ቤት---------------------------------------

እነ ሞሚና ዳውድ በአዴት ከተማ ቀበሌ 01 በምስራቅ ክፍት ቦታ፣በምዕራብ ተስፋ መኮንን፣በሰሜን መንገድ ፣በደቡብ ቻሌ ተመስገን የሚያዋስነው የመኖሪያ የምሪት ካርኒ ቁጥር 168875 እና ካርታ ቁጥር ከአገ/1277/2007 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የአዴት ከተማ አገ/ጽ/ቤት---------------------------------------

በከሣሽ አቶ የቻለ አድማሱ እና በተከሣሽ ወ/ሮ ሰርክአዲስ አከለ መካከል ስላለው የባልና ሚስት ክርክር ጉዳይ ተከሣሽ መከሰስዎን አውቀው ለህዳር 19 ቀን 2009 ዓ/ም 3፡00 7ኛ የፍታብሔር ችሎት እንዲቀርቡ፤ካልቀረቡ ጉዳዩ በሌሉበት የሚታይ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የይልማና ዴንሣ ወ/ፍ/ቤት---------------------------------------

አቶ ጥጋቡ አስማረ ላቀ በመርዓዊ ከተማ ቀበሌ 02 በምስራቅ ጌታነህ ፈንቴ ፣በምዕራብና በደቡብ መንገድ፣በሰሜን ገነት እንዳለው ተዋስኖ የሚገኘው የመኖሪያ ቦታቸው ካርኒ ቁጥር 860517 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የመርዓዊ ከተ/አገ/ጽ/ቤት---------------------------------------

ወ/ሮ ባንቻየሁ ቁሜ በደምበጫ ከተማ ቀበሌ 01 ሰፈር 3

በሰሜን ድረስ ተሻለ ፣በደቡብ መንገድ ፣በምዕራብ ፍቅር ደሣለኝ ፣በምስራቅ ጐዴ ዋሴ የሚያዋስነው ቦታ ካርኒ ቁጥር 011590 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የደምበጫ ከተማ አገ/ጽ/ቤት---------------------------------------

አቶ አምሣሉ መንግስት በሽንዲ 01 ቀበሌ ውስጥ በሰሜን አበበ መኩሪያው ፣በደቡብ እና በምስራቅ መንገድ፣በምዕራብ ሞሴ ቸኮል የሚያዋስነው የመኖሪያ ቤት የምሪት ካርኒ ቁጥር 01481 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የሽንዲ ከተማ መሪ ማ/ቤት---------------------------------------

አቶ ካሴ መንግስቱ በግሽ ዓባይ ከተማ ቀበሌ 01 በሰሜን መንገድ፣በደቡብ ሙሉ ካሴ፣በምስራቅ ፀጋዬ ደርሰህ ፣በምዕራብ ፀጋየና ጌታነህ መካከል ተዋስኖ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት የቦታ ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር 270/2006 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የግሽ ዓባይ ከተማ መሪ ማ/ቤት---------------------------------------

አቶ አዱኛ ደበበ በአዴት ከተማ ቀበሌ 02 በምስራቅ ማዕረጉ ፣በምዕራብ መንገድ ፣በሰሜን አድነው ፣በደቡብ መኖሪያ ቤት የሚያዋስነው የመኖሪያ ቤት የምሪት ካርኒ ቁጥር 202781 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የአዴት ከተማ አገ/ጽ/ቤት---------------------------------------

ምስራቅ ጐጃምእነ ተመስገን ብርሃኔ በደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 06 በቤት ቁጥር 206 በካርታ ቁጥር K/6897 የተመዘገበ የመኖሪያ ቤት ቋሚ ካርታ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የደ/ማርቆስ ከተ/አገ/ጽ/ቤት---------------------------------------

አዊአቶ ማንዴ ጫኔ ቀራለም በፈንድቃ ከተማ በ2001 ዓ/ም የተቆረጠ የከተማ ቦታ የተመሩበት ደረሰኝ ቁጥር 1612 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ አንድ ወር ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የፈንድቃ ከተማ ማዘጋጃ ቤት---------------------------------------

መሬም አስፋው በቻግኒ ከተማ ቀበሌ 02 ልዩ ሰፈራ አ/መናኸሪያ የሚገኘው የድርጅት ቤታቸው ውል የዞረበት ካርኒ ቁጥር 030067 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የቻግኒ ኢ/ከ/አገ/ጽ/ቤት---------------------------------------

አቶ ወርቅነህ ቦጋለ በአገው ግ/ቤት ቀበሌ 01 በቤት ማህበር ተደራጅተው የመሬት ካሣ የከፈሉበት ካርኒ ቁጥር 251003 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የአገው ግ/ቤት ከ/መሪ ማ/ቤት---------------------------------------

ወ/ሮ ትርንጎ ብርሔ በቲሊሊ ከተማ ቀበሌ 01 ለሚገኘው ቤታቸው በሰሜን ሙሉ ጋሹ፣በደቡብ መንገድ፣በምስራቅ መዝገቡ ጌትነት፣በምዕራብ ቢተው አበበ የሚያዋስነው የመኖሪያ ቤት የምሪት ካርኒ ቁጥር 042396 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የቲሊሊ ከተማ መሪ ማ/ቤት---------------------------------------

አመልካች አቶ ገናነው ፈንቴ እናቴ ወ/ሮ ትሁኔ አማረ የጠፋች ስለሆነ ትጠራልኝ ብለዋል፡፡ ስለዚህ ተፈላጊዋ ካሉ ለህዳር 13 ቀን 2009 ዓ/ም በ6፡00 እንዲቀርቡ ፍቤቱ አዝዟል፡፡

የፋግታ ለኮማ ወ/ፍ/ቤት

---------------------------------------

ደቡብ ጐንደርወ/ሮ ሙጭት ዋለ በመካነ ኢየሱስ ከተማ በቀበሌ 01 በምስራቅ እና በሰሜን አህመድ አሊ፣በምዕራብ መንገድ ፣በደቡብ ተመስገን ሲሣይ የሚያዋስነው 235.20 ካሬ ሜትር የመኖሪያ ቦታ የኘላን ቁጥር መኢከአገ 09/ሙ/1027 በቀን 25/09/2007 ዓ/ም የተሰጣቸው ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የመካነ ኢየሱስ ከ/አገ/ጽ/ቤት---------------------------------------

አቶ እንየው አለሜ በአዲስ ዘመን ከተማ በቀበሌ 03 በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ጌታሁን በላይ፣በደቡብ መቅደስ መኮነን፣በሰሜን አንባው ፀጋው ተዋስኖ የሚገኘው የምሪት ቤትና ቦታ ከመ/ቤቱ የነበረው ስታንዳርድ ኘላን /መረጃ/ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የአዲስ ዘመን ከ/አገ/ጽ/ቤት---------------------------------------

ደቡብ ወሎወ/ሮ በላይ ተገኘ አሊ በደሴ ከተማ በቧንቧ ውሃ ክ/ከተማ ክልል በቁጥር 10395 የተመዘገበ ካርታ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 10 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የቧንቧ ውሃ ክ/ከተማ አስ/ጽ/ቤት---------------------------------------

አመልካች እሌኒ አራጋው እና በተጠሪ ፈንታው አሊ መካከል ስላለው የመጥፋት ውሣኔ ጉዳይ ተጠሪው ለህዳር 15 ቀን 2009 ዓ/ም ለሆነው ቀጠሮ እንዲቀርቡ፤ ባይቀርቡ ግን ጉዳዩ በሌሉበት ታይቶ ውሣኔ የሚሰጥ መሆኑን እንዲያውቁት ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የአምባሰል ወ/ፍ/ቤት---------------------------------------

የኒው ጀኔሬሽን የመኖሪያ ቤትና አካባቢ ልማት ህ/ስ/ማህበር ኃላፊነቱ የተወሰነ በጠቅላላ ጉባኤው እንዲፈርስ ተወስኗል፡፡ ስለዚህ በህብረት ስራ ማህበሩ ላይ ገንዘብ ጠያቂዎች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ባሉት የሁለት ወራት ጊዜ ድረስ ደሴ ከተማ አስተዳደር ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ተጠሪ ጽ/ቤት በመምጣት እንድታመለክቱ እየገለፅን ቀኑ ካለፈ በኋላ አመልካቾችን የማንቀበል መሆኑን እናሣውቃለን፡፡

ጽ/ቤቱ---------------------------------------

ወ/ሮ ዘሙ መሐመድ ሐሰን በኮምቦልቻ ከተማ ቀበሌ 02 ክልል የሚገኘው የመኖሪያ ቤት በስሜ የተመዘገበ ቁጥር 8126 ኮ/ቴ/አገ/ቀ/02/2008 ዓ/ም ካርታ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ አስ/ጽ/ቤት---------------------------------------

ሰሜን ወሎወ/ሮ እራህመት ሱሌማን ሐሰን በወልድያ ከተማ በቀበሌ 02 የሚገኘው ቤታቸው በእጃቸው ያለው ኘላን እና ካርታ ቁጥር ወከ/ቦአ/6114/03 በቀን 20/10/03 ዓ/ም የተሰጣቸው ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የወልድያ ከተማ አገ/ጽ/ቤት---------------------------------------

ዋግኽምራአቶ ሐይሌ አማርጊስ በኒሯቅ ከተማ ቀበሌ 01 ቀጠና 2 በምስራቅና በምዕራብ መንገድ ፣በሰሜን ወንዝ፣ በደቡብ ክፍት ቦታ የሚያዋስነው የሆቴል ቦታ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር ኒ-311 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የኒሯቅ ከተማ መሪ ማ/ቤት---------------------------------------

ኦሮሞ ብሔረሰብከሣሽ ወ/ሮ ጦይባ ሰይድ መሐመድ እና ተከሣሽ አቶ አሊ አብዱ ሰይድ አብዱ መካከል ስላለው የባልና ሚስት ክርክር ጉዳይ ተከሣሽ ለ27/03/2009 ዓ/ም እንዲቀርቡ፡፡ ካልቀረቡ ጉዳዩ በሌሉበት የሚታይ መሆኑን ሸሪዓ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የዳዋ ጨፋ ወረዳ ሸሪዓ ፍ/ቤት---------------------------------------

Page 13: 12 03 2009.pdf

ገጽ 13በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. ፍትህ/መልካም አስተዳደር

አባትሁን ዘገየ

አጫጭር ዜናዎች

ላም የገደለው ግለሰብ እስራትና ገንዘብ ተወሰነበት

በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሽንኮራ ወረዳ ዋና ከተማ አረርቲ ቆለኛ፣ ቡልጋና ሌሎች መውጫ በሮች የጭነት ተሽከርካሪዎች በጭነት ላይ ህዝብን በመጫን ህገ ወጥ የትራፊክ እንቅስቃሴ እያስፋፉ መሆናቸውን ነዋሪዎች ጠቆሙ::

የባጅጅ አሽከርካሪው ጌታሁን ንጋቱ እንደሚለው ተቆጣጣሪ በሌለበት ሰዓት ርቀት ባላቸው መንገዶች ላይ አሽከርካሪዎች ከተፈቀደላቸው የጭነት ልከ እና ከታሪፍ በላይ ሲያስከፍሉ ይስተዋላሉ:: ለዚህ ደግሞ በተለይ ለማስከፈል የሚያስገድዳቸው የታሪፉ አነስተኛ መሆን ነው ብሏል::

የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽረፈዲን ሙሐመድ እንደገለጹት የትራፊክ እንቅስቃሴውን ህጋዊ ለማድረግና ሰላማዊ የመንገድ ፍሰት ለመፍጠር ከወረዳው ፖሊስ በመቀናጀት ባለሙያ መድበው እየሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል:: የጭነት ተሽከርካሪዎችም ህዝብን ለመጫን ህጋዊ ፈቃድ እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል::

በባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በሚያደረጉበት ሰዓት ከስምሪታቸው በመጥፋትና በምሽት ከተቆጣጣሪዎች በመደበቅ ከልክ በላይ እንደሚጭኑና ከተፈቀደላቸው ታሪፍ በላይ እንደሚያስከፍሉ ኃላፊው መረጋገጡን ገልፀዋል:: ይሁን እንጂ፤ ተከታትለው ርምጃ የመውሰድ ክፍተት እንዳለባቸው ጠቁመዋል::

የባጃጅ አሽከርካሪዎችም አድርሰው በሚመለሱበት ወቅት ሰዎች ስለሚያገኙ ታሪፍ ይህንን ከግምት ውስጥ አላሰገባም ብለው የሚያነሱት ጥያቄ ተገቢ ያልሆነና አሁን ያለው ታሪፍ ይህንን ታሳቢ አድርጐ 150 በመቶ ታስቦ የወጣ ነው ሲሉ የወረዳው መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊው ገልፀዋል::

ኃላፊው አክለውም በወረዳው ላይ በቂ የመደበኛ ተሽከርካሪዎች አለመኖር ለህገ ወጥ የጭነት አሽከርካሪዎች መበራከት ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል:: “በመስመሩም ተጨማሪ ተሽከርካሪዎችን በመመደብ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በመስራት ላይ ነን” ብለዋል::

የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የመንገድ ትራንስፖርት ደህንነት ማረጋገጫ ዋና የሥራ ሂደት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ማሞ የነ በበኩላቸው በመስመሮች ላይ ህገ ወጥ የትራፊክ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን አምነዋል:: ይህን ተከትሎም ከወረዳው መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት የግንዛቤ ፈጠራ ስራና ህጋዊ ርምጃ እየወሰድን ነው” ብለዋል:: በጽ/ቤታቸው የተሽከርካሪ አለመኖር እና የሰው ኃይል እጥረት ህገ ወጥ እንቅስቃሴውን በተገቢው መልኩ ለመቆጣጠር እንዳስቸገራቸው ጠቅሰዋል:: ዘገባው የወረዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው::

ወደ ገጽ 38 ዞሯል

ሕገ ወጥ የትራፊክ እንቅስቃሴ እየተስፋፋ ነውፊት

ለ ፊት

ዓለም ከተማ

“በጥናት ላይ ተመስርተው ምላሽ መስጠት አለባቸው”አቶ ብርቃብርቅ ተሾመ

“የፍትሀዊ ችግሩ ተቃሏል”ወ/ሮ እታገኘሁ በትረ

“ዘጠኝ ወር በጋ የውኃ ችግር አሰቃይቶናል”አቶ በለው አስጨናቂ

የዓለም ከተማ ነዋሪዎች ሰኔ 5 ቀን 2008 ዓ.ም ከአመራር አካላት ጋር ባንድ አዳራሽ ፊት ለፊት በመገናኘት አሉብን ያሏቸውን

ችግሮች በመዘርዘር እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል:: የአመራር አካላቱም ለጥያቄዎቹ ምላሽ ሰጥተዋል:: መልስ የሰጡትም መፈታት አለባቸው ያሏቸውን ችግሮች ለመፍታት እንደሚጥሩ ቃል በመግባት ነበር::

በዚህም መሠረት በቅርቡ በዓለም ከተማ በመገኘት ነዋሪዎችን የትኞቹ ችግሮች እንደተፈቱና እንዳልተፈቱ አነጋግረን የሚከተለውን ዘገባ አዘጋጅተናል::

መልካም ንባብ!

ውኃ"የንጹህ መጥጥ ውኃ እጥረት መፍትሄ

ሊፈለግለት ይገባል" የሚለው በስፋት ከተነሱት ችግሮች አንዱ ነበር:: "የውኃ እጥረት አለብን:: ስርጭቱም ፍትሀዊ አይደለም:: በተለይ እናቶች ሆስፒታል በሚወልዱበት ጊዜ መታጠቢያ አያገኙም:: ስለዚህ ችግሩ ይፈታ የሚል ሀሳብ አቅርቤ ነበር:: ሆኖም አሁንም ችግሩ ያው ነው፤ ምንም የተስተካከለ ነገር የለም" በማለት የችግሩን አለመቃለል ያስረዱን ወ/ሮ ዘውዲቱ ሙሉጌታ የተባሉ የከተማዋ ነዋሪ ናቸው::

ሌላው የዓለም ከተማ ነዋሪ አቶ አብዩ አማከለ እንደሚሉት ደግሞ ውሃ ከእጥረቱ ባሻገር የስርጭት አለመስተካከል ጐልቶ ይታያል:: "አንዱ አካባቢ ውኃ ደርሶት አያውቅም፤ ሌላው ደግሞ ሲሸጥ ይታያል" የሚሉት አቶ አብዩ ያለው አነስተኛ ውኃም ቢሆን ለነዋሪዎች እኩል ሊዳረስ እንደሚገባ ጠይቀዋል::

አቶ በለው አስጨናቂ የተባሉት ነዋሪ ደግሞ ከሰዉ ይልቅ ለአትክልት ቅድሚያ እየተሰጠ፣ ሰዉ እየተጠማ እንደሆነ ይናገራሉ:: "ዘጠኝ ወር በጋ የውኃ ችግር አሰቃይቶናል:: ስለሆነም ችግሩ እንዳይደገም ከአትክልት ይልቅ ለሰው ልጅ ቅድሚያ መሰጠት አለበት" ይላሉ::

ሲስተር አልማዝ አውግቸው በበኩላቸው "የከተማዋ ነዋሪ ቁጥር እየበዛ ነው፤ ባንጻሩም የውኃ አቅርቦቱ አልተሻሻለም:: ስለሆነም በመስኖ የሚተዳደሩ አርሶ አደሮች ካሳና ምትክ ቦታ ተሰጥቷቸው ኑሯቸውን የሚቀጥሉበት አማራጭ ይፈለግ" የሚል አስተያየት አቅርበው ነበር:: ነገር ግን ይሄን የመፍትሄ ሀሳብ ይዞ ችግሩን ለመፍታት የተንቀሳቀሰ አካል የለም:: በዚህ የተነሳም አርሶ አደሮቹ ውኃውን ለመስኖ ስለሚጠቀሙበት የውኃ እጥረቱ ተባብሶ ቀጥሏል:: ነዋሪዋ እንደሚሉት አርሶ አደሮቹ 18 ሰዓት እንዲሁም የከተማው ነዋሪ ስድስት ሰዓት እንዲያገኙ እየተደረገ ነው:: ስለሆነም ቅድሚያ ለሰው ልጅ መሰጠት ስላለበት ስድስት ሰዓት የተባለው ቢቻል 24 ሰዓት ቢሆን፣ ካልተቻለም እስከ 18 ሰዓት ተራዝሞ ለመጠጥ ሊውል እንደሚገባ ጠይቀዋል::

ወ/ሮ እታገኘሁ በትረ የዓለም ከተማ ውኃ

አገልግሎት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ በሰጡት ምላሽ "የውኃ ስርጭት ፍትሀዊነት ችግርን ለመፍታት ጥረት ተደርጓል:: በዚህም ችግሩ ውስጥ ገብተው በነበሩ ባለሙያዎች ላይ የደመወዝ ቅጣት ተወስኖባቸው ተግባራዊ ሆኗል:: የፍትሀዊነት ችግሩም ተቃሏል" ብለዋል:: ይሁን እንጂ፣ ስድስት ሰዓት ለመጠጥ፣ 18 ሰዓት ለመስኖ የሚለው አሠራር ችግር እያስከተለ ነው:: ቢሆንም መፍትሄ እንዳላገኘ ጠቁመዋል:: "አምና 15 ቀናት ጠብቀን ነው እናገኝ የነበረ:: ዘንድሮም ድልድሉ ካልተሻሻለ ተመሳሳይ ችግር ውስጥ እንገባለን" ሲሉም ስጋታቸውን ገልፀዋል::

ህብረተሰቡ እየተቸገረ አንድ ጀሪካን ውኃ አንድ ብር የሚሸጡ እንዳሉ የጠቆሙት ወ/ሮ እታገኘሁ ሰዎቹ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እየመከሩና እያስተማሩ እንደሆነ አስረድተዋል:: ከዚህ ድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆነም እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደዱ አስገንዝበዋል::

አቶ ብርቃብርቅ ተሾመ የዓለም ከተማ ከተማ

አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እንደጠቆሙት ከከተማው አምስት ኪሎ ሜትር ያህል ርቆ የሚገኘውንና የከተማው ህዝብ ለመጠጥ የሚጠቀምበትን ውኃ ለመስኖ ተጠቅመው ኑሯቸውን የሚገፉ ሁለት መቶ አርሶ አደሮች አሉ:: ስለሆነም የከተማውን ነዋሪና የአርሶ አደሮቹን ፍላጐት አጣጥሞ ውኃውን ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል:: ለዚህ ደግሞ “የከተማ አስተዳደሩና የወረዳ አመራሩ በጥናት ላይ ተመስርተው ምላሽ መስጠት አለባቸው” ብለዋል::

"ከከተማው የውኃ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ብዙ ችግሮች አሉ:: በተለይም ከአንድ ዓመት ወዲህ ከፍተኛ እጥረት እየተከሰተ ነው:: በሶስት ቀን አንድ ቀን እንኳን ውኃ ማግኘት እየቸገረ መጥቷል" በማለት የችግሩን አሳሳቢነት ለማሳየት ምላሽ የሰጡት ደግሞ የመርሐቤቴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ አሰፋ ናቸው:: የህዝቡ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመርና የተቋማት መስፋፋት ደግሞ ለችግሩ መባባስ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው::

ከዚህ በመነሳትም ችግሩን ለማቃለል የከተማ አስተዳደሩ፣ ወረዳው እንዲሁም ዞኑ ምክክር ማድረጋቸውን አቶ ዘውዱ አውስተዋል:: የምክክሩ ማጠቃለያም ከዞን ከፍተኛ ባለሙያዎች መጥተው የውኃውን የፍሰት መጠንና የማጠራቀሚያ አቅም እንደለኩ፣ ከዚያም የከተማው ህዝብ 24 ሰዓት ውኃ እዲያገኝ፣ ይህም ሆኖ የከተማውን ፍጆታ ማርካት ስለማይቻል ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈለግ የሚል እንደነበር አውስተዋል:: ይሁን እንጂ፣ ባለሙያዎች ሳይመጡ ክረምቱ እንደገባ አስረድተዋል:: አሁንም ቢሆን ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥልቅ ጥናት ሊደረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል:: በጥናቱ ውጤት መሠረትም በየደረጃው ያለ መዋቅርና አመራር ድርሻው ተለይቶ ወደ ሥራ መግባት እንደሚኖርበት አቶ ዘውዱ አሳስበዋል::

"የዓለም ከተማ የመጠጥ ውኃ ችግርን በጊዜያዊነት ለማቃለል የከተማና ወረዳ አስተዳደሮች በጋራ መሥራትና ከተማው የሚስብበትን የተወሰነ ሰዓት መጨመር ይኖርባቸዋል:: ይህን መፈፀም ካቅማቸው በላይ ከሆነ ለዞን ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል" ያሉን ደግሞ አቶ ብርሃኔ ቸኮል የሰሜን ሸዋ ዞን ውኃ፣ መስኖና ኢነርጅ መምሪያ ኃላፊ ናቸው::

በምዕራብ ጎጃም ዞን በደቡብ አቸፈር ወረዳ በዱርቤቴ ከተማ ዝብስት ቀበሌ ልዩ ቦታው ዛብዜ ጎጥ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ግለሰብ የእስራትና የገንዘብ ቅጣት እንደተወሰነበት የወረዳው ፍርድ ቤት አስታወቀ::

የፍርድ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ወ/ሪት አገርነሽ ምስክር እንደገለፀችው ተከሳሽ ጥላሁን ምትኬ የግል ተበዳይ የወ/ሮ በላይነሽ መንግስቱ ንብረት የሆነችውን ግምቷ አስራ አንድ ሺህ ብር የሆነች ክበድ ላም መጋቢት 28/2009 ዓ.ም በመርዝ ገድሏል:: በዚህም ግለሰቡ በሰው ንብረት ላይ ጉዳት በማድረሱ ፍርድ ቤቱ ድርጊቱን በመመርመር ውሳኔ ሰጥቷል::

ተከሳሽን ያርማል ሌላውን ህብረተሰብ ያስተምራል በማለት ጥቅምት 7/2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሁለት አመት ጽኑ እስራትና የአንድ ሺህ ብር የቅጣት ውሳኔ ፍርድ ቤቱ ማስተላለፉን የወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘገባ ያስረዳል::

“ፋብሪካ በአካባቢው እንዲገነባ ቦታ በማስረከብ ሂደት ላይ ነን”አቶ ዘውዱ አሰፋ

Page 14: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 14 ማስታወቂያ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበሰሜን ጐንደር ዞን የአይከል ከተማ አስተዳደር ገ/አ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2009 ዓ/ም በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ፣ሎት 1 ጠጠር፣ ድንጋይ እና አሽዋ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ሎት 3 ጀኔሬተር ሎት 4 ሲሚንቶ ሎት 5 የማሽን ኪራይ ሎት 6 የህንፃ መሣሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያላቸው፣4. የሚጫረቱት ዋጋ ከ50 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ

የሚችሉ፣5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን

መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡6. የሚገዛውን የእቃ ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፣7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት እያንዳንዱ ሎት

ብር ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 30.00 ብር በመክፈል ከረዳት ገ/ያዥ ቢሮ ቁጥር 17 ማግኘት ይችላሉ፣

9. ተጫራቾች የጨረታ ሃሣቡን አንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ 2 ቅጅዎች ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአ/ከ/አስ/ገ/አ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ይውላል፡፡ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም በ3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ የሚከፈት ሲሆን ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይታሸግና በዚሁ ቀን ይከፈታል፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ አ/ከ/አስ/ገ/አ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 333 11 54 ወይም 058 333 11 48 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

13. አሸናፊውን የምንለየው በጥቅል ዋጋው ስለሆነ ሙሉ እቃው መሞላት አለበት ካልሆነ ግን ከጨረታው ውጭ የሚያደርግ መሆኑን አውቃችሁ በጥንቃቄ እንዲሞላ ስንል እንገልፃለን፡፡

14. የእቃው ርክክብ ቦታ አይ/ከ/አስ/ገ/አ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ይሆናል፡፡ማሣሰቢያ፡- የድርጅትዎ ማህተም በየገፁ ማድረግዎን አይዘንጉ እንዲሁም የጨረታ ፖስታውን ሲልኩ የተቋማችን አድራሻ ይግለፁልን፡፡

የአይከል ከተማ አስተዳደር ገ/አ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበደቡብ ጎንደር ዞን ለአዲስ ዘመን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ እቃዎች ሎት 2 የጽዳት እቃዎች ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 4 ብትን የደንብ ልብስ ሎት 5 የቆዳ ውጤቶች አቅርቦቶችን /በጥቅል/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር /ተመዝጋቢ የሆኑ፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፈቃዳቸውን ያሣደሱ፣

3. የግዥ መጠኑ ብር 50 ሺህ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የሚገዙ እቃዎችን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ እቃ ብር 50.00 በመክፈል አዲስ ዘመን ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 2 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ የገቢ ደረሰኝ መቁረጥ አለባቸው፡፡

8. ጨረታው በአየር ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11፡30 ይቆያል፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አዲስ ዘመን ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሣጥን የጨረታ ማስከበሪያውን ከኦርጅናል ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ከተዘጋጀው ሣጥን እስከ 15 ቀን 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በ16ኛው ቀን 2፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ባይገኝ የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለተላለፉ ውሣኔዎች ተገዥ ይሆናል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

11. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ አለበት፡፡

12. መ/ቤቱ በሚገዛው እቃ ግዥ ላይ 20 በመቶ ከፍና ዝቅ የማድረግ መብት አለው፡፡

13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

14. በጨረታው ለመሣተፍ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አዲስ ዘመን ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 444 03 72 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአዲስ ዘመን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ጐንደር መስ/ዞን የሊቦ ከምከም ወ/ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት ለሊቦ ከም/ወ/ገጠር መንገድ ጽ/ቤት በ2009 በጀት ዓመት ከደሪጣ እስታማሪያም የቆረጣ፣ የድልዳሎ እና የሙሊት ስራ በመደበኛ በጀት ዶዘር ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የዶዘር አይነት የተሰራበት ዓ/ም የፈረስ ጉልበት ዶዘሩ የሚሰራበት

ሰዓት

የበጀት ምንጭ

1. D8R ከ2012 ወዲህ 305 200 ከመደበኛ በጀት

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች መወዳደር የሚችል መሆኑን ይጋብዛል፡፡1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ፈቃዳቸውን ያሣደሱ /የቲን/ ተመዝጋቢ የሆኑ፣3. የግዥ መጠኑ ብር 50 ሺህ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፣4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡5. ማሽኑን ከስራ ቦታው ድረስ ማድረስ የሚችል፣6. የማስጫኛ ኪራይ በራሱ የመሸፈን የሚችል፣7. የዶዘር ኦኘሬተርና ረዳት ኦኘሬተር በራሱ ማሰራት የሚችል፣8. ግሪስና ዘይት በራሱ መሸፈን የሚችል፣ 9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 በመክፈል ሊቦ ከም/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 ማግኘት ይችላሉ፡፡10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 1.5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ የጨረታ

ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ የገቢ ደረሰኝ መቁረጥ አለባቸው፡፡11. የጨረታ ሰነዱ የሚሸጠው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይሆናል፡፡12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሊቦ ከምከም ወ/ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት በግዥ እና ንብ/አስ/ደ/

የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን የጨረታ ማስከበሪያውን ከኦርጅናል ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እስከ 11፡30 ማስገባት ይኖርበታል፡፡

13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 16ኛው ቀን 2፡50 ታሽጎ 3፡00 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ባይገኝ የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለተላለፉ ውሣኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

14. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡16. ተጫራቾች ከሰነዱ እና ከፖስታው ላይ ክብ ማህተም ማድረግ አለበት፡፡17. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 444 01 95/10/22 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የሊቦ ከምከም ወረዳ ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት

Page 15: 12 03 2009.pdf

ገጽ 15በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. ኪንና ባህልኪንና ባህል

ወደ ገጽ 32 ዞሯል

አማርኛ በአማርኛ

መሀለቅ - በቀድሞ ዘመን ለመገበያያ ያገለግል የነበረ የገንዘብ አይነት

ሰበቀል - ያማረ፣ ተወደደ፣ ደማምቀጠራ - ያላፈራ እህል፣ በእንቡጥ

የቀረ፣ እንጭጭአምጃ - በደጋና በወይና ደጋ

አካባቢ ችግ ብሎ የሚበቅል የቁጥቋጦ አይነት

ወቄራ - የማረጃ ካራ፣ ቢለዋጓል - የተያያዘ፣ ያልደቀቀ፣ የተድቦለቦለ አፈር

ፀጋዬ የሺዋስ

ጊምባ ላይ እረኝነት ትልቅ ክብር የሚሰጠው ሥራ ነው። የጊምባ እረኞች ከብትና በግ ከማገድ ባለፈ ትልቅ

ማህበራዊ ሚናም አላቸው:: እረኞቹ መጪውን ጊዜ በስነቃሎቻቸው አማካኝነት የሚያሳዩ ትምቢት ተናጋሪዎች ናቸው:: ለዚህም ነው በወሎ ምድር ከበድ ያለ ወቅት ሲመጣ "የጊምባ እረኛ ምን አለ?" የሚባለው:: ማህበረሰቡም በእረኞቹ ትንቢት ትልቅ መተማመን አለው:: ለምን? ባለፉት ጊዜያት የእረኞቹ ስነቃሎች በትክክል ነገን ማሳየት ችለው ስለነበር ነው::

የጊምባ መሬት ከሌሎች የወሎ አካባቢዎች በተለዬ ሜዳ የበዛበትና ለእረኞች የሚመች ነው:: በጊምባ የተንጣለለ ሜዳ ላይ በርከት ያሉ እረኞችን ማየት የተለመደ ነው:: ከሌላው የወሎ መልክአምድር በተለዬ የጊምባ መሬት ደልደል ብሎ ለእረኞች

"አረቦን"

የተመቸ የሆነው በምክንያት ይሆን? ብለን እንድናስብ ያደርጋል:: በዚህ አካባቢ ስነ ቃል ትልቅ ቦታ አለው::

ቀደም ባሉት ዘመናት የነበሩ የአካባቢው እረኞች አህያ መጣች ተጭና ሞፈርከንግዲህ ቀረ ትልቅ ሰው ማፈርብለው እንደነበር ለ13 ዓመታት በእረኛነት

ህይወት ውስጥ የቆየው አሊ መካሻ ተናግሯል:: ይህ ትንቢታዊ ስነ ቃል የተነገረው በቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ዘመን መሆኑንና ትምህርት ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በዘር፣ በአባት ርስትና ጉልት መከበር ቀርቶ የተማረ ብቻ የሚከበርበት ቀን ይመጣል ሲሉ የተነበዩበት ስነ ቃል መሆኑን ያስረዳል::

ቱላ አውሊያ ላይ ይሠራዋል ቤት፣ከቁመቱ ርዘመት ከወርዱ ስፋት::ብለው መጪው ዘመን በአካባቢው ትልቅ

ግንባታ እንደሚገነባም ተንብየው እንደነበር ገልጿል:: ይህንን ትንቢትም ዛሬ ላይ በአካባቢው እየተገነባ ካለው ዩኒቨርሲቲ ጋር ያያይዙታል::

አህያ መጣች ተጭና ጦጣ፣ ቢታጣ ቢታጣ ስርቆት አይታጣ::በሚልም ነጣቂና አጭበርባሪ የሚበዛበት ጊዜ

ይመጣል ሲሉ መተንቢያቸውን ተናግሯል:: የጊምባ እረኞች በፍቅር ስንኞችም የተካኑ ናቸው::

የበጐቹ እረኛ ችክ ይላል በጊዜ፣

እሷን ስጡኝና ይቅር ደመወዜ::ይህ ስነ ቃል በአሰሪዎቹ ልጅ ፍቅር የተነደፈ

እረኛን ስሜት የሚገልጽ ነው::የበጐቹ እረኛ የነጀላሊት፣ቀን አይመቸኝም ልምጣ ወይ ሌሊት::በማለትም ለሚወዳት ቆንጆ መልዕክት ያለው

ስንኝ ይቋጥራል:: የጊምባ እረኛ ስነቃሎቹን በግጥም መልክ እየደረደረ ሌላ ጊዜ ደግሞ በዜማ አጅቦ ያንጐራጉረዋል::

ከርቀት ሆና እየናፈቀችው ላለች ቆንጆም በስነቃል አማካኝነት ምን ማድረግ እንዳለባቸው መልዕክቱን ያስተላልፋል::

አንቺ ፈረስ ግዥ እኔ ኮርቻውን፣ካንቺ ቤት እኔ ቤት መመላለሻውን:: አሊ መካሻ ለበርካታ ዓመታት ከቆየበት እረኛነት

ወጥቶ በአሁኑ ወቅት በእርሻ ሥራ ላይ ተሠማርቷል:: ልጁ የእሱን በጐች እንዲያግድ ያደርጋል፤ ወደ 180 በጐች አሉት:: ሆኖም በአሁኑ ወቅት በጎቹ እንጂ የአካባቢው መገለጫ የሆነው ስነ ቃል እየተዘነጋ መምጣቱን ያምናል:: የህብረተሰቡ የአኗኗር ዘይቤ እየተቀየረ መምጣትም ለዚህ ትልቅ ሚና እንደተጫወተ ተናግሯል::

በአሁኑ ጊዜ ግጦሽ እየቀነሰና እየቀረ መምጣቱ ለስነቃሉም እየጠፋ መምጣት የራሱን ሚና

እየተጫወተ መሆኑን ከግማሽ በላይ የእድሜ ዘመናቸውን በእረኛነት ያሳለፉት አቶ መካሻ እንድሬ ተናግረዋል::

ድንጋይ እያጋዙ አጥር ከማጠር፣ከጥርስ መሀል ምላስ ማሳጠር::በማለትም ምክር ያዘሉ ስነቃሎችን በማስተላለፍ

ትልቅ ማህበራዊ ኃላፊነት እንደሚወጡም አቶ መካሻ ገልፀዋል::

ከሁሉም ከሁሉም ምላስ ለስላሳ፣እሱ የወጋው አይድንምሳ::በማለትም የክፉ ንግግርን አስከፊነት

ይጠቁማሉ::የጊምባ እረኞች ስነቃሎቻቸውን በተረት

እያዋዙም ለማህበረሰቡ ያቀርባሉ:: አቶ ይማም እንድሬ የሚከተለውን ተረት ነግረውናል::

በአንድ ወቅት አዝመራው ይበላሽና ለሰው መሆን ስላልቻለ እንስሳት ይመገቡት ተብሎ አህያ፣ በቅሎና ላሞች ተለቀቁበት:: ይህንን አጋጣሚ ያገኙ እንስሳት እስኪበቃቸው ከተመገቡ በኋላ መፈንጠዝ ጀመሩ:: ስምንት አህዮች ጠግበው በመፈንጠዝ ላይ እያሉ ጅብ ልጁ ሞቶ ሀዘን ተቀምጦ ይመለከታሉ:: ይህን ጊዜ አህዮች ሀዘን መድረስ እንዳለባቸው ይስማማሉ:: አንዷ አህያ ግን ከጅብ ጋር ፍቅር የለንም ጠላቶች ነን አልሄድም ብላ ተነጥላ ትሄዳለች::

ሌሎቹ ሰባቱ አህዮች ለቅሶ ለመድረስ ወደ ጅብ ሄዱ::

ጨለማ ማይፈራ፣ ጉልበቱ ዳገት አይፈራ፣ ጥርሱ አጥንት አይፈራ፣ የአጅሬን ልጅ ሞት ወሰደበት ወይ? ያ አህያ

ማይፈራ ብላ አንዷ አህያ ማስለቀስ ጀመረች::ወዬው ልጄ! አዬ ልጄ! ታሳዝነኛለህ ተርበህ መሞትህ፣ ወዳድል /ትላልቅ/ አህያ እየመጣ ቤትህ:: ብሎ ጅብ ማልቀስ ጀመረ::አህያ መለሰች::አሁን ምን ያደርጋል ምር ንግግር፣እኔ የመጣሁት ፍቅር ልጀምር::የአህያና የጅብ የስነ ቃል ምልልስ እየከረረ

ይሄዳልእንዲህ ያለው ነገር አይመችም ለኛ፣ምን በልቶ ሊያድር ነው ይህ ሁሉ ሀዘንተኛ:: ብሎ

አህዮቹን በሙሉ ሆዳቸውን ዘንጥሎ ገደላቸው:: አቶ አሊ መካሻና አቶ መካሻ እንድሬ ልጆቻቸው ትውፊታቸውን እየዘነጉ መምጣታቸውን ያምናሉ

Page 16: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 16

በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያየምዕራብ ጎጃም ዞን የፍኖተሰላም ከተማ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን ማለትም ሎት 1 ቧንቧና መገጣጠሚያ ሎት 2 የውሃ ቆጣሪ ሎት 3 የኤሌክትሪክ እቃዎች

በድጋሜ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶችን የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ስለዚህ፡-

1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣

3. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ናምበር/ ያላቸው፣

5. የግዥው መጠን ከብር 50 ሺህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ብር 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በውሃ አገልግሎቱ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

7. ተጫራቾች ከ1-5 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

8. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይውላል፡፡ በ15ኛው ቀን 11፡30 ሣጥኑ ይታሸጋል፡፡ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው

ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች ሃሣቡን በአንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላል፡፡

10. በተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማስገባት አይችሉም፣

11. የጨረታ መክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

12. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ከአሸናፊው ጋር ውል እንደተያዘ የጨረታ ማስከበሪያው ይመለሣል፡፡

13. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 ብር ለቧንቧና መገጣጠሚያ ብር 30.00 ለሌሎች ሰነዶች በተመሣሣይ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡

14. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን የሎት እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን

10 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ለፍኖተሰላም ከተማ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት አስይዞ ውል በመፈፀም ያሸነፈበትን እቃ ፍ/ሠ/ከ/ው/ፍ/አገ/ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለበት፡፡

15. ተመሣሣይ የሆኑ እቃዎች በአንድ ምድብ ወይም ሎት በማድረግ ውድድሩ የሚገለፀው በጠቅላላ የድምር ውጤት ነው፡፡

16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

17. በጨረታው መሰረዝ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነትን አይወስድም፡፡

18. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 775 01 56 ወይም 058 775 00 75 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የፍኖተሰላም ከተማ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበምዕ/ጎጃም ዞን የአዴት ከተማ አስተዳደር ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች /በድጋሜ የወጣ/ ሎት 3 ተሽከርካሪ ግዥ ሎት 4 ህንፃ መሣሪያዎች ሎት 5 ህትመት ሎት 6 የጽዳት እቃዎች ሎት 7 የመኪና ጎማ ሎት 8 የደንብ ልብስ የተዘጋጁ ሎት 9 የደንብ ልብስ ብትን ሎት 10 የደንብ ልብስ ጫማ ሎት 11 የቤትና የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ያላቸው፣

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ እና ከ50 ሺህ ብር በላይ የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው መረጃ የሚያቀርቡና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

5. የእቃውን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

6. የጨረታ ሰነዱ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በአዴት ከተማ አስተዳደር ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 20 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቶች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

8. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

9. ጽ/ቤቱ እንደሁኔታው አይቶ 20 በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

10. የዋጋ መሙያ ፎርሙን በመሙላት በፖስታ በማሸግ በአዴት ከተማ አስ/ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በግዥና ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን በ16ኛው ቀን እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በ16ኛው ቀን 3፡00 ይታሸጋል፡፡ 3፡30 ይከፈታል፡፡12. በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ቢኖረውና ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆን መስሪያ ቤቱ አያስተናግድም፡፡ አሸናፊው የሚለየው በእያንዳንዱ እቃ ዝርዝር በጠቅላላ ድምር በሎት ይሆናል፡፡ በመሆኑም ዋጋ

ለይቶ መሙላት አይቻልም፡፡13. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0918022064 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

15. አሸናፊዎች የአሸነፉትን እቃ በአዴት ከ/አስ/ግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 20 ማቅረብ አለባቸው፡፡

16. መስሪያ ቤቱ የሚቀርቡትን እቃዎች ጥራቱን በባለሙያ አረጋግጦ የሚረከብ ይሆናል፡፡

የአዴት ከተማ አስ/የገ/አካ/ል/ጽ/ቤት

Page 17: 12 03 2009.pdf

ገጽ 17በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. ለወጣቶች

በአንድ ዓመት ከ100 ሺህ ብር በላይ ገቢ

ተገኘበኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደዋ ጨፋ

ወረዳ በእንስሳት ማድለብ ስራ የተሰማሩ ወጣቶች ገቢያቸውን ለማሳደግ ጠንክረው እየሰሩ መሆናቸው ተናገሩ::

በእንስሳት ማድለብ እና እርባታ ስራ ተሰማርተው የተሻለ ገቢ እያገኙ ካሉት መካከል በወረዳው በበተረፍ ቀበሌ ከብት በማድለብ ስራ የተሰማሩ ወጣቶች ይገኙበታል::

የሀረንገሞ ከብት አድላቢዎች ማህበር ሊቀመንበር ወጣት መሀመድ አሊ ከአምስት ጓደኞቹ ጋር በመተባበር ከመስከረም 2008 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጿል:: ወጣቶቹ መነሻ ካፒታል ከወረዳው አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም /አብቁተ/ 60 ሺህ ብር ወስደው ከብት በማድለብ ስራ በመሰማራት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺህ ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን ወጣቱ ተናግሯል::

ወጣቱ እንደሚለው አባላት በጋራ ገንዘባቸውን በመቆጠብ በቀጣይ የእህል ወፍጮ ለመንገዛት በዝግጅት ላይ ናቸው:: በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ሌሎች 10 በሬዎችን በማድለብ የተሻለ ገቢ ለማግኘት እየሰሩ መሆናቸው ተናግሯል::

ሌላው የማህበሩ አባል ወጣት ሁሴን ሙሀመድ በበኩሉ ከስደት ተመልሶ የከብት ማድለቡን ስራ ከጀመረ ወዲህ ራሱን እና ቤተሰቡን በአግባቡ እያስተዳደረ መሆኑን ተናግሯል::

የወረዳው እንስሳት ሀብት ተጠሪ ጽ/ቤት ተወካይ ሀላፊ አቶ ሰኢድ ተስፋዬ እንደተናገሩት ጽ/ቤቱ ከብት በማድለብ ስራ ለተሰማሩ የወረዳው ወጣቶች የእንስሳት ህክምና አገልግሎት በቀበሌያቸው እንዲያገኙ እያመቻቸ ነው::

ሪፖርተራችን አበዱ እንድሪስ እንደዘገበው በደዋ ጨፋ ወረዳ ከሁለት ሺህ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች በከብት ማድለበ እና በዶሮ እርባታ ስራ ተሰማርተዋል::

ከዚህም ከዚያም

ፀጋዬ የሺዋስ

በግብርናው ዘርፍ ከስድስት ሺህ በላይ ወጣቶችን የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን በደቡብ ጎንደር ዞን የደራ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ገለፀ::

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ጀማል ዑመር እንደተናገሩት ጽ/ቤቱ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከሚያደርገው ርብርብ ጎን ለጎን በተያዘው በጀት ዓመት በግብርናው ዘርፍ ባሉት የስራ አማራጮች ስድስት ሺህ 600 ወጣቶች በግብርና ተቋሙ ብቻ የስራ እድል ለመፍጠር አቅዶ ወደ ስራ ገብቷል::

ባለፈው የበጀት ዓመት ሁለት ሺህ 400 ወጣቶች በተቋሙ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው መጠቀም መጀመራቸውን አቶ ጀማል ገልፀዋል:: በዘንድሮው ዓመትም መሬት አልባ ወጣቶችን በመለየት በሰብል ልማት፣ በፍራፍሬ ችግኝ ዝግጅት፣ በለሙ ቦረቦራማና ተራራማ ስፍራዎች በቋሚ የፍራፍሬ ልማት ማሳተፍና በእንስሳት ርባታ በማደራጀት በዘላቂነት ተጠቃሚ ለማድረግ ወደ ስራ ገብቷል ብለዋል::

በጽ/ቤቱ ለወጣቶች በግብርናው ዘርፍ የስራ እድል ለመፍጠር ከታቀደው የስራ እድል ባሻገር ባለፈው ዓመት በተቋሙ የተደራጁ ወጣቶች ያሉባቸውን ችግሮች ለመለየት ከብድር ጀምሮ የቁጠባ ባህላቸውን አሳድገዋል::

በወረዳው ወንጨት ቀበሌ ችግኞችን ሲንከባከቡ ያገኘናቸው ወጣት አገሬ ይታየውና ሰንደቁ አምላኩ እንዳሉት እነርሱን ጨምሮ 61 ወጣቶች ተደራጅተው በተሰጣቸው መሬት ላይ ስራ ጀምረዋል:: በቀጣይ ከፍራፍሬ ልማቱ ጎን ለጎን ተጓዳኝ ስራዎችን በመስራት ለመለወጥ ተነሳሽነትን እንደፈጠረላቸውም ወጣቶቹ አስተያየታቸውን ለወረዳው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ሰጥተዋል::

በቀበሌው በችግኝ ዝግጅት ስራ ከተሰማሩት ወጣቶች መካከል ወጣት ሰጤ በበኩሉ ከ12 ጓደኞቹ ጋር በመሆን በችግኝ ማፍላት የስራ ዘርፍ በመሰማራቱ ባለፈው የክረምት ወቅት ብቻ ከ90 ሺህ ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናግሯል::

ከ6 ሺህ በላይ ወጣቶች በልማት

ስራ መሠማራታቸው ተገለፀ

ወደ ገጽ 28 ዞሯል

ፈቃዱ መንግሥቱና ጓደኞቹ በተማሩበት የትምህርት መስክ ተደራጅተው እየሰሩ ነው

ፈቃዱ መንግሥቱና ጓደኞቹ በደሴ ከተማ በኬብል ዝርጋታ የሽርክና ማህበር

መስርተው ድህነትን ለማሸነፍ በትጋት እየሰሩ የሚገኙ ወጣቶች ናቸው:: የሽርክና ማህበሩ አባላት ሁሉም ከወይዘሮ ስሂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በኬብል ዝርጋታ እስከ “ሌብል” አራት ተምረው የተመረቁ ናቸው:: ይህ መሆኑ ደግሞ ስራውን አውቆና አቀላጥፎ ለመስራት አግዟቸዋል::

ይሁን እንጅ፤ ወጣቶቹ ከተደራጁ በኋላ በቀጥታ ወደ ስራ አልገቡም:: ስድስት ወራት ያለ ስራ ለመቀመጥ ተገደው እንደነበር ያስታውሳሉ፤ አሁን ግን ስራ ጀምረዋል:: እኛ ስናገኛቸው እየዘረጉት የነበረ የስልክ መስመር /ኬብል/ ሁለተኛ ስራቸው ነው::

ማህበራቸው ከኢቲዮቴሌኮም ጋር ውል በመፈራረም ነው ስራውን እየሰራ የሚገኘው:: አባላት በየወሩ ከሁለት ሺህ ብር በላይ ደመወዝ ያገኛሉ:: ከሚያገኙት ገንዘብ ውስጥም 15 በመቶ ያህሉን ይቆጥባሉ:: ማህበራቸው ከደሴ ከተማ ባሻገር በሌሎች ከተሞችም እየተንቀሳቀሰ ስራ የመስራት እቅድ ይዟል::

ፍሬህይወት አረጋ የሽርክና ማህበሩ አባልና ገንዘብ ያዥ ናት:: ስራውን ለማቀላጠፍ የቀን ሰራተኛም ቀጥረው እንደሚያሰሩ ገልፃለች:: ማህበራቸው ከተደራጀ በኋላ የንግድ ፍቃድ ለማውጣት ትልቅ ችግር ገጥሞት እንደነበር ተናግራለች:: የከተማው ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ግን በቻለው መጠን እገዛ እንዳደረገላቸው አጫውታናለች::

አቶ ሲሳይ መሰለ በደሴ ከተማ ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች መምሪያ የኮንስትራክሽን ኦፊሰር ናቸው:: ወጣቶችን በተማሩበት የሙያ መስክ በማደራጀት የተግባርና የክህሎት ስልጠና በመስጠት ህጋዊ እውቅና እንዲያገኙ ይደረጋል ይላሉ:: ህጋዊ ከሆኑ በኋላም ወደ ስራ እንዲገቡና በትክክል ስራቸውን እንዲሰሩ ቁጥጥር እንደሚደረግ ገልፀዋል:: ስራ ከጀመሩ በኋላ ካላቸው ገቢ ላይ ከ20 እስከ 30 በመቶ እንዲቆጥቡ እንደሚደረግም ተናግረዋል::

ማህበራቱ እየተጠናከሩ መጥተው በቋሚነት መስራት ከሚችሉበት ደረጃ እንዲደርሱ እንደሚያደርጉም አስረድተዋል:: በከተማው በኬብል ዝርጋታ 32 ኢንተርፕራይዞች መኖራቸውንም አቶ ሲሳይ ገልፀዋል:: በፋይበር ዝርጋታ፣ በጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍና በሌሎችም የግንባታ ዛፎች ከ300 በላይ ወጣቶች ተደራጅተው እየሰሩ መሆኑንም ጠቁመዋል::

እስማኤል ማህመድ በከተማዋ በጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ ላይ የተሰማራ ማህበር አባል ነው:: ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በሰርቬይንግ ተመርቋል:: ተደራጅተው ወደ ስራ ሲገቡ ስልጠና ማግኘታቸውንና የከተማው ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ እገዛ እንዳደረገላቸው ገልጿል::

እስማኤል ይህንን ስራ ከጀመረ ወራት ተቆጥረዋል:: እሱ በዚሁ መንገድ የእለት ጉርሱን መሸፈን ቢችልም በርካታ ጓደኞቹ ግን የሚሰሩት በማጣት ያለ ስራ ተቀምጠው እንደሚውሉ

ታዝቧል:: እሱ ይሄንን እድል እንደ አጋጣሚና እንደ እድል ሆኖ እንዳገኘው ተናግሯል:: ለምሳሌ እሱ ሊመዝገብ ወደ ቀበሌ ሲያመራ “ሞልቷል” ተብሎ እንደነበርና ከብዙ እንግልት በኋላ እንደተመዘገበ ያስታውሳል:: በዛ ላይ በተማሩበት የትምህርት መስክ ለመደራጀት ቢፈልጉም ላይፈቀድላቸው የሚችልበት አሰራር መኖሩን ተመልክቷል::

ኑሩ ታደሰ ወደ እነ እስማኤል መንደር ባቀናሁበት ጊዜ ያገኘሁት ወጣት ነው:: ከወይዘሮ ስሂን ፖሊቲክኒክ ኮሌጅ በሰርቬይንግ ከሁለት ዓመታት በፊት የተመረቀ ቢሆንም እስካሁን ስራ መስራት አልጀመረም:: እንደ አንዳንድ ጓደኞቹ ለመደራጀት ፈልጐ ወደ ቀበሌ ሊመዘገብ ቢሄድም “ቀኑ አልፏል” እየተባለ መደራጀት አልቻለም:: ነገር ግን ወጣቶች እንዲደራጁ ሲወሰን መረጃው በቀላሉ እንደማይገኝ

አዝጋሚው ጉዞ

ተናግሯል:: የቀበሌዎች አሰራር ግልጽነት የጎደለው በመሆኑ እንደሱ ሁሉ በርካታ ወጣቶች ያለስራ መቀመጣቸውን ገልጿል::

አቶ ደመቀ ቦሩ የደሴ ከተማ ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ኃላፊ ናቸው:: እንደ እርሳቸው ማብራሪያ መምሪያው በ2008 ዓ.ም 19 ሺህ የስራ እድል ለመፍጠር እቅድ ይዞ በዓመቱ መጨረሻ ዘጠኝ ሺህ ያህል የስራ እድል ብቻ ነበር መፍጠር የቻለው:: ይህ ማለት ከእቅዱ አንፃር ዝቅተኛ የሚባል አፈፃፀም መሆኑን አቶ ደመቀ ያምናሉ:: ለዚህም ምክንያቱ ትኩረት አድርገው የሰሩባቸው እድገት ተኮር የሚባሉና ከምርት/ማኑፋክቸሪንግ/ ጋር የተያያዙ ስራዎችን ለመስራት ጥረት በማድረጋቸው መሆኑን ገልፀዋል::

Page 18: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 18 ከተማ ልማትከአብክመ ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ጋር በመተባበር የቀረበ

ወደ ገጽ 42 ዞሯል

አብርሃም በዕውቀት

በግራ በኩል የቆሙት አዳዲስ መተከል የጀመሩት የመካከለኛ ኪሎ ቮልት ተሸካሚ የኮንክሪት ምሰሶዎች

ባሕር ዳር

ልታሰናብት ነውየመብራት ችግሯን

በባሕር ዳር ከተማ ለዓመታት ኖሬያለሁ፤ የመብራት ጉዳይ አሳሳቢ ከሚባልበት ደረጃ ላይ ይገኛል:: መብራት ያልጠፋበትን ወር አላስታውስም፤ ምናልባት ያልጠፋበት ሳምንት ይኖር ይሆናል:: በተለይ በክረምት ወራት ሰማዩ ጠቋቁሮ ነጎድጓዱ ከርቀት ብልጭ ሲል የባሕር ዳር መብራት ዓይኑን ይጨፍናል፤ በዚያ ላይ ጨዋታ እንዳታለለው የተላከ ልጅ ከሄደ ቶሎ አይመለስም:: በዚህ የተነሳ ነዋሪዎችን ክፉኛ ሲያማርር ኖሯል::

እናቶች ማቀዝቀዣ (ፍሪጅ) ውስጥ ያስቀመጡት የልጆቻቸው ወተት እርጎ ሆኖ ሲጠብቃቸው፣ ያቀጠኑትን ሊጥ ሊጋግሩ ምጣዱን ማሞቅ ሲጀምሩ እልም ሲል፣ የእንጨትና ብረታ ብረት ቤቶች ለደንበኞቻቸው የታዘዙትን ዕቃ በተዋዋሉበት ቀን አጠናቅቀው ለማስረከብ ተፍ ተፍ ሲሉ ድንገት መብራት እልም ሲል፣ … ቆሽታቸው ድብን እያለ ለጨጓራ ሕመም የሚጋለጡትን ቤት ይቁጠራቸው:: ነዋሪዎች ምግባቸውን በኤሌክትሪክ ኃይል ማብሰል ቢፈልጉም ድንገት መብራት እልም እያለ ተስፋ ስላስቆረጣቸው ወደ ቀደመው የማገዶ እንጨት ተመልሰው በጭስ መጨናበስ ጀምረዋል::

በሌላም በኩል ትራንስፎርመሮች “ከአቅማቸው በላይ ሆኗል” በሚል ምክንያት አዳዲስ ኃይል ፈላጊዎች እንደልብ አይስተናገዱም:: እነዚህ ሁሉ እሮሮዎች ግን እስከወዲያኛው ሊዘጉ ይመስላሉ::

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሁሉን አቀፍ ኤሌክትሪክ ተደራሽነት ዘርፍ የስምንት ትላልቅ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኔትወርክ ማስፋፊያና ማጠናከሪያ ፕሮጀክት የባሕር ዳር ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ግርማ አምሳሉ እንደተናገሩት በ18 ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ በተጀመረው የባሕር ዳር ከተማን የኤሌክትሪክ ስርጭት የማዘመን ሥራ በርካታ የመብራት ችግሮችን ያስወግዳል:: ፕሮጀክቱ በሐምሌ ወር 2008 ዓ.ም የባሕር ዳር ሥራውን የጀመረ ሲሆን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም አቶ ግርማ ተናግረዋል::

ከአቶ ግርማ እንደተረዳነው በተጀመረው ፕሮጀክት የባሕር ዳር ከተማ ነባር ባለ15ሺህ ኪሎ ቮልት መስመሮች በአዲስ ይተካሉ፤ ከንዑስ ማሠራጫው (ሰብስቴሽን) በኩልም ኃይል በአምስት አቅጣጫ እንዲወጣ ይደረጋል:: ከአንድ ንዑስ ማሠራጫ ላይ ይደረግ የነበረው የመቆጣጠር ተግባርም ወደ ስድስት ንዑሳን መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች (ስዊችንግ ስቴሽንስ) ይከፈላል:: በአምስት አቅጣጫ የሚወጣው ኃይልም በቀለበት ቅርፅ (ሪንግ ሲስተም) እንዲገናኝ ይደረጋል:: ይህም ከአንደኛው መስመር ኃይል ሲቋረጥ ከሌላኛው መስመር በማግኘት ሕብረተሰቡ እንዳይቸገር

ማድረግ ያስችላል ተብሏል:: ስድስቱ ንዑሳን ማሰራጫዎችም የየራሳቸው

የሆነ “አውቶሪክሎዠርና ካፓሲተር/የኃይል ባንክ” ይኖራቸዋል:: አውቶሪክሎዠሩ ኃይል በሰው ሠራሽ ወይም በተፈጥሮ ምክንያት በሚቋረጥበት ጊዜ ችግሩን በራሱ ለማስወገድ ይሞክራል፤ይህ የማይሆንለት ከሆነ ደግሞ ችግሩን ባሕር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ግቢ ውስጥ የሚገነባ

መቆጣጠሪያ ማዕከል(ስካዳ) ያሳውቃል:: የስካዳ ማዕከሉ እያንዳንዱን ትራንስፎርመር፣ ቆጣሪና ምሰሶ እንዲሁም ገመድ ሁኔታ የሚከታተልና መረጃ የሚሰጥ በሰለጠኑ ባለሙያዎች ክትትል የሚደረግበት ክፍል ነው:: የኃይል ባንኩ ደግሞ የኃይል እጥረት በሚያጋጥምበት ጊዜ የቮልቴጅ ምጣኔውን ከፍ በማድረግ እጥረቱን የሚከላከል ነው::

አቶ ግርማ እንዳሉት አዲስ የሚዘረጉት የኤሌክትሪክ መስመሮችም ሙሉ በሙሉ በፕላስቲክ ስለሚሸፈኑ በአየር ላይና በመሬት ውስጥ የሚዘረጉት ዝናብ በመጣ ቁጥርና በዛፍ ንክኪ ችግር የማይፈጠርባቸው ናቸው:: የሚተከሉት ምሰሶዎችም ሙሉ በሙሉ የኮንክሪት ስለሚሆኑ የመበስበስና የመውደቅ ችግር አይገጥማቸውም:: ወደ መሸንቲ፣ ዘንዘልማ፣ ጭስ ዓባይና ዘጌ በሚሄዱ መስመሮች ላይ የሚፈጠረው የመብራት መቋረጥም ከእንግዲህ እንደማይኖር አቶ ግርማ ነግረውናል::

የኤሌክትሪክ መስመሮችን በመሬት ውስጥ ለመዘርጋት የአስፓልት መንገዶችን መቁረጥና መቆፈርም ቀርቷል፤ አዲስ በሚዘረጉት መስመሮች አስፓልት መንገድን ማቋረጥ ካስፈለገ በስር ቦርቡሮ ገመዱን ማሳለፍ የሚችሉ መሳሪያዎች በፕሮጀክቱ መምጣታቸውንም አቶ ግርማ ተናግረዋል::

በአጠቃላይ በባሕር ዳር ከተማ ባለ15ሺህ ኪሎ ቮልት 81 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መስመር እንደአዲስ ይዘረጋልም ብለዋል:: በባለዝቅተኛ ቮልቴጅ ደግሞ ለቀጣይ 10 ዓመታት የሚኖረውን የኃይል ፍሰት ሊሸከሙ በሚችል መልኩ ወደ 43 ቦታዎች ላይ ያሉ ትራንስፎርመሮች አንድም በአዲስና ዘመናዊ ትራንስርመሮች ይተካሉ፤ አልያም እንደ አዲስ እንደሚተከሉ አቶ ግርማ ተናግረዋል::

አዲስ የሚዘረጉት ዝቅተኛ ቮልቴጅ ተሸካሚ መስመሮችም በኮንክሪት ምሰሶ ሆነው ገመዶቹ ሙሉ በሙሉ በፕላስቲክ የተሸፈኑ ይሆናሉ:: ወደየቤቱ መብራት ለማስገባትም ገመድ እየላጡ ምሰሶዎቹ ላይ ማያያዝ አያስፈልግም፤ ከምሰሶዎቹ ላይ በሚገጠመው “ኮል ቶፕ ቦክስ” አማካኝነት ገመዶቹ በቀጥታ ተሰክተው ኃይል ወደቤት የሚያስተላልፉበት ዘመናዊ አሠራር እንደሚኖር ነው አቶ ግርማ ያስረዱን::

በጣም ብዙዎችን የመብራት ደንበኞች የሚያስመርረው ጉዳይ የመብራት ብልሽት ሲያጋጥም ስልክ ደውሎ ለማስመዝገብ ሲሞከር ያለመነሳት ችግር በአዲሱ ፕሮጀክት እስከወዲያኛው ይዘጋል ተብሏል:: ባገኘነው መረጃ መሠረት በአዲሱ ፕሮጀክት ውስጥ በስካዳ ግቢው “ትራቭል ኮል ማኔጅመንት” የሚባል ማዕከል ይኖራል:: ማዕከሉ በቀጥታ ከቴሌኮም ጋር የሚገናኝ ሆኖ ደንበኞች ስልክ ሲደውሉ በቀጥታ አንስቶ መልዕክታቸውን ቀርፆ ያስቀምጣል:: በየትኛው መስመርና ቆጣሪ ላይ ችግሩ እንደተከሰተም ይመዘግባል፤ ለሚመለከተው አካልም ያሳውቃል:: የሚመለከተው አካል ጥሪው የተመዘገበበትን ቀን፣ ደቂቃና ሰከንድ በማየት ለማን መቼና ምን ዓይነት ምላሽ እንደተሰጠም መረዳት ይችላል ብለዋል::

ለምሰሶ መትከያ በሚቆፈሩ ጉድጓዶች ውስጥ ነባር የስልክና የውኃ መስመሮች መገኘት ለሥራው ችግር ሆኗል

Page 19: 12 03 2009.pdf

ገጽ 19በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ከዓለም አካባቢ

አጫጭር ዜናዎች

አል አሳድ በትራምፕ ላይ ተስፋ አድርገዋል

ወደ ገጽ 26 ዞሯል

ወደ ገጽ 36 ዞሯል

አብርሃም አዳሙ

(አብርሃም አዳሙ)

ቢቢሲ በ11 ቋንቋዎች ተጨማሪ

ስርጭት ሊጀምር ነው

የሶሪያው መሪ በሽር አልአሳድ አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሃገራቸው ያለውን ብጥብጥ ለማስቆም የፀረ ሽብር ዘመቻው ተባባሪ ይሆናሉ ብለው ተስፋ ማድረጋቸውን ተናገሩ::

ትራምፕ በተደጋጋሚ ስለሽብር ያላቸውን ጥላቻ መግለፃቸውን ተከትሎ ዘመቻውን ይቀላቀላሉ ብለው እንደገመቱ የሶሪያው መሪ ገልፀዋል:: ነገር ግን ቁርጠኝነታቸው ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ተናግረዋል::

ዶናልድ ትራምፕ በሶርያ አማጽያን ላይ እና በአይ ኤስ የሽብር ቡድን የመረረ ጥላቻ እንዳላቸው የሚታወስ ነው:: ሶርያን መዋጋትም ሩስያን መዋጋት ሊያስከትል ይችላል ብለዋል::

የሶሪያ የእርስ በእርስ ግጭት ከተጀመረበት ከፈረንጇቿ 2011 ጀምሮ እስካሁን 300 ሺህ ዜጐች መሞታቸውን ቢቢሲ አስታውሷል::

የትራምፕ መንገድና የአፍሪካ እጣ ፈንታ

በመጭው ጥር 20 ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁትና 45ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆናቸውን በደጋፊዎቻቸው ድምጽ ያረጋገጡት ዶናልድ ትራምፕ በቅድመ ምርጫውና በምርጫው ሂደት እጅግ አወዛጋቢ ሆነው ቆይተዋል:: ግምቶችን ሁሉ አክሽፈው ህልማቸውን ያሳኩት ትራምፕ በተለይም በማይጠነቀቁለት ንግግራቸው፣ በስብዕናቸውና በፖሊሲያቸው ዓለምን እንደ ወንዝ ዳር ዛፍ ሲያወዛውዙት ከርመዋል::

የትራምፕ ወደ ስልጣን መምጣት ከአሜሪካውያኑ ጀምሮ እስከ መላው ዓለም ድረስ የተደባለቀ ስሜትን ፈጥሯል:: ከስጋት እስከ ተቃውሞ፣ ከሙገሳ እስከ ተስፋ የደረሱ የስሜትና የአቋም ልዩነቶች ተንፀባርቀዋል:: ፑቲንና አሳድ ሰውየውን ተስፋ ጥለውባቸዋል፤ ምዕራባውያኑ ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደ አፍሪካ ያሉቱ ደግሞ ስጋት ገብቷቸዋል:: ለመሆኑ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መፃዒ የስልጣን ዘመን አፍሪካን ምን ያሰጋታል? አፍሪካና ትራምፕ የወደፊት መንገዳቸው ያምር ወይስ ያደናግር? ለዚህ ምላሽ ይሆን ዘንድ ተንታኞች ከዋና ዋና ጉዳዮች አንፃር ያስቀመጧቸውን የትንበያ መረጃዎች እንመልከት::

የተቀዛቀዘ የምጣኔ ሃብት ዕድገትየአፍሪካ የምጣኔ ሃብት ጉዞ ከማሽቆልቆል

ተላቅቆ ወደ ፈጣን የዕድገት ሂደት ለመሸጋገር በትንቅንቅ ላይ ያለ ነው:: የትራምፕ ወደ ስልጣን መምጣት ግን ይህንን የተቀጣጠለ የለውጥ ሂደት ውሃ እንዳይቸልሰው ያሰጋናል የሚሉ አልጠፋም::

የኢኮኖሚ ተንታኙ ፖል ክሩግማን የዚህ ስጋት ተጋሪ ናቸው:: "ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ስለ ነፃ ንግድና ግንኙነት ያሳዩት የመረረ ወቀሳ እንዲሁም ጥላቻ ወደ ተግባር የሚቀየር ከሆነ ማብቂያ የሌለው ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ድቀት መምጣቱ አይቀሬ ነው" ይላሉ:: በተለይ ደግሞ ለአፍሪካ ተጽዕኖው የከፋ ሊሆን ይችላል ባይ ናቸው:: አፍሪካ በክሊንተንና በኦባማ ዘመን የግብርና ምርቶቿን ከቀረጥ ነፃ ወደ አሜሪካ የምትልክበት የአገዋ ድልድይ እንደተባለው በትራምፕ የሚሰበር ከሆነ አፍሪካ ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኪሳራ እንደሚደርስባት የኢኮኖሚ ተንታኙ ተናግረዋል:: ትራምፕ ለቻይና ብለው የከፈቱት የንግድ ጦርነት ለአፍሪካና ለሌሎች ታዳጊ ሃገራት ሊተርፍም እንደሚችል ሥጋት አላቸው::

የዶናልድ ትራምፕ የማሸነፍ ዜናን ተከትሎ በእስያ፣ በአውሮፓና በተለያዩ ዓለም አቀፍ የንግድ ተቋማት ላይ መቀዛቀዝ ታይቷል:: በደቡብ አፍሪካ የደህንነት ጥናት ተቋም ሊቀመንበር ጃኪ ሲሊየር ግን በስጋቱ አይስማሙም:: "ለራስ ነገር ቅድሚያ መስጠት ከአንድ መሪ የሚጠበቅ ነው:: ትራምፕም ያደረጉት ያንን ነው:: በእኔ እይታ እኛ በእርሱ የጥላቻ

ራዳር ውስጥ አይደለንም:: እንዲያውም መልካም ጠባቂያችን ይመስለኛል" ብለዋል::

አምባገነንነትን ማበረታታትበብዙዎች እይታ ከሆነ የትራምፕ የአመራር

ቅኝት በሳዳም ሁሴንና በፑቲን ፍቅር የወደቀ ነው ሲሉ ይተቹታል:: የእርሳቸውን ግለ- ስብዕና ከወደፊት የመሪነት ዘመናቸው ጋር በማስተሳሰርም "አምባገነንነት ይታይባቸዋል" የሚል ስጋት ተንፀባርቋል:: ይህ ስሜት ወደ አፍሪካም ተዛምቷል:: በተለይም የእርሳቸው የአሸናፊነት ዜና በተሰማበት ቅጽበት ውስጥ ለዘመናት የኡጋንዳን ስልጣን የሙጥኝ ያሉት ዮዌሪ ሙሴቬኒና አምባገነን ናቸው የሚባሉት የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ፔየር ንኩሩንዚዛ ለትራምፕ የላኩት 'የእንኳን ደስ ያለህ!' መልዕክት የብዙዎችን እይታ ሰቧል:: አንዳንዶቹ ሁኔታውን ከተማጽኖ አይን ሲመለከቱት በአንፃሩ ግን የትራምፕ ፕሬዝዳንት ሆኖ መመረጥ ለአምባገነን መሪዎች የልብ ልብ ሳይሰጣቸው እንዳልቀረ ገምተዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትራምፕ አሸባሪዎችን ብቻ ሳይሆን የአሸባሪ ቤተሰቦችንም ከመቅጣት ወደ ኋላ እንደማይሉ መናገራቸው ሳያበቃ

ከፍተኛ ተደማጭነትና ሽፋን ያለው የብሪቲሽ ብሮድ ካስት ሰርቪስ (ቢቢሲ) ዓለም አቀፍ አገልግሎት ከፈረንጆቹ 1940 ወዲህ ትልቅ የተባለውን የማስፋፊያ ስራ ተከትሎ በ11 ተጨማሪ አለም አቀፍ ቋንቋዎች ስርጭት አንደሚጀምር አስታወቀ::

ኬንያ የካምፑን መዝጊያ ጊዜ አራዘመችበኬንያ የሚገኘው ግዙፉ የስደተኞች መጠለያ (ዳዳብ) ለመጭዎቹ

ስድስት ወራት ሳይዘጋ እንደሚቆይ የኬንያ መንግስት አስታወቀ:: የዓለማችን ትልቁ መጠለያ የሆነው ዳዳብ ከ300 ሺህ በላይ

ሶማሊያውያንን የያዘ ሲሆን የኬንያ መንግስት በተደጋጋሚ ካምፑን ለመዝጋት መርሃ ግብር ሲያወጣ ቆይቷል:: ነገር ግን በዚህ ወር ይዘጋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የስደተኞች መጠለያ ለተጨማሪ ስድስት ወራት መራዘሙ ታውቋል::

ኬንያ ለስደተኞቹ መቋቋሚያ የሚሆን በቂ እርዳታ እስኪገኝ ድረስ ጊዜውን ለማራዘም መወሰኗን አስታውቃለች::

ጣቢያው ስርጭት ከሚጀምርባቸው ቋንቋዎች ውስጥ ሶስቱ በኢትዮጵያ የሚነገሩ እንደሆኑ አስታውቋል:: ጣቢያው አዲሱን ማስፋፊያ ያደረገው ከእንግሊዝ መንግስት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ነው:: “ይህ በቢቢሲ ታሪክ ትልቁ ቀን ነው” ያሉት የጣቢያው ዳይሬክተር ጀኔራል ቶኒ ሃል “ቢቢሲ ለእንግሊዛውያን የዘውዱ ፈርጥ ነው!” ብለውታል::

ለአዲሱ ማስፋፊያ 289 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የተመደበ ሲሆን በአዲስ የሚጀመሩ የቴሌቪዥን፣ የሬዲዮና የዲጂታል ሚዲያ አገልግሎቶች ይውላል:: በጣቢያው በአረብኛና በሩስያ ቋንቋ ተጨማሪ የቴሌቪዥን ስርጭት ይኖራል ተብሏል::

በመጪው የፈረንጆች ዓመት ተግባራዊ ሊደረግ በታሰበው በዚህ ማስፋፊያ አማርኛ፣ ኦሮምኛና ትግርኛ ቋንቋዎች ተካትተዋል:: ከ11ዱ አዳዲስ ቋንቋዎች ውስጥም ስድስቱ በአፍሪካ የሚነገሩ ሲሆን ቀሪዎቹ በእስያ የሚገኙ ናቸው::

ቢቢሲ በአዲሱ ማስፋፊያው አንድ ሺህ 300 አዲስ ስራ ይፈጥራል ተብሎ ሲጠበቅ 12 የቴሎቪዥን ጣቢያ፣ 40 የስርጭት ቋንቋና 500 ሚሊዮን ተመልካች ህዝብ ይኖረዋል ተብሏል::

Page 20: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 20

ነዋሪዎች በመጠጥ...ከገፅ 1 የዞረ

የእግረኞች ጥንቃቄ...ከገፅ 1 የዞረ

ደብረ ብርሃን፡- ...

ከገፅ 1 የዞረ

በበኩላቸው ፋብሪካውን በሌሎች አካባቢዎች ለማቋቋም ከፍተኛ ጥረት ተደርጎ እንደነበር ይገልፃሉ፤ ነገር ግን በብዙ ችግሮች ምክንያት ሳይሳካ ቆይቷል:: በደብረ ብርሃን ከተማ ያለው ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ የኩባንያውን ትኩረት እንደሳበው የተናገሩት አቶ ሙሉጌታ ከተማዋ እያደገች መሆኗ፣ የቦታ አከላሉ ለኢንቨስትመንት ምቹ መሆኑ እንዲሁም የአገልግሎት አሠጣጣቸው ቀልጣፋ መሆኑ ፋብሪካው ወደ ደብረ ብርሃን እንዲመጣ ምክንያት ሆኗል ::

የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪው አቶ ቅጣው ማሞም ከቅርብ አመታት ወዲህ ደብረ ብርሃን በፈጣን ለውጥ ላይ መሆኗን መስክረዋል፤ የተገነቡት ትልልቅና ዘመናዊ ህንፃዎች እንዲሁም ፋብሪካዎች ብዙ ህዝብ ወደ ከተማዋ እንዲገባ፣ የንግድ እንቅስቃሴውም እንዲስፋፋ አድርጓል፡፡ ወደፊት የተያዙ ትላልቅ የኢንቨስትመንት ኘሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ደግሞ ብዙ የሠው ኃይል በመያዝ የከተማዋን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ይሆናል

ብለው ተስፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል::የከተማ አስተዳደሩ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ

የሥራ ሂደት መሪ የሆኑት አቶ ሽፈራው ማሞ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት 14 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 337 ባለሀብቶች ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ ገብተዋል:: ከዚህም ውስጥ 13 ቢሊዮን የሚሆነው ካፒታል በአምራች ዘርፍ መያዙን ገልጸዋል:: "እስካሁን 345 ሄ/ር መሬት ለባለሃብቶች ተሰጥቷል" ያሉት አቶ ሽፈራው ኘሮጀክቶቹ መሉ ለሙሉ ወደ ስራ ሲገቡ ከ21 ሺህ በላይ ሊሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል:: እስካሁንም 15 ሺህ ለሚሆኑ ዜጐች የስራ ዕድል መፈጠሩን ጠቁመዋል:: "ከተማዋ ተመራጭ መዳረሻ እየሆነች ነው:: የኢንቨስትመንት ፍሠቱ በፍጥነት እያደገ ነው:: በ3 ወር ጊዜ ውስጥ እንኳ 60 ባለሃብቶችን አስተናግደናል” ብለዋል::

ወደፊትም ያሉ ችግሮችን በመፍታት ከተማዋን የኢንዲስትሪ ከተማ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል::

እንተገብረዋለን:: አስፓልቱን ስናቋርጥም ነጭ ቀለም በተሰመረልን በኩል ነው፤ ከዚያ ውጭ መንገድ አናቋርጥም፤ መንገዱ አስፓልት ካልሆነ ግን ምልክት ስለማይኖረው መኪና አለመኖሩን እያየን እንሻገራለን” ብለዋል::

በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማረጋገጫ ዋና የሥራ ሂደት መሪ ኮማንደር

ዋለልኝ ዳኛው ደግሞ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ላይ ለውጥ የመጣው በከፍተኛ ጥረት መሆኑን ገልጸዋል፤ ተሞክሮው ወደ ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ተስፋፍቶ ለውጦች መምጣታቸውን ተናግረዋል::

(ዝርዝር ዘገባ በገፅ 8 ይዘናል)

አብስለው የሚበሉበት ውኃ እያጡ እንደሚቸገሩም ጠቁመዋል::

በግቢያቸው ቧንቧ አስገብተው ውሀ ለማግኘት ቢጥሩም በቧንባው ውኃ ስለማይመጣ በየወሩ ለቆጣሪ ኪራይ ከመክፈል ውጭ ችግራቸውን ሊያቃልላቸው እንዳልቻለ ወ/ሮ ሙሉ ተናግረዋል:: ችግሩን ለማቃለልም የጋራ ውሃ መቅጃ ቦታ(ቦኖ) ሄደው ረጅም ስዓት ወረፋ ጠብቀው እንደሚቀዱ ገልጸዋል፤ የሚመለከታቸው አካላት ችግሩን ተመልክተው አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈልጉላቸውም ወ/ሮ ሙሉ ተናግረዋል::

የአጅባር ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልገሎት ጽህፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀይሌ ገናናው

ከተማዋ ተራማ የተባለ አንድ የውኃ መገኛ ምንጭ ብቻ እንዳለው ጠቁመዋል:: ምንጩ በ2000 ዓ.ም ተገንብቶ ሲጠናቀቅ በሰኮንድ ስድስት ነጥብ አምስት ሊትር ውሃ ያመነጫል ቢባልም በተግባር ግን በሰከንድ ሦስት ነጥብ አምስት ሊትር ብቻ የሚያመነጭ መሆኑን ማረጋገጣቸውን አቶ ኃይሌ ገልፀዋል::

ውኃው ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ከ10 እስከ 15 ዓመት ያገለግላል ቢባልም ሰባት ዓመት እንኳን ሳያገለግል መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን የገለፁት አቶ ኃይሌ የውኃው መጠን መቀነስ እያደገ ከመጣው የከተማዋ የህዝብ ቁጥር ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ የውሃ ዕጥረት መፈጠሩን ገልፀዋል:: ውኃው በመቀነሱም ለህብረተሰቡ ማዳረስ አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ በአንዳንድ ሰፈሮች ፈፅሞ ውኃ እንደማይደርስ ገልፀዋል:: ችገሩን በተወሰነ ደረጃ ለማቃለልም ለተለያዩ ሰፈሮች በየአራት ቀኑ በቦኖ የፈረቃ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ጠቁመዋል::

በአሁኑ ወቅት ምንጩ በሰከንድ ሁለት ሊትር

እንደሚያመነጭ የገለፁት ኃላፊው ከዚህ ውስጥ በሰከንድ ዜሮ ነጥብ አራት ሊትሩን ውሃ ምንጩ በሚገኝበት አካባቢ ለሚኖሩ የገጠሩ ነዋሪዎች ተሠጥቷል:: ወደ ከተማው የሚመጣው የውሃ መጠን አንድ ነጥብ ስድስት ሊትር በሰከንድ እንደሆነም አቶ ኃይሌ ተናግረዋል:: ይህ የውሃ መጠን በከተማዋ ለሚገኙ ዘጠኝ ሺህ 596 ነዋሪዎች መድረስ ባለመቻሉ በህብረተሠቡ ላይ ከፍተኛ ችግር እየተፈጠረ እንደሆነም ተናግረዋል::

የውሃ እጥረቱ በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ እያደረሰ የሚገኘውን ተጽእኖ ለውኃ ቢሮ ማሳወቃቸውን የተናገሩት አቶ ኃይሌ በ2008 ዓ.ም ቢሮው ባለሙያ ልኮ የከርሰ ምድር ውኃ በማስጠናቱ አንድ

ምንጭ መገኘቱንም ገልፀዋል:: የጥናት እና የዲዛይን ሥራው ቢጠናቀቅም ወደ ስራው ቶሎ ባለመገባቱ ህብረተሠቡ አሁንም ችግር ላይ እንደሆነም አቶ ኃይሌ አብራርተዋል::

በአማራ ክልል የመጠጥ ውሃ መስኖና ኢነርጅ ቢሮ የመጠጥ ውኃ የሥራ ሂደት ኃላፊ የሆኑት አቶ አሥራት ካሴ በበኩላቸው ለአጅባር ከተማ የመጠጥ ውኃ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ምንጭ የሚያመነጨው የውኃ መጠን አነስተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ በቂ ውሀ እንደማያገኝ ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል::

ችግሩን ለመፍታትም ባለፈው ዓመት ሌላ የውኃ ምንጭ ተለይቶ የጥናትና ዲዛይን ሥራው ተጠናቋል:: ከዓለም ባንክ በሚገኝ ከ50 እስከ 60 ሚሊዮን ብር በሚደርስ ገንዘብ የግንባታ ሥራውን ለማከናወን ጨረታ ወጥቶ ውጤት እየተጠበቀ መሆኑን አቶ አሥራት ተናግረዋል:: በታህሳስ ወር ሥራው እንደሚጀምርም ጠቁመዋል::

ከገፅ 9 የዞረ

ደረጃውን የጠበቀ...ጨዋታዎችን እና እንቅስቃሴዎችን ማድረግ አይችሉም:: እነዚህና ሌሎች ችግሮች ባሉበት ሁኔታ የትምህርት ጥራትም ሆነ የተሻለ ውጤት ማምጣት አስቸጋሪ መሆኑን ገልጻለች::

የትምህርት ቤቱ የተወሰኑ ብሎኮች ግድግዳ ቀለም መቀባታቸው በግቢው ውስጥ የተወሰኑ ችግኞች ከመተከላቸው በተጨማሪ ሌሎች ጥቃቅን ለውጦች መታየታቸውን ተማሪዎች አልሸሸጉም:: ከሁሉም በላይ ግን ትምህርት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ መምህራን በሚችሉት መንገድ ሁሉ እያገዟቸው መሆኑን ተማሪዎቹ ጠቁመዋል::

በአጅባር አጠቃላይ አንደኛ ትምህርት ቤት በዋነኛነት የትምህርት ጥራትን እና የተማሪዎችን ውጤት ወደ ኋላ ሊጐትቱ የሚችሉ ችግሮች መኖራቸውን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ግዛቸው ደባልቄ ተናግረዋል:: በከፊልም ቢሆን ችግሮቹን ለመቀነስ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነም ጠቁመዋል::

ርዕሰ መምህሩ እንደገለፁት ከመምህራን ጋር በመወያየትና በመግባባት ተማዎሪቹን ያለመታከት ለማገዝ በክረምቱ የቅድመ ዝግጅት ወቅት ጀምሮ ወደ ስራ ተገብቷል::

በአሁኑ ወቅት ሁሉም መምህራን ተማሪዎቻቸውን በአንድ ለአምስትና በልማት ቡድን አደራጅተው ጨርሰዋል:: ይህም ለጊዜውም ቢሆን አንዳንድ መጻህፍትን በጋራ እንዲጠቀሙ በማድረግ የመፅሀፍ እጥረቱን ችግር በመጠኑም ቢሆን ለመቅረፍ እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል:: በቂ የመማሪያ ክፍሎች ባይኖሩም ተጨማሪ ክፍለ ጊዜዎችን ሜዳ ላይ ጭምር በመስጠት ተማሪዎችን ለማገዝ እየተሞከረ እንደሆነም አብራርተዋል:: የመፅሀፍ ዕጥረቱ የተከሰተው በዋናነት ከሶስት እስከ

አምስት ዓመት እንዲያገለግሉ ተብለው የመጡት መፅሀፍት በአያያዝ ጉድለት ምክንያት ከአገልግሎት ውጭ በመሆናቸው እና የተማሪዎች ቁጥር በመጨመሩ እንደሆነ ርዕሰ መምህሩ ተናግረዋል:: ችግሩ አሳሳቢ በመሆኑ ከተማሪዎች ቁጥር አንፃር የሚያስፈልጉትን መፅሀፍት ለይተው ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ማሳወቃቸውን ተናግረዋል:: ይህን ተከትሎ ሁሉም መፅሀፍት ስለመጣላቸው በቅርቡ የመጽሐፍት ችግሩ ምላሽ እንደሚያገኝም ርዕሰ መምህሩ ገልፀዋል::

ተማሪዎች ከቤተ መፅሀፍት አጋዥ መፅሀፍ መዋስ ያልቻሉት ለጊዜው እንደሆነ የተናገሩት ርዕሰ መምህሩ ችግሩ የተፈጠረው የቤተ መጽሐፍት ባለሙያዎችም በንብረት ቆጠራ ላይ ስለ ነበሩ ነው ብለዋል:: ቆጠራው ተጠናቅቆ ርክክቡ ሲፈፀም መፅሀፉን የማዋስ ስራው እንደሚጀምርም ገልፀዋል::

ባለፈው ክረምት ወር ህብረተሰቡን በማስተባበር ከ550 በላይ ችግኞችን በትምህርት ቤቱ ግቢ ውሰጥ መትከል መቻላቸውን አብራርተዋል::ከዚህ በተጨማሪ አሽዋና ሲሚንቶ እንዲቀርብ በማድረግ አራት የመማሪያ ክፍሎችን ወለሎች ሊሾ ማድረጋቸውንም ርዕሰ መምህሩ ተናግረዋል:: በአሁኑ ወቅት በትምህርት ቤቱ የአፈር ወለል ያላቸውን ቀሪ ክፍሎች ሊሾ ለማድረግ አሸዋና ሲሚንቶው በህብረተሰቡ መቅረቡን እና ሥራው እንዲሰራ ጨረታ መውጣቱንም ጠቁመዋል::

ርዕሰ መምህሩ አክለውም በትምህርት ቤቱ አጠቃላይ የስምንት ክፍሎች እጥረት መኖሩን መለየታቸውን ተናግረዋል:: ችግሩ አስቸኳይ መፍትሄ የሚፈልግ በመሆኑም ከህብረተሰቡ ጋር በመወያየት ክፍሎችን ቆርቆሮ በቆርቆሮ ለመስራት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል:: ለዚህም 100 ዚንጎ ቆርቆሮዎች ለመግዛት ህብረተሰቡ 20 ሺህ ብር ለማውጣት ቃል ስለገባ ደረሰኝ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል::

ክፍሎች ተገንብተው ሲጠናቀቁ ተማሪዎች በሁለት ፈረቃ የነበረውን ትምህርት ሙሉ ቀን እንዲማሩ ያስችላል ብለዋል:: የማካካሻ ትምህርት (ቱቶሪያል) መስጫና የቤተ ሙከራ የሚሰሩባቸው ክፍሎችም እንደሚኖሩት የገለፁት ርዕሰ መምህሩ አብዛኞቹን ችግሮች በቅርቡ እንደሚቀረፍም ተናግረዋል:: ከግቢው ጥበትና ከስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር ለመቅረፉም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ርዕሰ መምህሩ ገልጸዋል:: ከከተማ አስተዳደሩ የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ተጨማሪ ቦታ ለማግኘት እየተጠባበቁ እንደሆነም ጠቁመዋል::

ርክክቡ ሲፈፀም መጽሐፍ የመዋስ ስራው ይጀምራልአቶ ግዛቸው ደባልቄ

ወደ ገጽ 42 ዞሯል

Page 21: 12 03 2009.pdf

ገጽ 21በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. የሔዋን ገጽየሔዋን ገጽ

ወደ ገጽ 24 ዞሯል

አጫጭር ዜናዎች

አባትሁን ዘገየ

“ሁለቱም እስክሞትእንዲለዩኝ አልፈልግም”

በ1952 ዓ.ም. አርሲ ሮቢ በምትባል ከተማ መወለዳቸውን ይናገራሉ:: ሆኖም የስድስት ዓመት ልጅ እያሉ ከወላጆቻቸው ጋር ወደ በሰሜን ሸዋ ዞን ዓለም ከተማ መምጣታቸውን ያስታውሳሉ:: ከ1962 እስከ 1969 ባሉት ዓመታትም በዓለም ከተማ እንዲሁም በአዲስ አበባ እስከ ስምንተኛ ክፍል ተምረዋል::

ለቤተሰባቸው ሶስተኛ ልጅ እንደሆኑ የሚገልጹት የዚህ እትም የሄዋን ገፅ ባለታሪካችን ወ/ሮ ዘውዲቱ ሙሉጌታ ከስምንተኛ ክፍል በኋላ ትምህርታቸውን መቀጠል አልቻሉም:: ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ በልጅነታቸው ለባል መሰጠታቸው ነው፤ “የታጨሁት 'ልጅህን ለልጀ' በሚለው ሥርዓታችን በአምስት ዓመቴ ነው:: በአስራ አንድ ዓመቴ ደግሞ አገባሁ፤ አንድ ወንድ ልጅም ወለድሁለት:: ትዳር ስይዝ መርሀ ቤቴ ላይ የሴት ልጆች የመማር ዕድል

ይሄን ያህል አልነበረምና ትምህርቴን አቋረጥሁ" ሲሉ ያንን ጊዜ በፀፀት ያስታውሳሉ::

ወይዘሮ ዘውዲቱ በወቅቱ ስለትዳርም ሆነ ፍቅር የሚያውቁት ነገር ስላልነበራቸው ከመጀመሪያው ባለቤታቸው ጋር ፍች ፈጽመው ለብቻቸው መቀመጣቸውን ያስታውሳሉ:: ከዚያም ሌላ ባል አግብተው ሶስት ወንዶች ልጆች ወልደዋል:: ይሁን እንጅ፣ ከሁለተኛው ባላቸው ጋርም በትዳር ህይወት መዝለቅ አልቻሉም:: ሶስተኛ ባል አግብተው ሁለት ልጆች አፍርተዋል::

ወይዘሮ ዘውዲቱ በህፃንነታቸው ለባል ተሰጥተው ትምህርታቸውን ማቋረጣቸው፣ ማግባት መፍታታቸው የህይወት ፈተና ቢሆንባቸውም በህጻንነት ህይወታቸው ብዙዎች የማያገኙትን ዕድል አግኝተዋል:: ወይዘሮዋ እንዳጫወቱን ጥር 28 ቀን 1965 ዓ.ም. አፄ ኃይለ ሥላሴ መርሐ

የተለየ ፍቅር አለኝ:: ሁለቱም እስክሞት እንዲለዩኝ አልፈልግም:: ዛፎች ሲቆረጡ ሳይ አልቅሸ የማልፍበት ጊዜ አለ:: ልጆች ተጐድተው ማየት አልፈልግም" የሚሉት ወ/ሮ ዘውዲቱ ለሁለቱም ያላቸው ፍቅር በልጅነት ተወጥኖ በጐልማሳነት ፍሬ እንዳፈራ በኩራት ይናገራሉ:: "ልጅ ሆኘ ዕቃ ዕቃ ስጫወት ድንጋዩን ሁሉ እየሰበሰብሁ ልጄ ነው፤ አትንኩብኝ እል ነበር" በማለት በልጅ ፍቅር የተሞላ የልጅነት ጊዜያቸውን ያስታውሱታል፡፡ ወይዘሮዋ ዛሬ በከተማ ግብርናም ሆነ በሰብአዊ ተግባራቸው ዓለም አቀፍ ዕውቅና እስከ ማግኘት ደርሰዋል::

ለዚህ ስኬት ደግሞ ፋና ወጊ የሆኗቸው ጀርመናዊው የበጐ አድራጐት ተግባራት አባት ዶክተር ካርልሄንዝ በም እንደሆኑ ያስረዳሉ:: ካርልሄንዝ በም ልዩ ልዩ የበጐ አድራጐት ተግባራትን ለማከናወን በ1980ዎቹ ወደ ዓለም ከተማ ማቅናታቸውን ያወሳሉ:: ካርል ዓለም ከተማ ውስጥ ዓለም ከተማ ሆስፒታል ገንብተው “እናት” ሲሉ መሰየማቸውንም ይገልጻሉ::

ካርል ሆስፒታሉን ለምን እናት እንዳሉት ሲገልጹም፤ “ካርል በም ዓለም ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ አንዲት ህፃን መንገድ ዳር ቁጭ ብላ ስታለቅስ በርቀት ያያሉ:: ወደ ህፃኗም ያመራሉ:: ፊቷ በእንባ ርሶ፤ አቧራ ለብሶ፤ ከንፈሮቿ ደርቀው ያዩዋታል:: እንዲያ መጐሳቆሏ ልባቸውን የነካው ካርል ጐንበስ ብለው ህፃኗን አቅፈው ካነሱ በኋላ ጉንጮቿን እየሳሙ ስምሽ ማነው? በማለት ጠየቋት:: ህፃኗም 'እናት' ስትል መለሰችላቸው:: ከዚያ በኋላ ዓለም ከተማ ውስጥ ሆስፒታል ከገነቡ በኋላ ዓለም ከተማ እናት ሆስፒታል በሚል በስሟ ሰይመውታል” ይላሉ::

“ይሄን የካርል ተግባር ስመለከት ይሄ ሰው በዘር፣ በሀይማኖት፣ በቋንቋ… አይወለደን፣ አይዘመደን ዓለም ከተማ እናት ሆስፒታል ግቢ የሚገኘው የወ/ሮ ዘውዲቱ አረንጓዴ

ልማት

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሴቶች በአመራርነትና በማስተማር ያላቸው ተሳትፎ መሻሻል አያሳየ መምጣቱን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ::

በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር ካባ ኡሮጌ ሁለተኛውን የትምህርትና ስልጠና ጉብኤ በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል:: በመግለጫቸውም ሴቶች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአመራርነት፣ በማስተማርና በመማር ያላቸው ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን ሚንስትር ዴኤታው ለኢዜአ ተናግረዋል::

ትምህርት በፍትሃዊነት ተደራሽ በማድረግ የሴት ተማሪዎችን ቁጥር ከማሳደግ ባለፈ ወደ ዩኒቨርሲቲ የገቡትን በማብቃት ውጤታማ ሆነው እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑንም ዶክተር ካባ ገልጸዋል::

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ማጠናቀቂያ 45 በመቶ ለማድረስ የታሰበው የሴት ተማሪዎች ተሳትፎ 35 በመቶ፤ የሴት መምህራን ቀጥሮ 12 በመቶ ማሳደግ እንደተቻለም ሚንስትር ዴኤታው ተናግረዋል::

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስርሜሽን እቅድ 20 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል::

በ2008 ዓ.ም መጀመሪያ የዩኒቨርሲቲ ምክትል ኘሬዚዳንት የነበሩት ሁለት ናቸው ያሉት ዶክተር ካብ በዓመቱ መጨረሻ ዘጠኝ መድረሳቸውን ገልፀዋል::

ሚንስትር ዴኤታው የሴቶች ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል ያሳይ እንጅ፤ ከተቀመጠው እቅድ ላይ ለመድረስ ብዙ መስራት ይጠይቃል ነው ያሉት::

የሚኒስትሩ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በበኩላቸው ትምህርት በፍትሃዊነት ተደራሽ እንዲሆን መንግስት የወሰደው አቋም አመርቂ ውጤት እንዲመዘገብ አስችሏል ብለዋል::

“በትምህርት ጥራት ረገድ ክፍተቶች አሉ” ያሉት ዶክተር ጥላዬ፤ ጥራትን የሚያስጠብቁ የተቀናጁ መርሃ ግብሮች በተከታታይ ተግባራዊ በማድረግ ውጤት ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል::

ሚኒስቴሩ የመምህራንን አቅም ማጐልበት፤ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ መጠበቅ፤ የመማሪያ ግብአቶችን ማሳደግ እና የትምህርት ጥራትን መጠበቅ በትኩረት የሚሰራቸው ጉዳዮች መሆናቸውም አቶ ጥላዬ አስረድተዋል::፡

ግብአቶችን በማሟላት ረገድ በ2009 ዓ.ም ብቻ ስድስት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን የሁለተኛ ደረጃ የመማሪያ መጽሐፍት ታትመው መሰራጨታቸውን ለአብነት አስታውሰዋል::

እንደ ዶክተር ጥላዬ ማብራሪያ ከ25 ዓመታት በፊት በአጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ አራት ሺህ ትምህርት ቤቶችና ከ2ሚሊዮን የማይበልጡ ተማሪዎች ነበሩ:: በአሁኑ ጊዜ ግን ከ39 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ተከፍተው 28 ሚሊዮን ተማሪዎች በመማር ላይ ይገኛሉ::

26ኛው የትምህርትና ስልጠና ጉባኤ በአፋር ክልል በሰመር ከተማ ህዳር አምስትና ስድስት ቀን 2009 ዓ.ም የትምህርትና የቴክኖሎጂ ልማት ሰራዊት ግንባታ፣ ለትምህርትና ስልና ጥራት፣ለሰላምና ለልማታችን! በሚል መሪ ሃሳብ ተካሄዳል::

በከፍተኛ

የትምህርት ተቋማት

የሴቶች ተሳትፎ

መሻሻል ማሳየቱ

ተገለፀ፡፡

ቤቴን ጐብኝተዋል:: እሳቸው ደግሞ ያኔ “ስካውት” ነበሩ:: በመሆኑም ከህፃናቱ ተመርጠው አበባ የማበርከት ዕድል አጋጥሟቸዋል::

ወ/ሮ ዘውዴቱ ለአፄ ኃይለ ሥላሴን አበባ ያበረከቱት አንዴ ብቻ አልነበረም፤ "አዲስ አበባ ቀለመ ወርቅ ትምህርት ቤት ስማር ጃንሆይ ትምህርት ቤቱን በየሳምንቱ ሊጐበኙ ሲመጡ አበባ የማበረክተው እኔ ነኝ:: አንድ አራቴ አበባ አበርክቼላቸዋለሁ” የሚሉት ወ/ሮ ዘውዲቱ ይሄን ዕድል በማግኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን አውግተውናል::

“ለአትክልትና ለልጅ

Page 22: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 22 ለህፃናት ለሕፃናት ከዚህም ከዚያምደረጀ አምባው

መልካም ጓደኛን ምረጡ

የውሻ እና የሰው ወዳጅነት

ሥነ -ቃል

1. ማምሻም ዕድሜ ነው2. ማር ሲበዛ ይመራል3. ሰው ባፉ አሞራ በክንፉ4. ቁመህ ተከራከር ዙረህ ተመሳከር

ለምሳሌያዊ አነጋገር ፍች ስጡ

አብዛኛዎቹ ወፎች በየቀኑ የክብደታቸውን እጥፍ የሚሆን ምግብ ይመገባሉ::

ዶልፊኖች በውሃ ውስጥ ሆነው እስከ 24 ኪሎ ሜትር ድረስ ድምፅን መስማት ይችላሉ::

ፍላሚንጐ የሚባሉት የወፍ ዝርያዎች ጭንቅላታቸውን ወደ ላይ ሳያደርጉ መመገብ አይችሉም::

መቀስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠራው በጥንታዊቷ ግብጽ ነው::

ምንጭ፡- Did you know.com

ስዕሉን በመሣል ተለማመዱ

ልጆች እንደምን ሰነበታችሁ? ዛሬ ደግሞ በባህር ዳር ከተማ የካቲት 23 አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጐራ በማለት አንድ በትምህርቷ ጐበዝ የሆነች

በማግኘት ነው ከክፍል ወደ ክፍል የምትዛወረው::

ሶስተኛ ክፍል ስትደርስ ግን ቤተሰቦቿ ሙሉ ትኩረት ሰጥታ እንድታጠና መከሯት:: ወላጆቿ የጥናት የጊዜ ሰሌዳ እንድታወጣ በማድረጋቸውም ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ጀመረች::

ቤተሰቦቿ "ወደ ፈለግሽው ደረጃ ለመድረስ በርትተሽ መማር አለብሽ" በማለት ይመክሯታል:: "በተለይ በትምህርት ቤት አብረውኝ የሚውሉ ጓደኞቼ በማጥናት ጥሩ ካልሆኑ አብሬያቸው እንዳልውል በምክራቸው ያግዙኛል" በማለትም ገልፃለች::

በዚህ ምክንያትም በሰፈሯ አካባቢም ሆነ በትምህርት ቤት ያሉት ጓደኞቿ ለትምህርት ፍቅር ያላቸው በመሆናቸው በጋራ ያነባሉ::

የኔወርቅ ከጠዋቱ የትምህርት ሠዓት በኋላ ከሰባት እስከ ስምንት ሰዓት ድረስ ቤተሰቦቿን በሥራ ታግዛለች። ከዚያ በኋላ ለአንድ ሰዓት ያህል ቴሌቪዥን ትመለከታለች::

የኔወርቅ ቴሌቪዥን የምትመለከተው ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ነው:: ወላጆቿ ቀኑን ሙሉ ተከታታይ ፊልም ሲያሳዩ የሚውሉትን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች እንድትከታተል አይፈቅዱላትም:: ከዘጠኝ ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ከሰፈር ጓደኞቿ ጋር ከተጫወተች በኋላ በግቢያቸው ውስጥ በሚገኘው የጥናት ክፍል እስከ ምሽቱ ሁለት ሠዓት ድረስ የቡድን ጥናት ያካሂዳሉ::

ልጆች ወላጅና መምህር የሚመክራቸውን በመስማት ትምህርታቸውን በትጋት ሊከታተሉ ይገባል የምትለው የኔወርቅ በተለይ በሰፈርና በትምህርት ቤት የሚመርጡት ጓደኛ ለትምህርት ልዩ ትኩረት ያለው መሆኑን ወላጆች ተከታትለው ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ታምናለች::

የተረት መጽሐፍትን በማንበብ አስተሳሰባቸውን ማስፋት፣ የቋንቋ ችሎታቸውን ማሳደግና መዝናናት ስለሚችሉ ትኩረት እንዲያደርጉ ትመክራለች::

ልጆች ካነበባችሁት ታሪክ ቁም ነገር አገኛችሁ? ጐበዞች!

የ4ኛ ክፍል ተማሪ አነጋግሬያለሁ:: የኔወርቅ ሹመቴ ትባላለች፤ 13 ዓመቷ ነው::

ባለፈው ዓመት ከሶስተኛ ወደ አራተኛ ክፍል ስትዘዋወር ያመጣችው አማካይ ውጤት 97 ነጥብ አራት ነው:: በዚህም ከክፍሏ ተማሪዎች ቀዳሚ በመሆን ተሸልማለች::

በአዴት ከተማ የተወለደችው የኔወርቅ ትምህርቷን የጀመረችው ከቤተሰብ ጋር ወደ ባህርዳር በመምጣት ነው:: ለትምህርቷ ትኩረት ሠጥታ በማንበቧ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ደረጃን

በድሮ ጊዜ ሁሉም እንስሳት ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ሰው ተመልክተው “ይህ ሁለት እግሮች ያሉት አዲስ እንስሳ ደግሞ ማነው?” ብለው ጠየቁ:: ቀጥለውም “ሁለት እግሮች ብቻ ነው ያሉት! እንደ ጦጣ ሁለት እጆች ብቻ ቢኖረውም ከጦጣ ግን ይለያል” አሉ::

ከዚያም መመራመራቸውን በመቀጠል “ከእኛ ምንድነው የሚፈልገው? ከእኛ ጋር በሰላም አብሮን መኖር ይችላል? እንዴት ነው የሚሆነው?” ማለት ጀመሩ::

ስለዚህ ውሻው ወደ ሰው ሄዶ እንዲያናግረው ሲልኩት ውሻው ትዕዛዙን ተቀብሎ ወደ አደም በመሄድ “አንተ ሰው! አንተ አዲስ እንስሳ! ከእኛ ጋር ሆነህ በምድር ላይ በሰላም አብረን እንድንኖር ከፈለክ ልጠይቅህ ነው የመጣሁት፣ ወይስ ልትጣላን ትፈልጋለህ?” አለው::

ሰውየውም “በሰላም አብሬአችሁ መኖር እፈልጋለሁ:: ለዚህ ስፍራ አዲስ ነኝ:: ከገነት ነው የመጣሁትና ከእናንተ ጋር መኖር እፈልጋለሁ::” አለው::

“አሃ! ይህ መልካም ዜና ነው” ካለ

በኋላ ውሻው ወደ ሌሎቹ እንስሳት በፍጥነት እየሮጠ ተመልሶ ሊነግራቸው ሄደ:: ነገር ግን ሌሎቹ እንስሳት ውሻው

በፍጥነት እየሮጠ በመመለስ ላይ መሆኑን ሲያዩ “ኧረ! ሰውየው

ውሻውን እያባረረው ስለሆነ እኛም መሸሽ አለብን” ብለው

ሽሽታቸውን ተያያዙት::ሁሉም እንስሳት በመሸሽ ላይ እያሉ

ውሻው ስለሁኔታው ነግሮ ሊያስቆማቸው በማሰብ “ውፍ!ውፍ!ቁሙ!ቁሙ!” እያለ ይከተላቸው ጀመር::

ሌሎቹ እንስሳት ስለፈሩ ሩጫቸውን ሲቀጥሉ ውሻው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ስለደከመው ወደ ሰውየው ተመልሶ ሲሄድ ሌሎቹ እንስሳት ግን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከሰው ሸሽተው ቀሩ:: ውሻው ግን የሰው ጓደኛ በመሆን “ውፍ!ውፍ!ቁም!ቁም!” እያለ በመጮህ ሰውን እና ሀብቱን ጠባቂ ሆኖ ቀጠለ::

ምሳሌያዊ አነጋገር መልስ

1. ባለህ ጊዜ ተጠቀም2. ከልክ በላይ የሆነ ነገር ያስጠላል3. ሰው በመልካም ንግግሩ ተስማምቶ ይኖራል4. የነገር ውሉ ማስረጃ ሲገኝለት ነው

ሰውም እንስሳቱ የማይፈልጉት መስሎት በጠላትነት ያያቸውና ያድናቸው ጀመር:: ውሻውን ግን አብሮት እየኖረ እንዲጠብቀው ጠየቀው::

Page 23: 12 03 2009.pdf

ገጽ 23በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. ጤናችን

ወደ ገጽ 40 ዞሯል

ከአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ ጋር በመተባበር የቀረበ አጫጭር ዜና

ሙሉጌታ ሙጨ

በመካከለኛ የእድሜ ክልል በሚገኙ ሰዎች ላይ የሚታይ ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት አዕምሯቸው በፍጥነት እንዲገረጅፍ እንደሚያደርግ አንድ ጥናት አመለከተ።

በእንግሊዙ የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የተደረገውና በኒዩሮ ባዮሎጂ ኦፍ ኤጂንግ የታተመው ጥናት፥ እድሜያቸው በመካከለኛው የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙና ከፍተኛ የስብ ክምችት ያለባቸው ሰዎች አዕምሯቸው ከመደበኛው የአእምሮ እድገት አንጻር ሲታይ በ10 አመት ፈጥኖ እንዲያረጅ ያደርጋል ብሏል። ተቋሙ ከ20 እስከ 87 አመት እድሜ ያላቸውን 473 ተሳታፊዎች ቀጭን እና በጣም ወፍራም በሚል በሁለት ቡድን ለይቶ ጥናቱን አድርጓል። በዚህም የሰውነት ክብደታቸው ከቁመታቸው አንፃር ሲታይ ወይንም በሰውነታቸው ውስጥ የሚገኘው የቅባት መጠን ከ25 አመት እድሜ በላይ ከሆኑ ሰዎችና እድሜያቸው ከ25 በታች ዓመት እድሜ ካላቸው ሰዎች ጋር ሲነፃፀር ከመጠን በላይ የወፈሩ ሰዎች አዕምሮ ውስጥ የሚገኘው ነጭ ህዋስ መጠን አነስተኛ መሆኑ ተረጋግጧል።

የተለያዩ የአንጎል ክፍልን እርስ በርስ የሚያገናኙትና ለማስታወስ እና በፍጥነት ለማሰብ የሚረዱት ነጭ ህዋሳት በተፈጥሮ ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ ከሚመጣው የመኮማተር ባህሪ ጋር ተመሳሳይነት አላቸው። ይህም የሆነው ከልክ በላይ በመወፈር እና ቦርጭ ምክንያትም ህዋሳቱ ሊጨማደዱ መቻላቸውን በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የጥናቱ መሪ ፕሮፌሰር ሊዛ ሮናን አብራርተዋል። ተመራማሪዎቹ የጥናቱን ተሳታፊዎች አዕምሮ ምስል ያነበቡ ወይም የቃኙ ሲሆን፥ የወፍራሞቹ ወጣቶች የአዕምሮ አወቃቀር በመደበኛ ሁኔታ ከሚታየው የሽማግሌዎች የአዕምሮ አደረጃጀት ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል። በርካታ የስብ ይዘት ያላቸው ህዋሳት “ሳይቶኪንስ” የተሰኙ ጎጂ ፕሮቲኖችን ሊያመርቱ ይችላሉ፤ ይህም አዕምሮን ይጎዳል ነው ያሉት ፕሮፌሰር ሮናን።

በጥናቱ ከልክ በላይ የወፈሩ ሰዎች በሰውነታቸው ውስጥ ከፍተኛ የስብ መጠን ስለሚኖር ጤናማ ክብደት ካላቸው እኩዮቻቸው ጋር ሲነፃፀር የአዕምሯቸው እድሜ በ10 ዓመት የገረጀፈ ይሆናልም ብለዋል። አጥኚዎቹ በአዕምሮ አስተሳሰብ ደረጃ ግን በወፍራም እና ቀጭን ሰዎች መካከል ምንም አይነት ልዩነት ማየት አለመቻላቸውን ተናግረዋል። የጥናቱን ተሳታፊዎች የአስተሳሰብ ደረጃ በጊዜ ሂደት በተከታታይ ሲጠና ምናልባትም የተሳታፈዎቹ የአስተሳሰብ አቅም እየተዳከመ መሄዱን ያረጋግጣሉ ብለው እንደሚያምኑም ነው ያብራሩት።

ሜንስ ሄልዝ ዶት ኮምን ጠቅሶ ኤዜአ እንደዘገበው የሰውነትን ክብደት መቆጣጠር በአጠቃላይ የአዕምሮ ጤናን ለመጠበቅ ይበጃልና ያስቡበት ብለዋል ተመራማሪዎቹ።

በስዊድን ለ30 ዓመታት በ9 ሺህ መንትዮች ላይ በተደረገ ጥናት በመካከለኛ እድሜያቸው ከልክ ላለፈ ውፍረት የተጋለጡ መንትዮች መደበኛ ክብደት ካላቸው ጋር ሲናፃፀር ለአዕምሮ መቃወስ የመጋለጥ እድላቸው 80 በመቶ መሆኑ ተረጋግጧል።

ከመጠን በላይ ውፍረት አዕምሮን

በፍጥነት ያስረጃል ተባለ

በወልድያ ሆስፒታል መድኃኒት በመጥፋቱ በተስፋ ይመጣል በሚል የሚጠብቁት ህሙማን

የታካሚዎች

አዲስ ብስራት ነዋሪነቱ በወልድያ ከተማ ሲሆን የ14 ዓመት ታዳጊ ነው:: በወልድያ የብሩህ ተስፋ የመጀመሪያ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነው:: አዲስ ብስራት ትምህርት ቤት እስከገባበት የእድሜ ደረጃ ድረስ ሙሉ ጤነኛ እንደነበር ወላጅ አባቱ አቶ ብስራት አየለ ጠቁመዋል::

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን የአዲስ ብስራት ጤና ታውኳል:: በመሆኑም የሚወደውን ትምህርት መከታተል ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል:: ወላጆቹም በመጀመሪያ በአቅራቢያቸው ወዳለው የባህል ህክምና መስጫ ተቋም በመውሰድ ለሰባት ቀናት የሚሰጥ መድኃኒት እንደታዘዘለት ተናግረዋል::

ይሁን እንጅ ከባህል የመድኃኒት አዋቂ የታዘዘለትን መድኃኒት ቢወሰድም ለውጥ አላሳየም፤ እያደርም የታዳጊው እግር አበጠ፤ ሆዱ ተቆዘረ::

የታዳጊው ህይወት አሳስቧቸው ሊጠይቁት የሚመጡ ጐረቤታሞች “ወደ ዘመናዊ የህክምና ተቋም ብትወስዱት ይሻላል” ሲሉ መከሩ፤ አንዳንዶቹም “ወስደን እናሳክመው” በማለት አጋርነታቸውን አሳዩ:: ለታዳጊው ቤተሰቦችም ያላቸውን አጋርነት አረጋገጡ::

ስለሆነም ታዳጊ አዲስ ብስራትን ወላጆቹ ወደ ወልድያ ጠቅላላ ሆስፒታል በመውሰድ አስመረመሩት:: ህመሙም ስኳር መሆኑ ተረጋገጠ::

ሀኪሞችም “ታዳጊው የታዘዘለትን መድሀኒት በአግባቡ ከወሰደ በቀላሉ ይፈወሳል:: ለዚህ ደግሞ የእናንተን የዕለት ተዕለት ድጋፍና ክብካቤ ይሻል:: የሚታዘዝለት መድኃኒት በነፃ ይሰጠዋል፤ እናም እድለኛ ነው:: መድኃኒቱን ከወሰደ ምንም የሚያሰጋ

ነገር የለበትም:: ታዲያ ድኗል ብላችሁ ያለ ሀኪም ትዕዛዝ ማቋረጥም ሆነ መድሀኒት መቀየር አደገኛ ነው” በማለት የታዳጊውን ወላጆች መከሩ::

የታዳጊው ወላጆችም “በጄ!” ብለው የሀኪሞችን ምክር አንድ በአንድ ለመተግበር ቃል መግባታቸውን አጫወቱን:: በዚህም መሠረት ልጃቸውን ሀኪም በነገራቸው ቀነ ቀጠሮ ወደ ወልድያ ጠቅላላ ሆስፒታል እየወሰዱ ያሰመረምሩታል፤ በነፃ የሚታዘዝለትን መድሀኒት ደግሞ ቀንና ሰዓት ሳያዛንፉ ይሰጡታል::

ወላጆች ተከታትለው ልጃቸው መድኃኒቱን እንዲወስድ በማድረጋቸው አብጦ የነበረው እግሩ ሟሸሸ:: የተቆዘረው ሆዱ ወደ መደበኛ ቦታው ተመለሰ:: የሞጨሞጨ ዐይኑ፣ የቀነሰው አካሉ፣ የቀላው ፀጉሩ… ወደ ተፈጥሯዊ ቅርፁ ተመለሰ:: አዲስም ቆረጠኝ፣ ፈለጠኝ፣ በላኝ፣ አሳከከኝ… ማለቱ ቀረለት::

ስጋት

በወልድያ ሆስፒታል የስኳር መድኃኒት በማጣቱ የሚሰቃየው ታዳጊ

Page 24: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 24

ከገጽ 21 የዞረ

“ ሁለቱም እስክሞት...”እንዲህ ያለ ታላቅ ተግባር ሲፈጽም እኔስ ለምን ለወገኔ አንዳች የሚጠቅም ነገር አልሠራም’ በማለት ወደ ራሴ ማየት ጀመርሁ:: ምን ላደርግ እችላለሁ ብየም አሰብሁ:: አስቤም አልቀረሁ፣ አትክልትና ልጅ ወደ መንከባከብና ማሳደግ ገባሁ" አሉን ግቢያቸው ውስጥ ወዳለው አትክልትና ወዳቀፏት ህፃን በጠቋሚ ጣታቸው እያመለከቱን:: ከዚያም “ኑ፤ አትክልቶችን አንድ ባንድ ላስጐብኛችሁ" አሉና ከተቀመጡበት ተነስተው ቀድመው አመሩ፤ እኛም ተከተልናቸው::

"ቡና፣ ሽፈራው፣ ጥንጉግ፣ የሻይ ቅጠል፣ ቅማማ ቅመም፣ አቦካዶ፣ ማንጐ እና ሌሎች ፍራፍሬዎችን እተክላለሁ:: የተለያዩ የአበባ ዝርያዎችም አሉኝ:: ችግኞችን የማፈላው ከጥር በኋላ ነው:: ያኔ ብትመጡ ይሄ የምታዩት ግቢ አንድም የእግር መርገጫ ቦታ አይኖረውም” አሉና ስለ እያንዳንዱ ተክል ያብራሩልን ጀመር::

“ሽፈራው ዛፍን ‘የግፊት መድኃኒት ነው’ እያሉ ብዙዎች ይወስዱታል:: ጥንጉግ የተባለውን ቅጠልም ድሮ የፀጉር ተኩስና ቅባት ባልነበረበት ጊዜ ከአደስ ጋር ወቅጠን ፀጉራችንን የምናስውብበት ነበር:: ፀጉር በጣም ያሳምራል:: ሻይ ቅጠልም ገዝቼ አላውቅ፤ ከዚሁ እያመረትሁ እጠቀማለሁ:: ወደ ውጪም እልካለሁ:: 128 እግር የቡና ተክልም አለኝ:: የቡና ቅጠሉ ተለቅሞና ታጥቦ በምጣድ ሞቅ ሞቅ ከተደረገ በኋላ የራሱ ቅመሞች ስላሉት ከቅመሞቹ ጋር ይለወስና ታሽጐ ወደ ጀርመን፣ እንግሊዝ፣… ይላካል፡፡ ጣዕሙም ልዩ ነው" ሲሉም አጫወቱን::

ተገርመን ማን እንደሚረከባቸው ጠየቅናቸው:: "ከካርል ጋር ዓለም ከተማ መጥተው የነበሩ 16 ፈረንጆች የግቢየን አትክልት ከጐበኙ በኋላ ሻይ ቅጠሉን ይጠጡ ነበር:: እነሱ ወደ አገራቸው ከሄዱ በኋላም በጣም ስለሚፈልጉት በየጊዜው እያሸግሁ እልክላቸዋለሁ" ሲሉ አወጉን:: ጥንጉጉንም አትራፊዎች ከእሳቸው በአንድ ብር እየተረከቡ ሶስት ብር እንደሚሸጡት ገለፁልን::

ይሄን የአትክልት ሥራ በመሥራታቸው በህይወታቸው ላይ ትልቅ ለውጥ እንደመጣላቸውም ወይዘሮ ዘውዲቱ አጫውተውናል:: ከዚህ አትክልት ሽያጭ በሚያገኙት ገቢ ልጆቻቸውን እንዳሳደጉና እስከ ሶስተኛ ዲግሪ እንዳስተማሩም ይናገራሉ:: ከዚህ በተጨማሪም በሶስት መቶ ሺህ ብር ወጪ መኖሪያ ቤት መሥራታቸውን ገልፀውልናል::

በግቢያቸው ውስጥ የሚያከናውኑትን ይህን የከተማ ግብርና ሥራ በወረዳው አስተባባሪነት በርካታ አርሶ አደሮችና የከተማ ነዋሪዎች እንደሚጐበኙት፤ በየስብሰባውም ስለሥራቸው

“ያንባዶ የነበረ ቦታም አልምቸ ደን አልብሸዋለሁ“ ወ/ሮ ዘውዲቱ ሙሉጌታ

“ለአትክልትና ለልጅ የተለየ ፍቅር አለኝ“ ወ/ሮ ዘውዲቱ ሙሉጌታ

እንዲሁም ስላገኙት ጥቅም እንደሚያስተምሩ ወይዘሮ ዘውዲቱ ይናገራሉ:: ይህ ጥረታቸው ውጤት እንዳመጣላቸው ሲገልፁም፤ "በፊት መርሐ ቤቴ ላይ የጓሮ አትክልት አይታወቅም ነበር:: አሁን ግን አብዛኛው ህዝብ የጓሮ አትክልትን ጥቅም እያወቀ በማልማት ላይ ነው" ይላሉ::

ጥረታቸውና ስኬታቸው በከተማ አስተዳደሩም ሆነ በወረዳው ዕውቅናንና ድጋፍን

እንዳስገኘላቸውም ወይዘሮዋ አጫውተውናል:: በ2000 ዓ.ም. የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ዓለም ከተማን ሲጐበኙ ወደ ሁለት ሺህ በሚጠጋ የከተማዋና የአካባቢዋ ነዋሪ ፊት መሸለማቸውንም ያወሳሉ::

ወይዘሮ ዘውዲቱ ያኔ በከተማ ግብርና ያከናወኑት ተግባርና ያመጡት ውጤት ተገልፆ በዚህ ጥረታቸውና ስኬታቸው ህዝብን ወክለው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ስጦታ እንዲያበረክቱ ሲጠሩ የተሰማቸው ደስታ ከፍተኛ ነበር "በዕለቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በባህሌ መሠረት እንቅ አድርጌ ስሜ ሽልማቱን ካበረክትሁላቸው በኋላ ወደ ጆሯቸው ጠጋ ብየ በ45 ዓመቴ አንድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሸለሜ በጣም ዕድለኛ ነኝ! አልኳቸው:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያኔ ያለ ገደብ ሳቁ:: ከዚያች ቅፅበት ጀምሮ 'ምን ብለሻቸው ነው እንደዚያ ከልባቸው የሳቁ?' እየተባልሁ ለሶስት ዓመታት ሙሉ ተጠይቄያለሁ:: ሆኖም ምስጢር ነው እያልሁ ሳልናገር ኖሬ ሲሞቱ ነው ምን እንዳልኳቸው የተናገርሁ" ሲሉ አውግተውናል::

ወ/ሮ ዘውዲቱ በ2000 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ከመሸለም ባሻገር እሳቸውም "ሞዴል አርሶ አደር" ተብለው አምስት ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ተሸልመዋል:: “ያን ባዶ የነበረ ቦታም አልምቸ ደን አልብሸዋለሁ” አሉን:: ቦታውን እንድናየውም ጠየቁን:: እኛም እርስዎ ባይሉም ቦታውን ማየታችን የግድ ነው አልናቸውና ጉዞ ጀመርን::

አምስት ደቂቃ ያህል እንደተጓዝን በመንገዱ የቀኝ ጠርዝ በመስመር ተተክለው ወደ ሚታዩት ዛፎች በጣታቸው እያመለከቱ "እነዚያን ዛፎች የተከልኳቸው እኔ ነኝ:: የሚገርማችሁ እነሱን ባልተክል ኖሮ ዛሬ በህይወት አታገኙኝም ነበር"

አሉን:: እኔና አብሮኝ ያለው የሥራ ባልደረባየ ግራ በተጋባ ስሜት ተያየንና እኮ እንዴት? ስንል ጠየቅናቸው::

"አሁን የምንሄድበትን ደን ያለማሁት በሌሊት በአስራ አንድ ሰዓት ሳይቀር በመሄድ ውኃ በማጠጣት፣ በማረምና በመኮትኮት ነው:: ይሄን የማደርገው ደግሞ ቀን በሥራ ስደክም እየዋልሁ ነው:: ማታ ደክሞኝ ስለምተኛ እንቅልፍ እንዳይጥለኝ ስልኬን ሰዓት ቀጥሬ ነው የማድረው:: ይሁን እንጂ፤ ስልኬን በአስራ አንድ ሰዓት እንድትቀሰቅሰኝ የሞላሁ መስሎኝ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ብዬ ሞልቻት ኖሮ ደጋግማ ጮኸች:: አስራ አንድ ሰዓት ሆኗል ብየ ስገሰግስ እዚህ ቦታ ላይ ጅብ አጋጠመኝ:: ወደ እኔ ሲመጣ በደመ ነፍሴ ሮጨ ተክየ ካሳደግሁት ዛፍ ላይ ወጣሁና በጅብ ከመበላት ዳንሁ:: ይሄውላችሁ አትክልት ለእኔ እንጀራ ብቻ ሳይሆን ህይወትም ነው" ሲሉ አስረዱን::

አሳዛኙን ገጠመኛቸውን እየተረኩልን ስንጓዝ በርቀት "ዜድ ሁለገብ መናፈሻ" የሚል የሰሌዳ ላይ ጽሁፍ ተመለከትን:: የልማት አርበኛዋ ወይዘሮ ዘውዲቱ እንደገለፁልን ቦታውን ለማልማት 180 ሺህ ብር ወጪ አድርገዋል:: ክትክታ፣ ዝግባ፣ ግራር፣ ኮሽም እና የመሳሰሉ ዝርያቸው በመጥፋት ላይ ያሉ እፅዋትን እንደተከሉ አስረዱን:: ወይራ፣ ቡና፣ አቦካዶ፣ ማንጐ፣ ጌሾ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ እንኮይ፣ ጥጥ፣… በወይዘሮ ዘውዲቱ የአትክልት ቦታ በስፋት ይገኛሉ:: ጤና አዳም፣ የሥጋ መጥበሻ፣ በሶ ብላ፣ እና ሌሎች ቅመማ ቅመሞችንም አሳዩን::

ወይዘሮ ዘውዲቱ መናፈሻ ውስጥ ያሉት እፅዋት ጥሩ እንክብካቤ እየተደረገላቸው ስለመሆኑ ውበትና ልምላሜያቸው ይመሰክራል:: ይህ ልምላሜና ውበት የወ/ሮ ዘውዲቱ የድካም ውጤት ነው:: በተጨማሪም የሚኮተኩታቸው፣ የሚያጠጣቸው የሚጠብቃቸው ዘበኛ ተቀጥሮላቸዋል:: አንዲት ከእነ ህፃን ልጇ ጐዳና ልትወድቅ የነበረችን ችግረኛ ወጣትም አስጠግተዋት ውኃ በማጠጣት፣ በማረምም ሆነ በመኮትኮት ታግዛቸዋለች::

የሌሎች ድጋፍም እንዳልተለያቸው፣ "ቀበሌው፣ ወረዳው፣… ሁሉም ከጐኔ ነው:: ብቻየን አይደለም ይሄን ሁሉ ያለማሁት:: ሾፌሮች በክረምት አትክልት በማጓጓዝ ይረዱኛል:: ግብርና ባለሙያ ይመድቡልኛል:: አንድ ባለሙያ ተመድቦልኝ አንድ ዓመት ሙሉ ረድቶኛል:: መርቄው፣ ምርቃቴ ደርሶለት አድጐ ወደ ዞን ሄዷል" በማለት ያመሰግናሉ::

ቦታው ላይ አትክልት ከመትከላቸው በፊት 28 ቢያጆ አፈር እንደተሞላበት የሚያወሱት ወይዘሮ ዘውዲቱ አንድ የአውራ ጐዳና ሠራተኛ “የምታለሚው ለህዝብ ጥቅምና ለአካባቢ ለውጥ ነው” በሚል ስምንት ቢያጆ አፈር በነፃ እንደደፋላቸውም ያስታውሳሉ::

ወይዘሮ ዘውዲቱ ይህ አረንጓዴ ቦታ ለመናፈሻነት እንዲያገለግል አልመው በመሥራት ላይ ናቸው:: ለዚህ ደግሞ “የቦታው ሰባ አምስት ከመቶው በደን መሸፈን አለበት” ስለሚባል በየጊዜው ችግኝ ተክለው ማሳደግ ይጠበቅባቸዋል:: ችግኞቹ አድገው ቦታው በዘር ሲሸፈን ወደ መናፈሻነት ይቀየራል:: ለሠርግ፣ ለልደት፣ ለስብሰባ፣ ለመዝናኛነት ያገለግላል:: ለዚህም አንድ መቶ ሀምሳ ሰው የሚይዝ አዳራሽና የቀረፃ ቦታ ለማዘጋጀት አስበዋል::

የልማት ጀግናዋ ወይዘሮ አንድ የግብርና ምርምር ባለሙያ “እዚህ ግቢ ንብ ብታንቢ ትጠቀሚያለሽ” በማለት እንደመከራቸውና እሳቸውም አስር ባህላዊ ቀፎዎች መናፈሻው ምሥራቃዊ ዳርቻ ሰቅለው እንደነበር ያወሳሉ:: ሆኖም አራጅ የሚባል አውሬ ቀፎውን በጭራው እየጠረገ ሲያጠፋባቸው አምስቱን ቀፎዎች ወደ ቤት እንደወሰዷቸው ገልጸዋል::

"ዓለም ከተማ እናት ሆስፒታል" ለሥራ በሄድንበት ጊዜም ግቢው ውስጥ የወይዘሮ ዘውዲቱ ሙሉጌታን አሻራ ተመልክተናል:: የግቢውን በር አልፈን ወደ ውስጥ ስንዘልቅ በቀኝ በኩል የተመለከትነው "ዘውዲቱ ሙሉጌታ ፓርክ" በሚል የተከለለው ቦታ በተለያዩ አበቦችና አትክልቶች የተዋበ ነው:: በመሆኑም የእናት ሆስፒታልን ግቢ ወደ ማስዋብ ሥራ እንዴት እንደገቡ ጠየቅናቸው::

ወደ ገጽ 30 ዞሯል

Page 25: 12 03 2009.pdf

ገጽ 25በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ሰሞነኛ ዜናዎች

አዲሱ አያሌው

(አዲሱ አያሌው)

የአውስትራሊያ አህጉር

ይንቀሳቀሳል ተባለ

ጠፈርተኛው ከህዋ ሆኖ መረጠ

ወደ ገጽ 28 ዞሯል

በዓለማችን በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ አቅራቢያ የሚገኘው የአውስትራሊያ አህጉር ከወቅቶች መቀያየር ጋር ተከትሎ እንደሚንቀሳቀስ ላይቭ ሳይንስ ዘግቧል፡፡

አህጉሩ እንቅስቃሴው ወደ ፊትና ኋላ ብቻ ሳይሆን ወደ ላይና ወደ ታች ከፍ ዝቅ እንደሚልም በተመራማሪዎች ተረጋግጧል፡፡ ይህ የአህጉሩ እንቅስቃሴ ከወቅቶች መቀያየር ጋር ተከትሎ በሚመጣው የውሀማ አካላት እንቅስቃሴ ምክንያት እንዲሆንም ተነግሯል፡፡

እንቅስቃሴው በጉልህ ሊለይና ሊታወቅ በሚችል መልኩ የሚከናወን ሲሆን ይህ ሁኔታ በደንብ መታወቁ ደግሞ ወደፊት በተለያዩ የሳይንስ ምርምሮች ትልቅ እገዛ እንደሚኖረውም ተመራማሪዎች ገልፀዋል፡፡

አዲሱ አያሌው

ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ለሆነ ጊዜ ሲያነጋግር ከቆየ በኋላ የተፈፀመው የአሜሪካ ምርጫ ያልታሰበውን ዶናልድ ትራምፕን የአገሪቱ ፕሬዝዳንት አድርጐ አልፏል፡፡ ድምፃቸውን የሰጡት ምድር ላይ የሚገኙት ብቻ ሣይሆን በህዋ ላይ የሚገኙት አሜሪካውያንም በምርጫው በመሳተፍ መብታቸውን ተጠቅመዋል፡፡

ኤች አይ ቪ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ልጆች ደም ውስጥ መኖሩ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት ባጭር ተቀጭቷል:: የፀረ ኤች አይ ቪ መድኃኒቱን ቫይረሱ ስለለመደውና የታለመለትን ግብ አለማሳካቱ ደግሞ ለሰዎች ሕይወት ባጭር መቀጨት አንዱ ምክንያት

ዓለማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ በጣም የተራቀቁ፣ የተወሳሰቡና የሰው ልጆች አዕምሮ እምቅ አቅም እንዳለው የሚያሳዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እያሳየችን ትገኛለች:: ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ የቴክኖሎጂውን ዘርፍ እጅግ የማራቀቅና በዓይን በቀላሉ ማየት ከሚቻለው ወደ ቅንጣቶች ደረጃ (Nanotechnology) የማሸጋገር ሁኔታዎች እየተስተዋለ ነው:: በአሜሪካው የሚችጋን ኢንስቲቲዩት ኦፍ ቴክኖሎጅ እውን የተደረጉት ፈንጅ ንጥረ ነገሮችን መለየት የሚችሉት ባዬኒክ ዕፅዋት ደግሞ ለዚህ ማሳያ ናቸው::

ባዩኒክ ዕፅዋት የሚባሉት በቅንጣት (ሞለኪውል) ደረጃ ከሚገኙ ንጥረ ነገሮች የተሠሩ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ክፍሎችን በተፈጥሯዊዎቹ ዕፅዋት ውስጥ በማስገባት የሚዘጋጁ ናቸው:: በተራቀቀ ዘዴ የሚገቡት እነዚህ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ክፍሎች ዕፅዋቱ ከተለመደው ውጭ የሆኑ ሌሎች አገልግሎቶችን (ተግባራትን) ያከናውናሉ::

በድረ ገፅ ከሚገኘው ዲስከቨሪ መፅሔት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የሚችጋን ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ኢንጅነሮች ስፒናች በሚባሉት ዕፅዋት ቅጠሎች ውስጥ እጅግ በጣም ትናንሽ ከሆኑት የካርቦን ቅንጣቶች የተሠሩ የሲሊንደር ቅርፅ ያላቸው ቱቦዎችን (Nanotechnology) በማስገባት ነው::

በሞለኪውል ደረጃ የሚገኙት ከካርቦን

የተሠሩት ቅንጣት ቱቦዎች ወደ ስፒናች ዕፅዋት ቅጠሎች ውስጥ ገብተው ከተቀበሩ ጀምሮ ቅጠሎቹ ፈንጅ ነገሮችን መለየት ወደሚችሉ ሴንሰርነት ይቀየራሉ:: እነዚህ ሴንሰር ቅጠሎችም ተቀጣጣይ ንጥረ ነገሮችን መለየት ብቻ ሣይሆን በሽቦ አልባ ዘዴ መረጃውን እንደ ተንቀሳቃሽ ስልክ በቀላሉ በእጅ ሊያዝ ወደሚችለው የማንበቢያ ትንሽ ኮምፒውተር ያስተላልፋሉ::

ምርጥ የምግብ ዕፅዋት በመሆን ለሰው ልጆች ፍጆታ እየዋሉ ባዩኒዝ ከሆኑ በኋላ የሚገኙ ስፒናቾች አሁን ከምግብነት ባሻገር እንደ ናይትሮ አሮማቲክስ

ያሉ ተቀጣጣይ የኬሚካል ንጥረ ነገሮችን መለየት ወደሚያስቸላቸው ደረጃ ተሸጋግረዋል::

ነገሩ እንዲህ ነው! በከርሰ ምድር ከሚገኘው ውሀ ውስጥ ከናይትሮ ኦሮማቲክስ ንጥረ ነገሮች አንዱ መኖሩ በዕፅዋቱ በተፈጥሯዊ መንገድ ናሙናው ከተለየ በቅጠሉ ውስጥ የተቀበሩት የካርቦን ቱቦዎች ይህንኑ የሚሳይ ምልክት ይለቁታል:: በዓይን በቀላሉ ሊታይ የማይችለው ይህ መረጃ ብልጭ ብልጭ የሚል ምልክት የሚሳይ ሲሆን ጨረርን በመጠቀም ምልክቱ መለየት በሚችሉ ካሜሪዎች ብቻ የሚነበብ ነው::

ስፒናችከምግብነት ወደ መርማሪነት

አዲሱ መመርመሪያ

ነው:: በየጊዜው በደም ውስጥ ስለሚገኘው የኤች አይ ቪ ሁኔታ በምርመራ በቀላሉ ማወቅ አለመቻሉ ደግሞ መድኃኒቱን ሙሉ በሙሉ ከመላመዳቸው በፊት አውቆ ሌሎች አማራጮችን መውሰድ አለመቻሉ ችግሩን ውስብስብ አድርጐት ቆይቷል::

ሳይንስቴክ ዴይሊ ሰሞኑን ያስነበበው ዘገባ በደም ውስጥ የሚገኘውን የኤች አይ ቪ ሁኔታ በቀላሉ ለማወቅ የሚያስችል የመመርመሪያ መሣሪያ እውን መደረጉን ያመለክታል:: ከለንደኑ ኢምፔሪያል ኮሌጅ እና ጀኖሚክስ እና ላይሲስ ከተባለው የግል

ኩባንያ የተውጣጡ ተመራማሪዎች የፈጠሩት ይህ መሣሪያ ኤች አይ ቪ አንድ የተባለው በደም ውስጥ የሚገኝ ቫይረስ ሁኔታ ለማወቅ የአሲድን መጠን የሚጠቀም ነው:: መሣሪያው የአሲዱን መጠን ከመረመረ በኋላ ውጤቱን በዩ ኤስ ቢ ስቲክ አማካኝነት የማሳወቅ አቅምም አለው::

ምርመራው የሚፈልገው አንድ ነገር ቢኖር ትንሽ የደም ጠብታን ብቻ መሣሪያው ላይ ማድረግ ነው:: የመመርመሪያ መሣሪያው ለአምራች ኩባንያዎችም ከማምረቻ ዋጋ አንፃር አዋጭና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኤች አይ ቪ በደማቸው ውስጥ ለሚገኝባቸው ሰዎች አገልግሎቱን በዝቅተኛ ዋጋ እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑንም ዘገባው ያመለክታል::

ምርመራው በደም ውስጥ የሚገኘውን የአሲድ መጠን ለውጥ መለካት የሚያስችል ሴንሰር እና በችፕ አማካኝነት መረጃውን ለዩኤስ ቢው የሚያሸጋግሩ ነገሮችን በማካተት የሚከናወን ነው:: ምርመራው አጠቃላይ ከግማሽ ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ የሚጠናቀቅ ሲሆን ከ90 በመቶ በላይ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ መሆኑም ተነግሮለታል::

የፀረ ኤች አይ ቪ መድኃኒቶች በኤች አይ ቪ ምክንያት ህመም እንዳይከሰት ለመከላከል የሚያስችሉ ጠቃሚ ነገሮች ናቸው:: ይሁን እንጅ አንዳንዴ ቫይረሱ መድኃኒቱን በሚላመድበት ጊዜ ፋይዳቸው ምንም ይሆናል:: ይህ ሲከሰት ደግሞ ሰዎቹ እና ሀኪሞቹ በቶሎ ማወቅ ይገባቸዋል:: የዚህ ሁኔታ በቶሎ መታወቁ ደግሞ በሽተኞች ሌሎች የመድኃኒት አማራጮችን እንዲያገኙ ከማገዙም በላይ መድኃኒቱን የተለመደው የኤች አይ ቪ ቫይረስ ዝርያ እንዳይሰራጭም የጐላ ጠቀሜታ አለው::

የመሣሪያው መገኘት በተለይ በድሀ ሀገራት ለሚገኙ እና የህክምና ተቋማት በአቅራቢያቸው ለማይገኝ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በቀላሉ ሁኔታዎችን ያለማንም እገዛ በራሳቸው ብቻ እንዲያውቁ ያስችላቸዋል::

በዓለም ዓቀፍ የህዋ ጣቢያ ላይ በአሁኑ ወቅት በምርምር ሥራ ላይ ተጠምዶ የሚገኘው ጠፈርተኛው ቫን ኪምብሮው ምሥጋና ለቴክኖሎጂ እንጅ ከህዋ ላይ ሆኖ ድምፁን ለሚፈልገው ዕጩ መስጠት ችሏል፡፡ በፌዴራል ፖስት ካርድ አፕልኬሽን አማካኝነት ከስድስት ወራት በፊት በመራጭነት የተመዘገበው ይህ ጠፈርተኛ በምርጫው ዕለት ድምፁን በመስጠት መብቱን ተጠቅሟል፡፡

ካሁን በፊት ዴቪድ ዎልፍ የተባለው አሜሪካዊ እ.ኤ.አ በ1997 በተደረገው አካባቢያዊ ምርጫ ሚር ከተሰኘችው የራሺያ የህዋ ጣቢያ ላይ በመሆን ድምፁን በመስጠት የመጀመሪያው አሜሪካዊ እንደሆነም ዘገባው ያመለክታል፡፡

Page 26: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 26

ትኩረት... ከገፅ 5 የዞረ

የመድኃኒት አቅርቦቱ ምን ያህል አስተማማኝ ነው?

በዚህ ወቅት በመድኃኒት አቅርቦት በኩል ችግር የለም፤ ከዚህ ቀደም ይቀርብ የነበረው የውስጥ ደዌ ሌሽማኒያሲስ (ካላዛር) መድኃኒት ብቻ ነበር::

አሁን ላይ ግን የቆዳ ላይ ሌሽማኒያሲስ መኃኒትም መቅረብ ጀምሯል:: በርግጥ ለአንድ ታካሚ የሚወጣው መድኃኒት ወጭ በጣም ከፍተኛ ነው፤ በሀገር ደረጃ ሲወሰድ በጣም ከባድ ነው:: ነገር ግን ወጭውን መንግሥት እየሸፈነ በነፃ ነው እየተሰጠ ያለው፤ ምክንቱም በሽታው በጣም ከባድና ማኅበራዊና ስነ-ልቦናዊ ጫና የሚያስከትል ከዚያም አልፎ ሕይወትን የ ሚ ነ ጥ ቅ ነውና::

ሕክምናው በመድኃኒት ብቻ ሳይሆን በምግብም መታገዝ ስላለበት ታካሚዎቹ የማዕድ ይዘታቸውን ማበልፀግ እንዳለባቸውም ያስገድዳል፤ ከተለመደው የምግብ ፍጆታ በላይ አሰባጥሮ መመገብንም ይጠይቃል:: ስጋ፣ እንቁላል፣ ወተት፣ … በተጨማሪነት መመገብን ይጠይቃል:: ከመድኃኒት አቅርቦት ጋር በተያያዘ ግን አሁን ላይ ችግር የለም፤ በእርግጥ ከዚህ ቀደም የከፋ ሊባል የሚችል ችግር ነበር::

በክልላችን ሌሽማኒያሲስ

በወረርሽኝ መልክ ተከስቶ ያውቅ ነበር፤ አሁን እንዳይከሰት የሚያስችል ሥራ ተሠርቷል ማለት ይቻላል?

በደቡብ ጎንደር መስተዳደር ዞን ሊቦከምከም አካባቢ በወረርሽኝ መልኩ በ1997 ዓ.ም ተከስቶ ነበር፤ እንዲያውም የበሽታው ምንነት ሳይታወቅ በርካታ የሰው ሕይወት ቀጥፏል:: ያኔ ለብዙ ሕይወት መጥፋት ምክንያት የሆነው ስለበሽታው ግንዛቤ አለመኖሩና ሕክምናውም በሰፊው የሚሰጥ ስላልነበረ ነው:: በዚህ ወቅት ግን ሕብረተሰቡም

ሆነ የጤና ባለሙያዎች የተሻለ ግንዛቤ ስላላቸው ወረርሽኝ የመከሰት ዕድሉ ጠባብ ነው:: አስተማማኝ የሆነ የሕክምና አቅምና ግንዘቤ ተፈጥሯል::

የሌሽማኒያሲስ አስተላላፊ አሸዋ ዝንቧን ንክሻ መከላከል የሚቻለው እንዴት ነው?

የአሽዋ ዝንቧ መከላከል የሚቻለው የመራቢያ ምቹ ቦታዎቿን በማጽዳት ነው:: በቤት ፍርስራሾች፣ በቀይ ግራር ቅርፊቶች፣ በምስጥ ኩይሳዎች፣ ሽኮኮዎችና ውሾች ሁሉ ለአሸዋ ዝንቧ መጠለያነት ያገለግላሉ:: ስለዚህ እነዚህን አካባቢዎችና አካላት ማጽዳት ተገቢ ነው:: በመቀጠል ደግሞ ቤትን ልክ ለወባ ትንኝ እንደሚረጨው በኬሚካል መርጨትና በላዩ ላይ ቀለም አለማስቀባትና አለመለቅለቅ ይገባል:: ሌላኛው አማራጭ ደግሞ የወባ ትንኝ አጎበርን መጠቀም ነው፤ በእርግጥ መጠኗ ከወባ ትንኝ በጣም ያነሰች ስለሆነች የአሸዋ ዝንቧ በአጎበሩ ቀዳዳዎች ማለፏ አይቀርም:: ነገር ግን አጎበሩ ኬሚካል የተነከረ

ስሚሆን ላዩ ላይ አርፋ ለመግባት ከመሞከሯ በፊት ትሞታለች::

ለአሸዋ ዝንቧ የሚሆን ራሱን የቻለ አጎበር አለ፤ ነገር ግን ዋጋው በጣም ውድ በመሆኑ እየቀረበ አይደለም:: ችግሩ አገር አቀፍ ነው፤ ምናልባት ወደፊት አማራጩ እንዲታይ ጥያቄዎችን እያቀረብን ነው::

የሌሽማኒያሲስ በሽታ የሚከሰትበት የራሱ ወቅት አለው?

የአሸዋ ዝንቧ ዓመቱን ሙሉ አለች:: በእርግጥ ከፍተኛ ጉዳት የምታደርሰው ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት እንደሆነ ይታመናል:: ነገር ግን የበሺታው ምልክቶች የሚታዩት ከሁለት ወር እስከ ስድስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ስለሆነ በአብዛኛው ታማሚዎች ወደ ጤና ተቋም የሚመጡት ከመስከረም እስከ ታህሳስ ባሉት ጊዜያት ነው:: ታማሚዎች ደግሞ የበሺታውን ምልክት ቢያሳዩም

ባያሳዩም በሽታውን ሊያስተላልፉ ስለሚችሉ በማናቸውም ወቅት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል::

ወደ ምዕራብ አማራ ቆላማ አካባቢዎች በብዛት ወጣቶች ለሥራ ይንቀሳቀሳሉ፤ በዚህ ወቅት ለበሽታው እንዳይጋለጡ ምን እየሠራችሁ ነው?

እንዳልከው ወጣቶቹ ከሰሊጥ እርሻዎች ከሚፈጠረው የሥራ ዕድ ተጠቃሚ ለመሆን ወደ ሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ … አካባቢዎች ይሄዳሉ:: በእነዚህ አካባቢዎች ደግሞ የበሽታው ስርጭት ከፍተኛ ነው:: ሙቀትም ስለሆነ ወጣቶቹ ስስና ሰውነትን የማይሸፍኑ አጫጭር ልብሶችን ይጠቀማሉ፤ ይህም ለአሸዋ ዝንቧ ያላቸውን ተጋላጭነት ከፍ ያደርገዋል:: ለማረፍ ሲፈልጉም ከግራሮቹ ሥር ነው የሚቀመጡት፤ ማታ ማታም ውጭ ላይ የማምሸትና ሌሊቱንም ውጭ ላይ የማሳለፍ ሁኔታዎች፣ በቂ ምግብ ያለማግኘት ጉዳይም ይኖራል:: እነዚህ ሁሉ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ናቸው::

ስለዚህ ወቅቶቹን ጠብቀን ባለሙያዎችን በመመደብ ሠራተኞቹ በሚሰባሰቡባቸው ቦታዎች ሁሉ እየተገኙ እንዲያስተምሩ እናደርጋለን:: ዛፍ ሥርም ሲቀመጡና ሲተኙ አጎበር በእንጨት ወጥረው እንዲጠቀሙ እያስተማርን ነው:: ምክንያቱም ወጣቶቹ ግንዛቤ ካልተፈጠረላቸው በበሽታው እንደተያዙ ምልክቱን ሳያሳዩ ወደ መጡበት አካባቢ ሊሄዱና ከዚያ ታምመው ሕክምና ሳያገኙ ሕይወታቸው ሊያልፍ ስለሚችልና ወደ አካባቢያቸው ወስደውም በሽታውን ሊያዛምቱ ስለሚችሉ ትኩረት ሰጥተን እየሠራን ነው:: የበሽታው ስርጭት ባለባቸው አካባቢዎች ሁሉ በበቂ ሁኔታ ግንዛቤው ተፈጥሯል፤ ነገር ግን ከእነዚያ አካባቢዎች ውጭ ሰፊ ሥራ የሚጠይቀን ነው::

የአማራ ክልል የሌሽማኒያሲስ ስርጭት ምን ያህል ነው?

በተጋላጭነት ደረጃ ከአማራ ክልል ሕዝብ ከዘጠኝ ሚሊዮን በላዩ ተጋላጭ ነው:: በተለይ

የክልሉ ምዕራባዊ ቆላማ አካባቢዎች ደግሞ የበለጠ ስጋት አለባቸው:: ከአጠቃላይ በአገሪቱ ሪፖርት ከሚደረግ የሌሽማኒያሲስ ስርጭት ሲሶው በአማራ ክልል የሚቀርብ ነው:: ሌሎች ክልሎች ማለትም ትግራይ፣ ኦሮሚያና ጋምቤላ ስርጭቱ ቢኖርም የአማራና ትግራይ ክልሎች ከአጠቃላይ ሀገሪቱ ሁለት ሦስተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ::

ይህን ያህል አሳሳቢ በሽታ ሆኖ ሳለ ለምን ትኩረት አልተሰጠውም?

ትኩረት ተነፍጎታል ያልከው ትክክል ነው:: ከዚህ ቀደም በተፈጠረ ሀገራዊ መድረክም ሌሽማኒያሲስና ሌሎችም ወደ ስምንት የሚደርሱ በሽታዎች ትኩረት እንዳልተሰጣቸው ተገምግሞ አቅጣጫ ተቀምጧል:: ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለሌሽማኒያሲስ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል፤ ለውጦችም እየመጡ ነው:: ሕክምናውም እንዲስፋፋ ተደርጓል፤ የአሰሳና ቅኝት ሁኔታም እንዲጠናከር እየተደረገ ነው:: የመገናኛ ብዙኃኑ ግን ትኩረት አልሰጡትም፤ ለዚያም ነው ለብዙው ሰው አዲስ በሽታ የሚመስለው::

ለሰጡን ሙያዊ ማብራሪያ

አመሰግናለሁ!

ግንዛቤ መፍጠር በሚያስፈልግበት ወሳኝ ወቅት እንግዳችሁ አድርጋችሁ ለብዙዎች ግንዛቤ የምፈጥርበትን ዕድል ስለሰጣችሁኝ እኔም በጣም አመሰግናለሁ!

ከገጽ 19 የዞረ

ኬንያ...

ሁኔታውን ሲቃወሙ የከረሙት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የኬንያን የጊዜ ማሻሻያ ተከትሎ ሃገሪቱ ውሳኔውን ደግማ እንድታጤነው እየወተወቱ ነው::

ባለፈው ግንቦት ወር የኬንያ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጆሴፍ ንካሴሪ ሃገራቸው የስደተኞቹን ጉዳይ በሚመለከት እንዴት መመለስ እንዳለባቸው ከተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ከሶማሊያ መንግስት ጋር በቅርበት ሲሰሩ መቆየታቸውን ያስታወሰው ቢቢሲ ውሳኔው የማይለወጥ እንደሆነ መናገራቸውን ጽፏል::

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ግን ውሳኔውን ተከትሎ በሶማሊያ ያለው ብጥብጥና አለመረጋጋት ደግሞ እንዲያገረሽ ያደርጋል በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ እያቀረቡበት ነው::

ኬንያ የዳዳብን የመዝጋት ውሳኔ ስታራዝም ይህ የመጀመሪያ አይደለም ያለው ቢቢሲ ቁርጥ ያለው ጊዜ ወደፊት እንደማይታወቅም ገልጿል::

ኬንያ ካምፑን ለመዝጋት የወሰነችው ከሽብር ጥቃት በነጨ መሆኑ የሚታወስ ነው::

Page 27: 12 03 2009.pdf

ገጽ 27በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. እጽዋት/እንስሳት

ሙዋሊሙ ኢልየኢል ዓሣ ሳይንሳዊ መጠሪያው አንጉሊፎረሞስ ይባላል:: በዓሣ ተመራማሪዎች ዘንድ “ኤፍ-ቢ ዋን” የሚል የቤተ-ሙከራ ክፍል ሥም ተሰጥቶታል:: በዓለም ላይ ከ800 በላይ የተለያየ ዝርያ አለው:: የዝርያው ልዩነት በቅርፁ፣ በመጠኑ፣ በቀለሙ፣… የመጣ ነው::

የኢል ዓሣ ቅርፁ እባብ የመሰለ ነው:: ጎንና ጎኑ ደግሞ እንደ ጎራዴ ሰይፍ አለው:: ሰይፉ በጣም ስል በመሆኑ ጠላቱን መትሮ ይጥልበታል:: ሲዋኝ አላስኬድ እያለ የሚያስቸግረው ዕፅዋት ቢገጥመው በሰይፉ ይቆራርጠዋል::

ይህን ዓሣ ለማስገር ተብሎ የተዘጋጀውን መረብ ሳይቀር የመበጣጠስ ብቃት አለው:: በመሆኑም አስጋሪዎች ትልቁን የኢል ዓሣ በጦር መሣሪያ ተኩሰው በማቁሰል ወይም በመግደል ይይዙታል እንጅ ለማጥመድ አይሞክሩትም::

የኢል ዓሣ የራስ ቅል ጠፍጣፋ ነው:: በጎንና በጎን በኩል ትልልቅ ሊባል የሚችል ጆሮ አለው:: ጆሮው ወደ ጎን የተወደረ ነው:: በውሀ ውስጥ ሰጥሞ (ጠልቆ) ሲዋኝ በጆሮው ቀዳዳ ውሀ እንዳይገባበት ጆሮውን እጥፍ አድርጐ ይዘጋዋል::

ከውሃ ውስጥ ይሁን ከውጭ የሚጣልን ነገር ድምፅ ይለያል:: በተለይ በቀን ንቁና ቁጡ ነው::

ከጆሮው ትንሽ ፈቀቅ ብሎ ትልልቅ ጥቋቁር ዐይኖቹን ከብለል-መለስ ሲያደርጋቸው ያስፈራል:: ዐይኖቹ በቀን ካልሆነ በሌሊት የማየት አቅማቸው ደካማ ነው:: ስለሆነም የኢል ዓሣ በሚርመሰመስበት ባህር ወይም ውቅያኖስ ሌሎቹ የዓሣ ቤተሰቦች የሚንቀሳቀሱት በሌሊት ይሆናል::

ጥርሱ በጣም ደቃቅ ይሁን እንጅ ስልና ጠንካራ ነው:: ሦስት- ሦስት ጥርሶች ተያይዘው ተዋቅረዋል::

ካልተሰበረ በስተቀር አንዱ ከተንቀሳቀሰ ወይም ከወለቀ ሦስቱንም ያጣል ማለት ነው:: ቅርፁም የእንግሊዝኛውን “W” ፊደል የመሰለ ነው::

በአፉ ግራና ቀኝ በኩል አንዳንዱ የኢል ዓሣ ሁለት አንቴናዎች አሉት:: በአንቴናው አማካኝነትም በሌሊት ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ይችላል:: ምክንያቱም አንቴናው አቅጣጫ ይጠቁመዋልና::

ኢል የሚተነፍሰው በጎንና በጎን ባለው ስንጥቡ አማካኝነት ነው:: አየር ሲያስገባና ሲያስወጣ ስንጥቡ በሀይለኛው ስለሚከፈት ቢደበቅ እንኳ ያለበትን አካባቢ ያሳብቅበታል::

የኢል ዓሣ በተፈጥሮው ኤሌክትሪክ ማመንጨት የሚያስችለው ስድስት ሺህ ገደማ ህዋስ (electrocyte cell) አለው:: ይህ ህዋስም 600 ሾልት ኮረንቲ እንዲያመነጭ ያደርገዋል::

አንድ የኢል ዓሣ ኮረንቲ ባመነጨበት ቅፅበት በቅርብ ርቀት የተገኘን ፍጡር ኩምትርትር አድርጎ ይገድለዋል:: በአቅራቢያው ከብረት የተሰራ ጀልባ ካለ እንኳ በኮረንቲው የማውደም (የማጋየት) አቅም አለው::

በዚህም ምክንያተ የሰው ልጅ የኢል ዓሣን አስቦ ለማስገር አይንቀሳቀስም- አይችልምም:: ስለሆነም የኢል ዓሣ ከዓሣ ዝርያዎች መካከል አደጋ ያልተጋረጠበት በሚል ተፈርጇል:: ቁጥሩም እያደር መጨመር እንጅ መቀነስ አይስተዋልበትም::

በልቶ ከጠገበ፣ ጠጥቶ ከረካ፣ አየሩ ደስ ሲለው ባህሩ ወይም ውቅያኖሱ ላይ ዥው ብሎ ይተኛል:: እርስ በርስ በመቀናጣት ይዝናናል:: በማዕበሉ አማካኝነት ወዲህ ይመጣና እንደገና እየዋኘ ይመለሳል:: ደግሞ ተመልሶ ይመጣል::

የኢል ዓሣ በሰዓት ያለ እረፍት ስምንት ኪሎ ሜትር ይዋኛል:: ሲዋኝ የሚያስቸግረውን “ፕላንክተን” የተሰኘ ተክል ጎንና ጎን ባለው ጐራዴ መሳይ ማጭዱ ይበጣጥሰዋል:: አንድም ተክል ወይም ሐረግ አይገድበውም::

የኢል ዓሣ ሥጋ ተመጋቢ ነው:: ዓሣ፣ ወፍ፣ … ዋነኛ የምግብ ምርጫዎቹ ናቸው:: የሰውን ሥጋ ሳይቀር ይመገባል:: በልቶ ከጠገበ ደም በመመጥመጥ ይረካል:: ዓሣዎችን ገድሎ በመጣልም ሀሴት ያደርጋል::

ኑሮው ጋርዮሻዊ ነው:: እንቁላል የሚጥሉት፣ የሚዝናኑት፣ የሚዋኙት፣ የሚሰደዱት በጋራ ነው:: አንድን ጠላት ሲያጠቁም በህብረት ነው:: መጠለያቸውንም ከባህር /ውቅያኖስ/ በታች ባለ ጭቃ ላይ ያደርጋሉ:: የኢል ዓሣ እስከ አራት ሺህ ሜትር ጥልቀት ባለው የቤርሙዳ ትሪያንግል አካባቢ ይመሽጋል:: እናም በዘመናዊ የዓሣ የማስገሪያ ቴክኖሎጂም ቢሆን አይደፈርም::

የሚተነፍሰው በየ10 ደቂቃው ልዩነት ነው:: እናም ድካም የለበትም::

ቀለሙ የተለያየ ነው:: ጥቁር፣ ነጭ፣ ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ግራጫ… ይጠቀሳሉ:: በተለይ ሰማያዊ ቀለም ያለው ኢል ከውሀው ጋር የተመሳሰለ ነው::

የኢል ዓሣ ፀሀይ ካሸለበችበት ሰዓት ጀምሮ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀሱን ያቆማል:: በቃ! በሌሊት አድፍጦ ይተኛል:: የዚህ ሁሉ ዋናው ምክንያት ዓይኑ በሌሊት የማየት አቅሙ ደካማ መሆኑ ነው::

እድሜዋ ለርቢ የደረሰ የኢል ዓሣ ሽሏ ሲሞቅ ተባዕቱን አፈላልጋ ትተናኮሰዋለች:: በቀለበት መሀል አስገብታ ትዞረዋለች:: ሲበዛ ታዋክበዋለች:: ከአካሏ ደስ የሚል ጠረን በማመንጨት አካባቢውን በማወድ ፍላጐቱን ታነሳሳዋለች:: ሳይወድ በግድ አሟሙቃ እንዲጎመርባት ታደርጋለች::

በተለይ የክረምቱ ወቅት አልፎ በጋው በሚጠባበት ጊዜ እንስቷ በሀይለኛው ትዳራለች:: እንቁላል የምትጥልበትን አካባቢ የሚመርጠው ተባዕቱ (ባልየው) ነው:: ሳሊቫ (Salivva) የተሰኘ ሙጫ መሳይ ፈሳሽ በማመንጨትም እንቁላሉን ከድንጋይ፣ ዕፅዋት… ጋር ያጣብቀዋል:: በየተራም እያሞቁ ይጠብቁታል:: ይንከባከቡታል:: በአንድ የርቢ ወቅት ብቻ አንዷ 17 ሺህ እንቁላል ትጥላለች::

የኢል ዓሣ ከሥጋው በበለጠ በኢንዱስትሪ የሚቀነባበረው የምግብ ዘይቱ ተፈላጊ ነው::

በእሳት ቃጠሎ የተጠቃ ግለሰብ የኢል ዓሣ ዘይትን ቢመገብ ቁስሉ በቀላሉ ይጠገናል:: የልብ ድካምን ያስወግዳል:: ካንሰርን ይከላከላል:: የአእምሮ ጭንቀትን ይቀርፋል:: መርሳትን ያስወግዳል:: አእምሮው አርቆ እንዲያስብ ያደርጋል:: የአፍና የቆዳ ካንሰርን ይከላከላል:: አስምን ያስወግዳል:: የጡትና የመራቢያ አካል ካንሰርን አስቀድሞ ይከላከላል:: የህፃናትን እድገት ያፋጥናል::

የኢል ዓሣ ዘይትን የተመገበ ሰው በስንፈተ ወሲብ በሽታ አይጠቃም::

የኢል ዓሣ ለርቢ የሚደርሰው በአምስት ዓመቱ ሲሆን አማካይ የእድሜ ጣሪያው ደግሞ 22 ዓመት ነው:: ዋነኛ ጠላቱ ሠው ነው:: www.fish life.com እና Eel.com የመረጃ ምንጮቻችን ናቸው::

ከኢል የተፈበረከ መድኃኒት

Page 28: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 28

በደሴ ከተማ በኬብል ዝርጋታ የሚሰሩ 32 ኢንተርፕራይዞች አሉ

ከገጽ 3 የዞረ

የመኸሩ...

ከገጽ 25 የዞረ

ስፒናች ...

በኩታ ገጠም ማሳ ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ ተጠቅመው በመስመር የተዘራ የስንዴ ሰብል

ከገጽ 17 የዞረ

አዝጋሚው...ይህም ማለት እነዚህን ተግባራት ለመከወን

ቦታ፣ ሼድ፣ መብራትና ውሀ የሚፈልጉ በመሆናቸው እነዚህን መሰረተ ልማቶች ለማሟላት የሚመለከታቸው አካላት አቅርቦቱን የማጓተት ችግር ስለነበር መሆኑን አብራርተዋል::

ሌላው በበጀት ዓመቱ መግቢያ ላይ የሚሰሩ ስራዎችን ለይቶ የመግባት ችግር እንደነበረባቸው ገልፀዋል:: “የለማ እና ያ ልለማ ቦታን መለየት አልቻልንም ነበር” ይላሉ:: በዚህም ምክንያት ወደ ስራ የተገባው ከህዳር ወር በኋላ እንደነበር አስረድተዋል::

ተገንብተው መብራት ባለመግባቱ ምክንያት ስራ ያልጀመሩ ሼዶች አሁንም ድረስ መኖራቸውን አቶ ደመቀ ጠቁመዋል::

በስራ ፈላጊው በኩልም በመንግሥት ፕሮጀክት ላይ ብቻ የማተኮር የአመለካከት ችግር መኖሩን አቶ ደመቀ አንስተዋል:: በራሳቸው ቆጥበው ገንዘብ ይዘው ወደ ስራ የሚገቡ ወጣቶች ችግርም አለ ብለዋል:: ለዚህም ችግሩ የነበረው በሁሉም አቅጣጫ ነበር የሚል እምነት አላቸው::

በዘርፉ የሚሰሩ ባለሙያዎች በየጊዜው ስራ መልቀቅ ሌላው ችግር መሆኑን አቶ ደመቀ ገልፀዋል:: አንድ ሙያተኛ ከለቀቀ በኋላ አዲስ ሙያተኛ መጥቶ ስልጠና ወስዶ ስራው ገብቶት ወደ ስራ እስከሚገባ ድረስ ደግሞ ጊዜ ያስፈልጋል ይላሉ::

አቶ ደመቀ በቀጣይ ችግሩን ለመቅረፍ ከቢሮውም ጋር በመነጋገር ወደመፍትሄ እያመሩ መሆኑን ተናግረዋል:: በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ላይም የተለያዩ ስራዎችን ሲሰሩ መቆየታቸውንም ገልፀዋል:: በተለይ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የሚሰሩ ቦታ የማዘጋጀትና መሰል ስራዎችን አጠናቀው ወደ ስራ እየገቡ እንደሚገኙ ነው የተናገሩት::

ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር መረጃ እየተለዋወጡ በሰፊው ለመስራትም እየሞከሩ እንደሚገኙ አቶ ደመቀ አስረድተዋል::

አንድ ኢንተርፕራይዝ ለማቋቋም እስከ ስምንት ሴክተሮች ድረስ መሄድና ጉዳይ ማስፈፀም ይጠበቅበት ነበር:: ይህም አሰራሩ ላይ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል:: ይህንን ችግር ለመቅረፍና ስራው ወደ አንድ

እንዲመጣ ለማድረግ በከንቲባው የሚመራ ምክር ቤት ተቋቁሟል:: ምክር ቤቱ በየወሩ እየገመገመ ስራውን ይከታተላል ብለዋል:: በምክር ቤቱም የኢንተርፕራይዞች ተወካዮች እንዲካተቱ ተደርጓል:: ይህም ዘንድሮ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር ያደርጋል የሚል እምነት አሳድሮባቸዋል::

በዚህ ዓመትም 20 ሺህ የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ እየሰሩ ነው:: ለዚህም የእድገት ተኮር ዘርፎች /ማኑፋክቸሪንግ/ ላይ የተሻለ ውጤት ለማምጣት እና የሼድ ግምባታዎችን በክላስተር ለማደራጀት እየተሰራ መሆኑን አቶ ደመቀ ተናግረዋል::

ወጣቶቹ በሚደራጁበት ጊዜም እንደየትምህርት ዝግጅታቸው እንዲሆን እንሰራለን ብለዋል::

ነባር ኢንተርፕራይዞችን ማጠናከርና ደረጃውን ማሻሻልም ሌላው ትኩረት የሚደረግበት ጉዳይ መሆኑን ጠቁመዋል::

በ018 ቀበሌ 478 ሄክታር የእርሻ መሬት እንዳለና ከዚሁ ውስጥ 321 ሄክታሩን ኩታ ገጠም ማሳ (በክላስተር) በስንዴ ለመሸፈን አቅደው ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረጋቸውን የገለፁልን ደግሞ የቀበሌው የግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰብስቤ እሸቴ ናቸው፡፡

እንደ አቶ ሰብስቤ እሸቴ ገለፃ በቀበሌው ኩታ ገጠም ማሳን በተመሣሣይ ዘር (በክላስተር) የመዝራት ቴክኖሎጅና ግብአት የመቀጠም ሁኔታ አደረጃጀቶችን በመጠቀም ባደረጉት ውይይትና መግባባት ያሳኩት ነው፡፡ በመሆኑም በተለይ መሬቱ “ለስንዴ አይሆንም” በሚል አርሶ አደሩ ብዙም ለእርሻ ሳይጠቀምበት በኖረው በአምባ መጣያ ጐጥ የሚገኘው 68 ሄክታር መሬት በክላስተር የተዘራውን ስንዴ ጨምሮ በሁሉም አካባቢ ሰብሉ በጥሩ ቁመና ላይ እንደሚገኝ አቶ ሰብስቤ አረጋግጠዋል፡፡

በአጠቃላይ የዝናቡ ስርጭት ጥሩ መሆኑ፣ አርሶ አደሩ ቴክኖሎጅን በአግባቡ ተጠቅሞ መስራቱ እና ግብአት በበቂ መቅረቡ ለዘንድሮ ሰብል ቁመና እንዲያምር እና ካለፉት ዓመታት የተሻለ እንዲሆን አግዘዋል፡፡ በዚህም በአንድ ሄክታር ከ25 እስከ 31 ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ የነበረ ሲሆን አሁን ባለው ቁመና ሲታይ ደግሞ በሄክታር እስከ 35 ኩንታል ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ሰብስቤ ተስፋቸውን ገልፀዋል፡፡

አርሶ አደሩ ምርቱን በወቅቱ ካነሳ በኋላ ወደ መስኖ ልማት እንዲገባ ዝግጅት እየተደረገና ስልጠና እየተሰጠ እንደሆነም አቶ ሰብስቤ ገልፀዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ አብዛኛው አርሶ አደር የዝናብ ውሀን በየጓሮው ጉድጓድ በመቆፈር ሰብስቦ መያዝ መቻሉንም ሀላፊው ነግረውናል፡፡

እንደ ወረዳው አጠቃላይ ተጨባጭ ሁኔታ

ሲታይ ቀበሌው ዝናብ አጠርነቱ መረጋገጡን የጽ/ቤት ሀላፊው ጠቁመዋል፡፡ በመሆኑም አርሶ አደሮቹ በየማሣዎቻቸው ላይ ጉድጓድ ቆፍረው ጅኦ ሜምብሬን በማንጠፍ የዝናብ ውሀን እንዲያጠራቅሙ ስልጠናና ድጋፍ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በዚሁ መሰረትም በየአካባቢው 19 የውሀ ማቆሪያ ጉድጓዶች ተቆፍረውና ጅኦ ሜምብሬን ለብሰው የዝናብ ውሀ እንዲያጠራቅሙ ተደርጓል፡፡

የጽ/ቤት ኃላፊው እንደተናገሩት አርሶ አደሮቹ ይህን የተጠራቀመ ውሀ በመጠቀም የተለያዩ የጓሮ አትክልቶችን በማልማት ከራሳቸው ፍጆታ ባለፈ ለገበያ አቅርበው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ታስቧል፡፡

በቀበሌው 16 ነጥብ አምስት ሄክታር መሬት በክረምት በተሰበሰበ ውሀ ለማልማት የታቀደ ሲሆን ከዚህ ውስጥ እስካለፈው ወር መጨረሻ ድረስ በ10 ነጥብ አምስት ሄክታሩ ማሣ የዝግጅት ሥራ መጀመሩን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን በድርቅ ተጠቅተው ከነበሩት እና ዝናብ አጠር ከሆኑት ወረዳዎች መካከል አንዷ እንደሆነች የገለፁት ደግሞ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ኦቶ ዳግማዊ መርሻ ናቸው፡፡ አቶ ዳግማዊ እንደነገሩን በ2008/2009 የምርት ዘመን የነበረውን የተስተካከለ የዝናብ ስርጭት እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ያለፈውን ለማካካስ ከቅድመ ዝግጅት ጀምረው ጠንካራ ስራ ሰርተዋል፡፡ በመኸሩ ወቅት በሰብል ሊሸፍኑት አቅደውት የነበረውን 20 ሺህ 741 ሄክታር መሬት በሙሉ አሳክተውታል፡፡ ከዚህ ውስጥ 7 ሺህ 830 ሄክታሩ በስንዴ የተሸፈነ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ደግሞ አራት ሺህ 613 ሄክታር በኩታ ገጠም ማሳ በተመሣሣይ ዘር (በክላስተር) መሸፈኑን አቶ ዳግማዊ አስረድተዋል፡፡

አጠቃላይ በመኸሩ ወቅት በተለያዩ ሰብሎች ከተሸፈነው ማሣ 523 ሺህ 012 ኩንታል ለማምረት ታቅዶ የተገባ እንደሆነ የገለፁት አቶ ዳግማዊ አሁን ባለው የሰብል ቅድመ ግምገማ ከዕቅዱ በላይ እንደሚሳካም ጠቁመዋል፡፡ እኛ በነበርንበት ወቅት

ከአበባ ሰብሎች በቀር ሌሎች ሰብሎች እየተሰበሰቡ እንደሆነም አቶ ዳግማዊ አጫውተውናል፡፡

ምርቱ ከተሰበሰበ በኋላ በመስኖ ልማት አርሶ አደሩ እንዲሰማራ ቅድመ ዝግጅት ከወዲሁ መጀመሩን የተናገሩት አቶ ዳግማዊ ለዚሁ ሥራም

ጅኦሜምብሬን መስራጨቱን ገልፀዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ የወንዝ ጠለፋ ስራዎችን፣ የህብረተሠብ ኩሬዎች የጉድጓድ ውሀን፣ ባህላዊ ምንጮችን የማጐልበት ሥራዎች እና ሌሎችም ተግባራት መከናወናቸውን አቶ ዳግማዊ ተናግረዋል፡፡

ካሜራው እንደተንቀሳቃሽ ስልክ በቀላሉ መያዝ በሚችለው ትንሽ ኮምፒውተር ጋር የሚያያዝ ነው:: ይህ ጨረርን የሚችሉ ካሜራዎች የተገጠመለት ትንሽ ኮሚፒውተር ምልክቱን ከሚያነበው ካሜራ መረጃው እንደደረሰው ለተጠቃሚው ሰው በኢሜል ያሳውቃል::

ይህ የተራቀቀና የመጠቀ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤት በሰው ልጆች እና በዕፅዋት መካከል ተደንቅሮ የኖረውን መረጃን የመለወጥ ችግር

የሚቀርፍ ግኝት እንደሆነ በሚችጋን የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የኬሜካል ኢንጅነርና የምርምሩ መሪ ፕሮፌሰር ማይክል ስትራኖ ለዲስክቨሪ ተናግረዋል::

ፕሮፌሰር ስትራኖ አክለውም ወደፊት ግኝቱ በአንድ አካባቢ በካይነገሮች ካሉ ቀድሞ አውቆ ለመጠንቀቅ ብሎም ስለ አካባቢው ሁኔታ ለመረዳት እና ለሌሎች ተግባራትም እንደሚያግዝ እምነታቸው ነው:: ዕፅዋት የአካባቢን ሁኔታ ለማወቅ የሚያግዙ ሁነኛ መሳሪያዎች እንደሆኑ የተናገሩት ፕሮፌሰር ስትራኖ ለዚህ ደግሞ ዕፅዋት ከአካባቢያቸው በርካታ መረጃዎችን መሰብሰብ የሚያስችል ሰፋ ያለ የሥራ ትስስር ስላላቸው መሆኑንም ጠቁመዋል::

Page 29: 12 03 2009.pdf

ገጽ 29በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ማስታወቂያ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለፍትህ ቢሮ አገልግሎት የሚውል ህትመት በግልጽ ጨረታ

አወዳድሮ ለማሣተም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች

መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያላቸው፣

4. የግዥው መጠን ብር 50 ሺህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ

መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን

ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የሚገዙ የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት

ይቻላል፡፡

7. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አብክመ ፍትህ

ቢሮ ባህር ዳር ከግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 የማይመለስ ብር 30.00

በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን ሰነዱን በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ

ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ኦርጅናል እና ኮፒ

በማለት በጥንቃቄ በታሸጉ በተለያዩ ፖስታዎች ማስገባት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የእቃውን

ወይም የአገልግሎቱን ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ

ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤቱ ገ/ያዥ ገቢ በማድረግ

ደረሰኙን ከሰነዱ ጋር በማያያዝ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡

9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ

ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በ16ኛው ቀን 2009 ከቀኑ በ3፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡00 ጨረታው

ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ጨረታው

ይከፈታል፡፡

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ

የተጠበቀ ነው፡፡

ማሣሰቢያ፡- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ

በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 220 36 29 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226

31 00 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበምዕ/ጎጃም አስተዳደር ዞን የሜጫ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለሜ/ወ/ቴክኒክና ሙያ ኢንተርኘራይዞች

ልማት ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት በአማሪት እና በወተት አባይ ቀበሌ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ሸድ

ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መስፈርቱን የሚያሟሉ ሁሉ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር

የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ ቲን ናምበር/ ያላቸው፣

3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣

4. ደረጃ 9 እና በላይ የሆኑ፣

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የግንባታውን ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 40.00 በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በሜ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግዥ ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይቻላል፡፡ በ22ኛው ቀን በ3፡30 ታሽጐ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 22ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተባለው ሰዓት ይከፈታል፡፡

8. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ አስይዞ ደረሰኙን ኮፒ አድርጎ ማያያዝ ይኖርበታል፡፡ ጥሬ ብር ፖስታው ውስጥ አድርጎ ማስገባት የተከለከለ ነው፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሜ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግ/ንብ/አስ/ደ/የስ/ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ጨረታው በአየር ላይ ከወጣበት ጀምሮ እስከ ሚታሸግበት ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

11. ተጫራቹ በኢንዱስትሪ ከተማ ልማት ተመዝኖ 50 እና በላይ ያመጣ መሆን አለበት፡፡

12. ሁሉም የግንባታ ማቴሪያሎች በአሸናፊው ተቋራጭ የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

13. በጨረታ መክፈቻ ቀኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡

14. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት አይወስድም፣

15. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 330 01 96 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 330 04 32

በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሜጫ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበምዕራብ ጎጃም ዞን በደቡብ አቸፈር ወረዳ የዱርቤቴ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አጠቃላይ ዓመታዊ ግዥ ለመፈፀም ማለትም ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ ሎት 2 የጽዳት እቃ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃ ሎት 4

ፈርኒቸር ሎት 5 የደንብ ልብስ ሎት 6 የደንብ ጫማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያላቸው፣

3. የግዥው መጠን ከብር 50 ሺህ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና ሌሎች ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡5. የጨረታ ሰነዱን ደ/አቸ/ወረዳ ዱርቤቴ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 01 ዘወትር በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት ብር 25.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡6. የጨረታ ዝርዝር መረጃ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በየምድቡ በተለያዩ ፖስታዎች በማድረግ በጥንቃቄ በማሸግ ደ/አቸ/ወረዳ ዱርቤቴ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋ/ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላል፡፡

9. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡40 ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነ በቀጣይ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

10. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የቅሬታ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡ ውል የማይወስድ ከሆነ ግን ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ውርስ ይሆናል፡፡

11. የጨረታ ውድድሩ የሚካሄደው በየሎቱ ጥቅል ድምር ስለሆነ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት ሁሉንም መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እንዲሁም የተጠየቀውን ስፔስፊኬሽን በራሱ መቀየር አይችልም፡፡12. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች የማውረጃ እና የማስጫኛ እንዲሁም የትራንስፖርት ወጪውን ችሎ ደ/አቸ/ወረዳ ዱርቤቴ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ ማቅረብና ንብረት ክፍል ማስረከብ

ይኖርበታል፡፡

13. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡14. ተጫራቾች የግዥ ደንብና መመሪያውን ማክበር ይኖርባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ ግዥ ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 01 በአካል በመምጣት መጠየቅ ይቻላል፡፡

የዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆፒታል

Page 30: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 30

ከገጽ 24 የዞረ

ማስታወቂያ

“ ሁለቱም እስክሞት...”እሳቸውም “አትክልት ከመውደዴም በላይ የካርልሄንዝ በም አደራ ስላለብኝ እናት ሆስፒታልን በማስዋብና ማፅዳት ሥራ እሳተፋለሁ”ሲሉ መለሱልን::

"አደራ" የምትለዋ ቃል ግራ አጋብታን በአርምሞ ስናስተውላቸው “መሬቱን ገለባ ያድርግለትና ካርል እናት ሆስፒታልን አስረክቦ ከዓለም ከተማ ሊወጣ ሲዘጋጅ እንዳይሄድብን ለመንነው:: እሱም ‘ከእናንተ የባሱ ሌሎች ድሆች አሉ:: እናንተን ይህን ያህል ካገለገልሁ ይበቃኛል:: እናንተ ለወገኖቻችሁ ስትሉ ሥራዎቼን እንደ እኔ አድርጋችሁ ውደዱልኝ፤ ጠብቁልኝ፤ ተንከባከቡልኝ፤ አደራ!...’ አለን:: ከዚያም ተሰናብቶን ወጣ:: ያ አባባሉ ሁልጊዜ በህሊናየ ይደውላል:: እሱ የሠራቸውን ሥራዎች በትጋት እንከባከባለሁ:: ሆስፒታሉን የማስውበውም በዚህ ምክንያት ነው" በማለት አብራሩልን::

ወ/ሮ ዘውዲቱ እንዳጫወቱን ክረምት በመጣ ቁጥር በፍላጐት ያለምንም ክፍያ ሆስፒታሉን በአትክልት ያስውባሉ:: "እንዳያችሁት ሆስፒታሉ በጣም ንፁህ ነው:: ግቢው ብቻ አክሞ ያድናል፤ አትክልትና ንፅህና የሚወድ ሰው ከህመሙ ተፈውሶ ይወጣል:: ይሄ ሆስፒታል ሁልጊዜም የተዋበ እንዲሆን ይህን ተግባሬን አላቋርጥም" ሲሉም የካርልን አደራ ጠብቀው ሆስፒታሉን የማስዋብ ሥራ እንደሚሠሩ አረጋግጠውልናል::

ወይዘሮ ዘውዲቱን መኖሪያ ቤታቸው ተገኝተን ስለግቢያቸው አትክልት ባነጋገርንበት ወቅት ህፃን አቅፈው ስለነበር ስለ እሷም እንዲያጫውቱን ጠይቀናቸዋል:: እሳቸውም፣ "የዚች ህፃን እናት ሆስፒታል ውስጥ ነው የሞተች:: የእናቷ ቤተሰቦች ከአስከሬን ጋር ጠቅልለው መኪና ላይ ጫኗት:: በኋላ በፖሊስ ተገደው አወረዷት:: ከዚያም አባቷ ከወ/ሮ ዘውዲቱ ሽልማቶች በከፊል

እንዲይዛት ተደረገ:: ሆኖም በጣም ህፃን ስለነበር ባግባቡ አልያዛትም:: አንድ ወር ከያዛት በኋላ እኔ ደጃፍ አምጥቶ ጥሏት ጠዋት ስነሳ አገኘኋት:: በደስታ አንስቼ አሜን! ብየ ያዝኋት:: አሁን አንድ ዓመት ከስድስት ወር ሆኗታል" በማለት ገለጹልን::

ወይዘሮ ዘውዲቱ በከተማ ግብርናና በጽዳት በሚያደርጉት ተግባር ብዙዎች በአርአያነት ያዩዋቸዋል:: ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ በዓለም ከተማ እናት ሆስፒታል በማገልገል ላይ የሚገኙት ሲስተር አልማዝ አውግቸው አንዷ ናቸው:: "ወይዘሮ ዘውዲቱ በከተማችን በጽዳትና በከተማ ግብርና አርአያችን ናቸው:: ሴትነታቸው ሳይበግራቸው ሁልጊዜ አረንጓዴ ልማት ለማስፋፋት እንዲሁም

ውብና ማራኪ አካባቢ ለመፍጠር ይጥራሉ:: ሆስፒታሉ ውስጥ በሚያደርጉት የአረንጓዴ ልማት ተሳትፎም በስማቸው የተሰየመ መናፈሻ አላቸው" ሲሉ እማኝነታቸውን ሰጥተዋል:: ወደ ሆስፒታሉ በየጊዜው ጐራ በማለት አትክልቶችን እንደሚተክሉ፣ እንደሚያርሙ፣ ውኃ እንደሚያጠጡም ገልጸውልናል::

የአረንጓዴ ልማታቸውን በየጊዜው የተመለከቱት የተለያዩ ግለሰቦችም አድናቆታቸውን በፅሁፍ ገልጸውላቸው ተመልክተናል:: ከእነዚህ አድናቂዎቻቸው ውስጥ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መጥተው ህዳር 26 ቀን 2003 ዓ.ም በመኖሪያ ቤታቸው እንዲሁም በመናፈሻ ሥፍራቸው

ያከናወኑትን የአረንጓዴ ልማት ተግባር የተመለከቱት አቶ አለባቸው ንጉሴ ይገኙባቸዋል:: አቶ አለባቸው "ወይዘሮ ዘውዲቱ በጣም ጠንካራና ለአካባቢ ልማት ተቆርቋሪ፣ ታታሪ፣ በራሷ ፈጠራ ጭምር ጠቃሚ ሥራ የሠራች በመሆኗ ለአካባቢውና ለሌላውም ሰው አስተማሪ መሆኗን በመናፈሻዎችና በቤቷ ያለማችውን በማየት አረጋግጫለሁ" በማለት በጽሁፍ አድናቆታቸውን ቸረዋቸዋል::

ታደሰ ጌታቸው የተባሉ አስተያየት ሰጪም ነሐሴ 18 ቀን 2001 ዓ.ም መናፈሻቸውን ከጐበኙ በኋላ ከዚህ በፊት የከብቶች መዋያ በመሆን ተራቁቶ በጐርፍና በአቧራ ይሸረሸር የነበረን አስቸጋሪ ቦታ ወደ አረንጓዴነት በመቀየር የሚያደርጉት ጥረት በአርአያነት የሚጠቀስ እንደሆነ መስክረውላቸዋል::

እነዚህን ለአብነት አነሳን እንጂ፤ በተለያዩ ጊዜያት ሥራቸውን የተመለከቱት በርካታ ወገኖች የተጐዳንና ለማልማት እጅግ አስቸጋሪ የነበረን መሬት ወደ አረንጓዴነት በመቀየራቸው አድናቆታቸውን ቸረዋቸዋል:: አስተያየት ሰጪዎቹ የሚመለከታቸው አካላት ትብብርና ድጋፍ እንዳይለያቸውም አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል::

ወይዘሮ ዘውዲቱ ለዚህ ታላቅ ተግባራቸው ከህዝባዊ አድናቆትና ምስጋና በተጨማሪ ከዓለም ከተማ እናት ሆስፒታል፣ ከዓለም ከተማ ከተማ አስተደደርና ከሌሎችም ተቋማት የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል::

ወይዘሮ ዘውዲቱ አስቸጋሪውን ቦታ አልምተው ከዚህ ደረጃ ደርሰዋል:: ሆኖም አንድ ነገር ይቀራቸዋል፤ መናፈሻውን ሥራ ማስጀመር:: ለዚህ ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንደማይለያቸው አቶ ብርቃ ብርቅ ተሾመ የዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አረጋግጠዋል፤ “መናፈሻው ገና ሥራ አልጀመረም:: አስፈላጊው ነገር ተሟልቶላቸው ወደ ሥራ ቢገቡ ለሌሎች ወጣቶችም የሥራ ዕድል ስለሚፈጥር ከውኃና መብራት ጋር ያለውን ጥያቄ እንመልሳለን:: በሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮችም የበለጠ እንደገፋቸዋለን" በማለት::

“ወይ ጠቅልለሽ ገዳም ግቢና እኛም እንረፍሽ!... እኛም እኮ እንደወላጅ ያንችን ፍሬ ማየት እንናፍቃለን… በቃ ገዳም ግቢልና!” ነገሩን አባባሱት::

“ይተው እንጅ ጋሽ አሰፋ! ቀሥ ብለን እንመካከርበት የለ!... ምንው አንችስ ልጀ የምንልሽን ብትሠሚ?… ሀዘንሽ አልሠማን ብሎ ይመሥልሻል…” አሉ እናቷ ወይዘሮ አትጠገብ ጣልቃ ገብተው ነገሩን ለማብረድ እየሞከሩ::

“እስከመቼ ነው የምንመካከርበት! እስኪ ዲግሪዋን ከጨረሰች እንኳ ስንት ዓመት ሆናት? ንገሪኝ!” ወደ ወይዘሮ አትጠገብ ዞረው ጠየቁ::

ወይዘሮ አትጠገብ በጣቶቻቸው የመቁጠር ምልክት አሣይተው፤ “እሱማ ስምንት ዓመት አለፋት” አሉ በትካዜ::

“እና ታዲያ ይሄ ቀላል ነው!… በሰዎች ቤት እኮ የአራት ልጆች አያቶች ይሆን ነበር! … ምን ያደርጋል ዕድሜ የሚጠብቃት ይመስል!?…” ጋሽ አሰፋ ጀምረው ተውት::

“ሥለ ዕድሜየ አትጨነቁ:: ገደል ይገባ! የተፌን ነገር ቁርጡን ሳላውቀው ምንም አትድከሙ! ሥላሰባችሁልኝ እግዜር ይሥጥልኝ!...” ረድኤት በተሠበረ ልብ መልሥ ሠጠች::

“ባክሽ ተይው! ተፌ ተፌ አትበይብን! በሕይወት ቢኖር እንዲህ ዝም ጥርቅም ይል ነበር:: ‘ተፌ! ተፌ!’ ላይመለስ ነገር… ታላዝናለች” መቼም ጋሽ አሰፋ ሲፈጥራቸው የግትር ግትር ናቸው:: ነገር ማለዘብ፤ ሰው አዝኗል፤ ሰው ይከፋዋልን አያውቁም!

“በቃ በማያገባህ! በማይመለከትህ አትናገር! . . . አላገባም ብያለሁ አላገባም! በቃ ባል አላገባም! ቁርጥህን እወቀው!” ረድኤት ነብርነቷ መጣ::

ሀዘንና ሀሣብ የማያጠቁረው ውብ ጠይም ፊቷ አሁንም ሳይጓደል አብሯት አለ:: ገና የ16 እና የ17 ዓመት ባለ አጐጠጐጤ ጡት አፍላ ወጣት እንጅ

ሁለተኛው...ከገጽ 11 የዞረ

30 ዓመት የሞላት አትመስልም:: ሰውነቷም የበለጠ ሸንቃጣ የበለጠ ሐረግ እንደመሠለ ነው:: ተፈራን በሀሣቧ እያወጣች እያወረደች የዕለት ተዕለት ምግቧ እና መጠጧ አድርጋዋለች::

እውነቷን ነው ተፈራን እንዴት ትረሣዋለች:: የፍቅር ሀሁን ያስተማራት፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የሱ ሰውነት ለእሷ የተሠጠ፤ የእሷም ሰውነት ለእሱ የተበረከተ መሆኑን ያሥተማራት፤ እነዚያን እንደመርፌ የሚዋጉ የሚመሥሉትን ጡቶቿን እንዳያማት ቀሥ ብሎ በመዳሰስ ያለማመዳት፤ ከንፈሮቿን በከንፈሮቹ የዳሠሠላትን እንዴት ትረሣዋለች:: መርሣትም የለባትም! ከልቧ ልታሥወጣው አለመቻሏም መሸ ነጋ ከጋሽ አሰፋ ጋር ያጨቃጭቃታል::

“እውነትሽን ነው! አያገባንምi ዳሩ እንቺ የት ታውቂውና! ወልዶ መዳርን! ድሮ የልጅ ልጅ ማየትን… ደስታውን አታውቂውማ!” አሉ ጋሽ አሰፋ ነገር ያበርዳሉ ተብለው ሲታሠቡ::

“ሀ.ሀ.ሀ. እሱ ነው! በቃ… በኔ ሀዘን የእናንተን ደስታ ነው የፈለጋችሁት… እርማችሁን አውጡ! እንደተቀበረች ልጃችሁ እርሡኝ! ረድኤት ከተፈራ ውጭ ሌላ ሰው አግብታ ወልዳ ታሥደሥታናለች ብላችሁ ከሆነ እርሡት! በከንቱ አትድከሙ!” ረድኤት ‘ቁርጡን እወቁት’ አለች::

“እንግዲያውስ ተፈራ ተፈራ ስትይ ዕድሜሽን ፍጂው! የሚሻልሽ ቁርጥ አድርገሽ ገዳም ብትገቢ ነው!” መቼም ጋሽ አሰፋ ለነገ የሚያሣድሩት ነገር የላቸውም::

“ተፌን ከሆነ አገባለሁ:: የፍቅር አምላክስ ምን ይለኝ! በሕይወት መኖሩንና አለመኖሩን ሳላውቅ… ገዳም መግባትን እመርጣለሁ! ከሌላ ሰው ጋር! ከሌላ ባል ጋር! ገዳም እገባለሁ!” ረድኤት የተፈራ ነገር ከልቧ አልወጣም::

“እንዲያውስ አንቺን ማን ተናግሮ ያሳምናል! ክርር ካልሽ መች ትመለሳለሽ!”

“እንግዲያውስ ልንገራችሁ… በፈጠራችሁ!…

በእግዚአብሔር ይዣችኋለሁ? በዚህ ጉዳይ ላይ ከዚህ በኋላ ሌላ ሀሣብ እንደማይኖረኝ አውቃችሁ ተውኝ! እርሡኝ! ተፌ ለእኔ ትናንትም አለ፤ ዛሬም አለ፤ ነገም ይኖራል፤ ከነገ ወዲያም…” ጋሽ አሰፋ ንግግሯን አቋረጧት::

“በቃሽ! በቃሽ ይሄ አጉል መመፀዳቅ ነው! ወግ ነው! ሁሉም እንዳንች ነው የሚለው!” አሉ::

በዚህ መሀል ወይዘሮ አትጠገብ ነገሩን ያበረዱ መሥሏቸው፣ “የኔ ረድኤት ቅድም…ያች ማን ናት ጓደኛሽ… ማንናት አያ! ስሟን ረስቸው… ጥሩሰው… እሷ መጥታ ይሄንን ስጭልኝ ብላኝ ነበር! ረስቸው ነው” አሉ::

ረድኤት ወይዘሮ አትጠገብ ያቀበሏትን የተጠቀለለ ጋዜጣ ተቀበለቻቸው። ጋዜጣውን ከተጠቀለለበት አስተካከለችና የፊት ለፊት ገፁ ላይ በእስክርቢቶ የተፃፈ ፅሁፍ አሥተዋለች:: “ረዱ ይሄን ጋዜጣ መቼም እንደምታነቢው አልጠራጠርም:: አሁን ለእማማ የላክሁልሽ እንድታነቢው ፈልጌ ሳይሆን ሁለተኛው ገፅ ላይ ያለው ነገር አሥደንግጦኝ ነው:: ሁለተኛው ገፅ ላይ የጋዜጣውን አዘጋጆች ስም ዝርዝር ሳይ የሆነ ነገር ወረረኝ!” የሚል ፅሁፍ ነው!

ረድኤት ዓይኗን አፈጠጠች:: ግራ ተጋባች:: “ገፅ ሁለት ምን ኖሮበት ነው!” አባቷም እናቷም ትኩረታቸው ወደ ረድኤት አደረጉ::

“ምንድነው ነገሩ ረድኤት” አሉ ወይዘሮ አትጠገብ አብረው እየጓጉ:: መልስ አልሰጠቻቸውም:: በፍጥነት የጋዜጣውን ሁለተኛ ገፅ ገለበጠች:: ከፍጥነቷ የተነሣ የጋዜጣው ወረቀት በሀይል ቋቋቋሽ… ኩሽ ኩሽ አለ::

“ገፅ ሁለት” አለች አሁንም ረድኤት በድጋሜ!“የአዘጋጆቹ ስም ዝርዝር…?” አሁንም ረድኤት

አጉተመተመች::የአዘጋጆቹ ስም ዝርዝር ላይ ስትደርስ ዓይኗ

ከዋሻው ተጐልጉሎ የወጣ መሠለ:: ጮኸች!“ምን! እግዚአብሔር ሆይ! ፀሎቴን፣ ንፅህናዬን

ሰምተህ ይሆን!”“ረዱ እኛንም እኮ ግራ አጋባሽን! ምንድን ነው

ነገሩ!” አሉ ወይዘሮ አትጠገብ ከቅድም አሁን በደስታ ሥትጮህ ቢመለከቷት ጊዜ ግራ ገብቷቸው::

“እማዬ አለ! በሕይወት አለ! ተፈራ ሰንደቁ እኮ ነው የሚለው! ተፈራ ሰንደቁ… መቼም እንደዚህ እሥከ አባቱ ስም አንድ አይሆንም” በፍጥነት ስልኳን አወጣች:: ለካ ጓደኞዋ ጋዜጣውን የላከችላት የተፈራን አባት በእርግጠኝነት ሥለማታውቀው ራሷ ረድኤት እንድታረጋግጠው ፈልጋ ነው::

ረድኤት ስልኳን አውጥታ በጋዜጣው ሁለተኛው ገፅ ላይ ተፈራ ሰንደቁ ከሚለው ስም ፊትለፊት የተቀመጠውን ቁጥር መነካካት ጀመረች:: ትንሽ ቆይቶ መጥራት ጀመረ:: በአራተኛው ጥሪ ተነሣ!

“አዎ ራሡ ነው! ተፈራ ሰንደቁ ነው ተፌ ነው!” አለች ምንም ሳታወራ ገና ድምፁን ሠምታ:: ጊዜ አላጠፋችም! ሌላ ወሬም ማውራት አልፈለገችም! “አላገባህም አይደል!”

“ምን አቅም ኖሮኝ” ከስልኩ ወደያኛው ጫፍ የተፈራ ድምፅ መልስ ሠጠ::

“እኔም አንተን ስጠብቅ አለሁ!” ረድኤት በግጥምጥሞሹ ተገረመች::

“ወይ ገፅ ሁለት” አለች ሳታስበው!“የምን ገፅ ሁለት” ግራ ገብቶት ተፈራ ጠየቃት::“ይሄው ያንተን መኖር የነገረኝ የምታዘጋጀው

ጋዜጣ ገፅ ሁለት ነው… ታገባኛለህ!”“ታዲያ ለማን ነበር እስከ ዛሬ ሳለገባ የኖርሁት!

የዚህ ምስጢር መቼም አይጠፋሽም!”“ኦ እግዚአብሔር ሆይ ሊያገባኝ ነው! ላገባ ነው!”

ስልኩን ዘግታ ወደ ቤተሠቦቿ ዞረች:: ለካ ከልባቸው ይወዷት ኖሯል:: ከጋሽ አሰፋ በላይ የተደሰተ ያለ አይመሥልም።

“ላገባ ነው!” ረድኤት በደስታ ብዛት የሚያደርጋትን አሳጥቷት ደገመችው::

Page 31: 12 03 2009.pdf

ገጽ 31በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበምስራቅ ጐጃም ዞን የስናን ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት በ2009 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ ፎልደር ፣ከለርድ ቁጥሮች ፣የችሎት ወረቀቶችንና ልዩ ልዩ ማህተሞችን ለማሣተም እንዲሁም የጽህፈት

መሣሪያዎችን ፣የጽዳት እቃዎችን ፣የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ፣ብትን ጨረቅ ፣የተሰፉ ልብሶችንና የተዘጋጁ ጫማዎችን ፣የህንፃ መሣሪያዎችን ለመግዛትና የፎቶ ኮፒ ማሽኖችን ፤ ኘሪንተሮችን ፣ላኘቶፖችን ፣ፋክስ

ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

1. በየዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ምዝገባ ያላቸው፣

4. የእቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሰነድ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

5. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ፣የጽህፈት መሣሪያዎችንና የህትመት ውጤቶችን የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ብር 10.00 በመክፈል ሌሎችን የሚጠገኑና የሚገዙ እቃዎችን የያዘውን ሰነድ ደግሞ የማይመለስ ብር

5.00 በመክፈል ከግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ከእለት ገ/ተቀባይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ከሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ

ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡

8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝባዊ በዓል ወይም እሁድ ፣ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

9. ተጫራቾች ከጠቅላላ ዋጋው ውስጥ 10 በመቶ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

10. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ የውል ዋጋውን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ወይም ሲፒኦ

በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈረም አለበት፡፡

11. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ ስናን ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት በሚገኘው ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

12. መ/ቤቱ የሚገዛውን የእቃ ብዛት 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው፡፡

13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

14. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 288 00 64 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

15. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡

16. የግዥው መጠን ብር 50 ሺህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ማሣሰቢያ፡- የጨረታ ውድድሩ በሎት መሆኑን እናሣስባለን፡፡

የስናን ወረዳ ፍርድ ቤት

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበምዕራብ ጎጃም ዞን የጎንጅ ቆለላ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2009 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል አላቂና

ቋሚ እቃዎች ጥቅል ግዥ ማለትም፡- ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች ሎት 2 የጽዳት እቃዎች ሎት 3

የኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ እቃዎች ሎት 4 ህትመትና የህትመት ውጤቶች ሎት 5 የደንብ ልብስ

ማለትም ብትን ጨርቅ ፣ጫማ ፣ ሸሚዝ ሎት 6 ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት

ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ

መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ያላቸው፣

4. የግዥው መጠን ከብር 50 ሺህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 5.00 በመክፈል ከጎንጅ ቆለላ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በታሸገ ፖስታ በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከህዳር 12/2009 ዓ/ም እስከ ህዳር 26/2009 ዓ/ም ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፍ/ቤቱ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ህዳር 27/2009 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ በመ/ቤቱ በሚገኘው ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09 41 48 02 22 ወይም 09 18 80 19 52

በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጎንጅ ቆለላ ወረዳ ፍ/ቤት

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያየምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በ2009 በጀት ዓመት አመታዊ የጽህፈት መሣሪያ ፣የጽዳት እቃዎች

፣ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የቢሮ መገልገያ ቋሚ እቃዎች፣ ብትን ጨርቅ፣ የተዘጋጁ ልብሶችና ጫማ እና

መጽሃፍት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያላቸው፣

4. የአገልግሎት መጠን ከብር 50 ሺህ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ

የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ

ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን

ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 10.00 በመክፈል የምዕ/ጐ/ዞን ከፍ/ፍ/ቤት የግዥ ፋ/ን/

አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎኘ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ በተዘጋጀው

የጨረታ ሣጥን ከመክፈቻ ቀኑና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡

8. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ

የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ

አለባቸው፡፡

10. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎኘ በማድረግ ከህዳር 13/2009 ዓ/ም እስከ ህዳር

27/2009 ዓ/ም ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚውል

ሲሆን በ16ኛው ቀን ህዳር 28/2009 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ በዚሁ እለት በ4፡00 ተጫራቾች

ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው

የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ

ነው፡፡

12. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በግንባር ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር

058 775 10 43 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

ማስታወቂያ

Page 32: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 32

ከገጽ 15 የዞረ

“አረቦን”... ከገጽ 8 የዞረ

የእግረኞች...ም/ኮማንደሩ እንደተናገሩት በብሔረሰብ

አስተዳደሩ ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ ከአዲስ አበባ- በቡሬ- ባሕር ዳር ያለው መንገድ ወደ አስፓልት ደረጃ ማደጉን ተከትሎ የእግረኞች በመኪና አደጋ የመሞት ሁኔታ በአሳሳቢ ደረጃ በመጨመሩ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ወደ ማስተማር ተገብቷል:: ሕብረተሰቡን ለማስተማር በየቀበሌው ያሉ የፖሊስ ኦፊሰሮች፣ የትራፊክ ፖሊሶችና በመምሪያ ደረጃ የነበሩ የትራንስፖርት ባለሙያዎች በጋራ በመሆን ዕቅድ አውጥተው በመሥራታቸው በረዥም ዓመታት ጥረት ለውጥ መምጣቱንም ም/ኮማንደሩ ተናግረዋል::

እንደ ም/ኮማንደር አዳሙ ገለፃ የትራፊክ አደጋ በደረሰባቸው ቦታዎች ላይ ተገኝቶ በድርጊቱ በማስተማር፣ በዕድር፣ በዕቁብ፣ በሰንበቴና ማኅበራት እንዲሁም በእምነት ተቋማት በመገኘት በተከታታይ የተሰጡት የእግረኛ መንገድ አጠቃቀም ትምህርቶች በብሔረሰብ አስተዳደሩ ነዋሪዎች የመንገድ አጠቃቀም ዙሪያ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት ችለዋል:: በየትምህርት ቤቶች ከፍተኛ የማስተማር

ሥራ መሠራቱም ተማሪዎች ራሳቸው የመንገድ አጠቃቀማቸውን እንዲያስተካክሉ ከማስቻሉም ባለፈ በየቤቱ ለቤተሰቦቻቸው እንዲያስተምሩ ስለሚደረግ ለለውጡ መምጣት ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ነው ም/ኮማንደሩ ያብራሩት::

ተሞክሮውን በብሔረሰብ አስዳደሩ 11 ወረዳዎች ለማስፋት ጥረት መደረጉን ያስታወቁት የሥራ ሂደት መሪው በተለይ ከአስፓልት መንገድ ውጭ ባሉ ወረዳዎች የእግረኛ ማቋረጫ ምልክቶች ካለመኖራቸውና እግረኞች መንገድ ለማቋረጥ ከመቸገራቸው ውጭ የግራ ጠርዝን ይዞ በመጓዝ በኩል በገጠሩ አካባቢ ስኬታማ ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል፤ በከተሞች አካባቢ ግን የእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም አሁንም አልፎ አልፎ ችግር እንደሚስተዋልበትና ቀጣይ ሥራ እንደሚጠይቅም አስረድተዋል:: በተለይ በከተሞች አካባቢ ለሚስተዋለው የእግረኛ መንገድ አጠቃቀም ችግር ትልቁን አስተዋፅዖ የሚያረክቱት ደግሞ ከብሔረሰብ አስተዳደሩ ውጭ የሚመጡ እንግዶች መሆናቸውንም ም/ኮማንደር አዳሙ ተናግረዋል::

በእግረኞች መንገድ አጠቃቀም ላይ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ሲሠራ የእግረኛ መንገዱ ምቹ ሆኖ ባለመሠራቱና በሕብረተሰቡ ውስጥ ከግራና ቀኝ መንገድ ጋር ተያይዞ የነበረው ልማዳዊ አመለካከት ትልቅ ፈተና እንደነበር ያስታወሱት ም/ኮማንደሩ በተለይ ወደ ዚገም አካባቢ “እንዴት ‘በቀኝ አውለኝ’ ብዬ የተነሳሁትን በግራ ሂድ ትለኛለህ?” ብለው የሚሞግቱ የሕብረተሰብ ክፍሎችን አመለካከት መቀየሩ ከፍተኛ ጥረት መጠየቁንም አብራርተዋል::

የብሔረሰብ አስተዳደሩ በእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም በፌዴራል ደረጃ የዋንጫ ተሸላሚ መሆኑን የተናሩት ም/ኮማንደር አዳሙ የጎንደር ከተማ አስተዳደር፣ የትግራና ኦሮሚያ ክልሎች ተሞክሮ መቅሰማቸውንም ተናግረዋል:: ብሔረሰብ አስተዳደሩ በእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ዙሪያ

ስኬት ለማስመዝገብ የተጓዘበትን ሂደትም በአውደ ጥናት ጭምር ለሌሎች ማካፈሉን ሂደት መሪው ገልፀዋል::

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ በእግረኞች ስህተት ምክንያት በየዓመቱ ከሦስት በላይ ሰዎች ይሞቱበት እንደነበር ያስታወሱት ም/ኮማንደር አዳሙ ከ2006 ዓ.ም አጋማሽ እስከ 2008 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ባሉት ሁለት ዓመት ተኩል ጊዜያት ውስጥ ግን በእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ችግር ምክንያት የደረሰ አንድም የሞት አደጋ አለመኖሩን ተናግረዋል:: አደጋዎች ቢደርሱም ምክንያቸው የእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ችግር ሳይሆን የአሽከርካሪዎች እና የተሸከርካሪዎች የቴክኒክ ችግሮች እንደሆኑም ም/ኮማንደሩ አስረድተዋል::

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የተማሪ ትራፊኮችም ከመደበኛ ትራፊኮች ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል:: በብሔረሰብ አስተዳደሩ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በሁሉም ደረጃ ባሉ አሽከርካሪዎች በተለያዩ የወረዳ ከተሞች ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ መሠራቱንና በአሽከርካሪዎች ስህተት የሚደርሱ አደጋዎችንም ለመቀነስ መሠራቱን ያብራሩት ም/ኮማንደር አዳሙ በዚህም ለውጥ መመዝገቡን ገልፀዋል::

በብሔረሰብ አስተዳደሩ ወደ ሕዳሴ ግድብና የተለያዩ ክልሎች የሚያስተላልፉ መንገዶች

በመኖራቸውና የረዥም ርቀት አሽከርካሪዎች አካባቢውን ጠንቅቀው ባለማዎቃቸው እንዲሁም የመንገድ ዳር ምልክቶችና አመላካቾች በአግባቡ አለመተከላቸው አሁንም የትራፊክ አደጋ እንዳይቀንስ እገዛ እያደረጉ እንደሆነም ም/ኮማንደሩ ተናግረዋል::

በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማረጋገጫ ዋና የሥራ ሂደት መሪ ኮማንደር ዋለልኝ ዳኛው በበኩላቸው በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ላይ ለውጥ የመጣው በከፍተኛ ጥረት መሆኑን ገልፀው ተሞክሮውን ወደ ክልሉ የሌሎች አካባቢዎች በማስፋት ለውጦች መምጣታቸውንም ተናግረዋል:: ኮማንደር ዋለልኝ እንዳሉት ከደቡብ ጎንደር መስተዳድር ዞን ወረዳዎች ሊቦከምከም፣ ፋርጣና ፎገራ በከፊል፣ ከምሥራቅ ጎጃም ማቻከል፣ ጎዛምንና አዋበል፣ ከምዕራብ ጎጃም ጃቢጠህናን፣ ደምበጫና ቡሬ በከፊል በእግረኛ መንገድ አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ለውጥ የታየባቸው ወረዳዎች ናቸው:: በሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ወሎና ሰሜን ሸዋ ወረዳዎችም እንዲሁ ተሞክሮውን በማስፋት በብዙ ወረዳዎች ለውጥ እንደመጣ ገልፀዋል::

ቆዬት ያሉ መረጃዎች እንደሚያመልክቱት ኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋ ከዓለም 14ኛ ስትሆን በአፍሪካ ደግሞ ከናይጀሪያ ቀጥላ ሁለተኛ ነች:: በኢትዮጵያ በ1998 ዓ.ም በተደረገ ጥናት ከ10 ሺህ ተሽከርካሪዎች በ126 አደጋ ይመዘገብ ነበር፤ በ2007 ዓ.ም በተደረገ ሌላ ጥናት ደግሞ ከ10 ሺህ ተሽከርካሪዎች በ65 አደጋ እንደሚደርስ ታውቋል:: በ2007 ዓ.ም በአፍሪካ ደረጃ በአማካኝ ከ10 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከ30 ባነሱት ብቻ አደጋ እንደሚመዘገብ ጥናቶች ያሳያሉ:: በኢትዮጵያ ከትራፊክ አደጋ ምክንያቶች ፍጥነት፣ ለእግረኞች ቅድሚያ አለመስጠትና መስመርን ይዞ አለማሽከርከር ቅድሚያውን የሚይዙ እንደሆኑም ጥናቶች ያሳያሉ::

ከመንጋው ተነጥላ የሄደችው አህያም ይህንን ታሪክ ስትሰማ እንደሚከተለው ሙሾ አወረደች::

አጅሬ ምን ይበል የኔ ናቸው እንጅ፣ወዳጅ እንኳ አይደለን ደመኛ ነን እንጅ ፣ፈሳ ፈሳ እያሉ ሄደው ከሰው ደጅ::የጊምባ እረኞች ተረቶች በሚማርኩ የግጥም

ስንኞች የተሞሉ ናቸው:: ይህም የአካባቢውን ቱባ ባህል አስተሳሰብና የአኗኗር ዘይቤ ማጥናት ለሚፈልግ ሁሉ የተመቸ ነው::

ዛሬ የጊምባ እረኞች በማህበረሰቡ አጠራር "አረቦን" ተብለው እንደሚጠሩና ትርጉሙም የነገን የሚተነብይ ማለት እንደሆነ የነገሩን ደግሞ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የስነ ጽሁፍና የፎክሎር መምህር አቶ ብርሃኑ ቦጋለ ናቸው:: እረኞቹ የሚናገሯቸው ንግግሮች ወደ ፊት እንደሚከሰቱ ሲገነዘብ ይህንን ስያሜ እንደሰጣቸውም አብራርተዋል::

ኒኬሉም ያልቅና፣ አርኩም ይሄድና ፣ጠቅል ይመጣና፣ያስተዛዝበናል ይሄ ቀን ያልፍና:: ብለው በጣሊያን ወረራ ጊዜ አፄ ኃይሌ ስላሴ

ተሰደው በነበረበት ወቅት የተናገሩትን ትንቢት አዘል የቃል ግጥም እንደምሳሌም አንስተውታል::

ኒኬል የተባለው በጣሊያን ጊዜ የነበረውን ገንዘብና ቁሳቁስ፣ አርክ ደግሞ የጣሊያንን አገዛዝ ማለት እንደሆነና ጠቅል ይመጣና የተባሉትም አፄ ኃይለስላሴ መሆናቸውን አብራርተዋል::

እረኞች በወቅቱ የህዝቡን ስሜት ማስተንፈሻም እንደነበሩ አቶ ብርሃኑ ያስረዳሉ:: በወቅቱ እረኛ ምን አለ? እንጂ በተናጠል የሚጠቀስ አካል ባለመኖሩ ተጠያቂ የሚሆንበት ዕድል አልነበረም:: ይህም እረኞቹ በነፃነት ስንኞችን ለመደርደር ዕድል ይፈጥርላቸው ነበር::

በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ የበግ ሀብት መኖር ለእረኞች መበርከት ትልቅ ድርሻ እንዳለው አቶ ሙሐመድ ፋንታው የለጋምቦ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የባህል ልማት ባለሙያ ገልፀዋል:: የጊምባ ሜዳ ደግሞ የማህበረሰቡ በጐችና ላሞች ተሠማርተው የሚውሉበት ነው::

በዚህ ሜዳ መሀል ለመሀል አልፎ የሚሄድ ዋና መንገድ አለ:: ጥንትም የንግድ መስመር ስለነበር መንገደኞች በዚያ ሲያልፉ የጊምባ እረኛን የቃል ግጥሞች ያዳምጡ ነበር:: እንዲያውም ነጋዴዎች ከስንቃቸው እየሰጡ እረኞች ትንቢት በግጥም እንዲናገሩ ያበረታቷቸው ነበር ይባላል:: በዚህ

የእረኞቹን ትንቢት አንዳንዶቹ ከሼህ ሁሴን ጅብሪልና መሰሎቻቸው ያገኙትን መረጃ መሠረት አድርገው ነው ሲሉ ከፊሎቹ ደግሞ የራሳቸው የእረኞች ሀሳብ ነው ይላሉ:: አቶ ሙሐመድ እንደሚሉት የትንቢቱ መነሻ ቱሉ አውሊያ ላይ ተሰባስበው ሲነጋገሩና ሲጨዋወቱ የሚፈጠር እንጂ ከሼሆቹ ጋር የሚያያዝ አይደለም ይላሉ:: እረኞቹ ግን የሼህ ሁሴን ጅብሪልንም ትምቢቶች በቃላቸው ይዘው "ሼሆቹ እንደዚህ ብለዋል" በማለት ግጥሞቹን ያሰማሉ:: አቶ ሙሐመድ ግን ትንበያው ሙሉ በሙሉ የእረኞቹ ፈጠራ ነው የሚል አቋም አላቸው::

አህያ መጣች ተጭና ሻሽ፣ኃይለስላሴ አጥብቀህ ሸሽ::ሲሉም ጣሊያን ዳግም ለወረራ ሲመጣ ለአፄ

ኃይለስላሴ ማስጠንቀቂያ የሚመስል ትንቢት ተናግረው ነበር::

ይህ ሁሉ የቃል ሀብት በአሁኑ ወቅት "ድሮ ቀረ" የሚባልበት ደረጃ ላይ ደርሷል:: የህብረተሰቡ የአኗኗር ዘይቤ መቀየርና ዓለምአቀፋዊነት /ግሎባላይዜሽን/

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር መንገድን ማቋረጥ የሚቻለው ነጭ ቀለም በተቀቡ መስመሮች ብቻ ነው፡፡

መንገድ ወደፊት ድርቅም ከሆነ፣ አዝመራው ጥሩም ከሆነ፣ መንግስት የሚገለበጥም ከሆነ የማይዛነፍ ትንቢት ይናገራሉ::

ለምሳሌ በ1966 አካባቢ ድርቅ በነበረበት ወቅትአህያ መጣች ተጭና ሞፈር፣ቅቤ እንደ ጭቃ እህል እንዳፋር:: በማለት መጪው ጊዜ ጥሩና ምርቱ የተትረፈረፈ

እንደሚሆን ተንብየው ነበር ይባላል::

እየተቀየረ መምጣትም ለዚህ ትልቁን ድርሻ ይይዛል:: እረኞቹ ቢናገሩም የሚያደምጥ ሰው እንደሌለ አቶ ሙሐመድ ተናግረዋል::

የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ባህሉ ቢያንስ ተሰንዶ እንዲቀመጥ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን አቶ ሙሐመድ ተናግረዋል:: ጥናት እንዲካሄድ በማድረግና በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን እንዲተዋወቅ ለማድረግም እየጣርን ነው ብለዋል::

የጊምባ እረኞች በማህበረሰቡ አጠራር "አረቦን" ተብለው እንደሚጠሩና

ትርጉሙም የነገን የሚተነብይ ማለት እንደሆነ የነገሩን ደግሞ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የስነ ጽሁፍና የፎክሎር

መምህር አቶ ብርሃኑ ቦጋለ ናቸው::

Page 33: 12 03 2009.pdf

ገጽ 33በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያበባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የጣና ሐይቅ አጠ/ከፍ/ትም/መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የትምህርት ቤቱን አጥር በአንድ በኩል ለማሣጠር ደረጃቸው G.C-8/B.C-7 የሆኑና በላይ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ስራ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ስለፈለገ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ጥሪ ያደርጋል፡፡1. በጨረታው መሣተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በርዕሰ መምህር ቢሮ ቁጥር 1 ማመልከቻ

በማቅረብና የማይመለስ 300.00 ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት የሚችል ሲሆን፣የግንባታዎች ማጠናቀቂያ ጊዜ ስራው ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 90 ተከታታይ ቀናት ነው፡፡

2. የጨረታ ማስከበሪያ የውለታውን 2 በመቶ ሲሆን የዋስትናውም አይነት በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ /የደረሰኙ ኮፒ/ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ሆኖ ለጣና ሃይቅ አጠ/ከፍ/ትም/መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከጨረታው ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡

3. የጨረታ ሰነድ መግዣ ጊዜው የጥሪ ማስታወቂያው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት እና በ22ኛው ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ ሲሆን ተጫራቾች ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀንም በተመሣሣይ ስዓት ከቀኑ 8፡30 ይሆናል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ፎርም /Bid form/ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ /Price Schedule/ በጥንቃቄ መሙላት የሚኖርባቸው ሲሆን ይህ ሣይሆን ከቀረ ግን በሰነዱ ላይ የቀረበው ስራ በውሉ አጠቃላይ ዋጋ የሚሸፈን ይሆናል፡፡

5. የሚከተሉት መስፈርቶች ካልተሟሉ ከጨረታ ውጭ ያደርጋሉ፡፡5.1. ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው

የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት እንዲሁም የግብር መለያ ቁጥር/ቲን ናምበር/ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡5.2. ተጫራቾች አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የጨረታ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪ

በዋናው ሰነድና በኮፒው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ገዥው ዋናው የጨረታ ሰነድ ይሆናል፡፡5.3. የጨረታ ሰነዱ የሚታሸግበት ፖስታዎች ጨምሮ በሁሉም የዋናውና በኮፒው የጨረታ ሰነዶች

ገጾች ላይ ማህተም በማድረግ በጥንቃቄ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡5.4. በጨረታ ሰነዱ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሚቀርበው ነጠላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለው ግልጽና

የማያሻማ መሆን አለበት፡፡6. ት/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡7. በጨረታው መሣተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በስልክ ቁጥር 058 220 00 57/09 18 01

66 02 በመደወል ወይም በአካል ቀርቦ መጠየቅ ይችላል፡፡

የጣና ሃይቅ አጠ/ከፍ/ትም/መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት

የጨረታ ማስታወቂያየአብክመ ትምህርት ቢሮ ግንባታቸው ተጀምሮ የተቋረጡትን በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ

የበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅና በሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ የሚገኘውን የወልድያ

መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የጥገና እና ቀሪ ስራዎች ለማሰራት G.C-8/B.C-7 የሆኑና በላይ የታደሰ

የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ስራ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ስለፈለገ መስፍርቱን

የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጥሪ ያደርጋል፡፡

1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በአብክመ ትም/ቢሮ ግን/ቁጥ /ክት/የስራ

ሂደት ቢሮ ቁጥር 12 ማመልከቻ በማቅረብና የማይመለስ 200.00 ብር በመክፈ የጨረታውን

ሰነድ መግዛት የሚችል ሲሆን፣የግንባታዎች ማጠናቀቂያ ጊዜ ስራው ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ

በሚቆጠር ለበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግንባታ 90 የካላንደር ቀናት እና ለወልድያ

መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግንባታ 70 የካላንደር ቀናት ናቸው፡፡

2. የጨረታ ማስከበሪያ የውለታውን 2% ሲሆን የዋስትናውም አይነት በ C.P.O ወይም በጥሬ ገንዘብ

(የደረሰኙ ኮፒ) ወይንም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ሆኖ ለአብክመ ትም/ቢሮ

ከጨረታው ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡

3. የጨረታ ሰነድ መግዣ ጊዜው የጥሪ ማስታወቂያው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት

ተከታታይ 21 ቀናት እና በ22ኛው ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ሲሆን ተጫራቾች ለዚሁ

ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡የጨረታው መክፈቻ ቀንም በዕለቱ ከቀኑ 8፡

30 ይሆናል፡፡

4. ተጨራቾች የጨረታ ፎርም /BID FORM/ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ /PRICE SCHEDULE/

በጥንቃቄ መሙላት የሚኖርባቸው ሲሆን ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን በሰነዱ ላይ የቀረበው ስራ በውሉ

አጠቃላይ ዋጋ የሚሸፈን ይሆናል፡፡

5. የሚከተሉት መስፈርቶች ካልተሟሉ ከጨረታ ውጭ ያደርጋሉ፡፡

5.1. ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የተጨማሪ አሴት ታክስ ተመዘጋቢ ለመሆናቸው

የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት እንዲሁም የግብር መለያ ቁጥር /T.I.N No/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5.2. ተጫራቾች አንድ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ የጨረታ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: በተጨማሪም

በዋናው ሰነድና በኮፒው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ገዥው ዋናው የጨረታ ሰነድ ይሆናል፡፡

5.3. የጨረታ ሰነዱ የሚታሸግባቸው ፖስታዎችን ጨምሮ በዋናውና በኮፒው የጨረታ ሰነዶች ገጾች

ላይ ማህተም በማድረግ በጥንቃቄ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5.4. ከዚህ በፊት ከአብክመ ትም/ቢሮ ፕሮጀክቶችን ወስደው ያቋረጡና በህግ የተከሰሱ ሁሉም

ተቋራጮች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፡፡

5.5. ከአብክመ ትም/ቢሮ ጋር ውል በመውሰድ በአሁኑ ሰዓት የግንባታ ስራዎችን እየሰሩ የሚገኙና

አፈጻጸማቸው ከ 90% በታች የሆኑ ተቋራጮች መሳተፍ አይችሉም፡፡

5.6. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከተማ ልማት፣ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ በ2008 ዓ.ም

ባሰራጨው የተቋራጮች አፈጻጸም ውጤታቸው 75 በመቶ እና ከዚያ በላይ ያላቸው መሆን

አለበት፡፡

5.7. በጨረታ ሰነዱ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሚቀርበው ነጠላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለው ግልጽና

የማያሻማ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ስርዝ ድልዙን ፈርሞ በፊደል ካልጻፈ ውድቅ ይሆናል፡፡

6. የብሎኮች አይነትና ብዛት፡- ሁሉም ብሎኮች ላይ የጥገናና ቀሪ ስራዎችን ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡

7. አሰሪ መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይንም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በሚከተለው አድራሻ ተጨማሪ ማስረጃ

ማግኘት ይችላል፡፡

አብክመ ትምህርት ቢሮ ስ.ቁ፡ 0582-221-435/0582-207-056, ፖ.ሳ.ቁ፡- 764, ባህር ዳር

የአብክመ ትምህርት ቢሮ

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያየምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ለመ/ቤታችን አገልግሎት የሚውል 1.

ህትመት 2. የኤሌክትሮኒክስና የኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች 3. የመኪና ጎማዎችና ጌጣጌጦች በግልጽ

ጨረታ ማስታወቂያ በሎት አወዳድሮ ከድርጅትዎ መግዛት ይፈልጋል፡፡በመሆኑም፡-1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያላቸው፣

3. ከብር 50 ሺህ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

5. የሚገዙት እቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ህትመቶችን ናሙና ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው እና ፓራፍ ከሌለው ጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡

6. ከላይ የተጠቀሱትን የቢሮ እቃዎች ሰነድ ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 14 ድረስ በመምጣት ከ1 እስከ 3 ቁጥር ያሉትን ብር 30.00 በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የቢሮ እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታው ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች ሃሣቡን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 14 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይችላል፡፡

9. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ወዲያውኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡

10. አሸናፊው ከአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡

11. አሸናፊው የአሸነፈባቸውን እቃዎች ምስ/ጎ/ዞ/ከፍ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 14 ድረስ በመምጣት ውል ይዞ እቃዎችን ማስረከብ አለበት፡፡

12. 20 በመቶ መቀነስም ሆነ መጨመር የምንችል መሆኑን እየገለጽን ነገር ግን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. የጨረታ መክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡14. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 14 ድረስ በአካል

በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 55 50 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

Page 34: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 34

በከተማዋ መሠረተ ልማቶች እየተስፋፉ ነው

ኢኮኖሚ እንዲሁም የፊዚካል ፓሊሲ ወሣኝ ናቸው:: ከዚህ አንፃር በደብረ ብርሃን የሚታየው የኢንቨስትመንት ፍሠትና ዕድገት የዚህ ጅምር ውጤት መሆኑን የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ የሥራ ሂደት የሆኑት አቶ ሽፈራው ይስማማሉ::

አቶ ሠይድ መሐመድ የአዚላ ኤሌክትሮኒክስ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ ናቸው:: ኩባንያው ወደ ደብረ ብርሃን የመጣው በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2013 እንደነበር የሚገልፁት ሥራ አስኪያጁ በአንድ ዓመት ተጠናቅቆ በ2014 ወደ ማምረት ተሸጋግሯል:: በአንድ ቀንም 250 ማቀዝቀዥ(ፍሪጆችን) አምርቶ ለገበያ ያቀርባል:: ኩባንያው በዚህ አጭር ጊዜ ውሰጥ እንዴት ዕውን ሊሆን እንደ ቻለ ሥራ አስኪያጅ ይገልፃሉ፤ “የኢንቨስትመንት አገልግሎት አሠጣጥና ሂደቱ በጣም ቀልጣፋ ነበር:: በወቅቱ የምንፈልገውን ጉዳይ ለማከናወን ፈጣንና ደስ የሚል መስተንግዶ ተደርጎልናል:: በመሠረተ ልማት በኩል ሁሉም ሙሉ ነው:: ከውኃ እጥረት በስተቀር መንገድና መብራት ተሟልቶልናል:: ወደዚህ የመጣነውና እንዲህ አይነት ምቹ ሁኔታ በመኖሩና ከተማ ከአዲስ አበባ በቅርበት መገኘቷ ነው” ብለዋል::

ጂኒፐር ግላስ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የግል ኩባንያ በአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ካፒታል በውጭ ባለሐብት የሚገነባ ግዙፍ የብርጭቆ ፋብሪካ ነው:: በቅርቡ ወደ ሥራ ይገባሉ ተብለው ከሚጠበቁ ፋብሪካዎች አንዱ ነው:: የኩባንያው ልዩ የኘሮጀክት ማናጀር የሆኑት አቶ ያሬድ ሙሉጌታ እንደሚሉት “ይህንን ፋብሪካ በሌሎች አካባቢዎች

ደብረ ብርሃን...ከገጽ 4 የዞረ

ለመትከል ብዙ ተሞክሯል፤ ነገር ግን ወደ ደብረ ብርሃን ስንመጣ በአንድ ቀን ውስጥ መሬት ልናገኝ ችለናል::”

ደብረ ብርሃንን የመረጡበት ምክንያትም አላቸው፤ “ወደዚህ የመጣነው እያደገ ያለ ከተማ በመሆኑ ነው:: የኢንዱስትሪ ዞን አከላለሉ በጣም የተመቸ ነው:: እዚህ የካሣ ክፍያና የሚነሣ ንብረት እንዲሁም ነዋሪ የለብህም:: ይህ በፍጥነት ወደ ሥራ ለመግባት አመች ነው፣፣ በከተማ አስተዳደሩ በኩልም ምንም ቅሬታ ኖሮን አያውቅም፡ ቢሯቸው ሁሌም ክፍት ነው:: ከዚያ ባሻገር ቅርበቱ፣ የአየር ሁኔታውና ወደፊት የሚኖሩ መሠረተ ልማቶች ለኩባንያችን ወሣኝ ይሆናሉ፣ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥም ወደ ግንባታ ለመግባት ተዘጋጅናል” ብለዋል::

የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ የሥራ ሂደት ባለቤት የሆኑት አቶ ሽፈራው እንደሚሉትም አገልግሎቱ ለባለሐብቶች ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ማድረጉና የባለሐብቶችን ችግሮች በመረዳት አመራሮችና ባለሙያዎች ፈጣን ምላሽ መስጠታቸው ከተማዋ የብዙ ባለሃብቶችን ይሁንታ አግኝታለች:: ለዚህ ማሣያው ባለፈው ዓመት 58 ባለሐብቶች መሬት እንዲያገኙ መደረጉ መሆኑን ገልፀዋል::

“ባለሐብቱ ሙሉ ሂደቱን ካጠናቀቀ ከአንድ ቀን እስከ አንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ ቦታ እንዲያገኝ ይደረጋል:: ሌሎች የመሠረተ ልማት አቅርቦቶችም በተመሣሣይ ፈጣን ናቸው:: በየጊዜው ሒደቱን ለመገምገም የሚያስችል ፎረም ይዘጋጃል:: ከዚህ ባሻገር መሬት በቅናሽ እናቀርባለን:: ይህንነቱ የተረጋገጠና የተረጋጋ አካባቢ መሆኑ፣ ከአዲስ አበባ በቅርበት መገኘቱ፣ ለገበያ ዓመች ስፍራ መሆኑ የአየር ሁኔታውና ህዝቡ ለስራ ያለው ፍላጐት ተደማምሮ ባለሃብቶች ወደ ደብረ ብርሃን እንዲመጡ ምክንያት ሆኗል” ሲሉ ገልፀዋል::

ከንቲባ ታገል አምሣሉ በበኩላቸው ከነዚህ ምቹ ሁኔታዎች ጀርባ ያለው ትክክለኛ ፓሊሲና ስትራቴጅ ዋናው አቅም እንደሆነ ተናግረዋል:: ይህንን የሚፈፅምና የሚያስፈጽም አካል ለውጥ ናፋቂ ከሆነው የከተማዋ ነዋሪ ጋር ተደማምሮ የባለሃሐብቱ ቁጥር በፍጥነት እያደገ እንዲመጣ አድርጓል ብለዋል::

ማን ተጠቀመ?የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው ይዞት

ከሚመጣው ዕድል ውስጥ የውጭ ምንዛሬ ክምችት፣ የቴክኖሎጅ ሽግግርና የተወዳዳሪነት እድል በተጨማሪ ሠፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር አጠቃላይ የምጣኔ ሐብቱን ሂደት ያፋጥናል:: አሳመረች ሐብተ ገብርኤል በአዚላ ኤሌክትሮንክስ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ውስጥ በማሸግ ሥራ ላይ ተሠማርታለች:: አሳመረች ከዚህ በፊት ለሁለት ዓመታት ያህል በጣና ሞባይል ኩባንያ ውስጥ ለሁለት ዓመታት ሰርታለች:: በአሁኑ ወቅት በትውልድ አካባቢዋ ሥራ የተፈጠረላት ወጣቷ ኩባንያው በተለይም ለሴቶች የተሻለ ዕድል መስጠቱን ትናገራለች:: “በጣም ጥሩ

ዕውቀትና ሙያ የምናገኝበት ፋብሪካ ነው:: የተሻለ ተከፋይ ለመሆንም ችያለሁ:: በአጠቃላይ ይህ ፋብሪካ ብቻ ሳይሆን በደብረ ብርሃን እየተቋቋሙ ያሉ ብዙ ኘሮጀክቶች የብዙ ወጣቶችና ሥራ አጥ ዜጐችን ህይወት እየቀየሩ ነው” ትላለች::

ልክ አንደ አሳመረች ሁሉ ከቴክኒክና ሙያ የተመረቁ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች የኢንቨስትመንት ፍሠቱን ተከትሎ ተጠቃሚ መሆን ጀምረዋል:: ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ከሆነም አጋጣሚውን በመጠቀም ወደ ከተማዋ የሚገባው የህዝብ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው:: የንግድ እንቅስቃሴውም አብሮ ማደጉን ይመሠክራሉ:: ከንቲባ ታገል አምሣሉ እንደሚሉት በኢንቨትመንት እንቅስቃሴው የከተማዋና የአጐራባች ህዝቦች ተጠቃሚ እየሆኑ ነው::

“የስራ ዕድል ሁኔታ ሠፍቷል፤ የንግድ እንቅስቃሴውም በጣም አድጓል:: በዚህ የተነሣ የከተማዋ ገቢ የመሠብሠብ አቅምም ክልሉ ከሚመድብልን ዓመታዊ በጀት በላይ በጣም ጨምሯል:: በአጠቃላይ ኢንቨስትመንቱ የከተማዋን ህዝብ ተጠቃሚ ያደረገና ገጽታዋን የለወጠ ነው” ይላሉ::

ፈተናዎችየደብረ ብርሃን የኢንቨስትመንት ፍሠት እጅግ

ፈጣን ለውጥ ቢያመጣም ሁሉም ነገር የተመቸ አለመሆኑን የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ የሥራ ሂደት መሪ የሆኑት አቶ ሽፈራው ማሞ ይናገራሉ:: በተለይም በኤሌክትሪክ ኃይል፣ በመሬትና በውኃ አቅርቦት በኩል ስጋቶች አሉ:: “ምንም አንኳ ወደፊት ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮች ቢሆኑም አሁን ላይ ግን

ትልቅ ስጋቶች ናቸው:: በቂ የሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የለንም፤ መሬትም ቢሆን በሚመጣው ባለሐብት ቁጥር ልክ አለማቅረባችን ሌላው ፈተና ነው:: ተፈላጊነታችን በጣም እየጨመረ በመሆኑ ያለን የኢንዱስትሪ መሬት አልቋል:: ከዚህ ሌላ የውኃ እጥረትም አለ:: ምንም እንኳ ከተማዋ የውኃ ፀጋ ባለቤት ብትሆንም ማልማት አልተቻለም:: በቅርቡ አራት የውኃ ጉድጓዶችን በመቆፈር ችግሩን ለመፍታት ታቅዷል:: እነዚህ በእኛ በኩል ያሉ ስጋቶች ናቸው:: በባለሐብቶች በኩል ያለው ትልቁ ፈተና ደግሞ መሬት ተረክቦ በተያዘለት ጊዜ ወደ ግንባታ አለመግባት ነው:: በልማት ባንክ በኩል ያለው የብድር ሒደት መጓተትም ፋብሪካዎች ዕውን እንዳይሆኑ አድርጓል” ብለውናል::

ፈጣኑ ጉዞና የወደፊት ተስፋዎቹየደብረ ብርሃን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ

ፈጣን ብቻ ሳይሆን ትልቅ ተስፋ ያለው ጭምር ነው:: በተለይም ከደብረ ብርሃን - አንኮበር- አዋሽ- ጅቡቲ የሚዘረጋው መንገድ ወደ አዲስ አበባ የሚደረገውን ጉዞ በ160 ኪሎ ሜትር የሚያሳጥር በመሆኑ ከተማዋን ይበልጥ ተስፋ እንዲጣልባት አድርጓል:: ይህን ተከትሎ የደረቅ ወደብ የሚገነባ ይሆናል:: ከዚህ ባለፈም በከተማዋ የፍጥነት መንገድ ለመገንባት ዕቅድ ተይዟል:: የኃይል ፍላጐቱን በዘላቂነት ለመፍታትም ባለ350 ሜጋ ዋት የኃይል ጣቢያው ለመገንባት 16 ሄ/ር መሬት ተከልሎ ከኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ጋር ርክክብ ተደርጓል:: በቅርቡም ወደ ሥራ ለመግባት እንቅስቃሴ ተጀምሯል:: ደብረ ብርሃን በፌዴራል መንግስቱ ለምግብ ኢንዱስትሪ ፓርክነት የተመጠች በመሆኑ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በ106 ሄ/ር መሬት ላይ የሚያርፍ የምግብ ኢንዱስትሪ ፓርክ ባለቤት ትሆናለች::

በዚህ ፓርክ ከ24 ሺህ በላይ ሠራተኞች የሥራ ዕድል ያገኛሉ:: አቶ ሽፈራው ማሞ አሁን ጊዜው የደብረ ብርሃን ነው ይላሉ:: “እየሠራን ያለነው ከተማዋን የኢንድስትሪ ከተማ ለማድረግ ነው:: እነዚህ በመንግስት የተያዙ ግዙፍ ኘሮጀክቶችና በግሉ ዘርፍ የሚከናወኑት ኘሮጀክቶች መሬት ላይ ሲያርፉ ከተማዋ በእጅጉ ትለወጣለች::

እናም በሐገሪቱ ሳሉ የኢንዱስትሪ ከተሞች አንዷ ትሆናለች፤ ይህ አያጠራጥርም” ይላሉ::

በአጠቃላይ በደብረ ብርሃን የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ግስጋሴ ሂደት እነዚህ ተስፋዎች ዕውን ሲሆኑ በከተማዋ ያለው ሥር የሠደደ ድህነትና ገጽታ ይበልጥ መለወጡ አይቀሬ ነው:: ከዚህ ባለፈም በሐገሪቱ የምጣኔ ሐብት መዋቅርና ለውጥ ላይ የራሱን አሻራ የሚያስቀምጥ ይሆናል::

ዘመናዊ ህንፃዎች የደብረ ብርሃን መገለጫ እየሆኑ ነው

“መሬት ያገኘነው በአንድ ቀን ውስጥ ነው” አቶ ያሬድ ሙሉጌታ

“የተሻለ ተከፋይ ለመሆን ችያለሁ” አሳመረች ሀ/ገብርኤል የአዚላ ኤሌክትሮኒክስ ሠራተኛ

Page 35: 12 03 2009.pdf

ገጽ 35በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ማስታወቂያ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያየታች አርማጭሆ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች የ2009 የበጀት ዓመት በተጠቃለለ ግዥ ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች ሎት 2 የጽዳት እቃዎች ሎት 3 የሰራተኞች የደንብ ልብስ ሎት 4 የመኪና ጎማ ሎት

5 የስፖርት እቃዎች ሎት 6 ህትመት /የደረትና የጠረጴዛ ባጅ/ ሎት 7 የውሃ ክሎሪን ሎት 8 የግንባታ እቃዎች/ሲሚንቶና አፍሬዲቪ ፓምኘ /አጃየ/ ከነ ሙሉ ሴቱ ሎት 9 የኤሌክትሮኒክ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ህጋዊ

የንግድ ፈቃድ ካላቸው በሎት ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ባቀረቡ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1. የዘመኑን የ2009 ዓ/ም ግብር የከፈሉና ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያላቸው፣

3. ጠቅላላ የእቃው ዋጋ ከብር 50 ሺህ እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡4. የሚገዙ የእቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡5. ተወዳዳሪዎች አጠቃላይ መረጃቸውን እያሣዩ የስራ ዝርዝር ሰነዱን ከታች/አ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉበት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጽ/

ቤቱ በመቅረብ የማይመለስ 30.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡6. የስራ ዝርዝሩን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒውን በመለየት በተለየ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡7. አሸናፊ የሚለየው በተገዙት የጨረታ ሰነዶች በሎት ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ባቀረበ በመሆኑ ሙሉ በሙሉ በተዘረዘሩት እቃዎች ዋጋ መሞላት አለበት ካልተሞላ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡

8. የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ አንድ በመቶ በጨረታው ወቅት በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡

9. ተወዳዳሪዎች የስራ ዝርዝሩን ሰነድ ማስገባት የሚችሉት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡00 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ በዚሁ ቀን 3፡00 ላይ ታሽጎ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

10. ሁሉም ሎቶች በአንድ ቀን የሚከፈቱ ሲሆን ሎት 1 በ3፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ሌሎች ሎቶች በተከታታይ በየአንድ ሰዓት ልዩነት ይከፈታሉ፡፡11. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ካላንደር የሚዘጋው ከሆነ በቀጣዩ ስራ ቀን እና በተመሣሣይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

12. በጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ኦርጅናል ማህተም፣ስምና ፊርማ መኖር አለበት፡፡13. አሸናፊው ድርጅት ውል በሚገባበት ወቅት 10 በመቶ ዋስትና ጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡14. አሸናፊው ውል ከገባ በኋላ ንብረቱን ሲያቀርብ በየሴክተር መ/ቤቱ እየተዘዋወረ በራሱ ወጭ ገቢ ያደርጋል፡፡

15. መ/ቤቱ ጨረታውን ላልተወሰነ ጊዜ የማራዘም፣በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡16. ንብረቱን በሰዓቱ ካላቀረበ ውል በገባበት ቀን መጠን 1 በመቶ ይቀንሣል፡፡

17. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 273 04 20 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የታች አርማጭሆ ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

የጨረታ ጥሪ ማስታዎቂያየአብክመ ትምህርት ቢሮ ግንባታቸው ተጀምሮ የተቋረጡትን በደቡብ ጎንደር ዞን በእስቴ ወረዳ የጅብ አስራ 2ኛ ደረጃ እና በሰሜን ሸዋ ዞን በጊሼ ራቤል ወረዳ የደል 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶችን ደረጃቸው G.C-8/B.C-7

የሆኑና በላይ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ስራ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ስለፈለገ መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጥሪ ያደርጋል፡፡

1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በአብክመ ትም/ቢሮ ግን/ቁጥ /ክት/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 12 ማመልከቻ በማቅረብና የማይመለስ 200.00 ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት

የሚችል ሲሆን የግንባታዎች ማጠናቀቂያ ጊዜ ስራው ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ለጅብ አስራ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 60 ተከታታይ ቀናት እና ለደል 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት 45 ተከታታይ ቀናት

ናቸው፡፡

2. የጨረታ ማስከበሪያ የውለታውን 2 በመቶ ሲሆን የዋስትናውም አይነት በ C.P.O ወይም በጥሬ ገንዘብ (የደረሰኙ ኮፒ) ወይንም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ሆኖ ለአብክመ ትም/ቢሮ ከጨረታው

ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡

3. የጨረታ ሰነድ መግዣ ጊዜው የጥሪ ማስታወቂያው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት እና በ22ኛው ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ ሲሆን ተጫራቾች ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው

ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡የጨረታው መክፈቻ ቀንም በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ይሆናል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ፎርም /BID FORM/ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ /PRICE SCHEDULE/ በጥንቃቄ መሙላት የሚኖርባቸው ሲሆን ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን በሰነዱ ላይ የቀረበው ስራ በውሉ አጠቃላይ ዋጋ

የሚሸፈን ይሆናል፡፡

5. የሚከተሉት መስፈርቶች ካልተሟሉ ከጨረታ ውጭ ያደርጋሉ፡፡

5.1. ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዘጋቢ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት እንዲሁም የግብር መለያ ቁጥር /T.I.N No/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡፡፡

5.2. ተጫራቾች አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የጨረታ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: በተጨማሪም በዋናው ሰነድና በኮፒው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ገዥው ዋናው የጨረታ ሰነድ ይሆናል፡፡

5.3. የጨረታ ሰነዱ የሚታሸግበትን ፖስታዎች ጨምሮ በሁሉም የዋናውና በኮፒው የጨረታ ሰነዶች ገጾች ላይ ማህተም በማድረግ በጥንቃቄ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5.4. ከዚህ በፊት ከአብክመ ትም/ቢሮ ፕሮጀክቶችን ወስደው ያቋረጡና በህግ የተከሰሱ ሁሉም ተቋራጮች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፡፡

5.5. ከአብክመ ትም/ቢሮ ጋር ውል በመውሰድ በአሁኑ ሰዓት የግንባታ ስራዎችን እየሰሩ የሚገኙና አፈጻጸማቸው ከ 90 በመቶ በታች የሆኑ ተቋራጮች መሳተፍ አይችሉም፡፡

5.6. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከተማ ልማት፣ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ በ2008 ዓ.ም ባሰራጨው የተቋራጮች አፈጻጸም ውጤታቸው 75 በመቶ እና ከዚያ በላይ ያላቸው መሆን አለበት፡፡

5.7. በጨረታ ሰነዱ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሚቀርበው ነጠላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለው ግልጽና የማያሻማ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ስርዝ ድልዙን ፈርሞ በፊደል ካልጻፈ ውድቅ ይሆናል፡፡

6. የብሎኮች አይነትና ብዛት፡- የተማሪዎች መማሪያ /ብዛት-2/፣ ላይበራሪ/ብዛት-1/ ፣ላቦራቶሪ/ብዛት -2/ ፣አይ ሲ ቲ ህንፃ /ብዛት -1/ ፣የተማሪዎች ሽንት ቤት/ብዛት-1/ እና የመምህራን ሽንት ቤት /ብዛት-1/ በድምሩ 8 ህንፃዎች /ብሎኮች ናቸው፡፡

7. አሰሪ መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በሚከተለው አድራሻ ተጨማሪ ማስረጃ ማግኘት ይችላል፡፡

አብክመ ትምህርት ቢሮ ስ.ቁ፡ 0582-221-435/0582-207-056, ፖ.ሳ.ቁ፡- 764, ባህር ዳር

የአብክመ ትምህርት ቢሮ

Page 36: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 36

ከገጽ 19 የዞረ

የትራምፕ... አሜሪካ በኦባማ ዘመን አዘጋዋለሁ ያለችውን

የጓንታናሞ ቤይ እስር ቤት ዳግም "በኔ ዘመን ትከፍተዋለች" ማለታቸው ሰውየው እውነትም አምባገነን ናቸው የሚለውን እሳቤ አጠናክሯል:: ያም ሆነ ይህ ግን "እባብ ለእባብ ይተያያል… ነውና ነገሩ" የትራምፕ ፀባይ ለአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ስጋት የሆነባቸው አይመስልም::

ዕርዳታበዓለም አቀፍ የረጅነት ደረጃ ውስጥ ግንባር

ቀደሙን ስፍራ የምትይዘው አሜሪካ በዚህ ረዥም እጇ በደሃ ህዝቦች ዘንድ "ተስፋችን!" እስከመባል ደርሳለች:: አፍሪካ ደግሞ ትልቋ ተጠቃሚ ናት:: ዋሽንግተን ባለፈው ዓመት ብቻ እንኳ 31 ቢሊዮን ዶላር የልማት እርዳታ ለአፍሪካ አበርክታለች:: አሜሪካ በአፍሪካ ውስጥ በሃይል፣ በኢንቨስትመንትና በጤና መስክም ትልቅ ተሳትፎ

አላለቀም:: በምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሚዛን ባለቤቷ ኢትዮጵያም በውስጥ የፖለቲካ ውጥረቷ አንዳች ዓለም አቀፍ ድርድርን ትሻለች::

ቻይና፣ ኮርያ፣ ቱርክ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የአፍሪካ አጋርነታቸውና የገንዘብ ተጽዕኗቸው ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክሯል:: የደቡብ ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት እና የምግብ እጥረት እንዲሁም የዴሞክራቲክ ኮንጐ የምርጫ ጦስ ተጨማሪ የራስ ምታት እንደሆኑ ቀጥለዋል:: እነዚህ ጉዳዮች ደግሞ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከአሜሪካ ጋር የሚገናኙና የልዕለ ሃያሏን ድጋፍ የሚፈልጉ ናቸው ሲል ቢቢሲ በትንታኔው አስፍሯል::

ታዲያ ትራምፕ ከእነዚህ ሁኔታዎች ጋር እንዴት ሊጋፈጡ ይችላሉ? ሲልም ይጠይቃል:: ምክንያቱም የዶናልድ ትራምፕ በአጥር የተከበበ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ አሜሪካ በአፍሪካ ያላትን ተሰሚነት ሊያሳጣት ይችላል:: ነገር ግን ሰውየው ካላቸው የዓለም አቀፍ የሽብርተኝነት ጥላቻ አንፃር ለአፍሪካ ስጋት በሆኑት የሽብር ቡድኖች ላይ ውጤት ሊኖራቸው እንደሚችል በአፍሪካ ደህንነት ጥናት ተቋም ተመራማሪ ዛክሪ ዶንፊልድ ተናግረልዋል::

በሌላ በኩል ግን ትራምፕ በሚያራምዱት የውጭ ፖሊሲ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን

አላት:: የባራክ ኦባማ የሃይል አፍሪካ ፕሮጀክት ብዙ ሚሊዮን አፍሪካውያንን ከኤሌክትሪክ ብርሃን ጋር ለማስተዋወቅ የነደፉትና ተግባራዊ ያደረጉት መርሃ ግብር ተስፋ የተጣለበት ነው::

ፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ በበኩላቸው ለአፍሪካ የኤች አይ ቪን ስርጭት ለመቀነስ ባወጡት ዕቅድ ሚሊዮኖች የፀረ ኤች አይቪ መድኃኒት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል:: እናም እንዲህ ያላው የአሜሪካ የድጋፍ እጅ በትራምፕ ዘመን ሊታጠፍ እንደሚችል ተሰግቷል:: ስጋቱ ደግሞ እንዲሁ የመጣ ሳይሆን ትራምፕ ራሳቸው በቅስቀሳ ወቅት ካሰሙት የእርዳታ ተቃውሞ በመነጨ ነው:: እርሳቸው ከዋሽንግተን ፓስት ጋር በነበራቸው ቆይታ "ትኩረቴ ወደ ውስጥ እንጂ፤ ወደ ውጭ እንደማይሆን ልነግራችሁ እፈልጋለሁ:: እኛ ለእርዳታ የሚሆን ገንዘብ የለንም!:: ምክንያቱም ሃገራችንን መገንባት ስለሚኖርብን!" ማለታቸውን ተከትሎ የአሜሪካ የወደፊት እርዳታ ጥያቄ ውስጥ ወድቋል:: ትራምፕ ይህን ይበሉ እንጂ፤ "ስለ አፍሪካ ያን ያህል እውቅና ያለው አይመስለኝም:: እውነታው ግን አሜሪካ አይኗን ከአፍሪካ ልትነቀል የምትችልበት ሁኔታ አልታየኝም" ነው ያሉት የደህንነት ጥናት ተቋሙ ሊቀመንበር ጃኪ ሲሊየር::

ጽንፈኝነት፣ ሽብርተኝነትና ደህንነትአሜሪካ በአፍሪካ ውስጥ ያላት ወታደራዊ

እንቅስቃሴ ለስላሳና ምስጢራዊ የሚባል ነው:: እንዲያውም እንቅስቃሴው ጽንፈኛ ሚሊሻዎችን ከመዋጋት ባለፈ ደምቆ አይታይም:: በአህጉሩ የደህንነት ስጋት ናቸው የሚባሉት አልቃይዳ ሰራሹ አልሸባብና የጽንፈኛ ታጣቂዎች በሚገኙባቸው ሃገራት ወታደራዊ ካምፖችን መስርታለች:: እንዲያም ሆኖ ግን “አሜሪካ በአህጉሩ ያላት ተጽዕኖ ጥያቄ ውስጥ ነው" ይላል ቢቢሲ:: በሳህል በረሃ የሚካሄደው ህገወጥ የሰዎችና የጦር መሳሪያ ዝውውር እንዲሁም የጽንፈኛ ሚሊሻዎች መጠናከር በአሁጉሩ የደህንነት ስጋት ነው:: የፌዴራል መንግስት ለመመስረት ትግል ላይ የምትገኘው ሶማሊያ አሁንም የቤት ስራዋ

ከሀገራቸው እንደሚያስወጡ መናገራቸው እንዲሁም በሶማሊያውያን ላይ የለጠፉት የሽብርተኝነት ታርጋ ምን አልባትም ብዙ አፍሪካውያን ወጣቶችን በስሜት ወደ ሽብር ቡድኖች ለመግባት እንዳይገፋፋቸው ስጋት ፈጥሯል::

የአየር ንብረት ለውጥየሶስተኛው ዓለም ሃገራት ሃብታም ሃገራትን

ከሚፋለሙባቸውና በንግግር ከሚረቱባቸው ጉዳዮች አንዱ ነው የአየር ንብረት ለውጥ:: ሁለቱ በተገናኙባቸው መድረኮች በትንሹም ቢሆን ታዳጊ ሃገራት የተሰሚነት ድምፃቸው ጐልቶ ይታያል:: ይህ የጐላ ድምጽም ውጤት አምጥቶ ባለፈው ዓመት የፓሪሱ የትግበራ ስምምነት እንዲፈረም ምክንያት ሆኗል::

ሃብታም ሃገራት ለአየር ንብረት ለውጥ ካላቸው የላቀ ድርሻ አንፃር ተጐጅ ሃገራትን በገንዘብ እንዲደግፉና በክፍለ ዘመኑ መጨረሻ የዓለም የሙቀት መጠን እንዲቀንስ የተስማሙበት ታሪካዊ መድረክ ሆኖም ይታወሳል::

በዚህ ስምምነት ታዲያ እንደ አፍሪካ ያሉ የችግሩ ገፈት ቀማሾች በገንዘብ ብቻ ሳይሆን አሜሪካን ጨምሮ የበለፀጉ ሃገራት ኢንዱስትሪዎቻቸውን ለመቀየር በተስማሙበት የፓሪስ ጉባኤ ተጠቃሚ ይሆናሉ:: ነገር ግን ትራምፕ ይህ ስምምነት "እኔ እያለሁ አይተገበርም" ማለታቸውና እንዲያውም የአየር ንብረት ለውጥ የሚባለው ነገር የቻይና ሴራ እንደሆነ መግለፃቸው ታሪካዊውን ስምምነት ጥላሸት ሊቀባው እንደሚችል ተነግሯል::

የአካባቢ ተቆርቋሪዎችም በሞሮኮ ማራካሺ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል:: ትራምፕ ይህንን ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ቀዳሚ ተጐጅ ሆና መቀጠሏ አይቀርም ተብሏል:: ያም ሆነ ይህ ግን የትራምፕ መንገድና የአፍሪካ እጣ ፈንታ ከጥር 20 በኋላ የሚታይ ይሆናል:: ቢቢስና አፍሪካን ሪፖርት የመረጃው ምንጭ ናቸው::

ከገጽ 48 የዞረ

የምርጦቹ...የናይጀሪያው ኑዋንክዎ ካኑ እ.ኤ.አ. በ1999

ከእንግሊዝ አርሰናል ክለብ ጋር ስሙ የናኘበት ዘመን ነበር:: በወቅቱ አርሰናል ቸልሲን 3ለ2 ሲረታ ካኑ በ17 ደቂቃ ውስጥ ሀት-ሪክ የሰራበት ዘመን ነበር::በመሆኑም በአርሰናልና በብሄራዊ ቡድኑ ባሳየው ድንቅ አቀም በቢቢሲ ተመርጦ ተሸልሟል::

በ2000 (እ.ኤ.አ.) የካሜሩኑ ፓትሪክ ሞቦማ ይጠቀሳል:: ሞቦማ አገሩ በ2000 በሲድኒ ኦሊምፒክ ስፔንን ረተታ የወርቅ ሜዳሊያ ስታጠልቅ ሞቦማ የቡድኑ ሞተር ነበር:: በተሰለፈበት የጣሊያኑ ፓርማ ክለብም ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል:: ስለሆነም በቢቢሲ ምርጥ ተብሎ ተሸልሟል::

የ2001 ዱን ሽልማት የተቀናጀው ደግሞ ጋናዊው ሳሙኤል ኩፎር ነበር:: ለጀርመኑ ባየርን ሙኒክ ክለብ የሚጫወተው ኩፎር ክለቡን ለድል አብቅቷል:: ሀት-ሪክ በመስራትም ይታወቃል::

155 ሺህ ድምጽም የኮትዲቮሩን ድሮግባንና የካሜሩኑን ኢቶን በልጦ ተመርጧል::

በ2009 ዲዲየር ድሮግባ ከኮትዲቮር፣ በ2010 አሳሞኽጋያን ከጋና፣በ2011 አንድሬ አየው ከጋና፣በ2012 ክሪስቶፈር ካቶንጎ ከዛምቢያ ሁሉም በአገራቸው ብሔራዊ ቡድን ባሳዩት ድንቅ እንቅስቃሴና ውጤታማነት ታጭተውአሸንፈዋል::

የ2013 የቢቢሲ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ክብርን የተቀናጀው ግዙፉና ቁመተ መለሎው ያያ ቱሬ ነው:: በዚሁ ዓመትም በፊፋ የባሎን ዶር የተሸላሚዎች የእጩ ዝርዝር ስሙ ተካቶ ነበር:: በማንቸስተር ሲቲ ባሳየው ብቃትም ምርጥ ሆኖ ተሸልሟል::

ሌላው የቢ.ቢ.ሲን የ2002 የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ክብርን የተቀናጀው “ቁጣው አፍንጫው ላይ ነው፤ ነገር ግን በቴክኒክና በታክቲክ ብቃቱ የተመሰከረለት - ፀባይ የለሹ፤ ብዙ ጊዜ የቢጫና ቀይካርድ ሰለባ ነው” የሚባለው ከሴኔጋል አል- ሀጂ ዲዮፍ ነው:: ለፈረንሳዩ ሌንስ ክለብ እንዲሁም ለእንግሊዙ ሊቨርፑል የተሰለፈው ዲዮፍ በወቅቱ ሀገሩን ለአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ አድርሷል:: በካሜሩን ተሸንፈው ዋንጫ ቢያጡም::

ናይጀሪያዊው ጄይ ጄይ ኦካቻ ደግሞ የ2003 ክብርን ተጎናጽፏል:: በወቅቱ በቦልተን ወንደር ርስ ክለብ “ጀግና” ተብሎ ተወድሷል:: በ2004ም ኦካቻ ድሉን ደግሞታል:: በናይጀሪያ ታሪክም አንድ ሺኛ ግብ በማስቆጠር ባለታሪክ ነው::

ከግብጽ ሙሐመድ ባራካት በችሎታና በባህርይ ተመሰክሮለት የ2005 የቢ.ቢ.ሲ ምርጡ ተጫዋች ለመሆን በቅቷል:: ባራካት በሰሜን አፍሪካ ታሪክ የመጀመሪያ የቢ.ቢ.ሲ ተሸላሚ ነው::

በ2006 የጋናው ሚካኤል ኢሴን ለእንግሊዙ ቼልሲ ሲጫወት ባሳየው ብቃቱና አገሩንም ለአለም ዋንጫ ማሳለፉ ሽልማቱን እንዲቋደስ አድርጎታል ::

ኢማኑኤል አዲባየር ደግሞ ከቶጐ የ2007 የቢ.ቢ.ሲ ክብርን ተጐናጽፏል:: አዲባየር በእንግሊዙ አርሰናል ክለብ እየተጫወተ በክለቡም በአገሩም ቡድን ተጽዕኖ መፍጠር ችሏል::እናም ለሸልማት በቅቷል::

በ2008 ሙሐመድ አቡትሪካ ከግብጽ፣ አገሩ የ2008 የአፍሪካን ዋንጫ እንድትወስድ አድርጓል::

አልጀሪያዊው ያሲኒ ብራሂሚ በፖርቱጋሉ ፖርቶክለብና በአልጀሪያ ብሔራዊ ቡድን ባሳየው ብቃቱና ውጤታማነቱ ተመዝኖ ቢ.ቢ.ሲ በ2014 ሸልሞታል::

በ2015 የኮትዲቮር አምበል የነበረው፤ በእንግሊዝ የማንቸስተር ሲቲ ክለብ ወሳኝ ጊዜን አሳልፏል:: ብሔራዊ ቡድኑም የአፍሪካን ዋንጫ እንዲወስድ የአንበሳውን ድርሻ ተወጥቷል፤ ያያ ቱሬ:: እናም ቱሬ ለሁለተኛ ጊዜ በቢ.ቢ.ሲ የአፍሪካ ምርጡ ተጫዋች ተብሎ ሽልማቱን ወስዷል::

እነሆ ለ2016 ደግሞ አምስት ተጫዋቾች በእጩነት ቀርበዋል:: እነሱም፦ ለጀርመኑ ዶርትሙንድ ክለብ የሚጫወተው የጋቦኑ ፔሬ ኢሚሪክ ኡባሜ ያንግ፣ ለእንግሊዙ ዌስት ሀም ክለብ የሚሰለፈው ጋናዊው አንድሬ አየው፣ ለእንግሊዙ ሌይሲስተር ሲቲ የሚጫወተው አልጀሪያዊው ሪያድ ማህሬዝ፣ለማንቸስተር ሲቲ የሚሰለፈው ኮትዲቮራዊው ያያ ቱሬና በ2016/17 በእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ከሳውዝ አምፕተን ሊቨርፑልን በ34 ሚሊዮን ፓውንድ በመቀላቀል ውዱ አፍሪካዊ ተጫዋች የተባለለት ሳዲዩ ማኔ ናቸው::ታዲያ ማን ያሸናፍ ይሆን?

ቢ.ቢ.ሲና ዴይሊ ሜይል እንደዘገቡት ምርጫው በመላው ዓለም ያሉየስፖርት ቤተሰቦች የሚሳተፉበት ይሆናል:: እ.ኤ.አ. ህዳር 28 ቀን 2016 ድረስ አንድ ሰውለአንድ ተጫዋች ድምጽ መስጠት ይችላል:: ውጤቱም ታህሳስ 12 ቀን 2016 በቢ.ቢ.ሲ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥንና ዌብ ሳይት በቀጥታ ስርጭት ከቀኑ አምስት ሰዓት ከ35 ደቂቃ ላይ ይፋ ይሆናል::

የሚረር የስፖርት ተንታኝ አለን ቦብ እንደገለፀው፤ በእጩነት የቀረቡት ተጫዋቾች

የቴክኒክና ታክቲክ ብቃት፣ ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው እና ምጡቅ ብቃታቸው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም:: በእኛ አገር “ቀጥ ያለ ሲታጣ፣ ይመለመላል ጎባጣ” የሚሉት አይነት:: ለማንኛውም ሌሲስተር ሲቲን ለዋንጫ ያበቃው ሪያድ ማህሬዝ ይመረጣል የሚል የቅድሚያ ግምቱን አስቀምጧል::

ቢቢሲ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ የእግር ኳስ ተጫዋች ብሎ መሸለም የጀመረው እ.ኤ.አ. በ1992 ነበር:: በወቅቱም የጋናው አቢዲ ፔሌ መሸለሙ ይታወሳል::

ያያ ቱሬ -ኮትዲቯር፤

አንድሬ አየው - ጋና፤

ኡባሜያንግ - ጋቦን፤

ሪያድ ማህሬዝ - አልጀሪያ፤

ሳዲዮማኔ-ሴኔጋል፤

Page 37: 12 03 2009.pdf

ገጽ 37በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. ማስታወቂያ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያየመርጡለ ማርያም ግብርና ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ለ2009 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1

የጽህፈት መሣሪያዎች ሎት 2 የደንብ ልብስ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች ሎት 4 የደንብ ልብስ ስፌት ሎት

5 ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ በጨረታው መሣተፍ የሚፈልግ

ማንኛውም ተጫራች እና የሚከተሉትን ማሟላት አለበት::

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት /ቲን

ናምበር/ ያላቸው፣

2. የእቃው ጠቅላላ ዋጋ ከ50 ሺህ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት

ማቅረብ የሚችሉ፣

3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ

ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

4. ተጫራቾች ሞልተው የሚያቀርቡት የጨረታ መወዳደሪያ ሃሣብ ወይም ሰነድ/Bid Docu-

ment/ ላይ የድርጅቱን ስም ፣ሙሉ አድራሻና ማህተም መርገጥ ያለባቸው ሲሆን በእያንዳንዱ

ገጽ ላይ የድርጅቱ ባለቤት ወይም የሕጋዊ ወኪሎቻቸው ፊርማ በማስቀመጥ ለዚሁ

በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በታሸገ ኢንቨሎኘ ማስገባት ይችላሉ፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ

ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50.00 በመክፈል ከግዥ ፋይ/ንብ/አስ ደጋፊ የስራ

ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ::

6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን

ከጠዋቱ 3፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል::

7. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል::

8. ተጫራቾች አሸናፊው ከተለየ በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/

ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ

ይኖርባቸዋል::

9. አሸናፊ ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸው በተገለፀላቸው በ5 ቀናት ውስጥ በአካል

በመቅረብ የውል ማስከበሪያ/Performance bond/ ገንዘብ የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ

በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርባቸዋል::

10. አሸናፊ ተጫራቾች በጨረታ ማሸነፋ ተገልጾለት በተጠቀሰው ቀን በአካል ቀርቦ በወቅቱ

ውል የማይዝ ከሆነ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ውርስ ሆኖ ኮሌጁ ወደ ሌላ የግዥ

አፈፃፀም ስርዓት የሚቀጥል ይሆናል::

11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ልዩ ልዩ ታክሶችን ያጠቃለለ መሆን ይኖርበታል::

12. የድርጅቱ ህጋዊ ወኪሎቻቸው የውክልና ማስረጃቸውን ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት

ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::

13. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታውን

መክፈት መብቱ ሲሆን ተጫራቾችም ኮሌጁ በሚያሣርፈው ውሣኔ ተገዥ ይሆናሉ::

14. ኮሌጁ የሚገዛውን እቃ ብዛት 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው::

15. የጨረታ አሸናፊዎች አስፈላጊውን ወጭ በራሣቸው ሸፍነው መ/ቤቱ ድረስ ማስረከብ

አለባቸው::

16. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ

የተጠበቀ ነው::

17. ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ ላይ ማብራሪያ /የማሻሻያ/ ሃሣብ ጥያቄ ካላቸው በአካል በመቅረብ

ወይም በስልክ ቁጥር 058 666 00 27 /058 666 00 08 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

የመርጡለ ማርያም ግብርና ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበደቡብ ጎንደር ዞን ታች ጋይንት ወረዳ የአርብ ገበያ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የአውቶ ማሰልጠኛ እቃዎች ፣የግብርና ማሰልጠኛ እቃዎች ፣የደንብ ልብስ እና አላቂ የትምህርት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ናምበር/ ያላቸው፣3. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣4. የግዥ መጠኑ ከብር 50 ሺህ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው፡፡ ማስረጃ ማቅረብ

ይኖርባቸዋል፡፡5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን

ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30.00 ከግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ በመገኘት ገንዘቡን በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጥ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በኮሌጁ የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ እና ያስገቡትን ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ዓ/ገ/ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት የስራ ቀናት ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአርብ ገበያ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 268 00 78 በስራ ቀናት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአርብ ገበያ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለክልል ም/ቤት ጽ/ቤት 2009 ዓ/ም በጀት ዓመት የተለያዩ የቢሮ

እቃዎችን ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 3 የጽዳት እቃዎች ሎት 4

የተሽከርካሪ ጎማና ሌሎች እቃዎች ሎት 5 የደንብ ልብስ ብትን ጨርቃ ጨርቃ ፣ ጫማ ፣ሸሚዝ ፣ቦት

እና ካፖርት ሎት 6 የህንፃ መሣሪያዎች ከላይ በተገለጹት ዝርዝሮች መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ

ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር

ይችላሉ፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ያላቸው፣

3. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የገንዘብ መጠን ከ50 ሺህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የእቃዎችን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30.00 በመክፈል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 48 ቀርበው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ለሞሉት ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚፈልጉ ለጽ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በሞዴል 85 በመክፈል ደረሰኙን ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በክልል ም/ቤት ጽ/ቤት በግዥ፣ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 40 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 2009 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ፣ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 40 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጽ/ቤቱ ጨረታውን ከመክፈቱም በተጨማሪ ጨረታው ሲከፈት ለሚተላለፉ ውሣኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡

10. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

11. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አማራ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 40 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 47 22 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 21 51 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

12. ተጫራቾች በውድድር አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች አማራ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት ድረስ

በማምጣት ለንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት

Page 38: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 38

ፊት ለፊት...ከገፅ 13 የዞረ

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም ለአርሶ አደሮች ምትክ ቦታና ካሳ ሰጥቶ የሚተዳደሩበትን አማራጭ መሻት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል:: ይህም በዋነኛነት የዞንና የክልል ድጋፍን እንደሚሻ አቶ ብርሃኔ ገልጸዋል::

የአማራ ክልል ውኃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ይመር ሀብቴ በበኩላቸው የዓለም ከተማን የንጹህ መጠጥ ውኃ ችግር ለመፍታት በጥናት ላይ የተመሰረተ የጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ መደረጉን አውስተዋል:: "ይሁን እንጂ፣ በተደጋጋሚ በተደረጉ ጥረቶች ውኃ የማግኘት አማራጭ ዓለም ከተማ አካባቢ የተዘጋ ጉዳይ ነው" ብለዋል:: አቶ ይመር እንዳሉት በከተማዋ አቅራቢያ አርሶ አደሮች ለመስኖ የሚጠቀሙበት የምንጭ ውኃ አሁን ላለው የዓለም ከተማ ህዝብ ከአምስት እስከ አስር ዓመት በቂ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ:: በመሆኑም የተሻለው መፍትሄ በአካባቢው ያሉት አርሶ አደሮች ኑሯቸውን ከመስኖ ወደ ሌሎች አማራጮች እንዲቀየሩ በማድረግ ውኃውን በሙሉ አቅም ለመጠጥ ማዋል እንደሆነ አብራርተዋል:: ይህን ሀሳባቸውንም፣ "ከውኃ ሀብት አስተዳደር ፖሊሲያችን አንጻርም ቅድሚያ ለሰው ልጆች መጠጥ፣ ቀጥሎ ለእንስሳት፣ በሶስተኛ ደረጃ ለአትክልት መዋል አለበት" በማለት ያጠናክራሉ::

መንገድከዓለም ከተማ እስከ ሙከጡሪ ያለው

አስፋልት መንገድ ግንባታ መዘግየት በመድረኩ ጥያቄ ቀርቦበት ነበር:: በወቅቱም የአመራር አካላት ችግሩን ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ ጠቁመው ነበር:: ቢሆንም ወ/ሮ ዘውዲቱ "የዚህ መንገድ ግንባታ ጉዳይ ተቀብሮ ይገኛል" በማለት ችግሩ አለመቃለሉን ገልፀዋል:: ባንጻሩም ከዓለም ከተማ መሀል ሜዳ ያለው እና የዓለም ከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች እየተሠሩ እንደሆነ ወይዘሮዋ ጠቁመዋል::

"ስልጣኔ የሚመጣው ከመንገድ ጋር ነው:: ሆኖም ከዓለም ከተማ ሙከጡሪ ያለው መንገድ ግንባታ አሁን ቢጀመርም ዘግይቷል" ሲሉ የጠቆሙት ደግሞ አቶ በለው አስጨናቂ ናቸው:: ነዋሪው እንዳሉት ግንባታው ከዚህ በኋላ እንዳይዘገይ ትኩረት መሰጠት አለበት::

አቶ ጌቱ ቅጣው የዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ኮንስትራክሽንና ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ፣ "አስር ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገድ ተከፍቷል:: በዚህም ቀበሌን ከቀበሌ ማገናኘት ተችሏል ሲሉ ከመድረኩ በኋላ ስለተደረገው እንቅስቃሴና ስለመጣው ለውጥ አብራርተዋል:: አቶ ጌቱ በማያያዝም ከሁለት ኪሎ ሜትር በላይ ነባር መንገድ መጠገኑን አስታውቀዋል:: "ይሄን ስንሠራ ግን ሽፋኑ የማደጉን ያህል ጥራቱ ላይ የሚፈለገው ለውጥ መጥቷል ማለት አይደለም" ብለዋል:: ስለሆነም በ2009 ህብረተሰቡን በማሳተፍ ጥርጊያ መንገዶችን ወደ ድንጋይ ንጣፍ ማሳደግ፣ ጠጠር ያልለበሱትን ደግሞ ማልበስ እንደሚገባ አስረድተዋል:: የተፋሰስ ግንባታም የመንገዶችን እንዲሁም ቤቶችን ደህንነት ከመጠበቅ አንፃር ትኩረት የሚሰጠው ተግባር እንደሆነ አቶ ጌቱ ተናግረዋል::

በገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የፕላኒንግና ኮንትራት አስተዳደር ኃላፊ አቶ አስፋው ድርብሳ የዓለም ከተማ መሀል ሜዳ መንገድ ግንባታ ዘግይቷል" የሚለው የተቋራጩ ችግር እንዳልሆነ ያብራራሉ:: ለዚህም ወደ ግንባታ ሲገቡ የነበረው የመንገድ ዲዛይን የሚያሠራ አልነበረም:: በመሆኑም ዲዛይኑን ለማስተካከል ሰባት ወራት ጠይቋል:: "አሁንም ዲዛይኑ በትንሽ በትንሹ እየተሰጠን ስለሆነ በሙሉ አቅማችን ወደ ሥራ አልገባንም" ይላሉ:: የአካባቢው መልክዓምድራዊ አቀማመጥ አመቺ አለመሆንም ሥራው በተፈለገው ፍጥነት እንዳይከናወን ስለማድረጉ አስረድተዋል::

ድርጅቱ እነዚህ ችግሮች ቢኖሩም ስራውን ለማከናወን ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል:: በዚህም፣ "ፕሮጀክቱ ከጠቅላላው

የውሉ የሥራ መጠን አንጻር 55 በመቶ መከናወኑን አስታውቀዋል:: አስፋልት ለማልበስ 15 ኪሎ ሜትር ዝግጅት መደረጉንም ገልፀዋል:: አቶ አስፋው የመንገዱ ግንባታ በ2013 መጀመሩን አውስተው በውሉ መሠረት ከአንድ ዓመት በኋላ ማለቅ እንዳለበት ጠቁመዋል::

ስለሆነም "የዘገየው ተካክሶ ሥራው በፍጥነት መከናወን አለበት:: በእኛ በኩል አስፈላጊው ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል" ሲሉ አቶ ሳምሶን ለመንገዱ ግንባታ የተሰጠው ትኩረት ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል::

ጤና ዓለም ከተማ እናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

የአገልግሎት አሰጣጥም ሆነ የመድኃኒት አቅርቦት ችግር እንደሌለበት የጠቆሙት አቶ በለው አስጨናቂ ናቸው:: ነዋሪው እንዳሉት የባለሙያ እጥረቱም ሙሉ በሙሉ ባይፈታም ተቃሏል::

ይሁን እንጂ፣ ሲስተር አልማዝ አውግቸው ሆስፒታሉ ስፔሻሊስት ሀኪም ስለሌለው ህሙማን ወደ ደብረ ብርሃንና አዲስ አበባ "ሪፈር" ስለሚባሉ ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል:: ችግሩ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠውም ጠይቀዋል::

ዶክተር ጌትነት ግርማ የዓለም ከተማ እናት ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር በበኩላቸው በተለይም ለዓይን፣ ማህፀንና ፅንስ እንዲሁም ለቀዶ ህክምና "ሪፈር" የሚባል ህሙማን በመንገዱ አመቺ አለመሆንና በመጓጓዣ እጦት ህክምና ሳያገኙ እንደሚቀሩ አስረድተዋል::

አቶ አየልኝ ሙሉ ዓለም የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ የዓለም ከተማ እናት ሆስፒታል የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመሆኑ ለደረጃው የሚመጥኑ ጠቅላላ ሀኪሞች መመደባቸውን ጠቁመዋል:: እነዚህ ሀኪሞችም በሆስፒታሉ ደረጃ የሚሰጡ ህክምናዎችን እንደሚሰጡ ገልፀዋል:: "ሲኒየር ወይም ስፔሻሊስት ሀኪም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ላይ እንመድብ ብንልም ያለው መዋቅር አይፈቅድም" ሲሉ እየቀረበ ያለው ጥያቄ ትክክል አለመሆኑን አስገንዝበዋል::

ሥራ ፈጠራ "መርሐ ቤቴ ወረዳ ላይ ማዕድናት አሉ::

ማዕድናቱ እየተጫኑ ከሚሄዱ እዚሁ ማልማት አለብን:: ይሄ ለወጣቱ የሥራ ዕድል ይፈጥራል:: ለአካባቢው ዕድገትም ጠቃሚ ነው" የሚል ሀሳብ መድረኩ ላይ ቀርቦ ነበር:: ሆኖም ጥያቄው ወደ ተግባር አልተቀየረም" በማለት ቅሬታ አዘል አስተያየታቸውን ያካፈሉን ደግሞ አቶ አብዩ አማከለ ናቸው:: አቶ አብዩ እንደሚሉት ማዕድናቱን በግብአትነት የሚጠቀም የብርጭቆ ፋብሪካ ለመገንባት ወጣቶች ጠይቀው ነገ ዛሬ ምላሽ ይሰጠናል በሚል እየተጠባበቁ ነው::

መምህር ታየሰው በላቸው የተባሉት ነዋሪም፣ "ማዕድናት እዚሁ ሊለሙና ወጣቶችም የሥራ ዕድል ሊፈጠርላቸው ሲገባ ይሄ ያልሆነው ለምንድን ነው?" የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን ያስታውሳሉ:: ሆኖም መልስ አልተሰጣቸውም፤ የአካባቢው ሀብት ለአካባቢው ልማት መዋል ሲገባው ባለሀብቶች ያለአግባብ እየጫኑ እየወሰዱት እንደሆነም ገልፀዋል::

አቶ ቴዎድሮስ ዘርጋው የመርሐ ቤቴ ወረዳ ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ፣ "ለፋብሪካ ግብአት የሚሆኑ ሲልካ

ሳንድና ላይምስቶን ማዕድናትን የማልማት ፈቃድ የሚሰጠው ክልል ነው" ብለዋል:: በዚህ የተነሳም ወጣቶች በዘርፉ መደራጀትና ተጠቃሚ መሆን እንዳልቻሉ አስረድተዋል::፡

ማዕድናቱን ቆፍሮ የመጫኑ ሥራም ወጣቶች ተደራጅተው ሊሠሩት ሲገባ ባለሀብቱ ወጣቱን በመቅጠር ያስቆፍራል፤ ያስጭናል:: ወስዶ ለፋብሪካዎች ያስረክባል" ሲሉም ኃላፊው የማዕድን ሀብቱ ለአካባቢው ልማት አለመዋሉን ያስገነዝባሉ::

በወረዳው በርካታ ምሩቃን ሥራ አጥ ወጣቶች እንዳሉ የጠቆሙት ነዋሪው ወጣቶቹን በዚህ ዘርፍ ለመሰማራት ተደራጅተው ወደ ክልል እንደተላኩና "ባለሀብቶች ናቸው የሚያለሙት" መባላቸውን አስታውቀዋል:: "በቅርቡ 'በዚህ ዘርፍ ለመሰማራት ለሚጠይቁ የድጋፍ ደብዳቤ እንዳትጽፉ' ተብለናል:: ማዕድናቱም ታግደዋል" ሲሉም አቶ ቴዎድሮስ አስረድተዋል:: አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በአካባቢው ብርጭቆም ሆነ ስሚንቶ ፋብሪካ ቢገነባ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ስለሚቻል ለዚህ ተግባራዊነት ትኩረት መስጠት አንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል::

አቶ ዘውዱ አሰፋ እንደሚሉት ደግሞ የወረዳ፣ የዞንም ሆነ የክልል ፍላጐት የአካባቢው ወጣቶች በአካባቢያቸው ባለው ፀጋ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ነው:: "ነገር ግን ለነጭ አሸዋና ለኖራ ድንጋይ ባህላዊ የማምረት ፈቃድ አልተሰጠም:: ስለሆነም መመሪያው ተሻሽሎ ለአካባቢው ወጣቶች የሥራ ዕድል መፈጠር አለበት" ሲሉ ያለውን ክፍተትና መፍትሄም አቶ ዘውዱ ጠቁመዋል:: በአካባቢው ፋብሪካ ተተክሎ ወደ ሌላ አካባቢ የሚሄደው ጥሬ ዕቃ በግብአትነት ቢያገለግል የሚኖረው ጠቀሜታ ስለታመነበትም አንድ የብርጭቆና ጠርሙስ እንዲሁም አንድ የሴራሚክስ ፋብሪካ በአካባቢው እንዲገነባ ቦታ በማስረከብ ሂደት ላይ ነን” ሲሉም አቶ ዘውዱ ጠቁመዋል::

አቶ ሰይድ አሊ የአማራ ክልል ማዕድን ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ምክትል ኃላፊም 'ማዕድናት የህብረተሰቡን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ መልማት አለባቸው' የሚለውን ሀሳብ መንግሥትም የሚደግፈውና እየተሠራበት ያለ መርህ አንደሆነ ጠቁመዋል:: የአካባቢው ወጣቶችም ማዕድኑን በጥሬው በማምረቱ ሥራ ተሰማርተው መቆየታቸውን አውስተዋል:: "ባለሀብቶችም ማዕድኑን በጥሬው እያጓጓዙ እንዲሸጡ ፈቅደንላቸው ሲሠሩ ቆይተዋል" ያሉት ኃላፊው ይሄ ግን ጥሩ አማራጭ እንዳልሆነ አስረድተዋል:: "ጥሬ ሀብቱን ከማጓጓዝ ይልቅ በአካባቢው ፋብሪካ ቢቋቋም ማዕድኑን እሴት ጨምሮ በማቅረብ ወጣቶች መሳተፍ ይችላሉ:: እሴት መጨመሩም ሆነ በአካባቢው ፋብሪካ መቋቋሙ ለበርካታ ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል:: ስለሆነም ወጣቶቹም ሆኑ ባለሀብቶች ወደዚህ አሠራር እንዲመጡ ትኩረት ሰጥተን እንሠራለን" ሲሉም አብራርተዋል:: "ጥሬ አምራች፤ ብስል ሸማች ከመሆን ለመውጣት በምናደርገው ጥረት ስኬታማ መሆን እንችል ዘንድም ባለን አቅም በትንሹ መጀመር እንዳለበን ግንዛቤ ተይዟል” ሲሉም አስረድተዋል:: ከዚሁ ጐን ለጐን ለመሠረተ ልማቱ አቅርቦት ትኩረት መሰጠት እንዳለበትም አቶ ሰይድ ገልፀዋል::

መልካም አስተዳደርአቶ ደመረ ኃይሉ በመድረኩ ላይ የውስጥ

ለውስጥ መንገድ ጠጠር ለማልበስ በሚል ያለ ደረሰኝ ገንዘብ እንደሚሰበሰብ በመግለጽ ችግሩ እንዲፈታ ጠይቀው እንደነበር አውስተዋል:: በጥያቄያቸው መሠረትም በአሁኑ ወቅት ገንዘብ በደረሰኝ እየተሰበሰበ እንደሚገኝ ተናግረዋል:: የግብር አጣጣሉም ከመድረኩ ወዲህ መሻሻሉንና ጫናው መቅረቱን ጠቁመዋል::

"ሥራዎች የሚሠሩት ምርጫ ሲመጣ ነው:: ይሄ መስተካከል አለበት፤ ለምርጫ ሲባል ሥራ መሠራት የለበትም " የሚል አስተያየት አቅርበው የነበሩት መሪጌታ ዓይነኩሉ ጥላሁንም ችግሩ መፈታቱን አስታውቀዋል:: ነዋሪው እንዳሉት ባሁኑ ወቅት ሁሉም ሥራዎች በተገቢው መንገድ እየተከናወኑ ነው::

“በእኛ በኩል አስፈላጊው ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል”አቶ ሳምሶን ወንድሙ

“የውኃ አቅርቦቱ አልተሻሻለም”ሲስተር አልማዝ አውግቸው

"የውኃ ስርጭት ፍትሀዊነት ችግርን ለመፍታት ጥረት

ተደርጓል:: በዚህም

ችግሩ ውስጥ ገብተው በነበሩ

ባለሙያዎች ላይ የደመወዝ ቅጣት

ተወስኖባቸው ተግባራዊ ሆኗል::

የፍትሀዊነት ችግሩም ተቃሏል"

አቶ ሳምሶን ወንድሙ በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ከዓለም ከተማ ሙከጡሪ ያለው መንገድ ለሁለት ተቋራጮች ተከፍሎ መስጠቱን ጠቁመዋል በዚህም መሠረት "ከሙከጡሪ እስከ ኮከብ መስክ ያለው መንገድ ወደ አስፋልት ለማደግ የጨረታ ሂደቱ በመከናወን ላይ ነው" ብለዋል:: ከኮከብ መስክ እስከ ዓለም ከተማ ያለውን ደግሞ በ2010 ለመገንባት እየተሠራ እንደሆነ ገልፀዋል::

ከዓለም ከተማ መሐል ሜዳ ያለው መንገድም በሁለት ተቋራጮች ተከፍሎ እንደሚሠራ አቶ ሳምሶን አስታውቀዋል:: "የመንገዱ ግንባታ በዲዛይን ለውጥና በቦታው አመቺ አለመሆን ዘግይቷል" የሚለውን የአቶ አስፋውን ሀሳብም ይጋራሉ::

Page 39: 12 03 2009.pdf

ገጽ 39በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ማስታወቂያ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበደቡብ ጎንደር ዞን የገ/ኢ/ል መምሪያ የእስቴ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ከክልል ባገኘው የበጀት ድጋፍ በእስቴ ወረዳ መ/እየሱስ ከተማ ለሚሰራው G+1 የቢሮ ግንባታ ስራን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡

፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በህንፃ ስራ ተቋራጭ ሆኖ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ናምበር/ያላቸው፣

3. ደረጃ ስምንትና ከዚያ በላይ የሆነና የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፣

4. የግዥው መጠን ብር 50 ሺህ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የሚሰሩ ስራዎችን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1.5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ

ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቴክኒካሉንና ፋይናንሻሉን/ ዋጋውን/ለየብቻ በተለያየ ፖስታ

በማድረግ በእስቴ ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ታህሣስ 3 ቀን

2009 ዓ/ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 2 ታህሣስ 3 ቀን 2009 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው

ባይገኙም የከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. ተጫራቾች የስራ አፈፃፀም ምዘናቸው ከ50 በመቶ በላይ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 447 0888/20 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የእስቴ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበአዊ ብሔ/አስ/ዞን የዳንግላ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈትና የጽዳት እቃዎች ፣የቤትና የቢሮ እቃዎች ፣ ኤሌክትሪክ ሲቲ፣ አውቶ ሞቲቭ

፣ግብርና ፣የኮንስትራክሽን እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ያላቸው፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግዥ መጠኑ ብር 50 ሺህ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የሚገዙ እቃዎች አይነት እና ዝርዝር መረጃ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ /ከ12/03/09 ዓ/ም እስከ 26/03/2009 ዓ/ም/ ድረስ በግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ እና ውል ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና

/በጥሬ ገንዘብ/ በገንዘብ ያዥ አስይዘው የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን አንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው

የጨረታ ሣጥን ቁጥር 1 ዘወትር በስራ ሰዓት ከ12/03/2009 ዓ/ም እስከ 26/03/2009 ዓ/ም እስከ 11፡00 ማስገባት ይኖርበታል፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 04 የማይመለስ ብር 30.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸውን ፣ፊርማቸውን እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ መ/ቤቱ ያወጣውን ጨረታ 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 በቀን በ27/03/2009 ዓ/ም በ3፡00 ይከፈታል፡፡

12. ተጫራቾች ከላይ ከተጠቀሱት ነጥቦች በተጨማሪ በክልሉ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተገዥ ይሆናሉ፡፡

13. አሸናፊው ተጫራች የአሸነፈባቸውን እቃዎች ዳ/ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ በተዘጋጀው መጋዘን ድረስ በራሱ ወጭ ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡

14. በጨረታው መሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 221 10 17 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

የዳንግላ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ

Page 40: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 40

“ባለቤት ያጣው” በሳጥን የታሸገ መድኃኒት

እውነት ለመናገር ሥራቸው ሙሉ በሙሉ ውድቀት ነው ብሎ ለመናገር አያስደፍርም:: ምክንያቱም ባሠራጩት ብዙ ምግብን ተጠቅሞ የፈለጉትን ያህል ዋጋ የመክፈል ዜና መሠረት እንዳሠቡት ብዙ ደንበኞችን ሊስቡ ችለዋል:: ነገር ግን ተጠቃሚዎቹ የሚከፍሉት የምግቡን ዋጋ 10 በመቶ ብቻ ነበር:: እንዲያውም አንዳንዶቹ በድፍረት ገንዘብ ጠረጴዛ ላይ እየጣሉ ይሄዳሉ::

ይሕ ማስታወቂያ በወጣ ልክ በሰባተኛው ቀን ግን ምግብ ቤቱ ለ15 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ኪሣራ ተደርጓል:: እንዲሁም ለዚህ ሁሉ ምክንያት የሆነው “የቻልከውን ክፈል” የሚል ማስታወቂያ እንዲዘጋ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም በደረሰባቸው ኪሳራ ምክንያት ሦስቱ ባለሀብቶች የከፋ ክርክር እና ጭቅጭቅ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል፤ እንዲያውም አንደኛው ባለሀብት ከተማዋን ለቆ ሄዷል::

ነገር ግን ሁኔታው እንደሚያመለክተው የሊው

ምግብ ቤት የምግብ አቅርቦት የዚያን ያክል ጥሩ የሚባል እንዳልሆነ እና በዚህም ምክንያት መክፈል እንዳልቻሉ ነው:: “የቻልከውን ክፈል” የሚል ማስታወቂያ በተዋወቀበት ወቅት ምግብ ቤቱ በተጠቃሚዎች ተሞልቶ ነበር። ማስታወቂያው ሲቆም ግን ተጠቃሚዎቹ እንደጉም ተነው ጠፉ።

“ድርጊቱ የሰዎችን ምግብ ተጠቅሞ ተገቢውን ክፍያ ያለመክፈል ፍላጐት እንዳላቸው ያመለክታል:: ማስታወቂያው ከቆመ በኋላ ሰዎች ለምን ተመልሠው እንዳልመጡ ሊገባኝ አልቻለም” ሲል ሊው የወቀሣ ንግግሩን አቅርቧል::

ከሦስት ዓመት በፊት እንዲሁ በሰዎች ዘንድ እምነት የሌለው እና በመጥፎ ዝናው የሚታወቅ አንድ የቻይና ምግብ ቤት ይኸንን ስልት ይጠቀም ነበር:: ይኸ ምግብ ቤት በወር 15 ሺህ የሚጠጋ ዶላር ኪሣራ ደርሶበታል::

(በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋዜጠኝነትና ተግባቦት ትምህርት ክፍል የ3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ደጀኔ

በቀለ በበኩር ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በተግባር ልምምድ ላይ እያለ ያዘጋጀው)

“ያሻህን ክፈል”...ከገጽ 6 የዞረ

አሁን አዲስ ብስራት ምንም ዓይነት የህመም ስሜት አይሰማውም:: በመሆኑም በ2009 የትምህርት ዘመን በሙሉ ጤንነት፣ በአዲስ ተስፋና ራዕይ ትምህርቱን ለመቀጠል ወስኖ ስምንተኛ ክፍል ተመዘግበ- መማርም ጀምሯል::

ይሁን እንጅ በቅርቡ በሀኪሞች በተቆረጠለት ቀነ ቀጠሮ መሠረት ወደ ሆስፒታል ጎራ ብሎ ሲመረመር ታዳጊው አሁንም ከህመሙ ሙሉ በሙሉ አለማገገሙን የሚያሳዩ የህመም መልክቶች እንዳሉ ሀኪሞች ተረዱ:: ታዳጊው ሙሉ በሙሉ ይድን ዘንድ መድኃኒት ታዘዘለት:: ልክ እንደ በፊቱ ሁሉ መድኃኒቱን በነፃ እንደሚሰጣቸው ተነገራቸው::

በዚህም መሠረት በወልድያ ጠቅላላ ሆስፒታል የነፃ መድሀኒት ቤት ጎራ ብለው ጠየቁ:: “መድኃኒቱ አልቋል” የሚል ምላሽም ከባለሙያዎች ተሰጣቸው:: “መቼ ይመጣል?” የታዳጊ አዲስ ብስራት ወላጆች ጠየቁ:: “ቀኑ ስለማይታወቅ ከግል መድኃኒት ቤት ይግዙ” የሚል ወሽመጥ የሚበጥስ መልስ ተሰጣቸው::

ወላጅም ከልጃቸው የሚበልጥ ባለመኖሩ “እሺ” ብለው ከሆስፒታሉ ወጡ፤ ወደ ግል መድኃኒት ቤቶች ሄደው ሲጠይቁ ግን የአንዱ መድኃኒት ዋጋ 500 ብር መሆኑን ተረዱ:: ለአሁኑ ተበድረው መድኃኒቱን ገዝተው ሰጡ፤ ነገን በተስፋ በመጠበቅ…

በመስከረም ወር 2009 ዓ.ም በቀነ ቀጠሯቸው መሠረት ወደ ሆስፒታል አመሩ:: አሁንም “መድሀኒቱ የለም” ተባሉ:: ገዝተው ለመስጠት ደግሞ አቅማቸው የሚፈቅድ አልሆነም::

ታዳጊ አዲስ ብስራት በወልድያ ጠቅላላ ሆስፒታል የነፃ መድኃኒት ቤት ክፍል በረንዳ “የወገን ያለህ!” ሲል ይማፀናል:: የታዳጊው አካል ዝሏል፤ አፉን ዝንብ ወሮታል:: ዐይኑ ቡዝዝ ብሎ አንደበቱ ተሳስሯል:: እንቅስቃሴው ሁሉ በአባቱ ድጋፍ ሆኗል::

* * *ከኢትዮጵያ የስኳር ህሙማን ማህበር ድረ ገፅ

ባገኘነው መረጃ፤ ማህበሩ ከዓለም የጤና ድርጅት (WHO)ና ከዓለም የስኳር ህሙማን ማህበር ባገኘው ድጋፍ መሠረት በኢትዮጵያ ዕድሜያቸው እስከ 15 ዓመት ለሚሆኑ ታዳጊዎች መድኃኒት በነፃ

እንዲሰጥ አድርጓል:: ከ15 ዓመት በላይ ለሚሆኑ ህሙማን ደግሞ በጣም ቅናሽ በሆነ ሂሣብ እንዲሸጥ ከኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ እየተሰራበት ነው::

በወልድያ ጠቅላላ ሆስፒታል ለስኳር ህሙማን የሚታዘዘው መድኃኒት ለምን ጠፋ?

ሌላው አስተያየት ሰጪ አቶ መላክ ስጦታው ይባላሉ:: በወልድያ ዙሪያ የመካ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ ናቸው::

አቶ መላክ ስጦታው በቲቢ በሽታ በመታመማቸው ጉልበታቸው ርዶ፣ ተስፋቸው ተሟጦ፣… በሬ መፍታታቸውን አጫውተውናል:: የእርሻ መሬታቸው ጦም ማደር በመጀመሩ በቤተሰባቸው ላይ ችግር አስከትሏል:: የማታ ማታም መሬታቸውን አከራይተው ለመጠቀም ወሰኑና አደረጉት:: እናም አሁን የእነ አቶ መላክ ጎተራ “ወና ነው” ከሚባልበት ደረጃ መድረሱን አቶ መላክ አጫወቱን::

በወልድያ ጠቅላላ ሆስፒታል የታዘዘላቸውን መድኃኒት በነፃ እየተቀበሉ በመጠቀማቸው ጤናቸው እየተመለሰ ነው:: በሚሰጣቸው ቀጠሮ መሠረትም ወደ ሆስፒታሉ ጎራ በማለት ይመረመራሉ:: የህመሙ ደረጃም ይገለጽላቸዋል፤ መድኃኒት በነፃ ይሰጣቸዋል:: በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት ወደ ሆስፒታል ሳይመጡ ሲቀሩ በቲቢ ህክምና ክፍል ውስጥ ባስመዘገቡት የስልክ ቁጥር እየተደወለ ይጠየቃሉ፤ ይመክራሉ::

የህክምና ባለሙያዎችን ምክር አድምጠው በመተግበራቸው፣ መድኃኒቱን በአግባቡ በመውሰዳቸው ያለማቋረጥ ያስላቸው የነበረው ደረቅ ሳል ጠፍቷል፤ የገረጣው ፊታቸው ወርዝቷል፤ የከሳው ሰውነታቸው ሞላ ብሏል:: አሁን ምንም ዓይነት ህመም አይሰማቸውም::

አቶ መላክ ያከራዩትን የእርሻ መሬት ራሳቸው በሬ ጠምደው፣ ሞፈርና ቀንበር አዋደው፣ ማረሻ ረግጠው ለማረስ ወስነዋል- በጤናቸው መመለስ ምክንያት::

“ጤናዬ ተመልሷል፤ ሙሉ በሙሉ መዳኔ የሚረጋገጠው ግን በሀኪም ነው:: ይኸው ብስራት በቀጠሮ እየጠበቅሁ ነው” ብለዋል::

ይሁንና በአሥራ አንደኛው ሰዓት ላይ ተስፋቸውን የሚያጨልም መርዶ አጋጥሟቸዋል:: በነፃ የሚያገኙትን መድኃኒት አጡ፤ “ለጊዜው መድኃኒት የለም:: ያለውት አማራጭ ከግል መድኃኒት

ቤት ገዝቶ መጠቀም ነው” ተባሉ:: በተባሉት መሠረት በየመድኃኒት ቤቱ ሲጠይቁ “የመድኃኒቱ ዋጋ 1000 ብር” ተባሉ:: በዚህ ገንዘብ መድኃኒቱን ገዝቶ ለመጠቀም አቅማቸው ሊፈቅድላቸው አልቻለም:: እናም ውሎ አዳራቸው ሁሉ ወልድያ ሆስፒታል መድኃኒት ቤት አቅራቢያ ሆነ:: “ለምን?” ካሉ “ከዛሬ ነገ መድኃኒቱ ይገባል” በሚል ተስፋ:: ይሁንና የቲቢ መድኃኒት የሰማይ ያህል በወልድያ ሆስፒታል ርቆባቸዋል:: ምክንያቱ ምን ይሆን?

የወይዘሮ አሚናት ገረመው ጉዳይም ተመሳሳይ ነው:: “በነፃ ይሰጠኝ የነበረውን መድኃኒት

የወልድያ ጠቅላላ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሠላማዊት አያሌው እንደገለፁት በሆስፒታሉ የመድኃኒት ቤት ሙያተኞች በተደጋጋሚ ከሥራ ገበታቸው ላይ በመቅረታቸው ህሙማን ተጉላልተዋል:: ሆስፒታሉ ሁኔታውን አጣርቶም አስተዳዳራዊ እርምጃ ወስዷል:: እናም በአሁኑ ወቅት ሰዓታቸውን አክብረው በምድብ ቦታቸው ላይ የሚገኙ ምስጉን ሙያተኞች ተመድበዋል:: ስለሆነም በመድኃኒት ቤት አካባቢ የሚሰማው ቅሬታ ተፈትቷል:: የመድኃኒትም ሆነ የባለሙያ እጥረት የለብንም ብለዋል::

* * *እኛ ለሥራ በቆየንባቸው ሁለት ቀናት የዋናው

መድኃኒት ግምጃ ቤት ባለሙያዎች በሥራ ገበታቸው ላይ ማግኘት ባለመቻላችን “ሙሉ ነው” የተባለውን መድኃኒት ቤት ተመልክተን የዓይን ምስክርነታችንን መስጠት አልቻልንም::

የታካሚዎች . . .ከገጽ 23 የዞረ

በማጣቴ አቋርጫለሁ:: በአንድ ወር ውስጥም ህመሙ እየተሰማኝ ነው:: ስለዚህ ነፍሴ በመንግሥት ሆስፒታል እጅ ውስጥ ናት” ሲሉ ተማጽነዋል::

በወልድያ ጠቅላላ ሆስፒታል የቲቢ ህክምና ክፍል ኃላፊ ሲስተር እናት ዓለም መስፍን እንደገለፁት በሆስፒታሉ የስኳርም ሆነ የቲቢ መድኃኒት እጥረት የለም:: የመድኃኒት ግምጃ ቤቱ ሙሉ ነው:: ዋናው ችግር መድኃኒት ቤቶች ምን ያህል መድኃኒት እንዳላቸውና የቱ እያለቀ መሆኑን በየጊዜው አይፈትሹም:: እጥረት ያለበትን ከዋናው መድኃኒት ቤት ጠይቀው ማውጣት ይችላሉና ብለዋል::

እንደ ሲስተር እናት ዓለም ገለፃ አልፎ አልፎ የዋናው መድኃኒት ቤት ሙያተኞች ዘግተው “ለሻይ” በሚል ሲወጡ እጥረቱ ይከሰታል:: ለሻይ ተብሎም ሁለት ሦስት ቀናት ድረስ የሚዘጋበት ሁኔታ አለ:: በዚህም የተነሳ ህሙማን ይጉላላሉ እንጅ እጥረት የለም::

እንጀራ ለሌሎች ሀገራትም ሲስፋፋ ግን ጠፍጣፋ ዳቦ (flat bread) ተብሎ መተርጐም ጀምሯል:: እንጀራ እንጀራ የሚለውን ስያሜ ሲያጣ የኢትዮጵያ ብቸኛ ምግብ መሆኑን የሚያመለክት ስያሜውን ያጣል::

ብቻ በስያሜና በተሰያሜ መካከል ያለው የምንነት ግንኙነት የነገሮችን አመጣጥና አፈጣጠር ለማጤን ቁልፍ ጉዳይ ነው::

ለዚህም ይመስላል የኢትዮጵያን የቆየ ታሪክ ለማጥናት ግዕዝ፣ የጣሊያንን ላቲን፣ የግሪክን የፅርዕ ቋንቋ ማጥናት ግድ የሚለው:: ምክንያቱም ከእያንዳንዱ ስያሜ ጀርባ ባህል አለ:: ታሪክ አለ:: መነሻ ሀሣብ አለ::

ለአብነት “ዴሞክራሲ” የሚለው ቃል ግሪክኛ ነው:: ስለዚህ ዴሞክራሲን ግሪክ እንደጀመረችው እንገምታለን::

በስያሜና በተሰያሜ መካከል ያለው ግንኙነት ለጥናትና ምርምር፣ ነገሮችን ነገ ላይ ሆኖ ለማጥናት አስፈላጊ ሆኖ ሳለ በግምት እንሰይማለን:: እንጠራለን:: ዓባይን ናይል ካለ አንድ ኢትዮጵያዊ ዓባይ ከኢትዮጵያ እንደማይነሳ መሰከረ ማለት ነው:: አሊያም የኢትዮጵያ ቋንቋ አረብኛ ነበር ማለት ነው:: በነገራችን ላይ ቅኝ ገዥዎች የቅኝ ግዛት አሻራቸውን በአፍሪካውያን ላይ ያስቀመጡት በሀውልት አይደለም:: በቋንቋ ነው::

ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው ፒያሳ፣ መርካቶ… የሚባሉ ቦታወችን ስትጠራ ጣሊያን ኢትዮጵያን መውረሯን ትመሰክራለህ:: ምክንያቱም ጣሊያን በቋንቋ ቅኝ እንደገዛች አረጋግጣለችና::

በአጠቃላይ፣ ሀቁ ይህ ቢሆንም፣ በሀገራችን የስም፣ የቦታ፣ የሁኔታ ስያሜዎቻችን ዘፈቀዳዊ ናቸው:: አሊያም “ፈረንጃዊ” ናቸው:: የንግድ ተቋማትን ስያሜ ቃኙ:: ተቋማቱ ብቻ ኢትዮጵያዊ ሆነው ስያሜያቸው ግን ሌላ ነው:: ስያሜ መታወቂያ ነው:: ስያሜ ማንነት ነው። ስለዚህ መታወቂያ አልባ ሰዎች፣ ተቋሞች፣ ቦታወች መታወቂያቸውን ሊይዙ ይገባል:: ያለመታወቂያ ከማን በር ይገባል? ከማንም::

ከገፅ 7 የዞረ

ስደተኛ...

Page 41: 12 03 2009.pdf

ገጽ 41በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.

የቅጥር ማስታወቂያየደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች ባለው ክፍት የስራ መደብ ላይ ከሰራተኞች መካከል አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የስራ መደቡ

መጠሪያ

ደረጃ መ/መ/ቁ ደመወዝ ብዛት የትምህርት ደረጃ እና ለመደቡ አግባብ ያለው የስራ

ልምድ

ተፈላጊ የትምህርት መስክ

1. ሣኒተሪ ሣይንስ

ኘሮፌሽናል

ኘሣ-1/1 8.40/ደታ-714 3145.00 1 የመጀመሪያ ዲግሪ 0 ዓመት የስራ ልምድ በአካባቢ ጤና አጠባበቅ የተመረቁና የሙያ ፈቃድ ያላቸው

2. በጀት ባለሙያ II ኘሣ-5 8.40/ደታ-847 3425.00 1 የመጀመሪያ ዲግሪና 6 ዓመት የስራ ልምድ የማስተርስ

ዲግሪና 4 ዓመት የስራ ልምድ የዶክትሬት ዲግሪና 2 ዓመት

የስራ ልምድ ያለው/ያላት፡፡

የስራ ልምድ፡-

በእቅድና በጀት ፣በበጀት ባለሙያነት፣በማንኛውም ደረጃ

የፋይናንስ ሂሣብ ሰራተኛነት ፣በክፍያና ሂሣብ አስተባባሪነት

የሰራ /የሰራች

ኢኮኖሚክስ ፣ትምህርት እቅድና ሥራ አመራር፣ማኔጅመንት፣አካውንቲንግ፣ስታስቲክስ

3. የመብራትና

ኤሌክትሪክ እቃዎች

ጥገና ሰራተኛ

እጥ-9 8.40/ደታ-979 2008.00 1 5ኛ ክፍል ያጠናቀቀና 13 ዓመት

6ኛ ክፍል ያጠናቀቀና 11 ዓመት

7ኛ ክፍል ያጠናቀቀ 9 ዓመት

8ኛ ክፍል ያጠናቀቀ 7 ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ያላት

ኤሌክትሪክ ሲቲ፣ ቢዩልዲንግ ኤሌክትሪካል ኢንስታሌሽን

4. የውሃ መስመር ጥገና

ሰራተኛ

እጥ-9 8.40/ደታ-980/985 2008.00 1 5ኛ ክፍል ያጠናቀቀና 13 ዓመት

6ኛ ክፍል ያጠናቀቀና 11 ዓመት

7ኛ ክፍል ያጠናቀቀ 9 ዓመት

8ኛ ክፍል ያጠናቀቀ 7 ዓመት የስራ ልምድ

ኘላምፒንግ፣ቧንቧ ስራ ሣኒተሪ ኢንስታሌሽን

5. መረጃ ማሰባሰብና

ማጠናቀር ባለሙያ II

ኘሣ-5 8.40/ደታ-844 3425.00 1 የመጀመሪያ ዲግሪ 6 ዓመት ፣የማስተርስ ዲግሪ 4 ዓመት

ዶክትሬት ዲግሪና 2 ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ያላት

ኢኮኖሚክስ፣ ሂሣብ ፣ስታስቲክስ፣ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ፣ኢንፎርሜሽን ሲስተም ፣ማኔጅመንት

1. እድሜ፡- 18 ዓመት እና በላይ 2. ጾታ፡- አይለይም3. የስራ ቦታ፡- ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ4. የምዝገባ ጊዜ፡- ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት5. ከተወዳዳሪዎች የሚፈለግ፡-

5.1. የትምህርት ማስረጃ እና የስራ ልምድ ኦርጅናል ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር5.2. ሲ ኦ ሲ ለወጣላቸው የትምህርት ዝግጅቶች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡5.3. ለኘሣ-መደብ ውድድር ተመዝጋቢዎች የዲኘሎማ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡5.4. የፈተና ቀን፡ - ወደፊት በማስታወቂያ ይገለፃል፡፡5.5. በፈተና ወቅት ተወዳዳሪዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

6. የምዝገባ ቦታ፡- ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሰው ኃብት ስራ አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ህንፃ ቁጥር 039 ቢሮ ቁጥር 7

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበምዕራብ ጐጃም አስተዳደር ዞን የሜጫ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለሜ/ወ/ውሃ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለውሃ ግንባታ አገልግሎት የሚውል አፍሬዲኘ ፓምኘ ፣በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አንዴ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟሉ ሁሉ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ናምበር/ያላቸው፣2. ተጫራቾች የሞሉት ጥቅል ዋጋ ብር 50 ሺህ እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡

3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

4. የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በሜ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግዥ ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር

4 መግዛት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡

7. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሜ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው የመዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8. በጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነት አይወስድም፡፡

10. አሸናፊዎች ያሸነፏቸውን እቃዎች ሙሉ ወጭ በራሣቸው ሸፍነው ሜ/ወ/ውሃ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡

11. መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ከአሸነፈው እቃ ላይ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡12. ማንኛውም ተጫራች ከዚህ የጨረታ ማስታወቂያ በተጨማሪ በግዥ መመሪያው ተገዥ ይሆናል፡፡

13. ተጫራቾች በዋጋ መሙያው ላይ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡14. እቃው በባለሙያ ተረጋግጦ ገቢ ይሆናል፡፡15. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 330 04 32/01 96 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሜጫ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

ማስታወቂያ

Page 42: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 42

በያዝነው የትምህርት ዘመን የትምህርት ተቋማትን ገፅታ ለመቀየር በመጀመሪያ ያለፈውን ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም ችግር ያለባቸውን ትምህርት ቤቶች መለየትና ችግሮች እንዲፈቱ የማድረግ ሥራዎች መሰራታቸውን የወረዳው የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መኮንን ገንብረው ገልፀውልናል:: በዚህም አዳዲስ የመማሪያ ክፍሎችን ከመገንባት ባለፈ ያሉትንም በተቻለው አቅም ሁሉ የማሻሻልና የመጠገን ሥራዎች መሰራታቸውንም ኃላፊው ጠቁመዋል::

ጥቁር ሰሌዳ፣ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበሮችን እና ሌሎችንም ለመማር ማስተማሩ ሂደት አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን በትምህርት ቤቶቹ አቅምም ሆነ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ማሟላታቸውን የገለፁት ኃላፊው የመፅሀፍት ዕጥረቱን ለመሙላትም ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት መጽሐፍት ቀርባላቸው በማከፋፈል ላይ እንደሆኑም ጠቁመዋል::

አቶ መኮንን አክለውም በአጅባር አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የነበረውን የቆየ ችግር ለመፍታት አመራሮችን ገምግሞ በአዳዲስ አመራሮች እንደተኩ ማድረጋቸውን አቶ መኮነን ገልፀዋል:: ከመፅሀፍ አያያዝ ጋር ተያይዞ የተነሳውን ችግር አዳዲሶቹ መሪዎች ወደ ፊት እንዲያስተካክሉ መነጋገራቸውን የገለፁት አቶ መኮንን አሁን ያለውን ክፍተት ለመሙላት ግን በቂ መፅሀፍ እንደተመደበላቸው ጠቁመዋል::

የትምህርት ቤቱ ግቢ ደረጃውን ያልጠበቀ ከመሆኑም በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች እና ተጨማሪ ክፍሎች ለመገንባትም ቦታ እንደሌለው አቶ መኮንን አረጋግጠውልናል::

ችግሩን ለመፍታትም ከመሪ መዘጋጃው ጋር በመነጋገር ከጐኑ ያለው ክፍት ቦታ ወደ ትምህርት ቤቱ የሚገባበት ሁኔታ ተመቻችቶ መሪ ኘላኑ ላይ አስተያየት እንደተሰጠበት ኃላፊው ተናግረዋል:: የቦታው ጥያቄ መልስ ማግኘት ለስፖርት ማዘውተሪያም ሆነ ተጨማሪ ክፍሎችን ለመገንባት እንደሚያስችል አቶ መኮነን ገልፀውልናል::

ከገፅ 20 የዞረ

ደረጃውን የጠበቀ...

በክረምቱ በነበረው አለመረጋጋት ወደ ደሴ ሄደው ሲሠሩ መቆየታቸውን ያስታወሱት አቶ አስማረ በግርግሩ ወቅት በተቆፈሯቸው የምሰሶ መትከያ ጉድጓዶች ድንጋይና አፈር መከተቱ አሁን ፍጥነታቸውን እንደቀነሰባቸው ጠቁመዋል:: ያም ሆኖ ግን ሥራውን በተያዘው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ እየሠሩ መሆኑን ጠቁመዋል::

የስምንት ትልልቅ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኔትወርክ ማስፋፊያና ማጠናከሪያ ፕሮጀክት በዓለም ባንክ ድጋፍ መካሄድ የጀመረው በምዕራፍ አንድ በአዲስ አበባ ሲሆን ከአማራ ክልል ባሕር ዳርና ደሴ በሁለተኛው ዙር ተጠቃሚዎች ናቸው:: በምዕራፍ ሦስትም የጎንደርና ደብረ ማርቆስ ከተሞች ዕድሉን ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል::

ከገፅ 18 የዞረ

ባሕር ዳር... ፕሮጀክቱ ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት ሰፊ

የሆነ የዳሰሳና የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናቶችም መካሄዳቸውን አቶ ግርማ ተናግረዋል:: በጥናቱ አዲሱ ፕሮጀክት የባሕር ዳር ከተማን የመብራት መቆራረጥና የኃይል አቅርቦት ችግር ለቀጣዮቹ 10 ዓመታት ያለእንከን እንደሚያስቀር መረጋገጡንም ነግረውናል::

በተፅዕኖ ግምገማ ጥናቱ መስመሮቹን ለማደስና እንደ አዲስ ለመዘርጋት ነባሮቹን መስመሮች ኃይል ማቋረጥ ማስፈለጉ፣ መንገዶች በጊዜያዊነት ሊዘጉ የሚችሉበት ዕድል መኖሩ፣ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ መስመሮቹ በሰዎች የግል ይዞታ ላይ በአየር ላይ ሊያልፉ እንደሚችሉና እንደ ስልክና ውኃ ያሉ መስመሮች ላይም ድንገተኛ የአገልግሎት መቋረጥ ሊያጋጥም እንደሚችል መለዬቱን ጠቁመዋል:: ለዚህም ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ የጥገና ቡድን ተቋቁሞ ወደ ሥራ መገባቱን ነው አቶ ግርማ ያስረዱት::

የከተማዋ ማስተር ፕላን ሲዘጋጅ ለመብራት፣ ስልክና ውኃ መሠረተ ልማቶች ከመንገድ ውጭ የተፈቀደው አንድ ሜትር ተኩል ብቻ ስፋት ያለው ነው፤ ይህም ከዚህ ቀደም በዘፈቀደ ጥቅም ላይ በመዋሉ ሥራውን ለማጓተት ምክንያት እየሆነ እንደሚገኝም አቶ ግርማ ተናግረዋል::

ግንባታውን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የገለፁት አቶ ግርማ ባለፈው ሐምሌና ነሐሴ ወር በባሕር ዳር ከተማ የነበረው አለመረጋጋት ያስከተለው ተፅዕኖ ግንባታውን ለማጓተት ምክንያት እንደሆነ አንስተዋል፤ “አሁን ላይ በየአካባቢው ተጋድመው የሚታዩት የኮንክሪት ምሰሶዎች በክረምቱ ለመትከል የተዘጋጁ ነበሩ፤ ነገር ግን የነበረው ሁኔታ የሚያሠራ ባለመሆኑ እስከ ጥቅምት ወር አጋማሽ ሥራው ቆሞ ቆይቷል፤ አሁን ሁኔታዎች ስለተረጋጉ ወደ ሀገራቸው ሄደው የነበሩ የውጭ ዜጎችም ስለተመለሱ ወደ ሥራ ገብተናል” ብለዋል አቶ ግርማ::

ከኃይል አቅርቦት አንጻር በባሕር ዳር ከተማ ችግር እንደሌለ ያስረዱት አቶ ግርማ “ነባሩ መስመር በማርጀቱና የስርጭት መረቡ (ኔትወርኩ) ብቁ ባለመሆኑ በተፈጠረ ችግር ኃይል ማዳረስ አልተቻለም::ይሁን እንጅ ከንዑስ ማሰራጫው/ሰብስቴሽን/ ያለው ኃይል አንድ አስረኛውም ጥቅም ላይ አልዋለም” ብለዋል:: መስመሮቹን ለማዘመን በሚደረገው ጥረትም ሁሉም ምሰሶዎችና መስመሮች የመብረቅ መከላከያ ይኖራቸዋል ብለዋል::

ዓለም አቀፍ ጨረታውን አሸንፎ ወደ ግንባታ የገባው የቻይና መንግሥት የልማት ድርጅት የሆነውና በእንግሊዝኛ ምሕጻረ ቃሉ ሲ ኢ

ኃላፊው አስታውቀዋል:: በስምንት ትልልቅ ከተሞች የኤሌክትሪክ መረብ(ኔትወርክ) ማስፋፊያና ማጠናከሪያ ፕሮጀክትም ድርጅቱ ከባሕር ዳር በተጨማሪ የደሴንና ሌሎችም ከአማራ ክልል ውጭ ያሉ ስድስት ከተሞችን መብራት መስመር እየሠራ ይገኛል::

በድርጅቱ ተቀጥረው እየሠሩ ያገኘናቸው ቀያሽና ተቆጣጣሪ (ሰርቬየር ኤንድ ፎርማን) አቶ አስማረ እያዩ እንደተናገሩት ደግሞ ሥራውን በሚፈለገው ጥራትና ፍጥነት እያካሄዱ ነው:: በቅርቡ ወደ ሥራ ከገቡ በኋላ ባሉት 10 ቀናት ብቻ ከ150 በላይ የኮንክሪት ምሰሶዎችን መትከል መቻላቸውንም ለፍጥነቱ እንደማሳያ ጠቅሰዋል፤ “በቀን ከ15 እስከ 18 ምሰሶዎችን እየተከልን ነው” ሲሉም አክለዋል::

የአነስተኛ ኃይል ተሸካሚ የኮንክሪት ምሰሶዎች በመተከል ላይ ሕዳር - 11 ክፍለ ከተማ

ቲ በመባል የሚታወቀው ድርጅት የባሕር ዳር ፕሮጀክት ኃላፊ በበኩላቸው በከተማዋ የነበረው አለመረጋጋት እስኪስተካከል ድረስ ሠራተኞቻቸውን ወደ ሌሎች አካባቢዎች አዛውረው መቆየታቸውን ገልፀዋል፤በአሁኑ ጊዜ ግን ወደ ባሕር ዳር በመመለሳቸው በተሻለ ፍጥነት የባከነውን ጊዜ ለማካካስ እንደሚሠሩ ተናግረዋል::

ሲ ኢ ቲ በኢትዮጵያ ከዴዴሳ አዲስ አበባ ድረስ አዲስ የተዘረጋውን የሕዳሴ ግድብ የኃይል ማስተላለፊ መስመር የሠራ፣ ከጊቤ ሦስት ወደ ኬንያ እየተዘረጋ ያለውን የኃይል ማስተላለፊያ መስመርም ግንባታ እያካሄደ የሚገኝ በመሆኑ ልምዱን ተጠቅሞ ግንበታውን በፍጥነት እንደሚያከናውን

አንድ ዓሳ አጥማጅ ከቤቱ ወጥቶ መረቡን በያዘ ቁጥር ሲባንን መዋሉ የታወቀ ነው:: ነገር ግን አንድ ዓሳ ሳያጠምድ መረቡን ጠቅልሎ ሲመለስ ተመልክቻለሁ:: ሳትታዘቡት አልፋችሁት ይሆን?

በጣና ሐይቅ ዳርቻ ልክ እንደ ሀዋሳ ሐይቅ የዓሳ መሸጫ ቤቶች እንዲስፋፉ የተለየ ጥረት ቢደረግ መልካም ነው:: በተለይ የክልሉ መንግሥት የዓሳ ምርት እንዲስፋፋ የተለየ ጥበቃ ለሐይቁ ማድረግ አለበት:: ምክንያቱም በሀዋሳ ከተማ ወደ ሐይቁ ምንም ዓይነት ፍሳሽ እንዲገባ አይፈቀድም:: በዚህም የዓሳ ምርት በመሻሻሉ በማንኛውም ጊዜና ሰዓት

“የላጭን . . .”ከገጽ 7 የዞረ

በሐይቁ ዳርቻ ባለው የእግረኛ መንገድ የዓሳ ቤቶች ለመበራከት አስችሏቸዋል::

ስለዚህ ወደ ጣና ሐይቅ ምንም ዓይነት ፍሳሽ እንዳይገባ መቆጣጠር ከቻልን የምንናፍቃቸውን ቀረሶ፣ ነጭ ዓሳ፣ ቢዞና አንባዛ ዓሳዎች የእግረኛ መንገድ ላይ “ብሉልን” “ብሉልን” የሚሉ ቤቶችን እንፈጥራለን:: ካልሆነ ግን ነገርየው “የላጭን ልጅ . . .” እንደሚባለው ተረት መሆኑ አይቀርም

(በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋዜጠኝነትና ተግባቦት ትምህርት ክፍል የ3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ደረሰ

አማረ በበኩር ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በተግባር ልምምድ ላይ እያለ ያዘጋጀው)

Page 43: 12 03 2009.pdf

ገጽ 43በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. ማስታወቂያ

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዶናበር እና ጣና ቅርንጫፍ ተበዳሪዎች ለጋራ መኖሪያ እና የድርጅት ቤት/ኮንዶምኒየም/መግዣ የወሰዱትን የብድር ገንዘብ በውሉ መሰረት ባለመክፈላቸው ለብድሩ አመላለስ ዋስትና

ይሆን ዘንድ በመያዣነት የሰጡትን /ኮንዶሚኒየም/ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና 216/1992 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

ተ

.ቁ

የተበዳሪው ስም የሚሸጠው ቤት የ ይ ዞ ታ

ማረጋገጫ /

ካርታ/ቁጥር

ቤቱ የሚገኝበት ህ ን ፃ

ቁጥር

የ ቤ ት

ቁጥር

የጨረታ መነሻ

ዋጋ

ሐራጅ የሚካሄድበትአይነት አገልግሎት ከተማ ሣይት ቀን ሰዓት ቦታ

1. የሱፍ ጌጤ ሐሰን ለንግድ 29727/04 ባ/ዳር ቄራ K/5 005 448,198.64 13/4/09 7፡00-9፡00 ቤቱ በሚገኝበት

2. መልካሙ ተስፋው ታደሰ ባለ 2 መኝታ ለመኖሪያ 29712/04 ባ/ዳር ቄራ K/1 002 179,252.54 13/4/09 9፡30-11፡30 ቤቱ በሚገኝበት

3. ትዕግስት ቀራለም ገላው ባለ 2 መኝታ ለመኖሪያ 29846/04 ባ/ዳር መሰናዶ P31 201 183,840.18 14/04/09 3፡00-5፡00 ቤቱ የሚገኝበት

4. መርሻ ጌትነት አለምነህ ባለ 3 መኝታ ለመኖሪያ 29748/04 ባ/ዳር መሰናዶ P31 305 171,041.53 14/04/09 7፡00-9፡00 ቤቱ በሚገኝበት

5. ታምሩ ሽቴ ጌቴ ስቱዲዮ ለመኖሪያ 29858/04 ባ/ዳር መሰናዶ P30 202 217,948.87 14/04/09 9፡00-11፡30 ቤቱ በሚገኝበት

6. ክንፈ ተስፋሁን መብአድዬን

ባለ 2 መኝታ ለመኖሪያ 29893/04 ባ/ዳር መሰናዶ P32 205 152,367.30 15/04/09 3፡00-5፡00 ቤቱ በሚገኝበት

7. አይናዲስ አለማየሁ ወርቁ ባለ 2 መኝታ ለመኖሪያ 29406/04 ባ/ዳር መሰናዶ P10 305 181,267.53 17/04/09 3፡00-5፡00 ቤቱ በሚገኝበት

8. ላንችስል አዳነ አለባቸው ባለ 1 መኝታ ለመኖሪያ 29455/04 ባ/ዳር መሰናዶ P33 104 148,753.33 17/04/09 9፡30-11፡30 ቤቱ በሚገኝበት

9. ማስረሻው ሲደልል ዶሰኛው

ባለ 2 መኝታ ለመኖሪያ 29439/04 ባ/ዳር መሰናዶ P28 301 172,614.90 17/04/09 7፡00-9፡00 ቤቱ በሚገኝበት

10. ታመነች ታሪኩ አካሉ ባለ 2 መኝታ ለመኖሪያ 29480/04 ባ/ዳር መሰናዶ P5 308 186,179.96 18/04/09 3፡00-5፡00 ቤቱ በሚገኝበት

11. ኤፍሬም ገበዜ በሪሁን ባለ 2 መኝታ ለመኖሪያ 29492/04 ባ/ዳር መሰናዶ P16 202 202,480.86 18/04/09 7፡00-9፡00 ቤቱ በሚገኝበት

12. ዘይንያ ዳውድ ሑሴን ባለ 3 መኝታ ለመኖሪያ 29605/04 ባ/ዳር መሰናዶ P19 302 210,675.43 18/04/09 9፡30-11፡30 ቤቱ በሚገኝበት

13. መለሰ አባት ዘሪሁን ባለ 2 መኝታ ለመኖሪያ 29485/04 ባ/ዳር መሰናዶ P33 206 190,480.62 19/04/09 3፡00-5፡00 ቤቱ በየሚገኝበት

14. አማረ ውቤ ተበጀ ባለ 2 መኝታ ለመኖሪያ 29321/04 ባ/ዳር መሰናዶ P2 107 194,160.30 19/04/09 7፡00-9፡00 ቤቱ በሚገኝበት

15. ገብያው አግደው በዛብህ ባለ 2 መኝታ ለመኖሪያ 29341/04 ባ/ዳር መሰናዶ P3 301 179,127.43 19/04/09 9፡30-11፡30 ቤቱ በሚገኝበት

ማሣሰቢያ፡- 1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል የሐራጁን መነሻ ¼ በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በማስያዝ ወይም በጥሬ ገንዘብ ይዞ በመቅረብ መጫረት ይችላል፡፡

2. የቤቱን ሁኔታ ቤቱ ከሚገኝበት ቦታ ድረስ በመገኘት ወይም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ዲስትሪክት ብድር ማገገሚያ ክፍል ወይም ከተራ ቁጥር 1-6 ጣና እና ከ7-15 ዶናበር ቅርንጫፎች ወይም በስልክ

ቁጥር 058 320 55 26 መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

3. ጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ካልከፈለ ለሐራጁ መነሻ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡

4. በንብረቱ ላይ ከመንግስት የሚፈለጉ የስም ማዛወሪያና ሌሎች ወጭዎችን የጨረታ አሸናፊ ይከፍላል፡፡

5. ባንኩ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ዲስትሪክት

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያየፍርድ ባለመብት ዘቢብ ሆቴል እቁብ ማህበር ያስፈረዱበትን ገንዘብ የፍርድ ባለዕዳ የ3ኛ ብርሃኑ ፈንታሁን ስላልከፈሉ የፍርድ ባለዕዳን ንብረት የሆነውን በእንጅባራ ከተማ 02 ቀበሌ የሚገኝ በምስራቅ አቶ

አላምነህ አስፋው፣ በምዕራብ አቶ ሰዋገኝ ወንድም ፣በሰሜን የቄስ አሣየ ቢተውና ብርሃኑ ፈንታሁን በደቡብ መንገድ የሚያዋስነውን መኖሪያ ቤት በግምት መነሻ ዋጋ ብር 410553.90/አራት መቶ አስር ሺህ

አምስት መቶ ሃምሣ ሶስት ብር ከ90/100 ሣንቲም/ህዳር 25 ቀን 2009 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 በመጀመሪያ ደረጃ ጨረታ ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልግ ሁሉ በቦታው ተገኝቶ መጫረት የሚችል

መሆኑን ፍ/ቤቱ ያሣውቃል፡፡

የአዊ ብሔ/አስ/ከፍ/ፍ/ቤት

የጨረታ ማስታወቂያየፍርድ ባለመብት ዘመኑ ደምለው የፍርድ ባለዕዳ አብርሃም ከበደ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የፍርድ ባለዕዳው ንብረት የሆነች ኮድ 3-04355 አ/ማ ፒክአኘ መኪና በመነሻ ዋጋ 133,900.

87/አንድ መቶ ሰላሣ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር ከ87/100 ሣንቲም/ ሆኖ በግንቦት 20 ክ/ከተማ 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ህዳር 24 ቀን 2009 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ ጨረታ

ትሸጣለች፡፡

ስለዚህ ማንኛውም መኪናዋን ለመጫረት የሚፈልግ ተጫራች ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ እንዲሁም ሰዓት በመገኘት መጫረት የሚችል መሆኑን እየገለፅን የጨረታ አሸናፊ የሆነው ሁሉ የአሸነፈበትን ገንዘብ

¼ ኛውን ወዲያውኑ በባ/ዳር እና አካባቢዋ ከፍ/ፍ/ቤት በኩል በሞ/85 የሚያስይዙ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የባህር ዳር እና አካባቢዋ ከፍ/ፍ/ቤት

Page 44: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 44

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የፍኖተሰላም መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አቅርቦቶችን ማለትም ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ፣ ሎት 2 ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች ሎት 3 የህንፃ መሣሪያዎች ሎት 4 የሙዚቃ

እቃዎች ሎት 5 የስፖርት እቃዎች ሎት 6 የመኪና ጎማና የመኪና እቃዎች ሎት 7 የጽዳት እቃዎች ሎት 8 የደንብ ልብስ ሎት 9 ቁሣቁስና ተገጣጣሚዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ

በዚህ ጨረታ መሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይገባቸዋል፡፡

1. በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ፈቃዱ የታደሰ መሆን አለባቸው፡፡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ናምበር ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

3. የግዥው መጠን ከ50ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. የጨረታ ሰነዱ መሸጫ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 30.00 ሲሆን በኮሌጁ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የሚገዙ እቃዎችን ዝርዝርና መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በፍ/ሰላም መም/ት/ኮሌጅ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡

7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ 2 ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የፍ/ሰላም መም/ትም/ኮሌጅ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት

ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፍ/ሰላም መም/ትም/ኮሌጅ የግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በ3፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት

በ4፡00 ይከፈታል፡፡ እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በራሣቸው ምክንያት ባይገኙም

የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፡፡

9. ተጫራቾች ሞልተው በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ የባለቤቶች ወይም የህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊርማና ማህተም ያለበት መሆን አለበት፡፡

10. ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው የሚያሸንፉባቸውን እቃዎች በራሣቸው ሙሉ ወጭ ፍ/ሰላም መም/ትም/ኮሌጅ ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ ገቢ ያደርጋሉ፡፡ እንዲሁም መ/ቤቱ 20 በመቶ መጨመር

ወይም መቀነስ ይችላል፡፡

11. በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

12. በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

13. አሸናፊ የሚመረጠው ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ በተያያዘው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መግለጫና በሚቀርበው ዝቅተኛ ዋጋ ሆኖ መ/ቤቱን በሚጠቅም በጥቅል /በነጠላ ዋጋ መሰረት ይሆናል፡፡

14. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

15. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ፍ/ሰላም መም/ትም/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 12 70/058 775 02 54 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የፍኖተሰላም መም/ትም/ኮሌጅ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃ መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ በመደበኛና በተለያየ በጀት ሎት 1 የሰራተኛ ደንብ ልብስ /ሸሚዝ/ የሴትና የወንድ ፣ካፖርት ፣የወንድና የሴት ጫማ ሎት 2 የቢሮ መገልገያ

እቃዎች /ፈርኒቸር/ ሎት 3 የመኪና ጐማ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያላቸው እና የግዥው መጠን ከብር 50 ሺህ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ከፋይነት

የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያያዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30.00 በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃ መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ ቁጥር 84 ማግኘት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ 1 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡

7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በውሃ መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 88 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ

ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርበታል፡፡

8. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በመሙላት እስከ 16ኛው ቀን 8፡00 ከመድረሱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00

ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 88 በ9፡00 ላይ ይከፈታል፡፡

10. የጨረታ መዝጊያ ቀን /16ኛው ቀን/ በዓል ከሆነ በተመሣሣይ ሰዓት በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡

11. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው የጨረታ ሰነድ /ቅጽ/ብቻ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡

12. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

13. ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 222 01 32/058 220 10 78 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአብክመ የውሃ መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ

ማስታወቂያ

Page 45: 12 03 2009.pdf

ገጽ 45በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. ሰዎች ምን ይላሉ?

ደረጀ አምባው

በህዳር ብቻ ቆሻሻን ማቃጠል?

አቶ ቻሌ ደምልሥራ ፈላጊ - ባህርዳር

ከተማ

በህዳር ቆሻሻን ማቃጠል ብቻ እንደሌለብን አምናለሁ:: ሁልጊዜም ዓመት ሳንጠብቅ ቆሻሻን በየጊዜው ማስወገድ ይገባናል:: ሁሉም በአንድ ቀን በሚያቃጥልበት ጊዜ የአካባቢን አየር መበከልም ስላለ ወሩን በሙሉ ቆሻሻ ሳይበዛ በጥቂት በጥቂቱ ማቃጠልና ማስወገድን ልንለምድ ይገባል::

ወ/ሮ ዓይናለም ደሴአትክልተኛ - ባህርዳር ከተማ

ቆሻሻ ምንጊዜም ለጥቅም ማዋል እስካልተቻለ ድረስ ማቃጠሉ መፍትሔ ነው:: በግቢ ውስጥ ቆሻሻ እንዳይኖር በየዕለቱ መጠንቀቅ አለብን:: ይህን የሚያግዘን ደግሞ ግቢያችንን በአትክልት ስናስውብ ነው:: ግቢያችን አንዴ ካማረ እንዳይቆሽሽ ለመንከባከብ ያመቸናል:: ትንሽም ቢሆን ቆሻሻ ሲኖር በቀላሉ መመልከት እና ማስወገድ ያስችለናል:: ስለሆነም ይህን መንገድ በመጠቀም ግቢንና አካባቢን ከቆሻሻ ነፃ ማድረጉ ይሻላል:: በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ማቃጠሉ ግን ዘላቂ መፍትሔ አይሆንም:: አቶ ክንዴ ሰንደቅ

በግል ሥራ የሚተዳደሩ - ባህርዳር ከተማ

ህዳር ሲታጠን ማለት ከመስከረም ጀምሮ የሚከሰተው የወባ እና የጉንፋን በሽታን ለማስወገድ እንደ ሁነኛ መፍትሔ አባቶቻችን ሲጠቀሙበት የነበረ የቆሻሻ ማቃጠል ስነ ስርዓት ነው:: ከሕዳር አጋማሽ በኋላ የወባ እና ጉንፋን በሽታዎች ማጠናቀቂያ ናቸው ተብሎ ይታመናል:: ባህሉ ጥሩ ነው:: ነገር ግን በየጊዜው ቆሻሻን ማስወገዱ የሚመከር ነው:: የግድ አንድ ዓመት መጠበቅ አይገባም:: ቆሻሻን በየጊዜው ማስወገድ በከተሞች የሚፈፀም ቢሆንም ገጠር አካባቢ ግን ይህን ባህል በማስወገድ ልክ ከተማ አካባቢ እንደሚደረገው የቤትንና የአካባቢን ንጽህና በየዕለቱ መጠበቅ ይገባል::

ወ/ት ፋሲካ ብርሃኑ የግል ሠራተኛ - ባህርዳር ከተማ

በህዳር ወር ቆሻሻን ማቃጠል በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የተለመደ ነው:: አሁን አሁን የገጠሩን ባህል ወደ ከተማውም በማምጣት በህዳር ወር ቆሻሻን ከየስርቻው ፈልገው የሚያቃጥሉ አያለሁ:: ይህን የሚያደርጉት ጉንፋን እንዲለቀን ነው ሲሉም እሰማለሁ::

አሁን ግን ዘመኑ ተቀይሯል:: የአኗኗራችን ዘይቤም በከተፍተኛ ደረጃ ተቀያይሯል:: በጥንት ጊዜ ብዙም ቆሻሻ ያልነበረው የህዝብ ብዛት አለመኖሩም ጭምር ይመስለኛል:: በአሁኑ ወቅት ግን ከህዝብ ብዛትና ከተረፈ ምርት ጋር ተያይዞ ከእያንዳንዱ ቤት በርካታ ቆሻሻ በየቀኑ ይከማቻል:: ስለዚህ ይህን ቆሻሻ ለማስወገድ እንደጥንቱ ዓመት እንጠብቅ ብንል በቆሻሻ ክምር እንጠፋለን:: ስለዚህ በየቀኑ አካባቢን ማፅዳት ጥያቄ የማያስፈልገው ሥራ ሆኗል:: ስለሆነም እንደ አጠቃቀማችን ቆሻሻን ጊዜ ሳንሰጥ ወዲያው ወዲያው ልናስወግድ ይገባል::

ወ/ሮ ገነት ወርቅነህየግል ሠራተኛ - ባህርዳር

ከተማ

በርካታ ሰዎች በህዳር ወር ቆሻሻን ሲያቃጥሉ እመለከታለሁ:: ይህን ስመለከት ለምን ሁልጊዜም የአካባቢያችንን ፅዳት እንደዚህ አንጠብቅም በሚል አስባለሁ:: ፅዳት አይደለም በዓመት ከወርም አልፈን በየቀኑ መከናወን ያለበት ትልቅ ቁም ነገር ነው:: ስለዚህ ህዳርን ብቻ ጠብቀን ማከናወን የለብንም:: በየዕለቱ ፅዱና ውብ የመኖሪያ አካባቢ ሊኖረን ይገባል::

Page 46: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 46

(i). The Terminated/Construction INVITATION TO BID

To All contractors of category GC-8,BC-7 and above with license valid for the year 2009 E.C who can present Trade licenses and Tax clearance certificates for the construction of the following site at the following Zones and Weredas of AmharaRegion.

SN Name of Project Zone WeredaC o m p l e t i n g Time (days)

1 Aseketema terminated Operation Room Wag-Himra Gazegabla 2501. Amhara National Regional State Health Bureau has planned to undertake the termination of health centers at sites listed above and has invited properly sealed bids from eli-

gible Bidders for Providing necessary labor, material & equipment for construction and completion of the works;2. Bid documents may be obtained by any interested eligible bidders on the submission of a written application to Amhara National

Regional State Bureau of Health P.O.Box 495 Tele: 058-226-66-63/058-2206150 Fax: 058-222-1626 and uponpayment of non-refundable Birr 250 (Two Hundred Fifty Birr) to whom all inquires and correspondences should be addressed;

3. Each bid must be accompanied by an acceptable bid bond CPO or Bank Guarantee in the sum equal to 2% of the bid amount including VAT, and must clearly state the bidding hospital and employer, which shall remain in forces for 90 calendar days from the bid opening date and shall be in separate envelope.

4. The successful bidder will be required to furnish a Bank Guarantee of 30% for advance payment and performance bond of 10% of the gross bid sum within 15 days from signature;

5. Bidders are advised that they must read and comply in full with the “ INSTRUCTION TO BIDDERS”;6. Of works shall be completed within a maximum of indicated Calendar Days above;7. All bid documents shall be in separate envelopes & properly sealed (one original & one copy);

8. All Bids will be evaluated based on financial least bidder; 9. Sealed bid documents shall be submitted to the ANRS Bureau of Health, Procurement and Finance Supporting Work Process on

or before 21 Calendar days from the first advertisement at 2:00 P.M and shall be publicly opened at 1st Calendar day starting from first advertisement date at 3:00 P.M. If the opening date lies on a non working day it will be shifted to the next working day in ANRS Bureau of Health where the name of bidders and the amount of their bids will be declared. Bidders are advised to attend the opening of bids;

10. Bidders may obtain further information from The Amhara National Regional State Health Bureau P.O.Box 495, Tele:058-226-66-63/058-220-61-50 and Fax: 058-222-16-26

11. A Bidder, who has less than 75 % progress achievement from expected progress (on January 2016 report) or has a reported qual-ity problem in any previous contractual performance with Amhara Bureau of Health cannot participate in this bid;

12. A Bidder, with in contract time who has less than 75 % progress achievement from expected progress (on september 2009E.C report) or any bidder who is out of contract time and do not complete the project or who has a reported quality problem in any previous contractual performance with Amhara Bureau of Health cannot participate in this bid;

13. Amhara National Regional State Bureau of Health reserves the right to reject any or all bids without giving reasons therefore and

to waive informalities and irregularities, which do not constitute a material Modification in the bids received.ANRS HEALTH BUREAU

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ የብቸና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል Bc/Gc 9 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮችን የካርድ ክፍል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው/ላት፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቀጥር/ቲን/ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣

2. ማንኛውም ተቋራጭ Gc/Bc- 9 እና በላይ የሆኑ የግንባታ የምስክር ወረቀት ከመሰረተ ልማት ሚኒስቴር/ከክልል የስራና ከተማ ልማት ቢሮ ማቅረብ የሚችልና ለGc/Bc 9 የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን ፤

ማቴሪያሎችንና የሰው ሃይል ችሎ ገንብቶ የሚያስረክብ ፤የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ እና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የሚችል ሆኖ ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ

በተከታታይ 90 ቀናት ውስጥ ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡

3. ዝርዝር መግለጫ/እስፔስፊኬሽን/ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢን ቦንድ/ለሚወዳደሩበት ብር ወይም ለዕቃው ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/በጥሬ ገንዘብ /ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ላይ የድርጅታቸውን አድራሻ በመግለጽና በፖስታ በማሸግ የድርጅታቸውን ማህተም እና ፊርማ በማሳረፍ ቢቸና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥና ፋ/ን/አስ/ደ/

የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ጨረታው በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ጨረታው በ22ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡የመጨረሻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች

/ወኪሎቻቸው/ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ ጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሣኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡

7. ተጫራቾች የሚሸጡበትን የአንዱ ዋጋ በዝርዝሩ መሠረት ግልፅ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

8. የጨረታው መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሣቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30.00/ሰላሳ/ በመክፈል መግዛት የሚቻል ሲሆን አጠቃላይ ቢልኦፍ ኳንቲቲ እና የአሰራር ዲዛይን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡ ለጨረታው ዝርዝር መረጃ

ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-665-0483 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡

10. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ አጠቃላይ ከተወዳደሩበት ዋጋ ላይ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የብቸና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

ማስታወቂያ

Page 47: 12 03 2009.pdf

ገጽ 47በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.

ባቲ እንደ ቅኝቱ...ከገጽ 48 የዞረ

ዋይኒ ሩኒ ለህፃን ካስቢያን ፊርማውን አስቀምጦ የላከለት መለያ፤

ምክንያቱ ደግሞ ቡድኑ ተሽከርካሪ ስለሌለውና ከበጀት አንፃር ቀደም ብለው እንዳይሄዱ ስለሚደረግ ነው:: በመሆኑም በመጀመሪያው አጋማሽ የውድድር ወቅት መሰብሰብ የቻለው ሁለት ነጥቦችን ብቻ ነበር:: ያ ወቅትም ቡድኑ ተስፋ የቆረጠበት እንደነበር ነው አሰልጣኙ የሚያስታውሰው::

ይሁን እንጂ የቡድኑ አባላት ባደረጉት ውይይትና በፈጠሩት አዲስ የአሸናፊነት መንፈስ በደጋፊው እየታገዙ የተነሱበትን አላማ ማሳካት ችለዋል:: በሁለተኛው አጋማሽ የውድድር ወቅትም ምንም አይነት ሽንፈት ሳያስተናግዱ አስር ነጥቦችን መሰብሰብ ችለዋል:: በአጠቃላይ ውጤትም በአስራ ሁለት ነጥቦች በምድቡ ከተደለደሉት አምስት ቡድኖች ቀዳሚ ሆኖ የውድድር ዘመኑን በስኬት አጠናቋል:: የበጀት እጥረት ቢከሰት እንኳ የቡድኑ አባላት ከኪሳቸው በማዋጣት ውጤታማ ጉዞ ማካሄዳቸውን ነው አሰልጣኙ የገለፀው::

በሁለት ዓመታት የውድድር ተሳትፎው አንድም ውድድር በሜዳው ሽንፈትን ያላስተናገደው የባቲ ከተማ እግር ኳስ ቡድን በ2008 ዓ.ም ቆቦ ላይ በተካሄደው የአማራ ሊግ የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር የዋንጫ አሸናፊም ነው:: በሜዳው ሽንፈትን አለማስተናገዱ ደግሞ የእግር ኳስ አፍቃሪውና የደጋፊው ከጐናቸው መሆን ነው:: "ይህም ሁሌም የአሸናፊነት ስነ ልቦና እንዲኖረን መሰረት ሆኖናል" በማለት ነው አሰልጣኙ የደጋፊውን የሜዳ ላይ ድጋፍ የገለፀው::

የሁለቱም ዓመት ውድድሮች የተካሄዱት በሙስሊሞች የፆም ወቅት ነበር:: ይህም በቡድኑ አባላት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሮባቸው እንደነበር አሰልጣኝ አብዱልቃድር ያስታውሳል:: ምክንያቱ ደግሞ ኣብዛኛዎቹ የቡድኑ አባላት

የእስልምና እምነት ተከታይ ናቸውና:: ይሁን እንጂ ተፅዕኖውን በመቋቋም የ2008ቱን ውድድር በዋንጫ ባለቤትነት አጠናቋል::

ስልጠናቸውንና ውድድር የሚያደርጉበት ሜዳ ምቹ ቢሆንም ከሌሎች አካባቢዎች አንፃር ሲታይ ግን የሚቀረው ነገር እንዳለው አሰልጣኙ ይናገራል:: ከዚህ በተጨማሪም ባቲ ከተማ በርካታ የእግር ኳስ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች መፍለቂያ ነች:: በማሳያነትም ከተማዋን ከወከላት ቡድን በተጨማሪ ባሳለፍነው ክረምት በሶስት የእድሜ ክልሎች (ከ13፣ 15 እና 17 ዓመት በታች) የተካሄደውን ውድድር እና በዚህ ውድድር ችሎታ ያላቸው ታዳጊዎች መታየታቸውን ያነሳል:: በእያንዳንዱ የእድሜ ክልልም 12 ቡድኖች የተካተቱበት ነበር::

ይሁን እንጂ በከተማዋ በቂ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ የለም:: ይህም ወጣቶች ጊዜያቸውን በአልባሌ ቦታዎች እንዲያሳልፉ ስለሚያደርግ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው::

የባቲ ከተማ እግር ኳስ ቡድን የመስመር ስፍራ ተጫዋቹ እንድሪስ ሙሐመድ በበኩሉ ላለፈው ዓመት የቡድኑ አሸናፊነት የቡድኑ አባላት

የወንድማማችነት ግንኙነት፣ የአሸናፊነት መንፈስና የደጋፊው ጠንካራ ድጋፍ ድምር ውጤት መሆኑን ነው የሚናገረው:: በዚህ የአሸናፊነት መንፈስም የ2009ን የአማራ ሊግ ዋንጫ ማንሳት ዕቅዳቸው መሆኑን ተናግሯል::

ከዚህ በተጨማሪም ባቲ ከተማ በርካታ የእግር ኳስ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች ያሉባት በመሆኑ የሚመለከተው አካል ትኩረት ይሰጠው ዘንድ የእንድሪስ መልዕክት ነው:: ከቡድኑ አባላት ውጪ የሆኑ ወጣቶች አብረው ጠንካራ ልምምድ መስራታቸውንም ለመልዕክቱ ማጠናከሪያነት ያነሳል:: ክረምት ላይ በተለያዩ የዕድሜ ደረጃዎች የተካሄደውን የእግር ኳስ ውድድርም ያስታውሳል::

አቶ ሙሐመድ አደም በባቲ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ተወካይ የስራ ሂደት ናቸው:: የጽ/ቤቱ ኃላፊዎች ቶሎ ቶሎ መቀያየር ስፖርቱ ላይ

ችግር መፍጠሩን ይናገራሉ:: ምክንቱም የተጀመሩ ተግባራት በጅምር እንዲቀሩ ያደርጋልና ባይ ናቸው:: በ2009 የበጀት ዘመን ግን ስፖርቱ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ነው የነገሩን:: አምስት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ልየታ ተደርጓልም ብለዋል::

እግር ኳስ በባቲዎች ዘንድ ባህል ሆኗል የሚሉት አቶ ሙሐመድ የዚህ ዓመት ዋና የትኩረት መስክ የስፖርት ማዘውተሪ ስፍራዎችን ማስፋፋት መሆኑን ነው የገለፁት:: ሌሎች የመዝናኛ ስፍራዎችም በከተማዋ ፕላን ተካተው እንደሚሰሩ ጠቁመዋል::

ከባቲ ከተማ የእግር ኳስ ቡድን የትራንስፖርት ችግር ጋር ተያይዞ ለሚነሳው ጥያቄ በዚህ ዓመት ለመፍታት የተጠናከረ ጥረት ይደረጋል ብለዋል::፡ የከተማዋን የስፖርት እንቅስቃሴ ለማጠናከርም እየተሰራ ነው:: ባሳለፍነው ክረምት ላይ ከ13 ዓመት በታች፣ ከ15 ዓመት በታችና ከ17 ዓመት በታች የዕድሜ ክልሎች የተካሄደውና 36 ቡድኖችን ያካተተው ውድድር የዚሁ አካል መሆኑን ነው የገለፁት::

ስፖርትን...ከገጽ 48 የዞረ

ታዲያ በስፖርታዊ እንቅስቃሴ (ጨዋታ) ሀብትና ዝናቸው ጣሪያ የነኩ ስፖርተኞች ተተኪዎች እንዲፈሩ መንገዱን ጠርገው ያመቻቻሉ:: ጤና የራቃቸውን ምንዱባን አፈላልገው ይደግፋሉ:: የማህበራዊ ግልጋሎት መስጫ ተቋማትን ይገነባሉ፤ ያስፋፋሉም::

አመት ህፃን ስኮትላንዳዊ ልቡ በሩኒና በማንቸስተር ዩናይትድ ፍቅር መሸነፉን የእንግሊዝ የመገናኛ ብዙሃን እየተቀባበሉ ዜናውን ናኙት::

ህፃን ካሳቢያንም “አዎ! ሩኒን እወደዋለሁ:: በእሱ የተነሳም ማንቸስተር ዩናይትድን አደንቃለሁ:: ማንቸስተር ዩናይትድ ወይም የእንግሊዝብሔራዊ

በዚህ መሰሉ ተግባር ስማቸው በታሪክ መዝገብ ከከተበው አፍሪካዊ የእግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል የላይቤሪያው የምንጊዜም የእግር ኳስ ኮኮብ ጆርጅ ዊሃ ትምህርት ቤት ገንብቶ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም እንዲውል አስረክቧል:: የናይጀሪያው ካኑ የጤና ጣቢያ አሠርቶ ለህዝብ ሰጥቷል:: የኮትዲቮሩ ዲዲየር ድሮግባ በየትምህርት ቤቶች ኳስና ትጥቅ አበርክቷል:: በዚህም ተተኪዎችን ወደ ሰፖርቱ ተማርከው እንዲገቡ ተነሳሽነትን ፈጥሯል:: በትምህርት ቤት የንጹህ የመጠጥ ውሃ አስገንብቶ አስረክቧል::

መሰል የምግባረ ሠናይ ሥራ ይብዛ- ይስፋፋ ያስብላል:: ዓላማው የተቀደሰ ነውና::

ከሰሞኑ ደግሞ የእንግሊዝ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን አምበልና የማንቸስተር ዩናይትድ ፊት አውራሪ ዋይኒሩኒ ሰሙ በበጎ እየተጠራ ነው::

ነገሩ እንዲህ ነው:: ሰሞኑን እንግሊዝና ስኮትላንድ ሩሲያ ለምታዘጋው 18ኛው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ነበራቸው:: እንግሊዝም 3ለ0 መርታቷ አይዘነጋም:: ታዲያ አንድ የስምንት

ቡድን ጨዋታ እያላቸው ሳላይ አልተኛም:: ትምህርት ቤት አልሄድም:: ዋይኒ ሩኒ የተሰለፈበት ቡድን ሲያሸንፍ በእጅጉ እደሰታለሁ:: ረጅም እድሜ ለሩኒ” ሲል አድናቆቱን በሰኮትላንድ ታይምስ ጋዜጣ በኩል አስተላልፏል::

የሚያሳዝነውና ልብ የሚነካው ህፃን ካሳቢያን የካንሰር ህመምተኛ መሆኑ ነው:: ታክሞ የመዳን እድሉ ሰፊ ቢሆንም የቤተሰቡ ገቢ ከዚህ ግባ የሚባል አይደለም::

ዋይኒ ሩኒም እንግሊዝ ከስኮትላንድ በነበራቸው ጨዋታ የለበሰው 10 ቁጥርመለያ ፊርማውን አኑሮ ልኮለታል:: ሩኒ አክሎም ተናገረ፤ “መለያ ስለላክሁልህ ይበልጥ እንደምትደሰት ተስፋ አለኝ” ብሏል::

የእንግሊዙ ዴይሊ ሜይል ጋዜጣ ውስጥ አዋቂዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው ህፃኑን ለማሳካም 10 ቁጥር ያረፈበትን መለያ ለጨረታ አቅርቧል:: በተወሰኑ ቀናትብቻም 20 ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግስተሰብስቦለታል:: የሊድስ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ለሩኒ ጥሪ ፈጣን ምላሽ መስጠቱን ጋዜጣው

ገልጿል:: ይኸውም ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ከማሳከም ባለፈ ትምህርቱን የሚቀጥልበት ሁኔታ ተመቻችቷል::

የ ማ ን ቸ ስ ተ ር ዩናይትድ ክለበ በበኩሉ “ሩኒ ሀሳብህን በገንዘብና በቁሳቁስ እንደግፋለን” ብለውታል::

የላንድ ሮቨር መኪና አምራች ኩባንያ በሩኒ በኩል ህፃን ካሳቢያን አሳክሞ ለቁም ነገርለማብቃት ቃልገብቷል::

በእኛስ አገር “ለሰው ልብሱ ሰው ነው” የሚለው አባባል የሩኒን ሀሳብ ያጠናክረው ይሆን?

በካንሰር የተጠቃው ህፃን ካስቢያን፤

ባቲ እንደ ቅኝቱ በስፖርቱም እየተነቃቃች ነው (የባቲ እግር ኳስ ቡድን)

አብዱልቃድር ሲራጅ የባቲ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ

Page 48: 12 03 2009.pdf

በኩር ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም.ገጽ 48 በኩር ስፖርትበኩር ስፖርትበኩር ስፖርትበኩር ስፖርት

ጌትሽ ኃይሌ

ወደ ገጽ 47 ዞሯል

ወደ ገጽ 47 ዞሯል

ስፖርትን ለበጎ ምግባር ያዋለው በጎ ሰው

የምርጦቹ ምርጥ ማን ይሆን?

ወደ ገጽ 36 ዞሯል

ባቲ እንደ ቅኝቱ በስፖርቱ…

ሙዋሊሙ

ሙሉጌታ ሙጨ

የእግር ኳስ ቡድኑ የአማራ ሊግ ተሳትፎውን የጀመረው በ2007 ዓ.ም ነው- የባቲ ከተማ የእግር ኳስ ቡድን::

በ2008 ዓ.ም በአማራ ሊግ ምስራቅ አማራ ምድብ "ለ" በመደልደል በሁለተኛ ዓመት የሊግ ውድድር ተሳትፎው ህልሙን እውን አድርጓል:: ምድቡን በቀዳሚነት በማጠናቀቅ የዋንጫ ባለቤት

ሆኗል:: ይሁን እንጂ የቡድኑ ስኬት አልጋ በአልጋ ጉዞን የተላበሰ አልነበረም::

አቶ አብዱልቃድር ሲራጅ የቡድኑ አሰልጣኝ ነው:: ከሜዳቸው ውጭ ጨዋታ ሲኖራቸው

እያቆራረጡ ስለሚሄዱና ለጨዋታው አንድ ቀን ሲቀረው ጉዞ መጀመራቸው የውድድር ዓመቱ ትልቁ ፈተና እንደነበር ነው የሚያስታውሰው::

ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የሚደረጉበት በርካታ ምክንያቶች አሉ:: አንዳንዶች ትርፍ ጊዜያቸውን እየተዝናኑ ለማሳለፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ይፈልጋሉ:: ሌሎች ደግሞ የማህበራዊ መስተጋብራቸውን ለማጠናከር ይሰራሉ::

አካላቸውን በስፖርት ገንብተው፣ ተሰጥኦቸውን አጠናክረው፣ ትምህርት ቀስመው የእንጀራ ገመዳቸው ለመገመድ የሚንቀሳቀሱም አሉ:: የተዛባውን ጤንነታቸውን ለመመለስ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚሰሩም ጥቂት አይደሉም::

“ስፖርት ለወዳጅነት፣ ለሠላም፣ ለጤንነት፣… መባሉስ ለዚህ አይደል?!

የእንግሊዝ የዜና ማሰራጫ ኮርፖሬሽን(ቢ.ቢ.ሲ)በየዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ የእግር ኳስ

ተጫዋቾችን “የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች” በሚል ይሸልማል::

እስካሁንስ እነማን ተሸለሙ? ብለን ስንጠይቅ የሁሉንም ስም ዝርዝር ለማስፈር አስቸጋሪ መሆኑን ተገነዘብንና ተውነው:: ለግንዛቤ ያህል ግን እ.ኤ.አ ከ1999 አመት ወዲህ ያሉትን ክዋኔዎች ለመዳሰስ እንሞክራለን:: ህፃን ካሳቢያንና ሩኒ